አብዛኛውን ጊዜ በኢትዮጵያ ያሉ ግዛቶች ከአንድ በላይ በሆኑ ብሔረሰቦች የባለቤትነት ጥያቄ ይነሳባቸዋል። በኢትዮጵያ ባለው ዘር ላይ የተመሰረተ የፌዴራል አወቃቀር ምክንያት በአጨቃጫቂ ግዛቶች ላይ የሚደረጉ የድንበር ውዝግቦች መደበኛ እና ኢ-መደበኛ የሆኑ ሁከቶችን ያስተናግዳሉ። በተለያዩ ብሔረሰቦች መካከል ያሉ ግጭቶች ብዙ ግዜ ሃብት ባለው መሬት ላይ ሲሆን ግጭቱ በአብዛኛው የሚካሄድባቸው ቦታዎች ደግሞ መተከል ዞን፣ ደቡብ ትግራይ ዞን፣ ምዕራብ ትግራይ ዞን፣ የአፋር/ሶማሌ ክልል ድንበሮች፣ የኦሮሚያ/ሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች፣ በኦሮሚያ/አማራ ክልሎች ድንበሮች የሚገኙ አካባቢዎች ናቸው። ይህ ክፍል ከእነዚህ ግጭቶች ጋር የተያያዙ ዘገባዎችን አካቷል።