ግጭት የተቀላቀለባቸውም ሆኑ ሰላማዊ የሆኑ ሰልፎች የኢትዮጵያን የፖለቲካ ምህዳር በመቅረጽ ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል። ከ2006 እስከ 2010 ከተደረጉ መጠነ ሰፊ ፀረ-ትህነግ ህዝባዊ ንቅናቄዎች ውጪ     በአሁኗ ኢትዮጵያ ሰልፎች በብዛት አይደረጉም ። ተያያዥነት  ያላቸው ተከታታይ ሰልፎች ሲደረጉ ብዙውን ጊዜ በአካባቢው ውስጥ ያለ በጣም አስፈላጊ የሆነ የፖለቲካ ለውጥ ያንፀባርቃሉ። ይህ ክፍል የኢትዮጵያን የሰላማዊ ሰልፍ እንቅስቃሴዎች የሚተነትኑ ዘገባዎችን ያካትታል።