የቤንች ሸኮ (ቤንች ማጂ) ዞን በህዳር 14, 2014 ላይ ከህዝበ ውሳኔ በኋላ   በተመሰረተው አዲሱ የኢትዮጵያ ክልል – የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል – ውስጥ የሚገኝ ነው። እንደ ዲዚ፣ ሱሪ፣ ሸኮ፣ ከፋ፣ ሸካ፣ መዠንገር፣ ቤንች፣ እና መኢኒት ያሉ ብሄረሰቦች የዞኑ ተወላጅ ተደርገው ይወሰዳሉ። በ1970ዎቹ አጋማሽ እና ከ1995 እስከ 1997 በተካሄደው የሰፈራ መርሃ ግብር በቤንች ሸኮ ዞን የሰፈሩ ሰዎች እንደ ‘ሰፋሪ’ ይቆጠራሉ። በእነዚህ ተወላጆች እና ሰፋሪዎች መካከል ያለው ግጭት በየጊዜው የሚከሰት ነው። ይህ ክፍል ከዚህ ግጭት ጋር የተያያዙ ዘገባዎችን ያካትታል።