EPO is a new initiative to enhance local data collection across Ethiopia.
Latest EPO Analysis
EPO Bulletin
6 November 2022: OLF-Shane members clashed with government forces in Nekemte city in East Wollega zone in Oromia region. OLF-Shane released an unidentified number of prisoners. Due to this clash, at least one civilian and five members of OLF-Shane were reported killed.
ጥቅምት 27, 2015: በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ወለጋ ዞን በነቀምት ከተማ የኦነግ-ሸኔ አባላት ከመንግስት ኃይሎች ጋር ተዋግተዋል። ኦነግ-ሸኔ ቁጥራቸው ያልታወቁ እስረኞችን መፍታቱ ተነግሯል። በዚህ ግጭት ቢያንስ አንድ ሰላማዊ ሰው እና አምስት የኦነግ-ሸኔ አባላት መሞታቸው ተዘግቧል።
Source: DW Amharic
2 November 2022: The Ethiopian government and TPLF signed a peace agreement in Pretoria, South Africa. In this agreement, among other issues, the two conflicting parties agreed to permanently cease hostilities and for the TPLF forces to disarm, demobilize and reintegrate.
ጥቅምት 23, 2015፡ የኢትዮጵያ መንግስት እና ትህነግ/ህወሓት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ። በዚህ ስምምነት ሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች ጦርነቱን ለዘለቄታው ለማቆም፣ የትህነግ/ህወሓት ኃይሎች ትጥቅ እንዲፈቱ እና ወደ ህብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ እና በሌሎች ተጨማሪ ጉዳዮች ላይ ተስማምተዋል።
Source: VOA Amharic
26 October 2022: Hundreds of people protested against the killing of a Somali regional council member in Jigjiga in Somali region. She was killed a day earlier by a federal police at Jigjiga airport. Some demonstrators threw stones and in return police fired tear gas to disperse the protestors. There were no causalities, but some demonstrators were arrested.
ጥቅምት 16, 2015፡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ከአንድ ቀን በፊት በጅግጅጋ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ በአንድ ፌዴራል ፖሊስ የተገደሉትን የሶማሌ ምክር ቤት አባል ግድያ ተቃውመዋል። አንዳንድ ተቃዋሚዎች ድንጋይ በመርወር ተቃውሟቸውን የገለጹ ሲሆን ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ በመተኮስ ተቃዋሚዎቹን በትኗል። የተጎዳ ሰው ባይኖርም በነበረው ግርግር የተወሰኑ ሰዎች ታስረው ነበር።
Source: BBC Amharic
25 October 2022: A federal police officer opened fire in the Jigjiga airport, Somali region, killing one woman member of the regional state council and injuring four other civilians. The reason behind this attack is unknown. Witnesses stated that the officer was seen arguing with another airport security guard prior to the shooting.
ጥቅምት 15, 2015፡ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ኤርፖርት በአንድ የፌዴራል ፖሊስ በተከፈተ ተኩስ አንድ ሴት የክልሉ ምክር ቤት አባል ሲገደሉ ሌሎች አራት ሰላማዊ ሰዎች ቆስለዋል። ከዚህ ጥቃት በስተጀርባ ያለው ምክንያት አልታወቀም። የፌዴራል ፖሊሱ ጥቃቱን ከማድረሱ በፊት ከሌሎች የኤርፖርቱ ጥበቃ አባላት ጋር ሲጨቃጨቅ መታየቱን የዓይን እማኞች ገልጸዋል።
Source: Somali Regional State Communication Bureau; BBC Amharic
22 October 2022: Hundreds of thousands of people have gathered in cities throughout Ethiopia to hold a pro-government rally, also denouncing western interference into Ethiopian sovereignty.
ጥቅምት 12, 2015፡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች በመሰባሰብ መንግስትን የሚደግፍ ሰልፎች ያደረጉ ሲሆን ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነትንም አውግዘዋል።
Source: Africa News, EBC
17 October 2022: Ethiopian and Eritrean forces have taken control of Shire town in North Western Tigray zone in Tigray. This comes shortly after an air strike targeting the city killed an aid worker, among other two other civilians on 14 October 2022.
ጥቅምት 7, 2015፡ በትግራይ ክልል በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ዞን ሽሬ ከተማን የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ኃይሎች ተቆጣጥረዋል። ይህ የሆነው ጥቅምት 4, 2015 በከተማይቱ ላይ ያነጣጠረ የአየር ጥቃት አንድ የእርዳታ ሠራተኛን እና ሌሎች ሁለት ሰላማዊ ሰዎችን ከገደለ በኋላ ነው።
Source: Reuters
12 October 2022: A member of the OLF party executive committee was shot and killed by unidentified gunmen near his residents in Sansusi in Burayu town in Finfine special zone in Oromia region.
ጥቅምት 1, 2015፡ በኦሮሚያ ክልል ፊንፊኔ ልዩ ዞን በቡራዩ ከተማ ሳንሱሲ በተባለ ቦታ አንድ የኦነግ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በጥይት ተመተው ተገድለዋል።
Source: BBC Amharic
11 October 2022: An unidentified armed group ambushed a convoy of woreda officials escorted by security forces in an area between Ajenta and Tuni Dabisha kebeles in Mandura woreda in Metekel zone in Benishangul/Gumuz region. At least seven people, including the Mandura woreda administrator, his driver and security forces, were reportedly killed and four others wounded. Two more people have also gone missing.
ጥቅምት 1, 2015፡ በቤኒሻንጉል/ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን በመንዱራ ወረዳ በአጄንታ እና ቱኒ ዳቢሻ ቀበሌዎች መካከል በሚገኝ ቦታ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በፀጥታ ሃይሎች ታጅበው ሲጓዙ የነበሩ የወረዳው ባለስልጣናትን አድፍጠው ማጥቃቸው ታውቋል። የማንዱራ ወረዳ አስተዳዳሪ፣ ሹፌሩ እና የጸጥታ ኃይሎችን ጨምሮ ቢያንስ ሰባት ሰዎች መሞታቸው እና ሌሎች አራት መቁሰላቸው ተነግሯል። ሁለት ተጨማሪ ሰዎችም ጠፍተዋል።
Source: DW Amharic; EMS
6 October 2022: Murle ethnic militias from South Sudan opened gunfire and killed three people in Longjok kebele in Makuey woreda in Nuwer zone in Gambela region. The group also abducted an 11-year-old boy.
መስከረም 26, 2015: ከደቡብ ሱዳን የመጡ የሙርሌ ብሄረሰብ ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል በኑዌር ዞን ማኩዬ ወረዳ በሎንግጆክ ቀበሌ ተኩስ ከፍተው ሦስት ሰዎችን ገድለዋል። ቡድኑ የ11 አመት ልጅንም አፍኖ ውስዷል።
3 October 2022: OLF-Shane members attacked a bus carrying employees of Muger Cement Factory around Mekoda area in Adaa Berga woreda in West Shewa zone in Oromia region, killing at least two people and injuring 16 others. A day earlier an unidentified armed group abducted the manager of the cement factory and his driver in Gatira area in West Shewa zone while traveling to the factory.
መስከረም 23, 2015: በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን አድአ በርጋ ወረዳ መቆዳ አካባቢ የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ሰራተኞችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ አውቶቡስ ላይ የኦነግ ሼኔ አባላት ባደረሱት ጥቃት በትንሹ 2 ሰዎች ሲገደሉ 16 ቆስለዋል። አንድ ቀን ቀደም ብሎ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች የሲሚንቶ ፋብሪካውን ስራ አስኪያጅ እና ሹፌራቸው ወደ ፋብሪካው ሲጓዙ በምዕራብ ሸዋ ዞን ጋቲራ አካባቢ አፍነው ወስደዋል።
Source: BBC Amharic; Addis Maleda
3 October 2022: TPLF announced that it forces have withdrawn from North Wello zone in Amhara region. Reports indicate that areas in North Wello zone which were previously under TPLF forces are now free.
መስከረም 23, 2015፡ ህወሓት/ትህነግ ተዋጊ ኃይሎቹ ከአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ለቀው መውጣታቸውን አስታወቀ። በሰሜን ወሎ ዞን ቀደም ሲል በህወሓት/ትህነግ ኃይል ቁጥጥር ስር የነበሩ አካባቢዎች አሁን ነጻ መሆናቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ።
Source: Twitter @TigrayEAO; Addis Maleda
1 October 2022: OLF-Shane clashed with kebele militias and Oromia state police in Dukele kebele in Miyo woreda in Borena zone in Oromia region after the group attacked the security forces. Due to this clash, 15 members of OLF-Shane were reported killed and more than 25 others were injured, while six members of government forces were reported killed.
መስከረም 21, 2015፡ በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን ሚዮ ወረዳ ዱከለ ቀበሌ ኦነግ-ሸኔ በአካባቢ ባሉት የቀበሌ ሚሊሻ እና የኦሮሚያ ፖሊስ ላይ ጥቃት ከሰነዘረ በኃላ ከመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ተዋግቷል። በዚህ ውጊያ 15 የኦነግ-ሸኔ አባላት መገደላቸውን ከ25 በላይ የሚሆኑት ደግሞ መቁሰላቸውን እና ስድስት የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውን ተዘግቧል።
Source: EMS
30 September 2022: Oromia regional special force and Oromo ethnic militias reportedly clashed with Somali ethnic militias in contested areas in Gura Damole woreda in Bale zone in Oromia region. An unknown number of people were reported killed due to this clash. This is the second reported clash between the two parties within a week.
መስከረም 20, 2015፡ በኦሮሚያ ክልል በባሌ ዞን በጉራ ዳሞሌ ወረዳ ይገባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው አካባቢዎች የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል እና የኦሮሞ ብሔር ታጣቂዎች ከሶማሌ ብሔር ታጣቂዎች ጋር መዋጋታቸው ተነግሯል። በዚህ ውጊያ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች መሞታቸው ታውቋል። ይህ በሳምንት ውስጥ በሁለቱ ወገኖች መካከል የተደረገ ሁለተኛው ውጊያ መሆኑ ተነግሯል።
Source: Hiiraan Online
30 September 2022: OLF-Shane attacked Layegnaw Awash Tefases Ersha Lemat area (Nuera Hera Ersah Lemat) in Boset woreda in East Shewa zone in Oromia. This attack forced an unidentified number of civilians to flee their residences.
መስከረም 20, 2015፡ ኦነግ-ሸኔ በኦሮሚያ በምስራቅ ሸዋ ዞን ቦሰት ወረዳ ላይኛዉ አዋሽ ተፋሰስ እርሻ ልማት አካባቢ (ኑሬ ሄራ እርሻ ልማት) ላይ ጥቃት ሰንዝሯል። በዚህ ጥቃት ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰላማዊ ሰዎች መኖሪያ ቤታቸውን ለቀው ለመሰደድ ተገደዋል።
Source: ESAT
22-23 September 2022: OLF-Shane and kebele militias clashed in kebele 01 in Jardega Jarte town in Horo Guduru zone in Oromia region after OLF-Shane began attacking civilians in the area. Reportedly, OLF-Shane killed at least two civilians and injured four civilians. EPO researchers are closely monitoring the event and will provide updates.
መስከረም 12-13, 2015፡ በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉዱሩ ዞን ጃርደጋ ጃርቴ ከተማ በቀበሌ 01 ኦነግ-ሸኔ በአካባቢው ሰላማዊ ሰዎችን ማጥቃት ከጀመረ በኋላ የኦነግ-ሸኔ እና የቀበሌ ታጣቂዎች ተዋግተዋል። ኦነግ-ሸኔ ቢያንስ ሁለት ሰላማዊ ሰዎችን ገድሎ አራት ሰላማዊ ሰዎችን ቆስሏል ተብሏል። የኢፒኦ ተመራማሪዎች ይህንን ኩነት በቅርበት እየተከታተሉ ሲሆን አዳዲስ መረጃዎችን እየተከታተሉ ያቀርባሉ።
Source: DW Amharic; DW Amharic
21 September 2022: An unidentified armed group from West Guji zone in Oromia region opened gunfire on civilians who were waiting for nine members of the FDRE House of Representatives assigned to investigate identity-based attacks on members of the Kore ethnic group in Melka Oda village in Dorbale kebele in Amaro special woreda in SNNPR. Due to this attack, five civilians were killed, while four others were injured.
መስከረም 11, 2015፡ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በአማሮ ልዩ ወረዳ በዶርባሌ ቀበሌ መልካ ኦዳ መንደር በኮሬ ብሄረሰብ አባላት ላይ ይፈፀማል የተባለውን የማንነት መሠረት ያደረገ ጥቃት ለማጣራት የተመደበውን የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዘጠኝ አባላትን በመጠባበቅ ላይ በነበሩ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን የመጣ ማንነቱ ያልታወቀ ታጣቂ ቡድን ተኩስ ከፍቷል። በዚህ ጥቃት አምስት ሰላማዊ ሰዎች ሲገደሉ አራት ሰዎች ቆስለዋል።
Source: DW Amharic
21 September 2022: An unidentified South Sudan armed group opened gunfire from Maluwal Gaot area on the South Sudanese side of the border on a motorboat transporting civilians from Jakawo bridge to Metehar town on Baro river in Nuer zone in Gambela region. Reportedly, the armed group opened fire over disputes related to tax payments. Due to this attack, one person was killed, and seven others were injured. Two more people were reported missing.
መስከረም 11, 2015፡ ማንነቱ ያልታወቀ የደቡብ ሱዳን ታጣቂ ቡድን በጋምቤላ ክልል ኑዌር ዞን ባሮ ወንዝ ላይ ሰላማዊ ዜጎችን ከጃካዎ ድልድይ ወደ መተሃር ከተማ በማጓጓዝ በነበረ የሞተር ጀልባ ላይ በደቡብ ሱዳን ድንበር ላይ ከሚገኘው ማሉዋል ጋኦት አካባቢ ተኩስ ከፍቷል። በዚህ ጥቃት አንድ ሰው ሲሞት ሰባት ሰዎች ቆስለዋል። ሁለት ተጨማሪ ሰዎችም ጠፍተዋል ተብሏል። የታጠቀው ቡድን ከታክስ ክፍያ ጋር በተያያዘ በተነሳ አለመግባባት ተኩስ መክፈቱ ተዘግቧል።
Source: Gambella Regional Gov’t Press Secretariat Office; DW Amharic
21 September 2022: Chairman of Alge kebele in Fentale woreda in East Shewa zone in Oromia was killed by an unidentified armed group.
መስከረም 11, 2015: በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ የአልጌ ቀበሌ ሊቀመንበር ማንነቱ ባልታወቀ ታጣቂ ቡድን ተገደሉ።
Source: Addis Maleda
2 September 2022: “Hundreds” of ethnic Tigrayans, who served as UN Peacekeeping forces in South Sudan and had taken refuge in Sudan following the beginning of Ethiopia’s northern conflict, have reportedly attacked Ethiopian government forces at the Ethiopia and Sudan border near Humera town in Western Tigray zone in Tigray. EPO researchers are closely monitoring the event and will provide updates.
ነሐሴ 27, 2014፡ በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ኃይል ሆነው ያገለገሉት እና የኢትዮጵያ የሰሜን ግጭት መጀመሩን ተከትሎ በሱዳን ጥገኝነት ጠይቀው የነበሩ “በመቶዎች” የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች በኢትዮጵያ እና በሱዳን ድንበር በትግራይ ክልል በምዕራብ ትግራይ ዞን ሁመራ ከተማ አቅራቢያ የኢትዮጵያ መንግስት ኃይሎች ላይ ጥቃት ማድረጋቸው ተዘግቧል። የኢፒኦ ተመራማሪዎች ይህንን ኩነት በቅርበት እየተከታተሉት ሲሆን አዳዲስ መረጃዎችን እየተከታተሉ ያቀርባሉ።
Source: Bloomberg
1 September 2022: Mayor of Shewa Robit was shot and killed by an unidentified armed group while he was heading to his residence in Shewa Robit town in North Shewa zone in Amhara region.
ነሐሴ 26, 2014፡ የሸዋ ሮቢት ከንቲባ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋ ሮቢት ከተማ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በማምራት ላይ ሳሉ ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች በጥይት ተመትተው ተገድለዋል።
Source: Addis Maleda
31 August 2022: ENDF and TPLF forces clashed in Bereket and Shererina areas at the border of Ethiopia and Sudan.
ነሐሴ 25, 2014፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የትህነግ/ህወሓት ኃይሎች በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር አካባቢ በሚገኙት በረከት እና ሸረሪና አከባቢዎች ተዋግተዋል።
Source: DW Amharic
29-31 August 2022: OLF-Shane killed 11 people and injured another 11 in Agamsa town in Amuru woreda in Horo Guduru zone in Oromia. The group also looted Ethiopian Commercial Bank, Awash Bank and Cooperative Bank of Oromia in Amuru woreda in Horo Guduru zone. The activity by OLF-Shane follows the killing of 55 civilians by Fano militias in the same location on 30 August 2022.
ነሐሴ 23-25, 2014: በኦሮሚያ በሆሮ ጉዱሩ ዞን አሙሩ ወረዳ አጋምሳ ከተማ ኦነግ-ሸኔ 11 ሰዎችን ገድሎ ሌሎች 11 ሰዎችን አቁስሏል። ቡድኑ በአሙሩ ወረዳ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን፣ አዋሽ ባንክን እና የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክንም ዘርፏል። ይህ የኦነግ-ሸኔ እንቅስቃሴ ነሐሴ 24, 2014 ፋኖ ታጣቂዎች 55 ሰላማዊ ሰዎችን መግደላቸውን ተከትሎ የተፈፀመ ነው።
Source: Addis Maleda; DW Amharic
30 August 2022: Fano militias opened gunfire and killed at least 55 civilians and injured more than 40 others in Agamsa town in Amuru woreda in Horo Guduru zone in Oromia after accusing them of cooperating with OLF-Shane. This attack occurred one day after OLF-Shane entered the town and disarmed 59 people. The Oromia regional special forces withdrew from the area on 28 August 2022.
ነሐሴ 24, 2014፡ በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉዱሩ ዞን በአሙሩ ወረዳ በአጋምሳ ከተማ ከኦነግ-ሸኔ ጋር ተባብራችሗል በማለት የፋኖ ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው ቢያንስ 55 ሰላማዊ ሰዎችን ሲገድሉ ከ40 በላይ የሚሆኑ ደግሞ ቆስለዋል። ይህ ጥቃት የተፈፀመው ኦነግ-ሸኔ በከተማው ገብቶ 59 ሰዎችን ትጥቅ ካሰፈታ ከአንድ ቀን በኋላ ነው። የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል አካባቢውን ነሐሴ 22, 2014 ለቆ ወጥቷል።
Source: DW Amharic
28-29 August 2022: Marehan clan militia attacked and clashed with Maqabul clan militia due to a dispute over land and revenge in Laanta Qurac Shire village near Shilabo town in Korahe zone in Somali region. At least 10 people were killed, and several others were injured.
ነሐሴ 22- 23, 2014፡ በሶማሌ ክልል ኮራሄ ዞን ሽላቦ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው በሊንታ ቁርአ ሽሬ መንደር በመሬትምክንያት በተቀሰቀሰ አለመግባባት እና በበቀል ምክንያት የማረሃን ጎሳ ታጣቂዎች በማቃቡል ጎሳ ታጣቂዎች ላይ ጥቃት በማድረሳቸው ሁለቱ ጎሳዎች ተዋግተዋል። በትንሹ 10 ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች ቆስለዋል።
Source: Kulmiye News Network
24 August 20221: TPLF and ENDF, Amhara regional special forces, Amhara and Fano militias clashed in multiple areas in Zobel mountain, Bisober and Wetwet areas around Kobo in Amhara region. EPO researchers are closely monitoring this event and will provide updates.
ነሐሴ 18, 2014: በአማራ ክልል በቆቦ ዙሪያ በዞብል ተራራ፣ ቢሶበር እና ወትወት አካባቢዎች የትህነግ/ህወሓት እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ክልል ልዩ ሃይል፣ የአማራ እና የፋኖ ታጣቂዎች ተዋግተዋል። የኢፒኦ ተመራማሪዎች ይህንን ኩነት በቅርበት እየተከታተሉ ሲሆን አዳዲስ መረጃዎችን እየተከታተሉ ያቀርባሉ።
Source: BBC Amharic; FDRE Government Communication Service; BBC Amharic; Reuters
23 August 2022: Ethiopian air force shot down an unidentified airplane as it crossed into Ethiopia’s air space from Sudan around Humera in Western Tigray zone in Tigray region. Reportedly the airplane was carrying weapons to the TPLF.
ነሐሴ 17, 2014: የኢትዮጵያ አየር ሃይል በትግራይ ክልል በምዕራብ ትግራይ ዞን ሁመራ አካባቢ በሱዳን በኩል የኢትዮጵያን የአየር ክልል አቋርጦ የገባ ማንነቱ ያልታወቀ አይሮፕላንን ተኩሶ መጣሉ ተነግሯል ። አውሮፕላኑ የጦር መሳሪያ ለትህነግ/ህወሓት ሊያቀብል ነበር ተብሏል።
Source: Ethiopian Broadcasting Corporate
21 August 2022: OLF-Shane clashed with ENDF and federal police in Dupa town in Darimu woreda in Ilu Aba Bora zone in Oromia region when OLF-Shane tried to attack the camps of government forces in the area and control the town. More than 50 members of OLF-Shane killed, and unidentified members of the group were reported injured. ENDF claimed to capture unidentified members of the group including three leaders with looted properties.
ነሐሴ 15, 2014: በኦሮሚያ ክልል ኢሉ አባ ቦራ ዞን በዳሪሙ ወረዳ ዱጳ ከተማ ኦነግ-ሸኔ በአካባቢው የሚገኙትን የመንግስት ታጣቂዎች ካምፖችን ለማጥቃት እና ከተማዋን ለመቆጣጠር ሲሞክር ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና ከፌዴራል ፖሊስ ጋር ተዋግቷል። ከ50 በላይ የኦነግ-ሸኔ አባላት መገደላቸው እና ማንነታቸው ያልታወቁ የቡድኑ አባላት መቁሰላቸው ተነግሯል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሶስት አመራሮችን ጨምሮ ማንነታቸው ያልታወቁ የቡድኑ አባላትን ከተዘረፉ ንብረቶች ጋር መያዙን ገልጿል።
Source: ESAT; FDRE Defense Force
11 August 2022: Afar ethnic militias clashed with Somali ethnic militias in Cundhufo, Danlahelay and in other disputed locations in Afder woreda in Sitti zone in Somali region. Casualties unknown. EPO is closely monitoring this event and will provide updates.
ነሃሴ 5, 2014፡ በሶማሌ ክልል በሲቲ ዞን አፍዴር ወረዳ በኡንዱፎ፣ ዳንላህላይ እና ሌሎች ውዝግብ ያለባቸው አካባቢዎች የአፋር ብሔረሰብ ታጣቂዎች ከሶማሌ ብሔረሰብ ታጣቂዎች ጋር ተዋግተዋል። የደረሰው ጉዳት ያልታወቀም። ኢፒኦ ይህንን ኩነት በቅርበት እየተከታተለ ሲሆን አዳዲስ ማረጃዎችን እየተከታተለ ያቀርባል።
Source: Hiiraan Online
8 August 2022: Murle ethnic militias from South Sudan attacked Ukugu refugee camp in Dima woreda in Anuak zone in Gambela region, killing two people and injuring one other person. The militias also abducted two children.
ነሐሴ 2, 2014: ከደቡብ ሱዳን የመጡ የሙርሌ ብሄረሰብ ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል አኝዋክ ዞን ዲማ ወረዳ በሚገኘው የኡኩጉ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ላይ ጥቃት ፈጽመው ሁለት ሰዎች ሲገደሉ አንድ ሰው አቁስለዋል። ታጣቂዎች ሁለት ህጻናትንም አፍነው ወስደዋል።
25 July 2022: Somali regional special forces and Al Shabaab clashed in Al Kudun area in Ferfer woreda in Shabelle zone in Somali region when the group tried to enter Ethiopia from Hiran area in Somalia. At least 85 members of Al Shabaab were killed, and several weapons were captured.
ሐምሌ 18, 2014፡ አልሸባብ ከሶማሊያ ሂራን አካባቢ ተነስቶ ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ሲሞክር ከሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ጋር በሶማሌ ክልል ሸበሌ ዞን ፌርፌር ወረዳ ኤል ቁዱን በተባለ አካባቢ ተዋግቷል። ቢያንስ 85 የአልሸባብ አባላት ሲገደሉ በርካታ የጦር መሳሪያዎችም ተማርከዋል።
Source: Somali Regional State Communication Bureau; FDRE Government Communication Service
20-21 July 2022: Al Shabaab and Somali regional special forces clashed in Yod and Ato villages in Bakul in Somalia and Hargele woreda in Afder zone in Somali region in Ethiopia, killing 17 people, including three civilians and Ethiopian police officers and 63 members of Al Shabaab. At the moment, Al Shabaab militants are reportedly surrounded by Somali regional special force in Goldhir area in Hulul in Hargele woreda in Afder zone in Somali in Ethiopia. EPO is closely following this event and will provide updates.
ሐምሌ 13-14, 2014: አልሸባብ እና የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል በሶማሊያ ባኩል ውስጥ ዬድ እና አቶ መንደሮች እና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን ሐረገሌ ወረዳ ተዋግል። በዚህም ሦስት ሰላማዊ ሰዎችን እና የኢትዮጵያ ፖሊስ አባላት ጨምሮ 17 ሰዎች እና 63 የአልሸባብ አባላት ተገለዋል። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን በሐርጌሌ ወረዳ በሁልሁል በጎልድሂር አካባቢ የአልሸባብ ታጣቂዎች በሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል ተከበው እንደሚገኙ ተነግሯል። ኢፒኦ ይህንን ኩነት በቅርበት እየተከታተለ ሲሆን አዳዲስ መረጃዎችን እየተከታተለ ያቀርባል።
Source: Reuters; BBC Amharic
Around 13 July 2022: ENDF carried out a military operation against OLF-Shane militants in Boset woreda in East Shewa zone in Oromia region. ENDF claimed to have killed an unknown number of the rebel militants and seized five AKM guns, two grenades, 200 ammunitions, 164 Bren gun ammunitions, four ballistic battle belts and 12 cluster munitions.
ሐምሌ 7, 2014 አካባቢ፡ በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሸዋ ዞን ቦሰት ወረዳ በኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ወታደራዊ ጥቃት ፈጽሟል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ የአማፂያኑን ታጣቂዎች መግደሉን እና ኤኬሜ (የክላሽ ) ጠብመንጃ፣ ሁለት የእጅ ቦምቦች፣ 200 ጥይቶች፣ 164 የብሬን ጥይት፣ አራት የወገብ ትጥቅ እና 12 ክላስተር ጥይቶች መያዙን ገልጿል።
Source: FDRE Defense Force
10-12 July 2022: Reportedly, clashes between OLF Shane militants and government security forces erupted in areas bordering Jilee Timuga woreda in Oromia special zone and Efratana Gedim woreda in North Shewa zone in Amhara region. At least six people and 19 members of security forces were reportedly killed. The residents of both woredas debate the cause for this clash. EPO is closely following this event and will provide updates.
ሐምሌ 3–5, 2014: በአማራ ክልል በኦሮሚያ ልዩ ዞን ጅሌ ጡሙጋ ወረዳ እና በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ገድም ወረዳ አዋሳኝ አካባቢዎች በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች እና በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች መካከል ግጭት መቀስቀሱ ተነግሯል። ቢያንስ ስድስት ሰዎች እና 19 የጸጥታ ሃይል አባላት መሞታቸው ተነግሯል። የሁለቱም ወረዳ ነዋሪዎች ለዚህ ግጭት መንስኤ የተለያየ ምክንያት ይጠቅሳሉ። ኢፒኦ ይህን ኩነት በቅርበት እየተከታተለ ሲሆን አዳዲስ መረጃዎችን እየተከታተለ ያቀርባል።
Source: VOA Amharic; Al-Ain; Reporter
9 July 2022: A landmine exploded near Kasagita in Ada’ar woreda in Awsi Rasu-zone 01 in Afar region, killing four teenagers. The Ethiopian government forces and TPLF have been fighting in the area until the government forces regained control over the area in late 2021.
ሐምሌ 2, 2014: በአፋር ክልል አውሲ ረሱ-ዞን 1 አድአር ወረዳ የተቀበረ ፈንጂ ፈንድቶ አራት ታዳጊዎች ሞተዋል። በታህሳስ 2014 የመንግስት ሃይሎች አካባቢውን እስኪ ቶጣጠሩ ድረስ የትህነግ/ህወሓት እና የመንግስት ሃይሎች በአካባቢው ውጊያ ያደርጉ ነበር።
Source: DW Amharic
5 July 2022: OLF-Shane militants allegedly killed three and wounded two farmers in Dano kebele in Amaro special woreda in SNNPR. The armed group also looted an unspecified number of cattle after the attack. The group denied this allegation.
ሰኔ 28, 2014፡ የኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ ዳኖ ቀበሌ ሦስት ሰዎችን ገድለው ሁለት አርሶ አደሮችን እንዳቆሰሉ ተዘግቧል። ታጠቂ ቡድኑ ከጥቃቱ በኋላ ቁጥራቸው በውል ያልተገለጸ የቀንድ ከብቶችንም ዘርፏል። ቡድኑ ይህንን ውንጀላ አስተባብሏል።
Source: VOA Amharic
4 July 2022: OLF-Shane allegedly opened gunfire and killed at least 150 civilians, mostly ethnic Amharas and injured at least 45 others in Mender 20 and 21 in Lemlem kebele in Hawa Gelan woreda in Kellem Wollega zone in Oromia region. An unidentified number of people were also abducted by the group. OLF-Shane denied this claim and accused the government forces of being responsible for the attack. The EPO is following developments closely and will provide updates.
ሰኔ 27, 2014፡ ኦነግ-ሸኔ በኦሮሚያ ክልል በቄለም ወለጋ ዞን ሃዋ ገላን ወረዳ ለምለም ቀበሌ መንደር 20 እና 21 ውስጥ ተኩስ በመክፈት ቢያንስ 150 በአብዛኛው የአማራ ብሔር ተወላጆች የሆኑ ሰላማዊ ሰዎችን ገድሎ በትንሹ 45 ሰዎችን አቁስሏል። ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎችም በቡድኑ ታፍነው ተወስደዋል። ኦነግ-ሸኔ ይህን ክስ ውድቅ አድርጎ የመንግስት ሃይሎችን ለጥቃቱ ተጠያቂ አድርጓል። ኢፒኦ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ ሲሆን ወቅታዊ ሁኔታዎችን እያተከታተለ አዳዲስ መረጃዎችን ያቀርባል።
Source: BBC Amharic; DW Amharic
30 June 2022: Government forces clashed with members of OLF-Shane in Tenze kebele in Begi woreda in West Wollega zone in Oromia region. Reportedly, 45 members OLF-Shane were killed and two others were captured with 35 Kalashnikov weapons. Further, government forces clashed with OLF-Shane in Bilo and Gube areas in Bila woreda in East Wollega zone in Oromia region. Causalities unknown.
ሰኔ 23, 2014: በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ቤጊ ወረዳ ቴንዘ ቀበሌ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና ኦነግ-ሸኔ ተዋግተዋል። በዚህ ውጊያ 45 የኦነግ-ሸኔ አባላት መገደላቸውን እና ሁለት የቡድኑ አባላት ከ35 ክላሽ ጠመንጃዎች ጋር መማረካቸው ተነግሯል። በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ወለጋ ዞን ቢላ ወረዳ ቢሎ እና ጎቤ በተባሉ አካባቢዎች የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና ኦነግ-ሸኔ ተዋግተዋል። ስለደረሰው ጉዳት የተባለ ነገር የለም።
29 June 2022: Amhara regional special forces, regional police and local militias clashed with an unidentified armed group near Bati town in Bati woreda in Oromo special zone in Amhara region. At least three government soldiers were killed including one member of regional special forces, one police officer and one local militia.
ሰኔ 22, 2014: በአማራ ክልል በኦሮሞ ልዩ ዞን በባቲ ወረዳ በባቲ ከተማ አቅራቢያ የአማራ ክልል ልዩ ሃይል፣ የክልሉ ፖሊስ እና የአካባቢ ታጣቂዎች ማንነቱ ካልታወቀ ታጣቂ ቢድን ጋር ተዋግተዋል። አንድ የክልሉ ልዩ ሃይል አባል፣ አንድ የፖሊስ አባል እና አንድ የአካባቢ ታጣቂን ጨምሮ ቢያንስ ሶስት የመንግስት ወታደሮች ተገድለዋል።
Source: DW Amharic
27 June 2022: Demonstrations against the killings of civilians in Tole kebele in Gimbi woreda in West Wollega in Oromia region continued. Today, protest against this killing was reported in an area between Georgis church and Papyrus hotel, Peda Gibi in Bahir Dar University and Felege Hiwot hospital in Bahir Dar City in Amhara region. Demonstrators were heard condemning both the ruling Prosperity party and OLF-Shane.
ሰኔ 20, 2014: በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ባልሆኑ ሰዎች ላይ የተደረገውን ግድያ የሚቃወሙ ሰልፎች መካሄዳቸውን ቀጥለዋል። ዛሬ በአማራ ክልል በጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን እና ፓፒረስ ሆቴል መካከል በሚገኝ ቦታ፣ ባህር ዳር ዩንቨርስቲ ፔዳ ጊቢ እና ባህር ዳር ከተማ ፈለገ ህይወት ሆስፒታል ውስጥ የተቃውሞ ሰልፎች ተደርገዋል። የሰልፉ ተሳታፊዎች ገዢው ብልጽግና ፓርቲ እና ኦነግ-ሸኔን አውግዘዋል።
Source: DW Amharic
27 June 2022: Sudanese armed group shelled Gelal Weha area in Korem in West Gondar zone in Amhara region. No causalities were reported. Few days ago, on 22 June 2022, Sudan armed group and Ethiopian farmers clashed in this area, resulting in the killing of one Ethiopian and 16 members of the Sudan armed group. Reportedly, seven of the 16 killed members of the armed group were Ethnic Tigrayans.
ሰኔ 20, 2014: የሱዳን ታጣቂ ቡድን በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ኮረም ውስጥ የሚገኘውን ገላል ውሃ አካባቢ በከባድ መሳሪያ ደብድቧል። ሟች መኖሩ አልተዘገበም። ከተወሰኑ ቀናት በፊት ሰኔ 15 ላይ የሱዳን ታጣቂ ቡድን በአካባቢው ከኢትዮጵያ ገበሬዎች ጋር ተዋግቶ አንድ ኢትዮጵያዊ እና 16 የሱዳን ታጣቂ ቡድኑ አባላት መገደላቸው ተዘግቧል። ከ16ቱ የቡድኑ ሟቾች ውስጥ ሰባቱ የትግራይ ብሄረሰብ አባላት መሆናቸው ተዘግቧል።
Source: DW Amharic
24 June 2022: Students of University of Gondar in Gondar in Amhara region protested against the killings of ethnic Amhara civilians in Tole kebele in Gimbi woreda in West Shewa zone in Oromia region.
ሰኔ 17, 2014: በአማራ ክልል ጎንደር የሚገኘው የጎንደር ዩንቨርስቲ ተማሪዎች በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ባልሆኑ አማራዎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ አውግዘው ሰልፍ አድርገዋል።
Source: University of Gondar
22 June 2022: Sudan armed group and Ethiopian Farmers clashed in Gelal Weha area in Korem in West Gondar zone in Amhara region. One Ethiopian and 16 members of the Sudan armed group were killed due to this clash. Reportedly, seven of the 16 killed members of the armed group were Ethnic Tigrayans.
ሰኔ 15, 2014: የሱዳን ታጣቂ ቡድን እና የኢትዮጵያ ገበሬዎች በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ገላል ውሃ አካባቢ ተዋግተዋል። አንድ ኢትዮጵያዊ እና 16 የሱዳን ታጣቂ ቡድን አባላት በውጊያው ተገድለዋል። ከ16ቱ ሟቾች ውስጥ ሰባቱ የትግራይ ብሄረሰብ አባላት መሆናቸው ተዘግቧል።
Source: DW Amharic
22 June 2022: TPLF forces clashed with Fano militias in various areas in Raya Kobo woreda in North Wello zone in Amhara region, controlling Jarota, Arengebo, Ageda and Addisu Mender areas in the woreda. TPLF forces looted different items from these areas. An unidentified number of people were reportedly killed and injured. More than 160 people were internally displaced due this battle.
ሰኔ 15, 2014: የትህነግ/ህወሃት ሃይሎች ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ የተለያዩ አካባቢዎች የተዋጊ ሲሆን በወረዳው ጃሮታ፣ አረንገቦ፣ አገዳ እና አዲሱ መንደር አካባቢዎችን ተዎጣጥረዋል። የትህነግ/ህወሃት ሃይሎች ከእነዚህ አካባቢዎች የተለያዩ ንብረቶች ዘርፈዋል። ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች መሞታቸውና መቁሰላቸውም ተነግሯል። በዚህ ጦርነት ከ160 በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል።
Source: VOA Amharic
22 June 2022: Sudan military and Ethiopia armed group clashed in al-Koresha town in al-Fashaga (al-Fushqa) area. The area is disputed by both Sudan and Ethiopia. Eight members of Sudan military and one civilian were killed. According to the government of Sudan, ENDF captured and killed seven members of Sudan military and one civilian. The Ethiopian government and ENDF refuted this claim.
ሰኔ 15, 2014: የሱዳን ሰራዊት እና የኢትዮጵያ ታጣቂ ቡድን በአል ፋሻጋ (አል ፉሽቃ) አካባቢ ተዋግተዋል። ስምንት የሱዳን ሰራዊት አባላት እና አንድ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆነ ሰው ተገድለዋል። እንደሱዳን መንግስት ከሆነ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አካባቢውን ተቆጣጥሮ ሰባት የሱዳን ሰራዊት አባላት እና አንድ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆነ ግለሰብን ገድሏል። የኢትዮጵያ መንግስት እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ክሱን ውድቅ አድርገዋል።
Source: DW Amharic; Sudan Tribune; BBC Amharic; The Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia; DW Amharic
23-25 June 2022 : TPLF militants clashed with ENDF, Amhara militias and Fano militias in Semiza Giorgis, Mekenet Garia and Jan Amora kebeles in Kobo woreda in North Wello zone in Amhara region. At least 10 people were killed. TPLF has taken control of the three kebeles of the woreda after the renewed fighting between the Ethiopian government and TPLF forces that lasted for three days.
ሰኔ 16-18, 2014: በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ወረዳ በሴሚዛ ጊዮርጊስ፣ መቀነት ጋሪያ እና ጃን አሞራ ቀበሌዎች የትህነግ/ህወሃት ታጣቂዎች ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ታጣቂዎችን እና ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር ተዋግተዋል። ቢያንስ 10 ሰዎች ተገድለዋል። ሶስት ቀን ከዘለቀው በኢትዮጵያ መንግስት እና የትህነግ/ህወሃት ሃይሎች መካከል የተደረገው ውጊያ በኋላ ትህነግ/ህወሃት በወረዳው ያሉ ሶስት ቀበሌዎችን ተቆጣጥሯል።
Source: Addis Maleda
18 June 2022: OLF-Shane and government forces clashed in Tole kebele in Gimbi woreda in West Wollega zone in Oromia region. At around the same time, or shortly after, OLF-Shane attacked and killed at least 338 civilians, mostly ethnic Amharas in the kebele. The attack also spread to the nearby Se kebele in Bolo Jingafoy (Miziga) woreda in Kamashi zone in Benshangul/Gumuz region, resulting in the death of ‘hundreds’ of civilians. OLF-Shane denied this claim and accused the government forces of being responsible for the attack. The EPO is following developments closely and will provide updates.
ሰኔ 11, 2014: ኦነግ-ሸኔ እና የመንግስት ሃይሎች በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ውስጥ ተዋግተዋል። በተመሳሳይ ሰዓት ወይም ብዙም ሳይቆይ ኦነግ-ሸኔ በቀበሌው ውስጥ ጥቃት በመሰንዘር ባብዛኛው የአማራ ተወላጆች የሆኑ በትንሹ 338 ሰላማዊ ሰዎችን ገድሏል። ጥቃቱ በአቅራቢያው ወደ ሚገኘው በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል በካማሺ ዞን ቦሎ ጂንጋፎይ (ምዥጋ) ወረዳ ሴ ቀበሌ በመዛመት ‘በመቶዎች’ ለሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች ሞት ምክንያት ሆኗል። ኦነግ-ሸኔ ይህንን ክስ ውድቅ ያደረገ ሲሆን የመንግስት ሃይሎችን ለጥቃቱ ተጠያቂ አድርጓል። ኢፒኦ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ ሲሆን ወቅታዊ ሁኔታዎችን እና መረጃዎችን ያቀርባል።
Source: AP News; Office of the Prime Minister – Ethiopia; DW Amharic
16 June 2022: Security forces in Gambela city shot and killed at least 10 civilians, many of them ethnic Oromo, after accusing them of being associated with OLF-Shane or the Gambela Liberation Front. The OLF-Shane is designated as a terrorist group by the Ethiopian government.
ሰኔ 9, 2014: የጸጥታ ሃይሎች በጋምቤላ ከተማ በኢትዮጵያ መንግስት አሸባሪ ከተባሉት ኦነግ-ሸኔ እና የጋምቤላ ነጻነት ግንባር ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል አብዛኞቹ ኦሮሞ የሆኑ ቢያንስ አስር ሰዎችን ገድለዋል። ኦነግ-ሸኔ በኢትዮጵያ መንግስት አሸባሪ ድርጅት ተብሎ የታወጀ ድርጅት ነው።
Source: Addis Standard
14 June 2022: Members of the Gambela Liberation Front (GLF) and OLF-Shane clashed with government security forces in Gambela town in Gambela region, resulting in the killing of at least 37 people, including 11 members of government security forces and 26 members of the armed groups. At least, 39 members of government security forces and three civilians were also injured due to this clash. One member of GLF who was injured and seeking help from a medical center was captured. The security forces managed to regain control of the town in the afternoon. A night curfew is in place and residents are advised to stay at home.
ሰኔ 7, 2014: በጋምቤላ ክልል ጋምቤላ ከተማ የጋምቤላ ነጻነት ግንባር እና ኦነግ-ሸኔ አባላት ከመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ጋር ባደረጉት ውጊያ 11 የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች እና 26 የታጣቂ ቡድኖቹን አባላት ጨምሮ ቢያንስ 37 ሰዎች ተገድለዋል። በዚህ ግጭት ቢያንስ 39 የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች እና ሶስት በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎች ቆስለዋል። ቆስሎ ከህክምና ማዕከል ድጋፍ እያገኘ የነበረ አንድ የጋምቤላ ነጻነት ግንባር አባል ተይዟል። የጸጥታ ሀይሎች ከተማዋን ከሰአት በኋላ በድጋሚ ለመቆጣጠር ችለዋል። የምሽት ሰዓት እላፊ የተደረገ ሲሆን ነዋሪዎች እቤት እንዲቆዩ ተመክረዋል።
Source: Gambella Regional Gov’t Press Secretariat Office; BBC Amharic
14 June 2022: OLF-Shane clashed with government security forces in Dembi Dollo town in Kellem Wollega zone and Gimbi town in West Wollega zone in Oromia region. The armed group managed to control part of these towns. Casualties unknown.
ሰኔ 7, 2014: ኦነግ-ሸኔ በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ደምቢ ዶሎ ከተማ እና ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ከተማ ላይ ከመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ጋር ተጋጭተዋል። ቡድኑ የከተሞቹን የተወሰኑ ቦታዎች መቆጣጠር ችሏል። የደረሰው ጉዳት አልታወቀም።
Source: BBC Amharic; TIKVAH Ethiopia; TIKVAH Ethiopia
10 June 2022: Three students were injured due to an explosion of a heavy artillery shell left in a garbage at Silk Amba School around Michael Jerba area in Dessie town in Amhara region.
ሰኔ 3, 2014: በአማራ ክልል ደሴ ከተማ ሚካኤል ጀርባ አካባቢ የሚገኘው ስልክ አምባ ትምህርት ቤት አካባቢ በቆሻሻ ውስጥ የተተወ ከባድ መሳሪያ ፈንድቶ ሶስት ተማሪዎችን ተጎድተዋል።
10 June 2022: ENDF announced it has conducted a military operation against OLF-Shane rebels in Likiti kebele in Kondala woreda in West Wollega zone in Oromia region. ENDF claimed to have fully liberated the village following the fighting that resulted in the killing of eight and capturing of 15 rebel militants. Several logistics and properties of the rebels were also seized.
ሰኔ 3, 2014: የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ቆንዳላ ወረዳ ሊኪቲ ቀበሌ በኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ማድረጉን አስታውቋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሰፈሩን ሙሉ በሙሉ ነጻ ማውጣቱን እና ስምንት የቡድኑን ታጣቂዎች ገድሎ 15 ታጣቂዎችን ማቁሰሉን አስታውቋል። ብዙ የታጣቂ ቡድኑ ሎጂስቲክስ እና ንብረቶችም መያዛቸውም ተገልጿል።
Source: FDRE Defense Force
9 June 2022: A member of Gambela Liberation Front who was hiding in Newland Secondary school in kebele 01 in Gambela town in Gambela region clashed with Gambela regional special force, injuring one member of the regional special force.
ሰኔ 2, 2014: በጋምቤላ ክልል ጋምቤላ ከተማ ቀበሌ 01 ኒውላንድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተደብቆ የነበረ የጋምቤላ ነጻነት ግንባር አባል ከጋምቤላ ክልል ልዩ ሃይል ጋር ተዋግቶ የክልሉን ልዩ ሃይል አንድ አባል አቁስሏል።
Source: Gambella Regional Gov’t Press Secretariat Office; ESAT
6 June 20222: Members of Burji ethnic group protest the attack against members of Guji ethnic group in Soyama town in Burji special woreda.
ግንቦት 29, 2014: የቡርጂ ብሄረሰብ አባላት በቡርጂ ልዩ ወረዳ ሶያማ ከተማ በጉጂ ብሄረሰብ ቡድን ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አውግዘው ሰልፍ አድርገዋል።
Source: Burji Special Woreda Government Communication Affairs
25 April – 6 June 2022: The Ethiopian National Defense Force (ENDF) has conducted military operations against OLF Shane militants in Dibate woreda, Metekel Zone, in Benshangul/Gumuz regional state since 25 April 2022. The ENDF claimed it has destroyed a training center used by the rebel militants in Bonfo Kebele, killing 43 members of the group, and taken over control of four villages in Dibate and Bulan woredas that had been under the control of the group for over three years. Several weapons and logistics were also seized.
ሚያዚያ 17 – ግንቦት 29, 2014: ሚያዚያ 17 – ግንቦት 29, 2014: የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት መተከል ዞን ድባጤ ወረዳ በኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች ላይ ከሚያዚያ 17 ጀምሮ ወታደራዊ ዘመቻዎችን አድርጓል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በቦንፎ ከተማ ታጣቂዎቹ የሚጠቀሙበትን የስልጠና ማዕከል አውድሞ 43 የቡድኑን አባላት መግደሉንና በድባጤ እና ቡለን ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙና ከሶስት አመታት በላይ በቡድኑ ቁጥጥር ስር የነበሩ አራት መንደሮች መቆጣጠሩን ገልጿል። በርካታ የጦር መሳሪያዎችና ሎጅስቲክስም በቁጥጥር ስር ውሏል።
Source: EBC
4 June 2022: Ethnic Burji rioters beat to death nine ethnic Oromos from Guji zone and injured 21 others at Soyama town market in Burji Special woreda in SNNPR. The victims were from Suro Bargudah woreda in Guji zone in Oromia region who travelled to the area to sell and buy items at the market. This attack was conducted after a rumor of one ethnic Burji person was killed by ethnic Oromos from Guji zone at an unidentified kebele resurfaced but according to officials he was killed by OLF-Shane.
ግንቦት 27, 2014: በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ቡርጂ ልዩ ወረዳ በሶያማ ከተማ ገበያ የቡርጂ ብሄረሰብ ተወላጆች ዘጠኝ የጉጂ ኦሮሞዎችን በድብደባ የገደሉ ሲሆን ሌሎች 21 አቁስለዋል። ተጎጂዎቹ ከኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ሱሮ ባርጉዳህ ወረዳ ሆነው ወደ አካባቢው የገበያ ላይ እቃዎችን ለመግዛት የተጓዙ ግለሰቦች ናቸው። ይህ ጥቃት የተፈፀመው ከጉጂ ዞን የመጡ የኦሮሞ ተወላጆች አንድ የቡርጂን ተወላጅ ባልታወቀ ቀበሌ ውስጥ ገድለዋል የሚል ጭምጭምታ ከተሰማ በኋላ ነው፤ ባለስልጣናት ግድያው የተፈጸመው ነው በኦነግ-ሸኔ ነው ብለዋል።
Source: DW Amharic
2-3 June 2022: Afar ethnic militias and local securities forces clashed for two days in Worku Addis area in Argoba Special woreda in Amhara region, following the Afar ethnic militias’ attack on civilians in the area. At least one fatality and two injuries were reported due these events. These armed clashes occurred after one ethnic Afar was killed by an unidentified person while returning from Medina marketplace in Argoba Special woreda on 31 May 2022.
ግንቦት 25 – 26, 2014: በአማራ ክልል አርጎባ ልዩ ወረዳ ወርቁ አዲስ በተባለው አካባቢ የአፋር ብሄረሰብ ታጣቂዎች በአካባቢው በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ባልሆኑ ሰዎች ላይ ያደረሱትን ጥቃት ተከትሎ የአፋር ብሄረሰብ ታጣቂዎች እና የአካባቢው የጸጥታ ሃይሎች ለሁለት ቀናት ተዋግተዋል። በእነዚህ ኩነቶች ቢያንስ አንድ ሟች እና ሁለት ቁስለኞች እንደነበሩ ተዘግቧል። እነዚህ ውጊያዎች የተከሰቱት ግንቦት 23 ላይ ከአርጎባ ልዩ ወረዳ መዲና ገበያ እየተመለሰ የነበረ አንድ አፋር ባልታወቀ ግለሰብ ከተገደለ በኋላ ነው።
Source: VOA Amharic
2 June 2022: Reportedly, two police officers beat journalist Temesgen Dessalegn in Sosetegna Police Station in Addis Ababa where he has been held since his arrest on 26 May 2022.
ግንቦት 25, 2014: ሁለት የፖሊስ አባላት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ከግንቦት 18 ጀምሮ በእስር ላይ ባሉበት አዲስ አበባ በሚገኘው የሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ድብደባ እንደፈጸሙባቸው ተዘግቧል።
Source: DW Amharic
1 June 2022: Members of Gumuz People’s Democratic Movement (GPDM) clashed with Benshangul/Gumuz regional special forces in Soge town in Miziga woreda in Kamashi zone in Benshangul/Gumuz region, resulting in the killing of 19 people, including 16 members of GPDM, the Miziga woreda chief administrator, a local investor and his son. On the next day, the regional special forces were also besieged by the GPDM militants in Kamashi town in Kamashi zone.
ግንቦት 24, 2014: በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ሚዚጋ ወረዳ ሶጌ ከተማ የጉሙዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉህዴን) አባላት ከቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል ልዩ ሃይሎች ጋር ባደረጉት ውጊያ 16 የንቅናቄውን አባላትን፣ የሚዚጋ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እንዲሁም አንድ የአካባቢውን ባለሃብት እና ልጃቸውን ጨምሮ 19 ሰዎች ተገድለዋል። በቀጣዩ ቀን የክልሉ ልዩ ሃይሎች በካማሺ ዞን ካማሺ ከተማ በጉህዴን ታጣቂዎች ተከበው ነበር።
Source: Ethiopian Reporter
1 June 2022: Members of Gambela Liberation Front and OLF-Shane shot and killed two civilians while they were farming in Goli kebele in Gambela woreda in Agnewak zone in Gambela region. Three more people were also abducted by the armed groups.
ግንቦት 24, 2014: የጋምቤላ ነጻነት ግ ንባር እና ኦነግ ሸኔ በጋምቤላ ክልል አኝዋክ ዞን ጋምቤላ ወረዳ ጎሊ ቀበሌ ውስጥ በእርሻ ላይ የነበሩ ሁለት በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ተኩሰው ገድለዋል። ሶስት ተጨማሪ ሰዎች በቡድኖቹ ታግተዋል።
28-29 May 2022: Tigray regional government accused the Eritrean Defense Forces (EDF) of shelling Shiraro town with artilleries, in North Western zone of Tigray Regional State on 28 May 2022 and 29 May 2022. At least one civilian was.killed and 18 people were injured. On 24 May 2022, the two forces also clashed in Western part of Adi Aw’ala, in Adi Hageray woreda, in North Western zone of Tigray Regional State. The TPLF claimed to have repelled the EDF attacks and killed 120 soldiers, including a brigade commander and three battalion commanders, wounded 195, and captured four EDF soldiers.
ግንቦት 20-21, 2014: የትግራይ ክልል መንግስት የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት ግንቦት 20 እና 21 ላይ በትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ ዞን ሽራሮ ከተማ ላይ ፈጸሟል ሲል ከሷል። ቢያንስ አንድ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆነ ሰው ተገድሏል እንዲሁም 18 ሰዎች ቆስለዋል። ግንቦት 16, 2014 ላይ ሁለቱ ሃይሎች በትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ ዞን አዲ ሃገራይ ወረዳ ምዕራብ አዲ አዋላ ተዋግተዋል። ትህነግ/ህወሃት የኤርትራ መከላከያ ሰራዊትን ጥቃት መመከቱን እና አንድ የብርጌድ እና ሶስት የሻለቃ አዛዦችን ጨምሮ 120 ወታደሮችን መግደሉን እንዲሁም 195 የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት አባላትን አቁስሎ አራት አባላትን መማረኩን ገልጿል።
Source: Reuters; BBC News Amharic
21 May 2022: An unidentified armed group attacked Ukugo Refugee Camp in Dema woreda in Anuak zone in Gambela region and killed four people. Similarly, on the same day, an unidentified armed group attacked civilians in Merkes kebele and killed two people.
ግንቦት 13, 2014: በጋምቤላ ክልል አኙዋክ ዞን ዲማ ወረዳ ኡኩጎ የስደተኞች መጠለያ ላይ ማንነቱ ያልታወቀ ታጣቂ ቡድን ጥቃት አድርሶ አራት ሰዎችን ገድሏል። በተመሳሳይ በዛው እለት ማንነቱ ያልታወቀ ታጣቂ ቡድን በመርከስ ቀበሌ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ባልሆኑ ሰዎች ላይ ጥቃት አድርሶ ሁለት ሰዎችን ገድሏል።
20 May 2022: Unidentified number were killed and at least nine people were injured due to a dispute between a youth group who asked for the release of one arrested person and security forces in Woldiya town in North Wello zone, Amhara region. Armed clashes between the unidentified armed group and security forces were also reported in Merawi in West Gojam zone. These clashes follow the regional government’s “law enforcement” operations in the region.
ግንቦት 12, 2014: በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ አንድ የታሰረ ግለሰብ እንዲፈታ በጠየቁ የወጣቶች ቡድን እና የጸጥታ ሃይሎች መካከል በተነሳ ግጭት ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች ሲሞቱ ቢያንስ ዘጠኝ ሰዎች ቆስለዋል። በምዕራብ ጎጃም ዞን መርዓዊም ማንነቱ ባልታወቀ ታጣቂ ቡድን እና የጸጥታ ሃይሎች መካከል ውጊያዎች መከሰታቸውም ታውቋል። እነዚህ ግጭቶች የክልሉ መንግስት በክልሉ የጀመረውን “የህግ ማስከበር” እርምጃ ተከትሎ የተፈጠሩ ናቸው።
Source: DW Amharic
19 May 2022: Members of Fano armed group and government forces clashed in Mota in East Gojam zone in Amhara region, when government forces tried to disarm the group’s members. Due to this clash, at least two people were killed. Public institutions, banks, schools, businesses and roads linking the town to Bahir Dar and Addis Ababa were closed due to the armed clash.
ግንቦት 11, 2014: በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ የመንግስት ሃይሎች የቡድኑን አባላት ትጥቅ ለማስፈታት መሞከራቸውን ተከትሎ የፋኖ ታጣቂ ቡድን አባላት እና የመንግስት ሃይሎች ተዋግተዋል። በዚህ ውጊያ ቢያንስ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል። በውጊያው ምክንያት የህዝብ ተቋማት፣ ባንኮች፣ ትምህርት ቤቶች፣ንግዶች እና ከተማዋን ከባህርዳርና አዲስ አበባ የሚያገናኙ መንገዶች ተዘግተዋል።
Source: BBC Amharic
19 May 2022: Members of OLF-Shane attacked civilians in Tifat kebele in Amaro Special woreda in SNNPR, killing two children. The group also looted around 40 cattle.
ግንቦት 11, 2014: በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ ትፋተ ቀበሌ የኦነግ-ሸኔ አባላት በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ባልሆኑ ሰዎች ላይ ባደረሱት ጥቃት ሁለት ህጻናት ተገድለዋል። ቡድኑ 40 የሚደርሱ የቀንድ ከብቶችንም ዘርፏል።
Source: VOA Amharic
17 May 2022: A bomb, reportedly left behind by TPLF fighters, exploded and killed one person and three children in Bati area of the Oromia special zone, Amhara region.
ግንቦት 9, 2014: በአማራ ክልል ኦሮሚያ ልዩ ዞን ባቲ አካባቢ በትህነግ/ህወሃት ታጣቂዎች የተተወ ነው የተባለ ቦምብ ፈንድቶ አንድ ሰው እና ሶስት ህጻናት ገድሏል።
Source: Fana Broadcasting Corporate
14 May 2022: An unidentified armed group opened gunfire on local officials and communal leaders attending an inter-communal mediation meeting in Chekorsa kebele, Bati woreda, in the Oromo Special zone of Amhara regional state, killing at least four people and wounding ten. The meeting was aimed at settling the sporadic clashes between pastoralists from Oromo Special Zone of Amhara and Zone 1 of Afar regional states.
ግንቦት 6, 2014: ማንነቱ ያልታወቀ ታጣቂ ቡድን በአማራ ክልል ኦሮሞ ልዩ ዞን ባቲ ወረዳ ጨቆርሳ ቀበሌ በማህበረሰቡ መካከል እየተካሄደ በነበረ የሽምግልና ስብሰባ ላይ በመሳተፍ ላይ የነበሩ የአካባቢ ባለስልጣናት እና የማህበረሰብ መሪዎች ላይ ተኩስ ከፍቶ ቢያንስ አራት ሰዎችን ሲገድል 10 አቁስሏል። ስብሰባው በአማራ ክልል ኦሮሞ ልዩ ዞን እና በአፋር ክልል ዞን 1 አርብቶ አደሮች መካከል አልፎ አልፎ የሚፈጠረውን ግጭት ለመፍታት ያለመ ነበር።
Source: VOA Amharic
9 May 2022: Ethiopian National Defense Force (ENDF), Federal Police, and Regional Special Police Forces of Southern Nations Nationalities and People’s Region (SNNPR) exchanged gunfire with communal armed groups in Hataya and Selele rural kebeles, near Gedole town in Derashe special woreda, SNNPR. The clash resulted in the deaths and displacement of an unknown number of people. The federal and regional military forces have jointly taken over the administrative and security responsibilities of Derashe special woreda, following the recent armed clashes that resulted in the killing of local government officials, destruction of property, and an unknown number of fatalities from both militants and government forces in April 2022.
ግንቦት 1, 2014: በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ደራሼ ልዩ ወረዳ ገዶሌ ከተማ አቅራቢያ በሚገኙት የሀታያ እና ሰለሌ የገጠር ቀበሌዎች የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ የፌደራል ፖሊስ እና የክልሉ ልዩ ፖሊስ ሃይሎች ከአካባቢ ታጣቂዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርገዋል። ግጭቱን ተከትሎ ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ ሰዎች ሲሞቱ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ተፈናቅለዋል። ሚያዚያ 2014 ላይ በአካባቢው በተከሰተው ውጊያ የአካባቢው የመንግስት ባለስልጣናት ከተገደሉ፣ ንብረት ከወደመ እና ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ተዋጊዎች ከታጣቂዎች እና ከመንግስት ሃይሎች ከሞቱ በኋላ የፌደራልና የክልል ወታደራዊ ሃይሎች በጋራ በመሆን የደራሼ ልዩ ወረዳን የአስተዳደርና የጸጥታ ሃላፊነት ተረክበዋል።
Source: DW Amharic
8 May 2022: TPLF forces launched artillery attacks against the Eritrean Defense Force (EDF) positions in Badme (Shambuqo, Gash Barka), around areas bordering Ethiopia with Eritrea. The EDF also exchanged gunfire with the TPLF following the attack on Eritrean troops in Rama, Central Tigray, Tigray region. Casualties are unknown. The EDF has controlled Badme town since November 2020, when the fighting started between TPLF and ENDF. The 2018 Ethio-Eritrean peace deal also marked the commitment of the Ethiopian government to return the town to Eritrea according to the 2002 UN Boundary Commission Decision in the Hague and Ethio-Eritrea Algiers Agreement in 2000.
ሚያዚያ 30, 2014: የትህነግ/ህወሃት ሃይሎች ኢትዮጵያን ከኤርትራ ጋር በሚያዋስኑ በኤርትራ መከላከያ ሰራዊት የተያዙ የባድመ (ሻምቡቆ፣ ጋሽ ባርካ) አካባቢዎች ላይ የመድፍ ጥቃት ሰንዝረዋል። ጥቃቱን ተከትሎ የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት ከትህነግ/ህወሃት ሃይሎች ጋር በትግራይ ክልል መአከላዊ ትግራይ ራማ የተኩስ ልውውጥ አድርገዋል። የደረሰው ጉዳት አይታወቅም። ባድመ ከተማ ህዳር 2013 ላይ በትህነግ/ህወሃት እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መካከል ጦርነት ከጀመረ አንስቶ በኤርትራ መከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ይገኛል። የ2010 የኢትዮ-ኤርትራ የሰላም ስምምነት የኢትዮጵያ መንግስት በ1992 በተደረሰው የኢትዮ-ኤርትራ አልጀርስ ስምምነት መሰረት በ1995 የተባበሩት መንግስታት የድንበር ኮሚሽን በሄግ ያሳለፈውን ውሳኔ በማክበር ከተማዋን ወደ ኤርትራ ለመመለስ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየበት ነው።
Source: BBC News Amharic
2 May 2022: Federal police dispersed rioters using tear gas and gunfire after clashes between police and Muslim worshippers were sparked in Addis Ababa’s Meskel Square during the Eid al-Fitr celebration. The exact cause of the riot is unclear, although some sources indicate that police fired tear gas in the women’s section of the prayer after some individuals started protesting the targeting of Muslims in Gondar city earlier in the week. Some injuries were reported, and no fatalities occurred.
ሚያዚያ 24, 2014: በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የኢድ አልፈጥር በአል ላይ በፖሊስ እና የእስልምና እምነት ተከታዮች መካከል ግጭት መፈጠሩን ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ እና ተኩስ በመጠቀም ተሳታፊዎችን በትኗል። የግጭቱ ትክክለኛ መነሻ ባይታወቅም አንዳንድ ምንጮች በሳምንቱ መጀመሪያ በጎንደር ከተማ በሙስሊሞች ላይ የደረሰውን ጥቃት በመቃወም አንዳንድ ግለሰቦች ተቃውሞ ማሰማታቸውን ተከትሎ ፖሊስ ሴቶች በሚጸልዩበት በኩል አስለቃሽ ጭሽ በመተኮሱ እንደሆነ ጠቁመዋል። ምንም ሞት ባይኖርም የተወሰኑ ጉዳቶች ግን ተዘግበዋል።
Source: DW
29 April 2022: Unrest continued in Silte zone in SNNPR. A third orthodox church was burned by Muslims in Silte zone. A day earlier, Muslim protesters in Werabe in Silte zone who protested the attack on Gondar Muslims attacked and burned two Orthodox and three Protestant churches.
ሚያዚያ 21, 2014: በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ስልጤ ዞን አለመረጋጋት ቀጥሏል። በስልጤ ዞን ሶስተኛ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በሙስሊሞች ተቃጥሏል። ከአንድ ቀን በፊት በጎንደር ሙስሊሞች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በመቃወም በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ሰልፍ የወጡ ሙስሊሞች ሁለት የኦርቶዶክስ እና ሶስት የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናትን አቃጥለዋል።
Source: EMS
29 April 2022: Muslims protested the attack on Muslims in Gondar city. Protests were held in Jimma (Oromia), Dire Dawa, Semera (Afar) and Werabe (SNNPR). The protest in Dire Dawa and Wearbe turned violent. One four-year-old child was killed while 22 members of Dire Dawa police were injured and banks, properties and vehicles were destroyed by protestors. Eighty-nine people were arrested in Dire Dawa. Muslim protesters in Werabe attacked and burned two Orthodox and three Protestant churches.
ሚያዚያ 21, 2014: በጎንደር ከተማ በሙስሊሞች ላይ የደረሰውን ጥቃት በመቃወም ሙስሊሞች ሰልፍ አካሂደዋል። በጅማ (ኦሮሚያ)፣ ድሬዳዋ፣ ሰመራ (አፋር) እና ወራቤ (ደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል) የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል። በድሬዳዋ እና በወራቤ የተካሄደው ሰልፍ ወደ ብጥብጥ ተለውጧል። አንድ የአራት አመት ህፃን ሲሞት 22 የድሬዳዋ ፖሊስ አባላት ቆስለዋል እንዲሁም ባንኮች፣ ንብረቶችና ተሽከርካሪዎች በሰልፈኞች ወድመዋል። በድሬዳዋ 89 ሰዎች ታስረዋል። በወራቤ ሙስሊም ሰልፈኞች ሁለት የኦርቶዶክስ እና ሶስት የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናትን አቃጥለዋል።
Source: DW Amharic; DW Amharic; EMS
28 April 2022: Two mosques were burned and at least two people were killed in Debark town in North Gondar zone in Amhara region after rumours of a burned orthodox church surfaced in the town.
ሚያዚያ 20, 2014: የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መቃጠሉ ጭምጭምታ በከተማው ከተንሰራፋ በኋላ በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ ሁለት መስጊዶች ሲቃጠሉ ቢያንስ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል።
Source: BBC Amharic
28 April 2021: Unrest continued in Gondar city. Three people were killed and properties were damaged due to unrest after a funeral ceremony of people who were killed by the 26 April 2022 attack on Muslims by Orthodox Christians in Gondar city.
ሚያዚያ 20, 2014: በጎንደር ከተማ ያለው አለመረጋጋት ቀጥሏል። ሚያዚያ 18, 2014 ላይ በጎንደር ከተማ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙስሊሞች ላይ በፈጸሙት ጥቃት ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች የቀብር ስነ-ስርዓት ከተፈጸመ በኋላ በተፈጠረ አለመረጋጋት የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ንብረቶች ወድመዋል።
Source: EBC; DW Amharic
27 April 2022: Konso ethnic militias attacked civilians and destroyed hundreds of civilians’ homes in Gato kebele in Derashe Special woreda in SNNPR, forcing thousands of civilians to evacuate the area. An unidentified number of civilians are also killed in this attack. A day earlier, Gumayde ethnic militias, who are allegedly supported by armed groups from Derashe Special woreda, kidnapped eight foreign tourists travelling from Arba Minch town to Jinka.
ሚያዚያ 19, 2014: በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ደራሼ ልዩ ወረዳ ጋቶ ቀበሌ የኮንሶ ብሄረሰብ ታጣቂዎች በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎች ላይ ጥቃት ሰንዝረው በመቶዎች የሚቆጠሩ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎችን ቤቶች ማውደማቸውን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ተገደዋል። በዚህ ጥቃት ቁጥራቸው ያልታወቁ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ህይወት አልፏል። ከአንድ ቀን በፊት በደራሼ ልዩ ወረዳ ታጣቂ ቡድኖች ይደገፋሉ የተባሉ የጉማይዴ ማህበረሰብ ታጣቂዎች ከአርባ ምንጭ ከተማ ወደ ጂንካ ይጓዙ የነበሩ ስምንት የውጭ አገር ጎብኚዎችን አግተዋል።
Source: VOA Amharic
27 April 2021: Thousands of Muslims in Addis Ababa protests against the attack on Muslims in Gondar and demanded justice for the victims in front of the Grand Anuwar Mosque in Addis Ababa. A similar protest was also held in Jimma town in Oromia region. According to the Addis Ababa Islamic Affairs’ High Council 21 people were killed, mosques and Qurans were burned, women were raped and properties belonging to Muslims were destroyed during the 26 April 2022 attack on Muslims by members of Orthodox Christian church in Gondar city on Amhara region.
ሚያዚያ 19, 2014: በሺዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ሙስሊሞች በአዲስ አበባ ታላቁ አንዋር መስጊድ ፊት ለፊት ተገኝተው በጎንደር ሙስሊሞች ላይ የደረሰውን ጥቃት አውግዘው ለተጎጂዎች ፍትህ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። በኦሮሚያ ክልል በጅማ ከተማም ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል። ሚያዝያ 18 ላይ በጎንደር ከተማ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ ባደረሱት ጥቃት 21 ሰዎች ተገድለዋል፣ መስጊዶች እና ቁርዓን ተቃጥለዋል፣ ሴቶች ተደፍረዋል እንዲሁም የሙስሊሞች ንብረቶች ወድመዋል ሲል የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አሳውቋል።
Source: Addis Standard; Tikvah-Ethiopia
26 April 2022: Gumayde ethnic militias, who are allegedly supported by armed groups from Derashe Special woreda, kidnapped eight foreign tourists and an unidentified number of Ethiopians travelling from Arba Minch town to Jinka, after attacking their vehicle, the driver and a member of ENDF in Derashe Special woreda in SNNPR. An unknown number of federal police officers and members of the SNNP regional special forces were also killed as they enter the woreda to rescue the kidnapped tourists.
ሚያዚያ 18, 2014: በደራሼ ልዩ ወረዳ ታጣቂ ቡድኖች ይደገፋሉ የተባሉ የጉማይዴ ማህበረሰብ ታጣቂዎች ከአርባ ምንጭ ከተማ ወደ ጂንካ ይጓዙ የነበረ መኪና ሹፌር እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባል ላይ ጥቃት ከፈጸሙ በኋላ ስምንት የውጭ ሀገር ጎብኚዎችን እና ቁጥራቸው ያልታወቀ ኢትዮጵያውያንን አግተዋል። ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የፌደራል ፖሊስ አባላት እና የክልሉ ልዩ ሃይሎች አባላት የታገቱትን ጎብኚዎች ለማስለቀቅ ወደወረዳው ሲገቡ ተገድለዋል።
Source: VOA Amharic
26 April 2022: Members of Orthodox Christian attacked Muslims in Gondar city in Amhara region after a conflict erupted at the funeral of a prominent local Sheik. More than 20 people were killed and 150 people were injured due to this unrest. Mosques were burned and properties of Muslims were also looted.
ሚያዚያ 18, 2014: በአማራ ክልል በጎንደር ከተማ በአንድ ታዋቂ ሼኽ የቀብር ስነስርዓት ላይ በተፈጠረ ግጭት የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙስሊሞች ላይ ጥቃት ፈጸሙ። በዚህ ጥቃት ከ20 በላይ ሰዎች ሲሞቱ 150 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል። መስጊዶች ተቃጥለዋል እንዲሁም የሙስሊሞች ንብረቶች ተዘርፈዋል።
Source: Amhara Media Corporation; BBC Amharic
17-18 April 2022: Armed clashes between OLF-Shane and Ethiopian military and Amhara regional special police forces erupted in Eferataena Gidim woreda and in Shewa Robit woreda in North Shewa zone in Amhara region. Due to the clashes, the main highway linking Addis Ababa to Dessie is closed. Causalities unknown.
ሚያዚያ 9-10, 2014: በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ እና ሸዋ ሮቢት ወረዳ በኦነግ-ሸኔ እና በኢትዮጵያ መከላከያ እንዲሁም የአማራ ክልል ልዩ ፖሊስ ሃይሎች መካከል ውጊያዎች ተከስተዋል። በግጭቱ ምክንያት አዲስ አበባን ከደሴ የሚያገናኘው ዋና አውራ ጎዳና ተዘግቷል። ጉዳቶች መኖራቸው አልታወቀም።
Source: DW Amharic
11 April 2022: Over the past few days, violent riots have erupted in Jinka and surrounding towns in South Western Omo zone, in Southern Nations Nationalities and People’s Regional State (SNNP), resulting in the death of at least one person and wounding of several people. The violence followed the Ari ethnic group’s demand to upgrade their woreda administration to zonal status. Public and private properties were also destroyed.
ሚያዚያ 3, 2014: ባለፉት ቀናት በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ጂንካ እና አካባቢው የሚገኙ የደቡብ ምዕራብ ኦሞ ዞን ከተሞች የተከሰቱ አመጾችን ተከትሎ ቢያንስ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ ብዙ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል። ግጭቱ የተቀሰቀሰው የአሪ ብሄር የወረዳ አስተዳደሩን ወደ ዞን አወቃቀር ለማሳደግ ያቀረበውን ጥያቄ ተከትሎ ነው። የህዝብ እና የግል ንብረቶች ወድመዋል።
Source: BBC News Amharic
10 April 2022: Members of ENDF and Fano militias exchanged fire in Woldiya town in North Wello zone in Amhara region after members of Fano militia tried to enter the town following rumors of one Fano militia leader arrest. One militia and one civilian priest were killed due to this clash. The two groups also clashed in Gobeye and Robit areas in North Wello zone. There were no casualties in these areas.
ሚያዚያ 2, 2014: በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ አንድ የፋኖ ታጣቂ አመራር በቁጥጥር ስር ስለመዋሉ ጭምጭታ በመሰማቱ የፋኖ አባላት ወደ ከተማዋ ለመግባት ሙከራ ማድረጋቸውን ተከትሎ ከኢትዮጵያ መከላከያ ጋር እተኩስ ልውውጥ አድርገዋል። በዚህ ግጭት አንድ ታጣቂ እና አንድ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ቄስ ተገድለዋል። በሰሜን ወሎ ዞን ጎበዬ እና ሮቢት አካባቢዎች ሁለቱ ቡድኖች ተዋግተዋል። በእነዚህ አካባቢዎች ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም።
Source: BBC Amharic
3 April 2022: Due to a communal conflict in Halela and Sucha kebeles in Chiri woreda in Sidama region and Shambel and Wero kebeles in West Arsi zone in Oromia region, five people were killed and 15 people were injured. The conflict erupted after a “renown” local elder was killed by an unidentified armed group in Halela kebele in Chiri woreda in Sidama region.
መጋቢት 25, 2014: በሲዳማ ክልል ጭሪ ወረዳ ሃሌላ እና ሱቻ ቀበሌዎች እና በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ሻምበል እና ወሮ ቀበሌዎች በተፈጠረ የአካባቢ ግጭት አምስት ሰዎች ሲሞቱ 15 ሰዎች ቆስለዋል። ግጭቱ የተቀሰቀሰው በሲዳማ ክልል ጭሪ ወረዳ ሀሌላ ቀበሌ አንድ “ታዋቂ” የሀገር ሽማግሌ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ከተገደሉ በኋላ ነው።
Source: Ethiopia Insider
3 April 2022: Organized Youths from Ethiopian Orthodox Christian followers attacked Protestant followers, over claims of worshipping land ownership located at Tullu Dalota, in Kaliti woreda, Finfinne Special Zone, Oromia. The attack resulted in the killing of one person and wounding of several people, as Oromia special police force intervened to stabilize the situation. A Protestant church in Akaki woreda was also damaged and properties destroyed.
መጋቢት 25, 2014: ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች የተወጣጡ ወጣቶች በኦሮሚያ ፊንፊኔ ልዩ ዞን ቃሊቲ ወረዳ ቱሉ ዳሎታ የሚገኝ የአምልኮ ቦታ ባለቤትነት ላይ ተመስርቶ በፕሮቴስታንት ተከታዮች ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል። በጥቃቱ የአንድ ሰው ህይወት ሲጠፋ እና በርካታ ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን የኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ ሃይል ጣልቃ በመግባት ጉዳዩን ለማረጋጋት ሞክሯል። በአቃቂ ወረዳ የሚገኝ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያንም ጉዳት ደርሶበታል፣ ንብረትም ወድሟል።
Source: OMN
2-3 April 2022: Government forces and OLF-Shane clashed in Moyale town in Borena zone in Oromia region. Causalities due to this armed clash is unknown.
መጋቢት 24-25, 2014: በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ሞያሌ ከተማ የመንግስት ታጣቂዎች እና ኦነግ-ሸኔ ተዋግተዋል። በዚህ ውጊያ ምክንያት ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ብዛት አልታወቀም።
Source: BBC Amharic
31 March 2022: Three police officers of Kamashi zone correctional facility (Benshangul/Gumuz) were abducted by an unidentified armed group near Nejo town in West Wollega zone in Oromia region.
መጋቢት 22, 2014: በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ከተማ አቅራቢያ የካማሺ ዞን ማረሚያ ቤት (ቤንሻንጉል/ጉሙዝ) ሶስት የፖሊስ አባላት ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ታፍነው ተወስደዋል።
Source: Ethiopia Insider
29 March 2022: Over the past five days, unidentified armed groups attacked several villages in Bench Sheko, Sheka, and Gura Ferda woredas in Bench Sheko zone of South West Ethiopia Peoples’ region killing three people and looting at least 20 cattle.
መጋቢት 20, 2014: ባለፉት አምስት ቀናት ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት በቤንች ሸኮ ዞን ቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ እና ጉራ ፈርዳ ወረዳዎች በሚገኙ በርካታ መንደሮች ላይ ጥቃት በማድረስ ሶስት ሰዎችን ገድለው ከ20 ያላነሱ ከብቶችን ዘርፈዋል።
Source: Addis Maleda
28 March 2022: Federal Police and Gambela regional police officers exchanged fire in Gambela University campus, in Gambela town, resulting in the death of one person and injuring one. The reason behind the clash between the two government forces is under investigation.
መጋቢት 19, 2014: በጋምቤላ ከተማ በሚገኘው የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የፌደራል ፖሊስና የጋምቤላ ክልል ፖሊስ አባላት የተኩስ ልውውጥ አድርገው የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ አንድ ሰው ቆስሏል። በሁለቱ የመንግስት ሃይሎች መካከል የተፈጠረው ግጭት መንስኤ በመጣራት ላይ ነው።
Source: Addis Maleda
24 March 2022: The Tigray regional government, led by members of the TPLF, has agreed to a “cessation of hostility” for humanitarian assistance.
መጋቢት 15, 2014: በትህነግ አባላት የሚመራው የትግራይ ክልላዊ መንግስት ለሰብአዊ እርዳታ ሲባል “ተኩስ እንዲቆም” ተስማምቷል።
Source: Tigray External Affairs Office
24 March 2022: The Ethiopian government has declared a humanitarian truce in Tigray region.
መጋቢት 15, 2014: የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ሰብአዊ እርዳታ ማድረስ የሚያስችል የተኩስ አቁም አውጇል።
20 March 2022: Somali Region Special Police officers exchanged fire with Somali ethnic militias at the election inauguration ceremony in Bombas, Gursum woreda (Fafan, Somali). Seven people were killed and more than twenty injured.
መጋቢት 11, 2014: የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ አባላት በጉርሱም ወረዳ ቦምባስ (ፋፋን፣ ሶማሌ) በተካሄደ የምርጫ ምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ ከሶማሌ ብሄረሰብ ታጣቂዎች ጋር ተኩስ ተለዋውጠዋል። ሰባት ሰዎች ሲሞቱ ከሃያ በላይ ቆስለዋል።
Source: OMN; Somali Guardian
19 March 2022: Three local militia members and a 12-year-old child died when a bomb explosion occurred during a graduation ceremony of local militias in Bulbula town stadium, East Shewa zone in Oromia region. 35 additional people were injured as a result of the blast. No group has claimed responsibility for the attack.
መጋቢት 10, 2014: በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ቡልቡላ ከተማ ስታዲየም የአካባቢው ታጣቂዎች የምርቃት ስነ ስርዓት ላይ በደረሰ የቦንብ ፍንዳታ ሶስት የአካባቢው ታጣቂ ቡድን አባላት እና የ12 አመት ህፃን ህይወት አልፏል። በፍንዳታው ተጨማሪ 35 ሰዎች ቆስለዋል። ለጥቃቱ ሃላፊነቱን የወሰደ አካል የለም።
Source: BBC Amharic
17 March 2021: Twenty people were injured and five students of Semera University were arrested in Semera town, Afar region when the Afar regional special force and police tried to disperse an anti-TPLF protest.
መጋቢት 8, 2014: በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ የአፋር ክልል ልዩ ሃይል እና ፖሊስ ትህነግን ለመቃወም የተደረገን ሰልፍ ለመበተን በሞከሩበት ወቅት ሃያ ሰዎች ቆስለዋል፣ አምስት የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ደግሞ ታስረዋል።
Source: Ethiopian Insider
15 March 2022: Members of Murle ethnic armed group from South Sudan clashed with Gambela regional special forces and militias in Aliya kebele in Itang special woreda in Gambela region.
መጋቢት 6, 2014: ከደቡብ ሱዳን የመጡ የሙርሌ ብሄረሰብ ታጣቂዎች ከጋምቤላ ክልል ልዩ ሃይሎች እና ታጣቂዎች ጋር በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ አሊያ ቀበሌ ተዋግተዋል።
13 March 2022 (as reported): Unidentified armed group from South Sudan attacked civilians, killing one civilian and injuring six others at the border of South Sudan and Ethiopia in Lare and Jikawo woreda in Nuer zone in Gambela region. Due to this attack, 9,500 people including South Sudanese are internally displaced.
መጋቢት 6, 2014 (እንደተዘገበው): በጋምቤላ ክልል ኑዌር ዞን ላሬ እና ጂካዎ ወረዳ በደቡብ ሱዳን እና ኢትዮጵያ ድንበር ላይ ከደቡብ ሱዳን የመጡ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ባልሆኑ ሰዎች ላይ ጥቃት ሰንዝረው አንድ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆነ ሰው ሲገድሉ ሌሎች ስድስት ሰዎች አቁስለዋል። በዚህ ጥቃት ደቡብ ሱዳናውያንን ጨምሮ 9,500 ሰዎች ተፈናቅለዋል።
Source: Fana Broadcasting Corporate
13 March 2022: An unknown number of students were injured due to ethnic-based conflict in Addis Ababa University in Addis Ababa. The government arrested an unidentified number of people who are accused of inciting the conflict.
መጋቢት 6, 2014: በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተነሳ ብሔርን መሰረት ያደረገ ግጭት ምክንያት ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ ተማሪዎች ቆስለዋል። መንግስት ግጭቱን አነሳስተዋል የተባሉ ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል።
Source: DW Amharic; Fana Broadcasting Corporate
6 March 2022: Fano militias and regional government security forces clashed in Mota town, in East Gojjam, Amhara Region, resulting in the death of four people. The combatants exchanged fire following the arrest of a Fano leader by government forces after he refused to stop training Fano members in Mota town.
የካቲት 27, 2014: በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ሞጣ ከተማ የፋኖ ታጣቂዎች እና የክልሉ መንግስት የጸጥታ ሃይሎች መካከል በተደረገ ውጊያ የአራት ሰዎች ህይወት አልፏል። በሞጣ ከተማ የፋኖ አባላትን ማሰልጠን አላቆምም ያለ አንድ የፋኖ አመራር በመንግስት ሃይሎች መታሰራቸውን ተከትሎ ሁለቱ ቡድኖች የተኩስ ልውውጥ አድርገዋል።
Source: Wazema Radio
3 March 2022: Various security forces associated with the Ethiopian military and regional special forces shot, killed, and burned 10 civilians (eight ethnic Tigrayans and two ethnic Gumuz). Security forces then burned alive an 11th Tigrayan in Ayceed kebele in Guba woreda in Metekel zone, Benshangul/Gumuz. Those killed were accused of providing information to an unidentified armed group that ambushed a bus transporting visitors to the Grand Ethiopia Renaissance Dam.
የካቲት 24, 2014: ከኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች እና ከክልሉ ልዩ ሃይሎች ጋር ግንኙነት ያላቸው የተለያዩ የጸጥታ ሃይሎች 10 በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ (ስምንት የትግራይ ተወላጆች እና ሁለት የጉሙዝ ብሄር ተወላጆች) ተኩሰው ገድለው አቃጥለዋል። በመቀጠልም በቤንሻንጉል/ጉሙዝ መተከል ዞን ጉባ ወረዳ አይሲድ ቀበሌ የጸጥታ ሃይሎች 11ኛ የትግራይ ተወላጅን በህይወት እያለ አቃጥለዋል። የተገደሉት ሰዎች ወደ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጎብኝዎችን ሲያጓጉዝ የነበረው አውቶብስ ላይ የደፈጣ ጥቃት ላደረሰው ያልታወቀ ቡድን መረጃ አቀብለዋል ተብሏል።
2 March 2022: Unidentified gunmen ambushed a bus transporting visitors to grand Ethiopia Renaissance Dam around Africa Agriculture Development area between Dangur and Guba woredas in Metekel zone in Benshangul/Gumuz region, killing more than 20 people including security forces. The bus was being escorted by security forces when the attack occurred.
የካቲት 23, 2014: ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር እና ጉባ ወረዳዎች መካከል የአፍሪካ ግብርና ልማት አካባቢ ጎብኚዎችን ወደ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሲያጓጉዝ በነበረ አውቶቡስ ላይ የደፈጣ ጥቃት አድርሰው የጸጥታ ሃይሎችን ጨምሮ ከ20 በላይ ሰዎች ገድለዋል። ጥቃቱ ሲደርስ አውቶብሱ በጸጥታ ሃይሎች ታጅቦ ነበር።
Source: DW Amharic; BBC Amharic
1 March 2022: Members of the Murle armed group from South Sudan attacked civilians in the Nuer and Agnewak zones in the Gambella region, killing two civilians and injuring another civilian.
የካቲት 22, 2014: ከደቡብ ሱዳን የመጡ የሙርሌ ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል ኑዌር እና አኝዋክ ዞኖች በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎች ላይ ጥቃት በመሰንዘር ሁለት ሰዎችን ገድለው አንድ ሰው አቁስለዋል።
Source: Ethiopian Insider
1 March 2022: On 28 February 2022, Gambella regional special police forces clashed with Murle ethnic militants from South Sudan in Ubuwa kebele, Gog woreda (Agnuwak, Gambella). The regional government police commission announced that the regional forces killed one militant and wounded a second. One special police officer was killed in the shootout. Several cattle were recovered as part of the operation.
የካቲት 22, 2014: የካቲት 21, 2014 ላይ በኡቡዋ ቀበሌ ጎግ ወረዳ (አኙዋክ፣ ጋምቤላ) የጋምቤላ ክልል ልዩ ፖሊስ ሃይሎች ከደቡብ ሱዳን የመጡ የሙርሌ ብሄረሰብ ታጣቂዎች ጋር ተዋግተዋል። የክልሉ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን እንዳስታወቀው የክልሉ ሃይሎች አንድ ታጣቂ ገድለው አንድ ሌላ ደግሞ አቁስለዋል። በተኩስ ልውውጡ አንድ የልዩ ፖሊስ አባል ተገድሏል። በተወሰደው እርምጃ በርካታ ከብቶችን መልሶ ማግኘት ተችሏል።
25 February 2022: Due to an explosion on a vehicle that was being searched by police at Azezo 5th police station in Gondar town two police officers and one civilian were killed. Another seven police officers and a civilian were injured.
የካቲት 18, 2014: በጎንደር ከተማ አዘዞ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ በፖሊስ ሲፈተሽ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ ፍንዳታ የሁለት ፖሊሶች እና የአንድ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆነ ግለሰብ ህይወት አልፏል። ሌሎች ሰባት የፖሊስ አባላት እና አንድ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆነ ሰው ደግሞ ቆስለዋል።
Source: DW Amharic
15 February 2022: Somali Region special police open gunfire on a passenger vehicle in Awbare village after the vehicle failed to stop at a checkpoint. Two people were reportedly killed. Angry demonstrators from the area later blocked the road with burning tires, demanding justice.
የካቲት 8, 2014: የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ በአውባሬ መንደር አንድ ተሽከርካሪ በፍተሻ ጣቢያ ላይ ባለማቆሙ ተኩስ ከፍቶበታል። በጥቃቱ ሁለት ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል። በአካባቢው የሚኖሩ የተበሳጩ ሰልፈኞች መንገዱን በሚቃጠል ጎማ መንገዱን ዘግተው ፍትህ ጠይቀዋል።
Source: BBC Somali
9 February 2022: Murle ethnic militias from South Sudan attacked the Dima refugee camp, and locations in Gog woreda in the Gambela region, killing two and injuring two others. The armed group also abducted three children.
የካቲት 2, 2014: ከደቡብ ሱዳን የመጡ የሙርሌ ብሄረሰብ ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል የዲማ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ እና ጎግ ወረዳ በሚገኙ ቦታዎች ላይ ጥቃት በማድረስ ሁለት ሰዎች ሲገድሉ ሌሎች ሁለት አቁስለዋል። በተጨማሪም ታጣቂ ቡድኑ ሶስት ህጻናትን አፍኖ ወስዷል።
Source: DW Amharic
8 February 2022: Members of OLF-Shane shot and killed one driver in the Koticha area in Wara-Jarso woreda in the North Shewa zone in the Oromia region. After the shooting member of the OLF-Shane clashed with the local militias.
የካቲት 1, 2014: በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ዋራ ጃርሶ ወረዳ ኮቲቻ በተባለ አካባቢ የኦነግ-ሸኔ አባላት አንድ ሹፌር ተኩሰው ገድለዋል። የኦነግ-ሸኔ አባላት ከተኩሱ በኋላ ከአካባቢው ታጣቂዎች ጋር ተጋጭተዋል።
Source: Ethiopian Insider
7 February 2022: An unidentified armed group attacked three tracks (FSR) and killed three civilians and injured four others in Yemekera Daget in Gelan woreda in the West Guji zone in the Oromia region.
ጥር 30, 2014: በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ገላን ወረዳ የመከራ ዳጌት ያልታወቀ ቡድን በሶስት የጭነት መኪኖች (ኤፍኤስአር) ላይ ባደረሰው ጥቃት ሶስት በግጭ ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ሲገደሉ አራት ደግሞ ቆስለዋል።
Source: DW Amharic
24 January 2022: TPLF forces clashed against Afar Region Special Police and Afar local militia, gaining control of Abaala and Berehale towns. Currently, the two forces are clashing in three fronts including in Megeale and Shehay Gubi woredas, (Zone 2, Afar).
ጥር 16, 2014: የትህነግ ሃይሎች ከአፋር ክልል ልዩ ፖሊስ እና ከአፋር የአካባቢ ታጣቂዎች ጋር ተዋግተው የአባላን እና በርሃሌ ከተሞችን ተቆጣጥረዋል። በአሁኑ ወቅት ሁለቱ ሃይሎች መገለሌ እና ሸሃይ ጉቢ ወረዳዎች (ዞን 2፣ አፋር) ጨምሮ በሶስት ግንባሮች እየተዋጉ ነው።
Source: DW Amharic
23 January 2022: According to the government OLF-Shane abducted five students and one businessman in the Bafano area in Gobu Seyo woreda in the East Wollega zone in the Oromia region while they were traveling from Addis Ababa to Asosa.
ጥር 15, 2014: ኦነግ-ሸኔ በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ወለጋ ዞን ጎቡ ስዮ ወረዳ በባፋኖ አካባቢ ከአዲስ አበባ ወደ አሶሳ በመጓዝ ላይ የነበሩ አምስት ተማሪዎችን እና አንድ ነጋዴን አፍኖ መውሰዱን መንግስት አስታውቋል።
Source: Fana Broadcasting Corporate
20 January 2022: Members of the Murle armed group from South Sudan attacked and killed eight civilians and injured five civilians including unidentified government officials in Akabo woreda in the Nuer zone in the Gambella region. A week ago the armed group abducted an unidentified number of children in the Nuer and Anuak zones.
ጥር 12, 2014: ከደቡብ ሱዳን የመጡ የሙርሌ ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል ኑዌር ዞን በአካቦ ወረዳ ማንነታቸው ያልታወቁ የመንግስት ባለስልጣናትን ጨምሮ ስምንት በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎችን ገድለው አምስት አቁስለዋል። ከሳምንት በፊት ታጣቂ ቡድኑ በኑዌር እና አኝዋክ ዞኖች ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ህጻናትን አፍኖ መውሰዱ ይታወሳል።
Source: DW Amharic
20 January 2022: Due to a dispute over a flag during an epiphany celebration security forces killed three people and injured many more at the borders of Addis Ababa and Burayu in the Oromia special zone.
ጥር 12, 2014: በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ልዩ ዞን ቡራዩ አዋሳኝ ድንበሮች ላይ በጥምቀት በአል ላይ በበባንዲራ ምክንያት በተፈጠረ አለመግባባት የጸጥታ ሃይሎች 3 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶችን አቁስለዋል።
Source: DW Amharic
10 January 2022: An airstrike conducted by the Ethiopian military struck a flour mill in May Tsebri (North Western Tigray), killing 17 people.
ጥር 2, 2014: በማይ ፀብሪ (ሰሜን ምዕራብ ትግራይ) በወፍጮ ቤት ላይ በተደረገ የአየር ድብደባ የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል።
Source: Bloomberg
18 December 2021: The Ethiopian government stated that its forces regain full control of North Wello zone in Amhara region.
ታህሳስ 9, 2014: የኢትዮጵያ መግስት ሃይሎቹ በአማራ ክልል የሰሜን ወሎ ዞንን በድጋሚ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠራቸውን ተናግሯል።
16 December 2021: Pupils protested US and EU intervention in Ethiopia in Debre Markos town in Amhara region.
ታህሳስ 7, 2014: ተማሪዎች በአማራ ክልል ደብረ ማርቆስ ከተማ አሜሪካ እና አውሮፓ በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ሰልፍ አካሂደዋል።
Source: Ethiopian Press Agency
6 December 2021: Government forces regained control of several areas including Dessie, Kombolcha, and Bati in the Amhara region.
ህዳር 27, 2014: የመንግስት ሃይሎች በአማራ ክልል ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ እና ባቲን ጨምሮ በርካታ አካባቢዎችን መልሰው ተቆጣጥረዋል።
5 December 2021: ENDF conducted drone-assisted airstrikes in Mekelle in the Tigray region. No reported causalities.
ህዳር 26, 2014: የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል መቀሌ ላይ በሰው አልባ አውሮፕላኖች የታገዘ የአየር ድብደባ አድርጓል። ምንም አይነት ሞት አልተዘገበም።
Source: DW Amharic
3 December 2021: Pupils and teachers protested foreign countries’ intervention in Ethiopia in Bahir Dar city, Amhara region.
ህዳር 24, 2014: በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ ተማሪዎች እና መምህራን የውጭ ሀገራት በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት ተቃውመው ሰልፍ አካሂደዋል።
2 December 2021: Members of Addis Ababa University protested foreign countries’ intervention in Ethiopia in front of the US embassy in Addis Ababa.
ህዳር 23, 2014: የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ አባላት የውጭ ሃገራት በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት በአዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት ተቃውመዋል።
Source: Ethiopian Press Agency
1 December 2021: ENDF and allied Amhara forces are reportedly in control of Lalibela town and its airport in the Amhara region.
ህዳር 22, 2014: የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና አጋር የአማራ ሃይሎች በአማራ ክልል የሚገኘውን የላሊበላ ከተማ እና አየር ማረፊያውን ተቆጣጥረዋል።
1 December 2021: ENDF and allied Amhara forces are reportedly in control of a number of towns in the North Shewa zone of the Amhara region, including Shewa Robit, Molale, Mezezo, and Rasa.
ህዳር 22, 2014: የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና ተባባሪ የአማራ ሃይሎች ሸዋ ሮቢት፣ ሞላሌ፣ መዘዞ፣ እና ራሳን ጨምሮ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኙ የተለያዩ ከተሞችን መቆጣጠራቸው ተሰምቷል።
28 November 2021: Ethiopian National Defence Force soldiers and allied Afar Regional special forces have reportedly taken control of Chifra, located along the Afar/Amhara regional borders.
ህዳር 19, 2014: የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደሮች እና አጋር የአፋር ክልል ልዩ ሃይሎች በአፋር/አማራ ክልሎች አዋሳኝ የሚገኘውን ጭፍራ ከተማ መቆጣጠራቸው ተሰምቷል።
Source: Fana Broadcasting
26 November 2021: ENDF and allied Afar regional special forces and Afar militias have taken control of Kasa Gita in the Afar region.
ህዳር 17, 2014: የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና አጋር የአፋር ክልል ልዩ ሃይሎች እንዲሁም ታጣቂዎች በአፋር ክልል የሚገኘውን ካሳ ጊታን ተቆጣጥረዋል።
26 November 2021: ENDF conducted a drone-assisted airstrike in Mekele city. There were no causalities.
ህዳር 17, 2014: የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በመቀሌ ከተማ በሰው አልባ አውሮፕላኖች የታገዘ የአየር ድብደባ አካሂዷል። በጥቃቱ ህይወቱ ያለፈም ሆነ የተጎዳ ሰው የለም።
Source: DW Amharic
25 November 2021: Protests under the slogan “Hands off Ethiopia” were held in front of US and UK embassies in Addis Ababa. Protesters also protested against “fake news published by international media”.
ህዳር 16, 2014: “ከኢትዮጵያ ላይ እጃችሁን አንሱ” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ባሉት የአሜሪካና የእንግሊዝ ኤምባሲዎች ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል። ተቃዋሚዎች “በአለም አቀፍ ሚዲያዎች የሚታተሙ የውሸት ዜናዎችን”ም ተቃውመዋል።
23 November 2021: An unidentified armed group ambushed a vehicle carrying civil servants killing four security forces and injuring six civil servants in Selam Ber kebele in Yeki woreda in South Western Ethiopia region. This attack occurred on the day of the official inauguration of the new eleventh region of Ethiopia, the South Western Ethiopia region.
ህዳር 14, 2014: በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል የኪ ወረዳ ሰላም በር ቀበሌ የመንግስት ሰራተኞችን ጭኖ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ ማንነቱ ያልታወቀ ታጣቂ ቡድን አድፍጦ በፈጸመው ጥቃት አራት የጸጥታ ሃይሎችን ገድሎ ስድስት የመንግስት ሰራተኞችን አቁስሏል። ይህ ጥቃት የተፈፀመው አስራ አንደኛ የሆነው አዲሱ የኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ይፋዊ የምስረታ በአል እለት ነው።
Source: Ethiopia Insider
23 November 2021: Last week, OLF-Shane ambushed and killed three officials of Midakegni woreda of West Shewa zone in Oromia region while traveling back from Ambo town to their woreda. The deputy administrator of the woreda was injured due to this attack. The spokesperson of OLF-Shane denied this accusation.
ህዳር 14, 2014: ባለፈው ሳምንት ኦነግ-ሸኔ ከአምቦ ከተማ ወደ ወረዳቸው ሲመለሱ የነበሩ ሶስት ባለስልጣናትን በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ሚዳከኚ ወረዳ አድፍጦ ገድሏል። የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ በዚህ ጥቃት ቆስለዋል። የኦነግ-ሸኔ ቃል አቀባይ ይህንን ክስ አስተባብለዋል።
Source: BBC Amharic
19 November 2021: Following an attack by unidentified gunmen on Amhara militiamen in Mettu Sellasie, Amhara militiamen reportedly attacked ethnic Oromo civilians in Nono, West Shewa (Oromia), killing 20 people. Local government officials have ordered an investigation to be conducted.
ህዳር 10, 2014: በመቱ ስላሴ ያልታወቁ ታጣቂዎች በአማራ ታጣቂዎች ላይ ያደረሱትን ጥቃት ተከትሎ በምዕራብ ሸዋ (ኦሮሚያ) ኖኖ የአማራ ታጣቂዎች በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ኦሮሞዎችን አጥቅተው 20 ሰዎች መግደላቸው ተዘግቧል። የአካባቢው የመንግስት ባለስልጣናት ምርመራ እንዲካሄድ አዘዋል።
Source: DW Amharic
18 November 2021: The government reportedly regained control of two strategic areas/mountains in Kasa Gita front (Afar) after two weeks of armed clashes between government forces and TPLF forces.
ህዳር 9, 2014:- በመንግስት ሃይሎች እና በትህነግ ታጣቂዎች መካከል ለሁለት ሳምንት ከተካሄደ ውጊያ በኋላ መንግስት በካሳ ጊታ ግንባር (አፋር) ሁለት ስትራቴጂካዊ ቦታዎችን/ተራራዎችን መልሶ መቆጣጠር መቻሉ ተዘግቧል።
18 November 2021: The head of the regional anti-insurgency force, the head of the Metekel zone communication office, and the mayor of Gelgelbeles town were arrested under suspicion of having links with armed groups and for failing to perform their duties in the Benshangul/Gumuz region.
ህዳር 9, 2014:- የቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል ፀረ-ሽምቅ ሃይል ሃላፊ፣ የመተከል ዞን ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ፣ እና የገልገልበለስ ከተማ ከንቲባ ከታጣቂ ሃይሎች ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ጥርጣሬ እና በክልሉ ሃላፊነታቸውን ባለመወጣት በቁጥጥር ስር ውለዋል።
Source: Ethiopian Reporter; DW Amharic
18 November 2021: According to the government, 345 members of OLF-Shane were killed by security forces from 12 October to 17 November 2021 in West Shewa zone in Oromia region.
ህዳር 9, 2014:- መንግስት ከህዳር 3 እስከ ህዳር 8, 2014 ባለው ወቅት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን 345 የኦነግ-ሸኔ አባላት በጸጥታ ሃይሎች መገደላቸውን ገልጿል።
15 November 2021: TPLF forces shelled Ataye town, reportedly killing at least four civilians.
ህዳር 6, 2014: የትህነግ ሃይሎች አጣዬ ከተማን በከባድ መሳሪያ ደብድበው ቢያንስ አራት በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎችን ገድለዋል።
Source: Amhara Communications
10 November 2021: Unidentified gunmen attacked civilians in Mandura woreda, Metekel Zone (Benshangul/Gumuz), killing four people. According to reports, a subsequent security crackdown resulted in the deaths of 19 people.
ህዳር 1, 2014: ያልታወቁ ታጣቂዎች በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ (ቤንሻንጉል/ጉምዝ) በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ባልሆኑ ግለሰቦች ላይ ባደረሱት ጥቃት 4 ሰዎች ገድለዋል። እንደዘገባዎቹ ከሆነ ይህንን ተከትሎ በተወሰደ የጸጥታ እርምጃ 19 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
Source: DW Amharic
8 November 2021: Protests against TPLF and OLF-Shane were held in Hawassa town, Sidama region.
ጥቅምት 29, 2014: ትህነግ እና ኦነግ-ሸኔን የሚያወግዙ ሰልፎች በሲዳማ ክልል ሃዋሳ ከተማ ተካሂደዋል።
Source: Ethiopian Broadcasting Corporate
7 November 2021: Protests against the TPLF and OLF-Shane continued for the third day across the country. Protests were held in Addis Ababa, East Hararghe zone, Bule Hora, Ambo, Harar, Halaba, Silte, Gamo, and Asosa. Protesters in Addis Ababa demonstrated against foreign intervention in Ethiopia and “biased” international media reports.
ጥቅምት 28, 2014: በመላው ሃገሪቷ ትህነግ እና ኦነግ-ሸኔን የሚያወግዙ ሰልፎች ቀጥለው ውለዋል። ሰልፎች በአዲስ አበባ፣ ምስራቅ ሃረርጌ ዞን፣ ቡሌ ሆራ፣ አምቦ፣ ሃረር፣ ሃላባ፣ ስልጤ፣ ጋሞ፣ እና አሶሳ ተካሂደዋል። በአዲስ አበባ የተሳተፉ ሰልፈኞች በኢትዮጵያ የውጭ ጣልቃ ገብነትን እና ‘የተዛቡ’ የአለም አቀፍ ሚዲያ ዘገባዎችን አውግዘዋል።
Source: Fana Television
6 November 2021: Protests against the TPLF and OLF-Shane continued for a second day across the country. Protests were held in all zones of Somali region; Hossana, Wolayita Sodo, Dilla in SNNPR; and Goba in Oromia region.
ጥቅምት 27, 2014: በመላው ሃገሪቷ ትህነግ እና ኦነግ-ሸኔን የሚቃወሙ ሰልፎች ለሁለተኛ ቀን ሲካሄዱ ውለዋል። ሰልፎቹ በሱማሌ ክልል በሚገኙ ሁሉም ዞኖች፤ በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች፣ እና ህዝቦች ሆሳእና፣ ወላይታ ሶዶ፣ እና ዲላ፤ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል በጎባ ተካሂደዋል።
Source: EBC; EBC; Fana Broadcasting Corporate
5 November 2021: Protests against the TPLF and OLF-Shane were held across 19 towns in the Oromia region, in Dire Dawa city, and in the Gambela region. Protesters condemned attacks by TPLF and OLF-Shane.
ጥቅምት 26, 2014: ትህነግ እና ኦነግ-ሸኔን የሚቃወሙ ሰልፎች በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ 19 ከተሞች፣ በድሬ ዳዋ ከተማ፣ እና በጋምቤላ ክልል ተካሂደዋል። ተሳታፊዎች በትህነግ እና ኦነግ-ሸኔ የሚደርሱ ጥቃቶችን አውግዘዋል።
Source: DW Amharic; Ethiopian News Agency
3 November 2021: ENDF conducted an airstrike targeting the Adibukeray training center used by TPLF around Adihageray in the Tigray region.
ጥቅምት 24, 2014: የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል አዲሃገረይ አካባቢ በትህነግ ጥቅም ላይ የሚውለው የአዲቡከራይ ማሰልጠኛ ማእከል ላይ የአየር ጥቃት አድርሷል።
2 November 2021: The cabinet of Ethiopia declared a state of emergency.
ጥቅምት 23, 2014: የኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል።
31 October 2021: The ENDF conducted another airstrike in the Tigray region. The airstrike targeted the Agulala training center which is located near Mekelle city.
ጥቅምት 21, 2014: የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል ሌላ የአየር ጥቃት ፈጽሟል። የአየር ጥቃቱ ኢላማ ያደረገው በመቀሌ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘውን የአጉላላ ማሰልጠኛ ማዕከል ነው።
Source: Fana Broadcasting Corporate
31 October 2021: Tigray residents in Semera and Logya protested against the TPLF. Protesters asked for the TPLF to withdraw from Amhara and Afar regions.
ጥቅምት 21, 2014: በሰመራ እና ሎጊያ ከተሞች የሚገኙ የትግራይ ነዋሪዎች ትህነግን የሚያወግዝ ሰልፍ አካሂደዋል። ሰልፈኞች ትህነግ ከአማራ እና አፋር ክልሎች እንዲወጣ ጠይቀዋል።
Source: Fana Broadcasting Corporate
30 October 2021: ENDF and OLF-Shane clashed in Begi and Kondala woredas in the West Wollega zone in the Oromia region. An unidentified number of people were reported killed as a result of the clashes in addition to more than 3,000 people that have been internally displaced.
ጥቅምት 20, 2014: የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና ኦነግ-ሸኔ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ቤጊ እና ኮንዳላ ወረዳዎች ውስጥ ተዋግተዋል። በውጊያው ያልታወቁ ቁጥር ያላቸው ሰዎች መገደላቸው እና ከ3000 በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተዘግቧል።
Source: DW Amharic
29 October 2021: The TPLF shelled Dessie town, killing one. TPLF forces and the ENDF also clashed around Wello University in Dessie town.
ጥቅምት 19, 2014: ትህነግ ደሴ ከተማን በከፍተኛ መሳሪያ ደብድቦ አንድ ሰው ገድሏል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የትህነግ ሃይሎች በደሴ ከተማ ወሎ ዩንቨርስቲ አካባቢ ተዋግተዋል።
Source: BBC Amharic
28 October 2021: The TPLF shelled Dessie town five times, killing one civilian and injuring three others. The shelling reportedly targeted civilians residents and an IDP temporary shelter.
ጥቅምት 18, 2014: ትህነግ ደሴ ከተማን አምስት ግዜ በከባድ መሳሪያ ደብድቦ አንድ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆነ ሰው ሲገድል ሶስት ሌሎች አቁስሏል። የከባድ መሳሪያ ድብደባው በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን እና ጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ ያሉ ተፈናቃይ ሰዎችን ኢላማ ማድረጉ ተዘግቧል።
Source: BBC Amharic
28 October 2021: The ENDF conducted another airstrike in Mekelle city, capital of Tigray region. The airstrike reportedly targeted the Mesfin Industrial Engineering PLC, which was hit in a previous strike last week. The government claims that the TPLF store military equipment at the site. At least three people were killed in the airstrike, with some sources indicating higher fatalities.
ጥቅምት 18, 2014: የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ተጨማሪ የአየር ጥቃት የትግራይ ክልል ዋና ከተማ በሆነችው መቀሌ ላይ አድርሷል። የአየር ጥቃቱ ባሳለፍነው ሳምንት በሌላ የአየር ድብደባ ጉዳት የደረሰበትን የመስፍን ኢንደስትሪያል ኢንጅነሪንግ ኢላማ ማድረጉ ተዘግቧል። መንግስት ፋብሪካው የትህነግ የጦር መሳሪያዎች የሚቀመጡበት ነው ብሏል። ቢያንስ ሶስት ሰዎች በዛሬው ጥቃት የተገደሉ ሲሆን አንዳንድ ምንጮች ከፍ ያለ ቁጥር ያለው ሟች እንደነበር ዘግበዋል።
26-27 October 2021: Unidentified gunmen shot and killed three civilians, including two brothers, in Kerkerte, Maderyana Gizaba, and Hejena Kebeles of Ale Special Woreda in the Southern Nations, Nationalities and Peoples Region. Two additional residents of the area were killed when they mistakenly opened fire on each other while attempting to repel the attack by the gunmen.
ጥቅምት 16-17, 2014: በደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል አለ ልዩ ወረዳ ከርከርቴ ማደርያና ግዝባ እና ሄጄና ቀበሌዎች ያልታወቁ ታጣቂዎች ሁለት ወንድማማቾችን ጨምሮ ሶስት በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ ተኩሰው ገድለዋቸዋል። ተጨማሪ ሁለት የአካባቢው ነዋሪዎች ጥቃቱን ለመመከት ሲሞከሩ በስህተት እርስ በእርስ ተታኩሰው ሞተዋል።
Source: DW Amharic
26 October 2021: The ENDF conducted another airstrike in Kuyeha in the Tigray region. The airstrike reportedly targeted a training center used by the TPLF.
ጥቅምት 16, 2014: የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል ኩየሃ ሌላ የአየር ጥቃት አድርሷል። የአየር ጥቃቱ በትህነግ ጥቅም ላይ የሚውል ሌላ ማሰልጠኛ ተቋም ኢላማ እንዳደረገ ተዘግቧል።
Source: DW Amharic
25 October 2021: Supporters of Eskinder Nega, founder of a popular opposition party mostly active in Addis Ababa, protested outside of a police station in Addis Ababa to demonstrate their support and solidarity after reports indicated that he had been injured in an altercation with another prisoner. Eskinder was arrested last June and is being held in the Kilinto federal prison.
ጥቅምት 15, 2014: በዋናነት በአዲስ አበባ የሚንቀሳቀሰው የታዋቂው ተቃዋሚ ፓርቲ መስራች እስክንድር ነጋ ከሌላ ታሳሪ ጋር በነበረ ግጭት መጎዳቱን ዘገባዎች ካስነበቡ በኋላ ደጋፊዎቹ በአዲስ አበባ ያለ ፖሊስ ጣቢያ በመገኘት ድጋፍ እና አጋርነታቸውን ለማሳየት ሰልፍ አድርገዋል። እስክንድር ሰኔ 2012 ላይ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በቂሊንጦ ፌደራል እስር ቤት ይገኛል።
Source: Addis Standard
24 October 2021: The ENDF conducted another two airstrikes in Adwa and Mai Tsemri in the Tigray region. In Adwa (Central Tigray), the airstrike reportedly targeted a manufacturing company that produced “fake military uniforms and equipment used by the TPLF to mislead the perpetrators of attacks,” while the airstrike in Mai Tsemri (North-Western Tigray) targeted an area reportedly used as a training center by TPLF.
ጥቅምት 14, 2014: የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ተጨማሪ ሁለት የአየር ጥቃቶችን በትግራይ ክልል አድዋ እና ማይ ጸምሪ ላይ ፈጽሟል። በአድዋ (ማእከላዊ ትግራይ) የአየር ጥቃቱ ”የጥቃት አድራሾችን ማንነት ለማሳሳት ለትህነግ ሃሰተኛ የሰራዊት መለዮ” የሚያመርት ድርጅትን ኢላማ ያደረገ ነበር የተባለ ሲሆን በማይ ጸምሪ (ሰሜን ምዕራብ ትግራይ) የደረሰው ጥቃት ደግሞ በትህነግ ለማሰልጠኛ ማእከልነት የሚውል ቦታን ኢላማ ማድረጉ ተዘግቧል።
Source: Reuters; Ethiopian Press Agency
23 October 2021: The head of the Nekemte city Work Innovation Office was shot and killed by an unidentified armed person around his home in Nekemte city, Oromia region.
ጥቅምት 13, 2014: የነቀምት ከተማ ስራ ፈጠራ ቢሮ ሃላፊ በኦሮሚያ ክልል ነቀምት ከተማ በሚገኝ መኖሪያ ቤታቸው ባልታወቀ ታጣቂ በተኩስ ተገድለዋል።
Source: BBC Afaan Oromoo
22 October 2021: The ENDF conducted another airstrike in the Tigray region. This airstrike reportedly targeted the former ENDF training center in Mekelle city, which the government says is currently used as a training center and “serving as a battle network hub” by the TPLF. ENDF’s airstrikes in Tigray began on Monday, 18 October 2021.
ጥቅምት 12, 2014: የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል ተጨማሪ የአየር ጥቃት ፈጽሟል። የዛሬው የአየር ጥቃት በአሁኑ ወቅት በትህነግ እንደ ማሰልጠኛ እና ”የውጊያ አውታር ማዕከል ሆኖ በማገልገል ላይ የሚገኝ” የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ማሰልጠኛ ተቋምን ኢላማ ማድረጉ ተዘግቧል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በትግራይ የአየር ጥቃት የጀመረው ሰኞ ጥቅምት 8, 2014 ነበር።
21 October 2021: The ENDF conducted an airstrike for a fourth time this week in Tigray region. According to reports, the airstrike targeted a former ENDF north command post center, allegedly used as a TPLF training camp and storage site for weapons.
ጥቅምት 11, 2014: የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል በዚህ ሳምንት ለአራተኛ ጊዜ የአየር ጥቃት ፈጽሟል። በዘገባው መሰረት የአየር ጥቃቱ ኢላማ ያደረገው ትህነግ ለማሰልጠኛ እና መሳሪያ ለማከማቻ እየተጠቀመበት እንደሚገኘ የተነገረ በቀደመው ጊዜ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ ማእከል የነበረ ቦታን ነው።
20 October 2021: The ENDF conducted at least two airstrikes in Tigray region on Wednesday. The first targeted a factory complex in Mekelle, the regional capital, while the second struck a military training center in Agbe, Tembien. TPLF-linked sources claim that civilian casualties occurred as a result of the strikes.
ጥቅምት 10, 2014: የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ቢያንስ ሁለት የአየር ሃይል ጥቃቶችን በትግራይ ክልል ፈጽሟል። የመጀመሪያው በመቀሌ የሚገኝ የፋብሪካ ግቢን ኢላማ ያደረገ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በተምቤን አግቤ የሚገኝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማእከልን አጥቅቷል። ከትህነግ ጋር ግንኙነት ያላቸው ምንጮች በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች በጥቃቶቹ ሞተዋል ብለዋል።
Source: BBC Amharic
18 October 2021: The TPLF reportedly shelled Wuchale in South Wello zone in Amhara region and Chifera in zone 1 in Afar region, killing at least 30 people.
ጥቅምት 8, 2014: ትህነግ በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ውጫሌን እና በአፋር ክልል ዞን 1 ጭፍራን በከባድ መሳሪያ በመደብደብ ቢያንስ 30 ሰዎችን መግደሉ ተዘግቧል።
Source: Fana Broadcasting Corporate
18 October 2021: The ENDF launched airstrikes near Mekele city in Tigray region, reportedly killing at least three people and injuring another 10. The Ethiopian government stated that the attack targeted a federal government institution that is currently being used as a communication center for TPLF forces.
ጥቅምት 8, 2014: የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ አካባቢ ባደረገው የአየር ድብደባ ሶስት ሰዎች ገድሎ አስር ሰዎች አቁስሏል ተብሏል። የኢትዮጵያ መንግስት ጥቃቱ ኢላማ ያደረገው ትህነግ እንደመገናኛ ማዕከል የሚጠቀምባቸውን የፌደራል መንግስቱ መስሪያ ቤቶች መሆኑን አሳውቋል።
Source: Reuters; DW Amharic; Ethiopian Press Agency
14 October 2021: An armed group reportedly attack Galesa kebele in Debate woreda in Metekel zone in the Benshangul/Gumuz region, killing four people. The group is said to have damaged Meserete Kirestos Church and burned 10 houses. Government security forces reportedly burned the houses of 13 other individuals, accusing them of having links with the armed group. Officials have denied the accusations against the security forces and alleged that OLF-Shane was behind the attack.
ጥቅምት 4, 2014: በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ደባቴ ወረዳ ጋሌሳ ቀበሌ አንድ ታጣቂ ቡድን ባደረሰው ጥቃት አራት ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል። ቡድኑ መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን አውድሟል እንዲሁም አስር ቤቶችን አቃጥሏል ተብሏል። የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ከቡድኑ ጋር ግንኙነት አላቸው ያሏቸውን 13 ግለሰቦች ቤቶች ማቃጠላቸው ተዘግቧል። እንደ ኮማንድ ፖስቱ ከሆነ ኦነግ-ሸኔ ከጥቃቶቹ ጀርባ ያለ ሲሆን በጸጥታ ሃይሎች ተፈጸመ የተባለውን ክስ ውድቅ አድርጓል።
Source: DW Amharic
11 October 2021: The ENDF, along with Amhara regional special forces, reportedly launched a ground attack against the TPLF in Wegeltena, Wirgesa, and Haro towns in Amhara region. On 7 and 8 October 2021, the ENDF also launched multiple airstrikes against the TPLF in these areas and on the road linking Afar to Amhara regions. The ENDF denied reports of the ground attack.
ጥቅምት 1, 2014: በአማራ ክልል ዋገልጤና፣ ውርጌሳ፣ እና ሃሮ ከተሞች ውስጥ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከአማራ ክልል ልዩ ሃይሎች ጋር በመሆን በትህነግ ላይ በመሬት ላይ ጥቃት መፈጸም መጀመሩ ተዘግቧል። መስከረም 27 እና 28, 2014 ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በእነዚህ አካባቢዎች እና አፋርና አማራ ክልሎችን በሚያገናኘው መንገድ ላይ ትህነግን በአየር ድብደባ አጥቅቷል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በትህነግ ላይ በእግረኛ ሰራዊት ጥቃት ፈጽሟል መባሉን ውድቅ አድርጓል።
Source: Reuters
10 October 2021: TPLF reportedly attacked Euwa area in Fanti Rasu-zone 4 in Afar region with heavy artillery, killing six civilians.
መስከረም 30, 2014: ትህነግ በአፋር ክልል በሚገኘው ፋንቲ ራሱ-ዞን 4 ኡዋ አካባቢን በከባድ መሳሪያ ደብድቦ ስድስት በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ገድሏል።
Source: VOA Amharic
10 October 2021: OLF-Shane reportedly attacked and killed 15 civilians in Haro kebele in Kirmu woreda in East Wollega zone, Oromia region. An unknown number of OLF-Shane members were then killed in a retaliatory attack by Oromia regional special forces.
መስከረም 30, 2014: በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ሃሮ ቀበሌ ውስጥ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ 15 ሰዎችን መግደሉ ተዘግቧል። በተጨማሪም የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይሎች በወሰዱት የመልስ እርምጃ ያልታወቀ ቁጥር ያላቸው የኦነግ-ሸኔ አባላት መገደላቸው ተዘግቧል።
Source: Amhara Media Corporation; Fana Broadcasting Corporate
7-8 October 2021: The ENDF attacked the TPLF through multiple airstrikes in areas near the towns of Wirgesa and Wegel Tena, and on the road linking the Afar region to the Amhara region.
መስከረም 27/28, 2014: የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አፋር ክልልን ከአማራ ክልል ጋር በሚያገናኘው መንገድ እና በውርጌሳ እና ወገል ጤና ከተሞች አካባቢ በሚገኙ አካባቢዎች ላይ አየር ድብደባዎች በመፈጸም ትህነግን አጥቅቷል።
Source: Reuters
7-8 October 2021: The ENDF attacked the TPLF through multiple airstrikes in areas near the towns of Wurgessa and Wegel Tena, and on the road linking the Afar region to the Amhara region.
መስከረም 27/28, 2014: የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አፋር ክልልን ከአማራ ክልል ጋር በሚያገናኘው መንገድ እና በውርጌሳ እና ወገል ጤና ከተሞች አካባቢ በሚገኙ አካባቢዎች ላይ አየር ድብደባዎች በመፈጸም ትህነግን አጥቅቷል።
Source: Reuters
5 October 2021: The Gambela police commission stated that three members of the Gambela Liberation Front were killed and two others were detained at the borders of the Gambela region and Kellem Wollega zone of the Oromia region. The police report claims that the group is working with the TPLF to destabilize the region.
መስከረም 25, 2014: በጋምቤላ ክልል እና ኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ወሰን ላይ ሶስት የጋምቤላ ነጻነት ግንባር አባላት ሲገደሉ ሁለት መታሰራቸውን የጋምቤላ ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቋል። በዘገባው መሰረት ቡድኑ ከትህነግ ጋር የሚሰራ ሲሆን ክልሉን ለመበጥበጥ እያሴረ ነበር።
Source: Fana Broadcasting Corporate
2 October 2021: Some participants of the Irrecha festival in Addis Ababa protested against the government and asked for the release of Jawar Mohamed and other Oromo politicians.
መስከረም 22, 2014: በአዲስ አበባ በተካሄደው የኢሬቻ ስነ-ስርአት ላይ የተሳተፉ የተወሰኑ ግለሰቦች መንግስትን የተቃወሙ ሲሆን ጃዋር መሃመድ እና ሌሎች የኦሮሞ ፖለቲከኞችም እንዲፈቱ ጠይቀዋል።
Source: DW Amharic
24 September 2021: Gumuz armed group abducted around 145 members of the Gumuz ethnic community, including women and children, accusing them of not supporting the group. Reportedly, at least two of the abducted people were killed by the armed group. It is also estimated that approximately 5,000 people are internally displaced from Sedal woreda due to an attack by the Gumuz armed group on 24 September 2021.
መስከረም 14, 2014: የጉሙዝ ታጣቂ ቡድን ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ 145 የጉሙዝ ብሄር አባላትን ቡድኑን አልደገፋችሁም በሚል አስገድዶ ወስዷል። ከተወሰዱት ውስጥ ቢያንስ ሁለቱ በቡድኑ መገደላቸው ተዘግቧል። በተጨማሪም የጉሙዝ ታጣቂ ቡድኑ መስከረም 14, 2014 ላይ ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ በግምት 5000 አካባቢ ሰዎች ከሴዳል ወረዳ ተፈናቅለዋል።
Source: EHRC
21 September 2021: Residents from North Wello zone demonstrated in front of the WFP and UNICEF offices in Addis Ababa asking that international organizations provide humanitarian assistance to victims of the conflict. Demonstrators asked that organizations providing aid to Tigray also provide humanitarian assistance (food and medicine) to those who were displaced from North Wello.
መስከረም 11, 2014: የሰሜን ወሎ ዞን ተወላጆች በአዲስ አበባ በሚገኙት የአለም ምግብ ፕሮግራም እና ዩኒሴፍ ጽ/ቤቶች ፊት ለፊት ሰልፍ አድርገው አለም አቀፍ ድርጅቶች ሰብአዊ እርዳታ ለግጭቱ ተጎጂዎች እንዲያደርሱ ጠይቀዋል። የሰልፉ ተሳታፊዎች ለትግራይ እርዳታ የሚያደርሱ ድርጅቶች ከሰሜን ወሎ ለተፈናቀሉ ግለሰቦችም ሰብአዊ እርዳታ (ምግብ እና መድሃኒት) እንዲያቀርቡ ጠይቀዋል።
Source: ESAT
16 September 2021: the Oromo Liberation Front (OLF)-Shane reportedly killed 17 people and six people are still missing in Kiremu woreda in East Wollega zone in Oromia.
መስከረም 6, 2014: የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ 17 ሰዎችን መግደሉን እና ተጨማሪ ስድስት ሰዎች የገቡበት አለመታወቁ ተዘግቧል።
Source: DW Amharic
10 September 2021: TPLF forces allegedly killed more than 600 civilians, committed human rights violations, and destroyed infrastructure and property in Kobo city of North Wollo. Many have fled the area. The chairperson of the TPLF has denied the accusation and called for an investigation.
ጷጉሜ 5, 2013: በሰሜን ወሎ ቆቦ ከተማ የትህነግ ሃይሎች ከ600 በላይ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን መግደላቸው፣ ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መፈጸማቸው፣ እንዲሁም መሰረተ ልማቶች እና ንብረቶች ማውደማቸው ተዘግቧል። ብዙ ሰዎች ከአካባቢው ተሰደዋል። የትህነግ ሊቀመንበር ክሱን አጣለው ማጣራት እንዲካሄድ ጠይቀዋል።
Source: VOA Amharic
8 September 2021: A Gumuz armed group reportedly shot and killed five security officers and two civilians, including a Chinese citizen, in Dangur woreda in Metekel zone, Benshangul/Gumuz region. Two more security officers were also injured. An unidentified number of the Gumuz armed group members were allegedly killed in a retaliatory attack by the ENDF and regional special forces.
ጷጉሜ 3፤ 2013፡ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ የጉሙዝ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት አምስት የጸጥታ ኃይሎችን ጨምሮ አንድ ኢትዮጵያዊ እና አንድ ቻይናዊ መገደላቸው ተዘገበ። በጥቃቱ ሁለት የጸጥታ ኃይሎችም ቆስለዋል። ይህን ጥቃት ተከትሎ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የልዩ ኃይል አባላት በወሰዱት እርምጃ ቁጥራቸው ያልታወቀ የጉሙዝ ታጣቂዎች መገደላቸውም ተዘግቧል።
Source: Ethiopia Insider
1-2 September 2021: TPLF forces reportedly killed more than 120 civilians, including children, in Chena Tekele-Haymanot kebele in Dabat woreda in North Gondar zone, Amhara region. The killings are alleged to have taken place while TPLF forces controlled the area.
ነሃሴ 26-27, 2013: በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ጨና ተክለ-ሃይማኖት ቀበሌ ውስጥ የትህነግ ሃይሎች ህፃናትን ጨምሮ ከ120 በላይ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን መግደላቸው ተዘግቧል። ግድያው የትህነግ ሃይሎች አካባቢውን በተቆጣጠሩበት ወቅት የተፈፀመ ነው።
Source: Reuters, Amhara Media Corporation
6 September 2021: An unidentified armed group reportedly shot and killed two people while they were farming in Jelo kebele in Amaro special woreda in the Southern Nations, Nationalities and Peoples Region. One of the deceased is vice chairman of Jelo kebele.
ጷጉሜ 1, 2013: በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች፣ እና ህዝቦች ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ ጀሎ ቀበሌ ያልታወቀ ታጣቂ ቡድን እያረሱ የነበሩ ሁለት ሰዎችን ተኩሶ መግደሉ ተዘግቧል። ከሟቾቹ አንዱ የጀሎ ቀበሌ ምክትል ሊቀመንበር ነበር።
Source: DW Amharic
30-31 August 2021: Members of the Gumuz People’s Democratic Movement armed group reportedly killed more than 50 civilians in Belo Jingafoy woreda in Kemashi zone, Benshangul/Gumuz region. Most of the deceased civilians are women. The armed group has also been clashing with regional forces in different areas of the Kemashi zone. An unknown number of fatalities were reported due to these clashes.
ነሃሴ 24-25, 2013: የጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ታጣቂ ቡድን አባላት በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን በሎ ጅጋንፎይ ወረዳ ከ50 በላይ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ገድለዋል። በጥቃቱ ህይወታቸው ያለፈው በአብዛኛው ሴቶች ናቸው። ታጣቂ ቡድኑ በተለያዩ የካማሺ ዞን አካባቢዎች ከክልሉ ሃይሎች ጋር እየተዋጋ ነው። በክልሉ ውስጥ ባሉት በእነዚህ ውጊያዎች ቁጥራቸው ያልታወቀ ሟቾች መኖራቸው ተዘግቧል።
Sources: VOA Amharic
31 August 2021: The Oromo Liberation Front (OLF)-Shane attacked a police station in Sasiga woreda in East Wollega zone, Oromia region. Reportedly, more than 40 police officers were injured due to this attack and around 100 prisoners escaped from the police station.
ነሃሴ 25, 2013: የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ሳሲጋ ወረዳ የሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት አድርሷል። በጥቃቱ ከ40 በላይ ፖሊሶች እንደቆሰሉ እና 100 ያህል እስረኞች ከፖሊስ ጣቢያው እንዳመለጡ ተዘግቧል።
Source: BBC Amharic
31 August 2021: An unidentified armed group shot and killed five people and injured two others in Bulen woreda in Metekel zone, Benshangul/Gumuz region.
ነሃሴ 25, 2013: በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ ውስጥ ያልታወቀ ታጣቂ ቡድን አምስት ሰዎችን ተኩሶ ሲገድል ሌሎች ሁለት ሰዎችን ደግሞ አቁስሏል።
Source: DW Amharic
30 August 2021: An unidentified armed group shot and killed three people and injured five others in Gambela town in the Gambela region.
ነሃሴ 24, 2013: በጋምቤላ ክልል ጋምቤላ ከተማ ውስጥ ያልታወቀ ታጣቂ ቡድን ሶስት ሰዎችን ተኩሶ ሲገድል ሌሎች አምስት ሰዎችን
Source: DW Amharic
19 August 2021: TPLF forces reportedly shelled Debre Tabor town in the Amhara region. Five people were killed and two others were injured.
ነሐሴ 13,2013፡ የትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሓት) ሃይሎች በአማራ ክልል የሚገኘው ደብረታቦር ከተማ ላይ ከባድ ድብዳባ ፈፅመዋል። በድብደባው አምስት ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች ሁለት ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።
Source: Amhara Media Corporation
15 August 2021: An attack by unidentified militants reportedly resulted in the death of three people and the injury of five others in Segen town of Konso zone in the Southern Nations, Nationalities and Peoples Region. The militants attacked a restaurant with gunfire and a hand grenade.
ነሐሴ 9, 2013: በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ኮንሶ ዞን ስር በምትገኘው ሰገን ከተማ ማንነቱ ባልታወቀ ታጣቂ ቡድን በደረሰ ጥቃት ሶስት ሰዎች ሲገደሉ አምስት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸው ተዘግቧል። ታጣቂዎቹ አንድ ምግብ ቤትን በተኩስ እና በእጅ ቦምብ አጥቅተዋል።
Source: Ethiopia Insider
14 August 2021: More than 170 members of an unidentified armed group, including 12 members of the TPLF, were reportedly killed by security forces in Guba woreda (Metekel zone, Benshangul/Gumuz region). The armed group is alleged to have entered Guba through the Sudan border to create unrest in the woreda where the Grand Ethiopian Renaissance Dam is under construction.
ነሃሴ 8, 2013: ጉባ ወረዳ (መተከል ዞን, ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል) ውስጥ 12 የትህነግ ታጣቂዎችን ጨምሮ ማንነቱ ካልታወቀ ታጣቂ ቡድን የሆኑ ከ170 በላይ የሚሆኑ ታጣቂዎች በጸጥታ አካላት መገደላቸው ተዘግቧል። ታጣቂዎቹ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እየተገነባ ወደሚገኝበት ጉባ ወረዳ የገቡት በሱዳን ድንበር በኩል ሲሆን የአካባቢውን ሠላም ለማደፍረስ እቅድ እንደነበራቸው ተገልጿል።
13 August 2021: Roads between Gimbi and Najjo, Gimbi and Dembi Dollo, and Gidami and Asosa have reportedly closed down periodically over the past few days due to ongoing clashes between the Oromia special force and the OLF-Shane.
ነሃሴ 7, 2013: በኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይል እና በኦነግ-ሸኔ ኃይሎች መካከል ባለው ውጊያ ምክንያት ከጊምቢ ወደ ናጆ፣ ከጊምቢ ወደ ደምቢ ዶሎ፣ እና ከጊዳሚ ወደ አሶሳ የሚወስዱ መንገዶች ላለፉት ጥቂት ቀናት በተደጋጋሚ መዘጋታቸው ተዘግቧል።
Source: BBC Amharic
5 August 2021: The TPLF reportedly attacked IDPs at a Galikuma kebele health center in Golina woreda in Fanti Rasu-Zone 4 of Afar region. It is estimated that more than 200 IDPs, including 107 children, were killed and that 40 IDPs were injured in the attack. TPLF officials have denied their forces were involved and have agreed to cooperate with an investigation by the relevant bodies.
ሀምሌ 29, 2013፡ በአፋር ክልል ፈንቲ ረሱ/ዞን 4 ያለውን ጦርነት ሸሽተው በጎሊና ወረዳ በሚገኘው በጋሊኮማ ቀበሌ ጤና ጣቢያ በተጠለሉ ሰዎች ላይ የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር (ህወሃት) ባደረስው ጥቃት 107 ህጻናትን ጨምሮ ከ200 በላይ ተፋናቃዮች ሲገደሉ ወደ 40 የሚጠጉ ደግሞ ቆስለዋል። የህወሃት ተወካይ ይህን ጥቃት የህወሃት ሃይሎች እንዳልፈፀሙት እና በሚመለከተው አካል ለሚደረግ ምርመራ ለመተባበር ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።
Source: BBC Amharic; UNICEF
29 July 2021: Eritrean refugees residing in Addis Ababa demonstrated against reported abuses faced by Eritrean refugees in the Tigray region in front of the International Organization for Migration (IOM) office in Addis Ababa. They asked IOM to protect refugees in the Tigray region.
ሀምሌ 22, 2013: በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑ የኤርትራ ስደተኞች በትግራይ ክልል በሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ በመቃወም በአዲስ አበባ በሚገኘው የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት መስሪያ ቤት ፊት ለፊት ሠላማዊ ሠልፍ አካሂደዋል። የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት በትግራይ ክልል የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞችን እንዲጠብቃቸው ጠይቀዋል።
Source: Fana Broadcasting Corporate S.C.
28 July 2021: Members of the Gumuz armed group reportedly shot and killed at least three civilians in Gilgel Beles town in Metekel zone, Benshangul/Gumuz. Following this attack, an armed clash was recorded between the Gumuz armed group and the zone’s command post security forces.
ሀምሌ 21, 2013: በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ የጉሙዝ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ ቢያንሰ ሦስት በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ተገድለዋል። ጥቃቱን ተከትሎ በጉሙዝ ታጣቂዎች እና በዞኑ ኮማንድ ፖስት ፀጥታ ሃይሎች መካከል ውጊያ ተመዝግቧል።
Source: ESAT
28 July 2021: Government forces reportedly killed more than 100 militants from the Gumuz People Democratic Movement in Awelebegu kebele, Sherkole woreda, Asosa zone of the Benshangul/Gumuz region.
ሀምሌ 21, 2013: በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ሸርቆሌ ወረዳ በሚገኘው አወሌቤጉ ቀበሌ ከ100 በላይ የጉሙዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ታጣቂዎች ተዋጊዎች በመንግስት ሃይሎች ተገድለዋል።
27 July 2021: Somali residents have blocked the Djibouti-Addis Ababa road to protest recent attacks on Garba Issa, Undhufto, and Aydetu towns by armed men from the Afar region.
ሀምሌ 20, 2013፡ የሶማሌ ነዋሪዎች በቅርቡ ከአፋር ክልል በሆኑ ታጣቂዎች ጋርባ ኢሳ፣ ኡንድሁፍቶ፣ እና አይደቱ ከተሞች ላይ የተፈፀመውን ጥቃት በመቃወም የጅቡቲ-አዲስ አበባን መንገድ ዘግተዋል።
25 July 2021: Demonstrations against the TPLF and supporting the ENDF and the second-round water filling of GERD continued in Ethiopia. Demonstrations were held in Abala, Asayita, and Semera-Logiya cities of the Afar region; Enjibara and Gondar cities of the Amhara region; Asela, Jimma, Robe, and Shahemene cities of the Oromia region; Dansha city of the Tigray region; and Dire Dawa city.
ሀምሌ 18, 2013: የትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሃት)ን የሚያወግዙ እንዲሁም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የሕዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር የውኃ ሙሌትን የሚደግፉ ሠልፎች በኢትዮጵያ መካሄድ ቀጥለዋል። ዛሬ በአፋር ክልል በአባላ፣ አሳይታ፣ እና ሠመራ-ሎግያ ከተሞች፤ በአማራ ክልል እንጅባራ እና ጎንደር ከተሞች፤ በኦሮሚያ ክልል አሰላ፣ ጅማ፣ ሮቤ፣ እና ሻሸመኔ፤ በትግራይ ክልል በምትገኘው ዳንሻ ከተማ፤ እና በድሬደዋ ከተማ ተካሂዷል።
Source: DW Amharic;Ethiopian Broadcasting Corporation;Ethiopian Broadcasting Corporation; Ethiopian Press Agency; Amhara Media Corporation
25 July 2021: Demonstrations against the TPLF and supporting the ENDF and the second-round water filling of GERD continued in Ethiopia. Demonstrations were held in Abala, Asayita, and Semera-Logiya cities of the Afar region; Enjibara and Gondar cities of the Amhara region; Asela, Jimma, Robe, and Shahemene cities of the Oromia region; Dansha city of the Tigray region; and Dire Dawa city.
ሀምሌ 18, 2013: የትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሃት)ን የሚያወግዙ እንዲሁም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የሕዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር የውኃ ሙሌትን የሚደግፉ ሠልፎች በኢትዮጵያ መካሄድ ቀጥለዋል። ዛሬ በአፋር ክልል በአባላ፣ አሳይታ፣ እና ሠመራ-ሎግያ ከተሞች፤ በአማራ ክልል እንጅባራ እና ጎንደር ከተሞች፤ በኦሮሚያ ክልል አሰላ፣ ጅማ፣ ሮቤ፣ እና ሻሸመኔ፤ በትግራይ ክልል በምትገኘው ዳንሻ ከተማ፤ እና በድሬደዋ ከተማ ተካሂዷል።
Source: DW Amharic;Ethiopian Broadcasting Corporation;Ethiopian Broadcasting Corporation; Ethiopian Press Agency; Amhara Media Corporation
24 July 2021: Violent conflict has reignited in the disputed areas at the border of the Somali and Afar regions. It is believed that hundreds have been killed due to the recent violence. EPO is closely monitoring the conflict in the area.
ሀምሌ 17, 2013፡ በአፋር እና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸው አካባቢዎች ላይ ግጭት በድጋሚ ተቀስቅሷል። በዚህ ግጭት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደሞቱ ይገመታል። ኢፒኦ በአካባቢው ያለውን ግጭት በቅርበት እየተከታተለ ነው።
Source: BBC Amharic
24 July 2021: The Sudanese Army clashed with Ethiopian militia members in Basanda on the Sudan-Ethiopia border while searching for three children abducted on 23 July 2021. One Sudanese soldier was reported killed in the incident.
ሀምሌ 17, 2013፡ ሀምሌ 16, 2013 የተወሰዱ ሦስት ህፃናትን በመፈለግ ላይ የነበሩ የሱዳን መከላከያ ሰራዊት አባላት ከኢትዮጵያ ታጣቂዎች ጋር በባሳንዳ አካባቢ (ሱዳን እና ኢትዮጵያ ድንበር የሚገኝ) ተጋጭተዋል። በግጭቱ አንድ የሱዳን ሰራዊት ህይወቱ አልፏል።
Source: Sudan Tribune; Sudan Tribune
24 July 2021: A demonstration in support of the Ethiopian National Defense Force was held in Arbaminch city of the Southern Nations, Nationalities and Peoples Region.
ሀምሌ 17, 2013፡ በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አርባምንጭ ከተማ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሠላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል።
24 July 2021: A demonstration in support of the Ethiopian National Defense Force was held in Adama city, Oromia region.
ሀምሌ 17, 2013፡ በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሠላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል።
Source: Ethiopian Press Agency
23 July 2021: The Ethiopian National Defense Force clashed with the Sudanese Army in Shenfa around the Merterad area and Metema. One member of the Sudanese Army was reportedly killed while one ENDF member was injured.
ሀምሌ 16, 2013፡ የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት እና የሱዳን መከላከያ ሰራዊት በሸንፋ መርትራድ በሚባል አካባቢ እና በመተማ አካባቢ ተጋጭተው አንድ የሱዳን መከላከያ ሰራዊት አባል ሲገደል አንድ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባል ደግሞ ቆስሏል።
Source: ESAT
23 July 2021: A demonstration in support of the Grand Ethiopian Renaissance Dam second-round water filling was held in Shashemene, West Arsi zone, Oromia region.
ሀምሌ 16, 2013፡ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን በምትገኘው ሻሸመኔ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር የውኃ ሙሌትን በመደገፍ ሰልፍ ተካሂዷል።
Source: Ethiopian News Agency
23 July 2021: Parents of students attending universities in the Tigray region held a demonstration in front of the United Nations Economic Commission for Africa’s office in Addis Ababa, asking the UN to facilitate the return of their children stuck in the region after the withdrawal of federal forces following the unilateral ceasefire.
ሐምሌ 16, 2013፡ የአንድ ወገን የተኩስ አቁም ውሳኔውን ተከትሎ የፌደራል ወታደሮች ከትግራይ ክልል ሲወጡ በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ልጆቻቸው መውጣት ያልቻሉ ተማሪዎች ወላጆች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የመመለስ ሂደቱን እንዲያመቻች የሚጠይቅ ሰልፍ በአዲስ አበባ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ፊት ለፊት አካሂደዋል።
Source: The Reporter
22 July 2021: Gunmen from an unidentified armed group reportedly killed a young man in an area known as Mangi Ber in Bulen woreda of Metekel zone, Benshangul/Gumuz. Following this incident, a suspected member of the Ethiopian National Defense Force shot at mourners, injuring four people. The head of the command post in the zone denies that soldiers under his command shot at civilians.
ሀምሌ 15, 2013፡ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ ልዩ ስሙ ማንጂ በር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አንድ ወጣት ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገድሏል። ይህንን ጥቃት ተከትሎ ለሐዘን የተቀመጡ ሰዎች ላይ የመከላከያ ሠራዊት አባል ነው የተባለ ታጣቂ በከፈተው ተኩስ አራት ሰዎች ቆስለዋል። በዞኑ የሚገኘው የኮማንድ ፖስቱ አመራር ግን በስራቸው ያሉ ወታደሮች በግጭት ውስጥ ያልተሳተፉ ግለሰቦች ላይ መተኮሳቸውን አስተባብለዋል።
Source: BBC Amharic
22 July 2021: An unidentified armed group killed three individuals, including the former head of the Benshangul/Gumuz regional special forces, in Oda Bilgudul woreda, Asosa zone of Benshangul/Gumuz region.
ሀምሌ 15, 2013፡ የቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል ልዩ ኃይል የቀድሞ አዛዥን ጨምሮ ሦስት ሰዎች ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በክልሉ ውስጥ በሚገኘው አሶሳ ዞን ኦዳ ብልጉዱል ወረዳ ተገድለዋል።
Source: Ethiopia Insider
22 July 2021: An unidentified armed group killed three individuals, including the former head of the Benshangul/Gumuz regional special forces, in Oda Bilgudul woreda, Asosa zone of Benshangul/Gumuz region.
ሀምሌ 15, 2013፡ የቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል ልዩ ኃይል የቀድሞ አዛዥን ጨምሮ ሦስት ሰዎች ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በክልሉ ውስጥ በሚገኘው አሶሳ ዞን ኦዳ ብልጉዱል ወረዳ ተገድለዋል።
Source: Ethiopia Insider
22 July 2021: A protest against the TPLF and in support of the Ethiopian National Defense Force was held in the Hadiya zone of the Southern Nations, Nationalities, and People’s Region.
ሀምሌ 15, 2013፡ በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በምትገኘው የሀዲያ ዞን የትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሃት) የሚያወግዝ እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሠልፍ ተካሂዷል።
22 July 2021: Protests against the TPLF and in support of the Ethiopian National Defense Force have continued. Today, peaceful protests were held in the capital city, Addis Ababa, and Jinka town in the Southern Nations, Nationalities, and People’s Region.
ሀምሌ 15, 2013፡ የትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባርን (ትህነግ/ህወሃት) የሚያወግዝ እና የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሠልፍ ቀጥሏል። ዛሬ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ እና በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በምትገኘው ጂንካ ሠላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል።
Source: Fana Broadcasting Corporate; DW Amharic; Ethiopian Broadcasting Corporation
21 July 2021: Protests against TPLF operations were held in Wolaita zone, Sodo city and Kembata Tembaro zone in the Southern Nations, Nationalities, and People’s Region.
ሀምሌ 14, 2013፡ የትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሃት) የጦርነት እንቅስቃሴን የሚያወግዝ ሠልፍ በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ እና ከምባታ ጠንባሮ ዞን ተካሄደ።
Source: Ethiopian Broadcasting Corporation; Ethiopian Broadcasting Corporation
21 July 2021: Demonstrations in support of the second-round water filling of the Grand Ethiopian Renaissance Dam’s have been held in Hawassa city of the Sidama region.
ሀምሌ 14, 2013፡ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት በመደገፍ በሲዳማ ክልል ሐዋሳ ከተማ ሰልፍ ተካሂዷል።
19 July 2021: A candidate from the Baro Democratic Party running for Benshangul/Gumuz regional council in Mandura woreda election constituency was found dead in Gilgel Beles city.
ሀምሌ 12, 2013፡ ቦሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲን ወክለው በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ምርጫ ክልል ለቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት የሚወዳደሩ እጩ በግልገል በለስ ከተማ ሞተው ተገኝተዋል።
Source: TIKVAH-ETHIOPIA
17 July 2021: TPLF forces have attacked pastoralists in Yalo woreda, Fantí Rasu-Zone 4 of the Afar region.
ሐምሌ 10, 2013፡ የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር (ትህነግ/ህወሃት) በአፋር ክልል ፈንቲ ረሱ-ዞን 4 ያሎ ወረዳ የሚኖሩ አርብቶ አደሮችን ማጥቃቱ ተዘግቧል።
Source: Amhara Media Corporation
17 July 2021: A convoy of 60 vehicles carrying food and non-food items en route to Mekelle via Afar region was delayed when TPLF forces shelled locations near the road.
ሐምሌ 10, 2013፡ በአፋር ክልል በኩል ወደ መቀሌ ሲጏዙ የነበሩ 60 ምግብ እና ምግብ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን የጫኑ መኪኖች የትህነግ ሀይሎች በመንገዱ አካባቢ ያሉ ቦታዎችን በመዝጋታቸው ዘግይተዋል።
Source: Amhara Media Corporation
15 July 2021: The unrest that began on 10 July 2021 has continued this week in Bulen woreda, Metekel zone. Eight people were killed in Denbe kebele in the Benshangul/Gumuz region. It is reported that around 4,000 people have been internally displaced due to this unrest.
ሐምሌ 8, 2013፡ በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በሀምሌ 3, 2013 አካባቢ የተነሳው የአካባቢ ግጭት በዚህ ሳምንትም ቀጥሏል፡፡ በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል ደንቤ ቀበሌ ስምንት ሰዎች ተገደለዋል። አለመረጋጋቱን ተከትሎ ወደ 4000 የሚጠጉ ሰዎች ከቀበሌው የተፈናቀሉ መሆናቸው ተዘግቧል።
13 July 2021: Oromo Liberation Front (OLF)-Shane members killed eight militia members and one farmer and injured two militia members in Jarte Jardega woreda in the Horo Guduru zone in the Oromia region.
ሐምሌ 6, 2013፡ በኦሮሚያ ክልል ሆሮጉድሩ ዞን በምትገኘው ጃርቴ ጃርደጋ ወረዳ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ )-ሸኔ ታጣቂ ቡድን አባላት ባደረሱት ጥቃት ስምንት ታጣቂዎች እና አንድ አርሶ አደር ሲገደሉ ሁለት ተጨማሪ ታጣቂዎች አቁስለዋል።
Source: Ethiopia Insider
12 July 2021: An active armed clash is reported between Amhara regional forces and TPLF fighters in the Korem area of southern Tigray zone, Tigray region. EPO is monitoring the incident closely.
ሐምሌ 5, 2013፡ በትግራይ ክልል ደቡባዊ ትግራይ ዞን በምትገኘው ኮረም አካባቢ በአማራ ክልል ሃይሎች እና በትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሓት) ታጣዊዎች መካከል ውጊያ እየተካሔደ ነው። ኢፒኦ ይህንን ኩነት በቅርበት እየተከታተለ ነው።
Source: Reuters
11 July 2021: Oromo Liberation Front-Shane members have reportedly killed nine civilians and kidnapped four children in the Elamo area of Emur woreda, Horo Guduru zone, Oromia region.
ሐምሌ 4, 2013፡ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር-ሸኔ ቡድን አባላት በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉድሩ ዞን ኢሙር ወረዳ ኢላሞ በተባለ አካባቢ ዘጠኝ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎችን ሲገድሉ አራት ህፃናትን ደግሞ አፍነው ወስደዋል።
Source: Wazema Radio
10 July 2021: A communal conflict has reportedly killed at least 14 in Bulen woreda, Metekel zone in Benshangul/Gumuz region. In response, the command post stationed in the Metekel zone has set a curfew in the woreda.
ሐምሌ 3, 2013፡ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ በተፈጠረ የአካባቢ ግጭት ቢያንስ 14 ሰዎች ሞተዋል። በምላሹ በመተከል ዞን የሚገኘው ኮማንድ ፖስት በወረዳው የሰዓት እላፊ ገደብ ጥሏል።
Source: Ethiopia Insider
8 July 2021: According to statements issued by the Raya Rayuma Democratic Party, militants from the TPLF have reportedly killed at least 50 civilians in the Raya area of Tigray region since the ENDF evacuated the area.
ሐምሌ 1, 2013:- የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ትግራይ ክልልን ለቆ መውጣቱን ተከትሎ የትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሃት) በትግራይ ክልል ራያ አካባቢ ቢያንስ 50 በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን እንደገደለ የራያ ራዩማ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አስታውቋል።
Source: VOA
6 July 2021: Reports indicate that TPLF fighters are heading to the borders of the Western Tigray zone, where the long-contested areas of Wolkait Tegede, Raya, and Humera are currently controlled by Amhara regional forces. EPO is closely monitoring the activities in the Western Tigray zone.
ሰኔ 29, 2013: የህዝበ ወያነ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ተዋጊዎች ለረዥም ጊዜ ሲያከራክሩ የቆዩትን የወልቃይት ጠገዴ፣ ራያ፣ እና ሁመራ ቦታዎችን የሚይዘው እና በአሁኑ ወቅት በአማራ ክልል ሀይሎች ስር ወደሆነው የምዕራብ ትግራይ ዞን ወሰኖች እያመሩ መሆኑን የሚያመላክቱ ዘገባዎች እየወጡ ነው። ኢፒኦ የምዕራብ ትግራይ ዞን ሁኔታን በቅርበት እየተከታተለ ነው።
Source: BBC Amharic
4 July 2021: Members of Oromo Liberation Front (OLF)-Shane killed at least four civilians and injured three others in Gebergum kebele in Horo woreda of Horo Guduru zone in the Oromia region. An unknown number of civilians are still missing after the attack.
ሰኔ 26, 2013: የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ዞን ሆሮ ወረዳ ውስጥ በምትገኘው ገበርጉም ቀበሌ ቢያንስ አራት በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎችን ሲገድሉ ሌሎች ሶስት ሰዎችን አቁስለዋል። ከጥቃቱ በኃላ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰላማዊ ሰዎች እስካሁን ያሉበት አልታወቀም።
Source: ESAT
2 July 2021: On 1 July 2021, the Tekeze river bridge — one of the main access points for humanitarian assistance in the Tigray region — was destroyed. It is not immediately clear who damaged the bridge as the federal government and the TPLF blame each other. The Ethiopian National Defense Force is trying to build a temporary mobile bridge over the Tekeze river and provide security to the bridge.
ሰኔ 25, 2013: ለትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ ማድረሻ ዋና መግቢያዎች ከሆኑት አንዱ የሆነው የተከዜ ወንዝ ድልድይ ሰኔ 24, 2013 ላይ ወድሟል፡፡ ድልድዩን ማን እንዳወደመው ግልፅ ባይሆንም የፌደራል መንግስቱ እና የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር (ትህነግ) ለጥፋቱ መድረስ እርስ በእርስ እየተወነጃጀሉ ነው። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በተከዜ ወንዝ ላይ ጊዜያዊ ተንቀሳቃሽ ድልድይ ለመገንባት እና ለድልድዩ ጥበቃ ለማድረግ እየሞከረ ነው፡፡
Source: Ethiopian Foreign Minister Briefing; Ethiopian Broadcasting Corporation; Reuters
29 June 2021: TPLF forces enter the town of Shire, with some clashes reported to the north in Adi Daero. Eritrean and Ethiopian forces have reportedly vacated the cities of Shire, Axum, Adwa, and Adigrat.
ሰኔ 22, 2013: የህወሃት ሃይሎች ሽሬ ከተማ የገቡ ሲሆን የተወሰኑ ውጊያዎች በስተሰሜን በአዲ ዳእሮ ተዘግበዋል። የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሀይሎች ሽሬ፣ አክሱም፣ አድዋ፣ እና አዲግራት ከተሞችን ለቀው ወጥተዋል።
Source: Reuters and local partners
28 June 2021: Following the federal government’s announcement of a unilateral ceasefire, the TPLF has gained control of the capital city of the Tigray region, Mekele. EPO is closely following developments in the Tigray region.
ሰኔ 21, 2013: የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት የተናጠል የተኩስ አቁም ስምምነት መወሰኑን ተከትሎ የህዝበ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) የትግራይ ክልል ዋና ከተማ የሆነችውን መቀሌ ተቆጣጥሯል። ኢፒኦ በትግራይ ክልል ያሉ ለውጦችን በቅርበት እየተከታተለ ነው።
Source: Ethiopia Insider
24 June 2021: The Ethiopian government announced that TPLF members killed three Doctors Without Borders employees in Abi Adi woreda, Central Tigray zone in the Tigray region.
ሰኔ 17, 2013: በትግራይ ክልል በማዕከላዊ ትግራይ ዞን አቢ አዲ ወረዳ ሦሰት የድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን ሰራተኞች የተገደሉ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ድርጊቱ በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አባላት መፈፀሙን ገልጿል።
Source: Doctors Without Borders; Fana Broadcasting Corporate
23 June 2021: TPLF fighters reportedly killed a member of the Tigray provisional government in Mekele city.
ሰኔ 16, 2013: የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አባላት አንድ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳድር አባልን በመቀሌ ከተማ ገድለዋል።
22 June 2021: More than 50 people were reportedly killed in an airstrike by the Ethiopian Air Force in Togoga area, Tigray region. ENDF army sources insist that the strike was carried out against a group of TPLF fighters and did not target civilians.
ሰኔ 15, 2013: በትግራይ ክልል ቶጎጋ በሚባል ስፍራ የኢትዮጵያ አየር ኃይል በሰነዘረው የአየር ጥቃት ከ50 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ምንጮች የአየር ጥቃቱ የተፈፀመው የህወሃት ተዋጊዎች ላይ መሆኑን እና በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ኢላማ አለማድረጉን ተናግረዋል።
21 June 2021: Members of Oromo Liberation Front (OLF)-Shane killed one higher official, one member of a communal militia, and one police officer at Liben Jawi woreda in the North Shewa zone in the Oromia region. The election process was interrupted due to this attack in two polling stations of the Nono election constituency.
ሰኔ 14, 2013: በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሊበን ጃዊ ወረዳ ላይ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ቡድን አባላት ባደረሱት ጥቃት አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን፣ አንድ የአካባቢ ታጣቂ፣ እና አንድ ፖሊስ ገድለዋል። በዚህ ጥቃት የተነሳ የምርጫው ሂደት በኖኖ የምርጫ ክልል የሚገኙ ሁለት የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ተስተጏጉሏል።
Source: BBC Amharic
21 June 2021: The Amhara regional police commission reports that an attack by unidentified gunmen on a polling station in Dabat woreda, North Gondar zone left one officer dead and a second injured. Two of the attacking gunmen were killed after police returned fire.
ሰኔ 14, 2013: የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ በምርጫ ጣቢያ ላይ ያልታወቁ ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት አንድ ፖሊስ ሕይወቱ ሲያልፍ ሌላ አንድ የፖሊስ ኃይል ደግሞ መቁሰሉን አሳውቋል። ፖሊስ ለጥቃቱ በሰጠው ምላሽ ጥቃቱን ካደረሱት መካከል ሁለት ሰዎች ተገድለዋል።
Source: Amhara Media Corporation
18 June 2021: According to the Oromia Police Commission, 295 Oromo Liberation Front (OLF)-Shane fighters have been killed in western Oromia. The Commission also stated that one top leader of OLF-Shane is among those killed during the last two months.
ሰኔ 11, 2013: የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በምዕራብ ኦሮሚያ ባለፉት ሁለት ወራት 295 የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ቡድን ታጣቂዎች መገደላቸውን ገለፀ። ከሟቾቹ መሀል አንድ የኦነግ-ሸኔ ከፍተኛ አመራር እንደሚገኝበት ኮሚሽኑ ጨምሮ ገልጿል።
Source: Oromia Police Commission
17 June 2021: Members of the Oromo Liberation Front (OLF)-Shane killed the head of Bule Hora Security Bureau and three Oromia region militias around Megada Den Limat, Bule Hora (West Guji zone, Oromia region).
ሰኔ 10, 2013: የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ታጣቂዎች በኦሮሚያ ምዕራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ልዩ መጋዳ ደን ልማት አካባቢ የቡሌ ሆራ ደህንነት ቢሮ ሃላፊን እና ሦስት የኦሮሚያ ክልል ታጣቂዎችን ገድለዋል።
Source: ESAT
16 June 2021: Suspected Oromo Liberation Front (OLF)-Shane gunmen killed nine Federal and Oromia Roads Authority workers and one resident in Loya Godane kebele in Meta Wolkite woreda, West Shewa zone of Oromia region.
ሰኔ 9, 2013: በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ሜታ ወልቂጤ ወረዳ ሎያ ጎዳኔ ቀበሌ ዘጠኝ የፌደራልና የኦሮሚያ መንገዶች ባለስልጣን ሰራተኞች እና አንድ የቀበሌው ነዋሪ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ቡድን አባላት ናቸው ተብለው በተጠረጠሩ ታጣቂዎች ተገድለዋል።
Source: BBC Amharic
14 June 2021: An unknown number of people were reportedly killed and more than 580 households displaced after an armed clash between Jarso (Oromo ethnic group) and Dir (Somali ethnic group) clans at the borders of the Oromia and Somali regions broke out last week. EPO is closely monitoring the situation.
ሰኔ 7, 2013:- በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ በጃርሶ (የኦሮሞ ብሔር ቡድን) እና ድር (የሶማሌ ብሔር ቡድን) ጎሳዎች መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ሕይወት ሲጠፋ ከ580 በላይ አባወራዎች ከቀያቸው ተፈናቅለዎል። ኢፒኦ ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለ ነው።
Source: DW Amharic
13 June 2021: Protests against reported abuses committed by the Tigray People’s Liberation Front (TPLF) as well as foreign intervention in Ethiopia’s internal issues have continued for the fourth day. Protests are being held in Dansha city in Welkait in the Tigray region.
ሰኔ 6, 2013: በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሲደርሱ የነበሩ ግፎችን እና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚያወግዙ ሠልፎች ለአራተኛ ቀን ቀጥለው ውለዋል። ሰላማዊ ሰልፎች በትግራይ ክልል ወልቃይት በምትገኘው የዳንሻ ከተማ ውስጥ እየተካሄዱ ነው።
Source: Fana Broadcasting Corporate; Amhara Media Corporation
12 June 2021: Protests against reported abuses committed by the Tigray People’s Liberation Front (TPLF) as well as foreign intervention in Ethiopia’s internal issues have continued for the third day. Protests are being held in Wef Argif city in Welkait in the Tigray region.
ሰኔ 5, 2013: በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሲደርሱ የነበሩ ግፎችን እና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚያወግዙ ሠልፎች ለሶስተኛ ቀን ቀጥለው ውለዋል። ሰላማዊ ሰልፎች በትግራይ ክልል በምትገኘው የወልቃይት ወፍ አርግፍ ከተማ ውስጥ እየተካሄዱ ነው።
Source: Amhara Media Corporation
12 June 2021: Protests against reported abuses committed by the Tigray People’s Liberation Front (TPLF) as well as foreign intervention in Ethiopia’s internal issues have continued for the third day. Protests are being held in Wef Argif city in Welkait in the Tigray region.
ሰኔ 5, 2013: በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሲደርሱ የነበሩ ግፎችን እና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚያወግዙ ሠልፎች ለሶስተኛ ቀን ቀጥለው ውለዋል። ሰላማዊ ሰልፎች በትግራይ ክልል በምትገኘው የወልቃይት ወፍ አርግፍ ከተማ ውስጥ እየተካሄዱ ነው።
Source: Amhara Media Corporation
11 June 2021: Protests against reported abuses committed by the Tigray People’s Liberation Front (TPLF) as well as foreign intervention in Ethiopia’s internal issues have continued. Protests are being held in Kadrawonz (Maikarda) in the Tigray region.
ሰኔ 4, 2013:- በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሲፈፀሙ የነበሩ ግፎችን እና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚያወግዝ ሠልፍ ቀጥሎ ውሏል። ሰላማዊ ሰልፍ በትግራይ ክልል በምትገኘው ካድራወንዝ (ማይካድራ) እየተካሄደ ነው።
Source: Amhara Media Corporation
10 June 2021: Suspected Oromo Liberation Front (OLF)-Shane gunmen reportedly killed 27 security forces and injured 10 more in Jardega Jarte woreda (Horo Guduru, Oromia).
ሰኔ 3, 2013:- የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ አባላት እንደሆኑ የተጠረጠሩ ታጣቂዎች በጃርደጋ ጃርቴ ወረዳ (ሆሮ ጉዱሩ፣ ኦሮሚያ) 27 የጸጥታ ኃይሎች ሲገድሉ ተጨማሪ 10 ደግሞ አቁስለዋል።
Source: Ethiopia Insider
10 June 2021: Protests against reported abuses by the Tigray People’s Liberation Front (TPLF) as well as foreign intervention in Ethiopia’s internal issues have continued in Humera in the Tigray region. Protests are being held in Ba’eker city.
ሰኔ 3, 2013: በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሲደርሱ የነበሩ ግፎችን እና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚያወግዝ ሠልፍ በትግራይ ክልል በምትገኘው ሁመራ ቀጥሎ ውሏል። ሰላማዊ ሰልፎች በባዕከር ከተማ እየተካሄዱ ነው።
Source: Amhara Media Corporation
10 June 2021: Protest against US sanctions on Ethiopia was held by women supporters of Prosperity Party in Debark city in Amhara region.
ሰኔ 3, 2013: በአማራ ክልል በደባርቅ ከተማ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በብልጽግና ፓርቲ ሴት ደጋፊዎች ተካሄደ።
Source: Amhara Media Corporation
9 June 2021: A protest against reported abuses committed by the Tigray People’s Liberation Front (TPLF) as well as foreign intervention in Ethiopia’s internal issues was held in Humera city in the Tigray region.
ሰኔ 2, 2013:- በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሲደርሱ የነበሩ ግፎችን እና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚያወግዝ ሠልፍ በትግራይ ክልል በምትገኘው የሁመራ ከተማ ተካሂዷል።
3 June 2021: After a final adjudication of the Federal Supreme Court Cassation Bench, the National Electoral Board of Ethiopia (NEBE) has begun registering four Balderas for True Democracy Party leaders as candidates for the upcoming election. The Balderas party leaders were imprisoned one year ago after being accused of inciting unrest in Addis Ababa.
ግንቦት 26, 2013፡ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በወሰነው መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አራት የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮችን በዕጩ ተወዳዳሪነት መመዝገብ ጀምሯል። እነዚህ አመራሮች ከአንድ አመት በፊት በአዲስ አበባ ውስጥ አለመረጋጋት እንዲፈጠር አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው ታስረዋል።
Source: Addis Ababa Balderas; BBC Amharic
2 June 2021: The Afar Regional Government has stated that it is re-administrating the Sawne Kebele, administered by authorities from Tigray Region over the last 30 years. EPO is closely monitoring the situation.
ግንቦት 25, 2013፡ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ላለፉት 30 አመታት በትግራይ ክልል ባለስልጣናት ሲተዳደር የነበረውን ሳውኔ ቀበሌን መልሶ ማስተዳደር መጀመሩን ገለጿል። ኢፒኦ ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለው ነው።
Source: Wazema Radio
1 June 2021: More than 40 Americans of Ethiopian descent protested in front of the United States Embassy in Addis Ababa against the sanctions imposed on Ethiopia by the United States.
ግንቦት 23, 2013፡ ቁጥራቸው ከአርባ በላይ የሚገመት ትውልደ ኢትጵያውያን የአሜሪካ ሀገር ዜጎች አዲስ አበባ በሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ፊት ለፊት ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ በመቃወም ሰልፍ አካሂደዋል።
Source: DW Amharic
30 May 2021: A protest under the slogan of “our voice for our independence and sovereignty” was held in Addis Ababa. More than 10,000 protesters took part and asked the United States to reconsider its “wrong” policy against Ethiopia. Similar protests have been held in Asosa, Dire Dawa, Gambela. Harar, Hosana, Silte, and Welaita Sodo cities.
ግንቦት 22, 2013:- በአዲስ አበባ ከተማ “ድምፃችን ለነፃነታችን እና ለሉአላዊነታችን” በሚል መሪ ቃል የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል። በሰልፉ ላይ ከ10,000 በላይ ግለሰቦች የተሳተፉ ሲሆን አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ያላትን ´የተሳሳተ´ አቋም በድጋሚ እንድታጤን ጠይቀዋል። ተመሳሳይ ሰልፎች በሀረር፣ ሆሳእና፣ ስልጤ፣ አሶሳ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ድሬ ዳዋ፣ እና ጋምቤላ ከተሞች ተካሂደዋል።
Source: Fana Broadcasting Corporate; Ethiopian Broadcasting Corporation; BBC Amharic; Ethiopia Broadcasting Corporation
28 May 2021: The Gondar administration reported that Amhara security forces successfully defended attacks by an unidentified armed group in Qusqam, Belajig Dabreka, and Azezo Sayid areas of Gondar city in the Amhara region.
ግንቦት 20, 2013 :- የጎንደር ከተማ አስተዳደር በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ ውስጥ በሚገኙ የቁስቋም፣ ብላጅግ ዳብርቃ፣ እና አዘዞ ሳይድ አካባቢዎች ላይ ጥቃት ለመፈፀም የመጡ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎችን የአማራ የፀጥታ ኃይል መመከቱን ገልጿል።
Source: DW Amharic
28 May 2021: The Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) announced that they are monitoring reports of Ethiopian and Eritrean forces detaining as many as 200 people on 24 May 2021 from the camps of internally displaced people in Shire town in the North-Western zone of the Tigray region. The detainees were released on 28 May 2021.
ግንቦት 20, 2013 :- የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ ዞን ሽሬ ከተማ ተፈናቅለው በካምፕ ውስጥ ተጠልለው ከሚገኙ ግለሰቦች ውስጥ እስከ 200 ሰዎች ግንቦት 16, 2013 ላይ አስረዋል የሚሉ ዘገባዎችን እያጣራ መሆኑን አስታውቋል። የታሰሩት ግለሰቦች ግንቦት 20, 2013 ላይ ተለቀዋል።
Source: EHRC; VOA Amharic
27 May 2021: The National Electoral Board of Ethiopia (NEBE) stated that it is impossible to implement the Federal Cassation Court’s decision to register three members of the Balderas for True Democracy party as candidates due to administrative and legal limitations.
ግንቦት 19, 2013 :- የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ሶስት የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አባላት እጩዎች ሆነው እንዲመዘገቡ ያሳለፈውን ውሳኔ በአስተዳደራዊ እና ህጋዊ ገደቦች ምክንያት ለመፈፀም እንደማይቻል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
Source: NEBE
20 May 2021: At least four students were killed and around 12 people injured after Prosperity Party´s election campaign in Merawi town, West Gojam Zone in Amhara Region turned violent.
ግንቦት 12፤ 2013፡ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን መርዓዊ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ በጠራው የቅስቀሳ ሰልፍ ላይ በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ አራት ተማሪዎች ሲገደሉ 12 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።
Source: DW Amharic
18 May 2021: Six special forces and three police officers were killed by an unidentified armed group at Aybera Sanka Kebele in Sheko Woreda, Bench Sheko Zone of the Southern Nations, Nationalities, and Peoples Region. Three more security forces were wounded by the attack.
ግንቦት 10, 2013፡ በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ሸኮ ወረዳ አይበራ ሳንቃ ቀበሌ ውስጥ ያልታወቀ ታጣቂ ቡድን ስድስት ልዩ ኃይሎች እና ሶስት ፖሊሶችን ገድሏል። በጥቃቱ ሌሎች ሶስት የፀጥታ አባላት ደግሞ ቆስለዋል።
Source: DW Amharic
18 May 2021: Head of West Wollega Zone Roads’ Authority was reportedly shot and killed with his driver and three guards by Oromo Liberation Front-Shane (Oromo Liberation Army) militias while driving with two cars at the border of Oromia and Benshangul/Gumuz regions.
ግንቦት 9, 2013፡ የምዕራብ ወለጋ ዞን የመንገዶች ባለስልጣን ኃላፊ በኦሮሚያ እና ቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልሎች ወሰን አካባቢ ከሹፌራቸው እና ሦስት ጠባቂዎቻቸው ጋር በሁለት መኪኖች እየተጓዙ ሳሉ በኦሮሞ ነፃነት ግንባር ኦነግ-ሽኔ (ኦሮሞ ነጻነት ጦር) ታጣቂዎች በጥይት ተገድለዋል።
Source: BBC Amharic
9 May 2021: A journalist from the state-affiliated Oromo Broadcasting Network (OBN) was killed by suspected Oromo Liberation Front (OLF)-Shane militants near his residence in Kellem Wollega Zone, Oromia region.
ግንቦት 2, 2013፡- በመንግስት የሚደገፈው የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (ኦቢኤን) ጋዜጠኛ የሆነ ግለሰብ በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን በሚገኝ መኖሪያ ቤቱ አካባቢ በሁለት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) – ሸኔ ታጣቂዎች እንደሆኑ በተጠረጠሩ ግለሰቦች ተገድሏል።
9 May 2021: Police prohibited Muslims in Addis Ababa from attending an Iftar program at Meskel Square. Members of the Muslim community objected to the restrictions, and security forces dispersed the gathering with tear gas. Today, the Addis Ababa city administration apologized for the disruption.
ግንቦት 2, 2013፡ ትላንት በአዲስ አበባ ፖሊስ የእስልምና እምነት ተከታዮችን መስቀል አደባባይ ላይ ሊያደርጉት የነበረው የአፍጥር ስነ-ስርዓት ከልክሏል። የእምነቱ ተከታዮች የፖሊስ ክልከላ ላይ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፤ የደህንነት ሀይሎች የነበረውን ህዝብ ለመበተን አስለቃሽ ጭስ ተጠቅመዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለተፈጠረው መስተጓጎል በዛሬው እለት ይቅርታ ጠይቋል።
30 April 2021: Sudan militias have attacked Endiblo Mendoka (West Gonder Zone, Amhara Region) today between 5:00 am and 10:00 am, damaging property. The administrator of Metema woreda has confirmed the reports and stated Ethiopian defense forces, local militia, and anti-insurgency forces have defended the attack.
ሚያዚያ 22, 2013: በእንዲብሎ መንዶካ (ምዕራብ ጎንደር ዞን፣ አማራ ክልል ) ውስጥ የሱዳን ታጣቂዎች ዛሬ ከንጋቱ 11:00 እስከ ጠዋት 4:00 በፈፀሙት ጥቃት በንብረት ላይ ጉዳት አድርሰዋል። የመተማ ወረዳ አስተዳዳሪ የዘገባውን እውነተኝነት አረጋግጠው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ የአካባቢ ሚሊሻዎች፣ እና ፀረ-ሽምቅ ሀይሎች ጥቃቱን መመከታቸውን ተናግረዋል።
Source: DW Amharic
29 April 2021፡ A command post has been established for security reasons in Chiliga and surrounding area of Central Gonder. ACLED records show that conflict between Qemant ethnic militias and Amhara regional special forces erupted on 12 April 2021 after a town hall meeting in Aykel city turned violent.
ሚያዚያ 21, 2013፡ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የጭልጋና አካባቢውን ጸጥታ ለማስጠበቅ ኮማንድ ፖስት ተቋቁሟል። በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በአይከል ከተማ ውስጥ ይካሄድ የነበረ ስብሰባ ወደ ግጭት መቀየሩን ተከትሎ በቅማንት የብሄር ታጣቂዎች እና የአማራ ክልል ልዩ ሃይሎች መካከል ግጭት ሚያዚያ 4, 2013 እንደጀመረ የአክሌድ መዛግብት ያሳያሉ።
27 April 2021: Six Isuzu semi-truck cars traveling from Addis Ababa to Gojam were attacked by an unidentified armed group between Kuyu and Degem Woredas in the North Shewa Zone of Oromia Region at around 10:30 pm. It is reported that at least five people are injured. According to ACLED records, government forces claimed to have killed 14 OLF-Shane militants in the same location in March of this year.
ሚያዚያ 19, 2013: ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም በመጓዝ ላይ የነበሩ ስድስት አይሱዙ መለስተኛ እቃ ማመላለሽ መኪኖች በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በኩዩ እና ዳግም ወረዳ መካከል ከምሽቱ 4፡30 አካባቢ ባልታወቀ ታጣቂ ቡድን ጥቃት ደርሶባቸዋል። በተፈጸመው ጥቃት ቢያንስ አምስት ሰዎች መቁሰላቸው ተዘግቧል። ። በዚህ ቦታ ላይ መንግስት ከዚህ ቀደም 14 የኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎችን መግደሉን የአክሌድ መዛግብት ያሳያሉ።
23 April 2021: Demonstrations against violent attacks and displacement of Amharas have continued, for a fourth day, in Amhara region. Demonstrations are being held in Debre Birhan and Debark cities.
ሚያዚያ 15, 2013፡ በአማራዎች ላይ የሚፈፀሙ ማንነትን መሰረት ያደረጉ ግድያዎችና መፈናቀሎችን የሚያወግዙ ሰልፎች በአማራ ክልል ለአራተኛ ቀን ቀጥለው ውለዋል። ሰልፎች በደብረ ብርሃን እና ደባርቅ እየተካሄዱ ነው።
Source: Amhara Media Corporation
22 April 2021: The Ethiopian Human Rights Commission announced that since 19 April 2021, militants have taken control of Sedal Wereda (Kemashi, Benshangul/Gumuz). The Commission added that militants have killed and kidnapped civilians and burned private and public properties. Many have fled from the area. The region´s police commissioner has since confirmed the Gumuz People Democratic Movement is controlling Diza town; an administrative center in Sedal Woreda.
ሚያዚያ 14, 2013፡ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከሚያዚያ 11, 2013 ጀምሮ ሴዳል ወረዳ (ከማሺ፣ ቤንሻንጉል/ጉምዝ) በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቋል። ኮሚሽኑ ጨምሮም ታጣቂዎቹ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን እንደገደሉ እና እንዳገቱ እንዲሁም የመንግስት እና የግለሰብ ንብረቶችን እንዳቃጠሉ ገልጿል። ብዙዎች አካባቢውን ጥለው ሸሽተዋል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ከዚያ ወዲህ በሰጡት መግለጫ የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የሴዳል ወረዳ ዋና ከተማ የሆነችው ዲዛን መቆጣጠሩን አረጋግጠዋል።
22 April 2021: Demonstrations against violent attacks and displacement of Amharas have continued, for a third day, in Amhara region. Demonstrations are being held in Bahir Dar, Debre Birhan, Gonder, and Injibara. Protesters in Bahir Dar are blocking roads and gunfire has been reported around the St George church.
ሚያዚያ 14, 2013፡ በአማራዎች ላይ የሚፈፀሙ ማንነትን መሰረት ያደረጉ ግድያዎችና መፈናቀሎችን የሚያወግዙ ሰልፎች በአማራ ክልል ለሶስተኛ ቀን ቀጥለው ውለዋል። ሰልፎች በባህር ዳር፣ ደብረ ብርሃን፣ ጎንደር እና እንጅባራ ከተሞች ወስጥ እየተካሄዱ ነው። በባህር ዳር ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አካባቢ ሰልፈኞች መንገድ እየዘጉ ሲሆን የተኩስ ድምፆች እየተሰሙ ነው።
21 April 2021: Demonstrations against violent attacks and displacement of Amharas have continued, for the second day, in Amhara region. There were demonstrations in Bahir Dar, Debre Birhan, Wollo, Lalibela, Kon, and Wadela cities; during today´s demonstration, protesters in Debre Birhan have urged the government to fulfill its responsibility to protect citizens.
ሚያዚያ 13, 2013: በአማራዎች ላይ የሚፈፀሙ ማንነትን መሰረት ያደረጉ ግድያዎችና መፈናቀሎችን የሚያወግዙ ሰልፎች በዛሬው እለትም በአማራ ክልል ቀጥለዋል። ሰልፎች በባህር ዳር፣ ደብረ ብርሃን፣ ወሎ፣ ላሊበላ፣ ኮን፣ እና ዋድላ ከተሞች ወስጥ የተካሄዱ ሲሆን በዛሬው እለት በደብረ ብርሃን ከተማ በተካሄደው ሰልፍ መንግስት የዜጎችን ደኅንነት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ተጠይቋል።
21 April 2021: Today the Ethiopian Citizens for Social Justice Party (EZEMA) stated that the party’s chairperson in Ephrata and Gidim electoral constituency was killed during a violent attack that occurred in Ataye city, North Shewa zone. See our latest EPO-weekly for more details on the violent conflict occurring in the area.
ሚያዚያ 13, 2013: የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በኤፍራታ እና ግድም ምርጫ ወረዳ የፓርቲው ሊቀመንበር የነበረው ግለሰብ በሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማ በተፈፀመው ጥቃት መገደሉን ዛሬ አስታውቋል። በአጣዬ ሰለተፈጠረው ግጭት የበለጠ ለማወቅ የዚህን ሳምንት ኢፒኦ ሳምንታዊ ይመልከቱ።
20 April 2021: Demonstrators are protesting violent attacks and displacement of Amharas in Bahir Dar, Debre Markos, Woldiya, Desse, and Kombolcha cities of Amhara region. Protesters in Bahir Dar chanted anti-Prosperity Party slogans and burned the party’s billboards.
ሚያዚያ 12, 2013: በአማራዎች ላይ የሚፈጸሙ ማንነትን መሰረት ያደረጉ ግድያዎችንና መፈናቀሎችን የሚያወግዙ ሰላማዊ ሰልፎች በአማራ ክልል በባሕርዳር፣ ደብረማርቆስ፣ ወልደያ፣ ደሴ፣ እና ኮምቦልቻ ከተሞች እየተካሄዱ ነው፡፡ በባሕርዳር እየተደረገ ባለው ሰልፍ ላይ ያሉ ተሳታፊዎች ብልፅግና ፓርቲን የሚያወግዙ መፈክሮችን ያሰሙ ሲሆን የፓርቲውን የማስታወቂያ ሰሌዳዎችንም አቃጥለዋል።
Sources: Ethiopian Broadcasting Corporation; Amhara Media Corporation
13 April 2021: Election dispute update — On 13 April 2021, the Federal High Court of Ethiopia upheld the decision of NEBE, which resulted in the cancelation of the Oromo Liberation Democracy Front. EPO is tracking how the party and its supporters react to this decision.
ሚያዚያ 5, 2013: የምርጫ ጉዳይ: የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ነጻነት ዲሞክራሲያዊ ግንባርን ከፓርቲነት ለመሰረዝ ያሳለፈው ውሳኔ አግባብ ነው ሲል በሚያዝያ 5, 2013 ወሰኗል። ኢፒኦ ፓርቲው እና ደጋፊዎቹ ለዚህ ውሳኔ የሚሰጡትን ምላሽ ይከታተላል።
Source: Fana Broadcasting
10 April 2021: On Saturday, 10 April 2021, a grenade was thrown in a hotel in Nekemte, Oromia Region, killing at least one person and injuring nine. EPO is monitoring the event and will provide the latest information in this week’s report.
ሚያዚያ 2, 2013: ቅዳሜ ሚያዚያ 2, 2013 ላይ በኦሮሚያ ክልል ነቀምት ከተማ በሚገኝ አንድ ሆቴል ውስጥ በተወረወረ የእጅ ቦምብ ቢያንስ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ ዘጠኝ ሰዎች ቆስለዋል። ኢፒኦ ሁኔታውን እየተከታተለ ሲሆን ዝርዝር መረጃውን በቀጣዩ ኢፒኦ-ሳምንታዊ ላይ ይጠብቁ።
Source: Borkena
7 April 2021: Approximately 100 people are reported dead from clashes in the Afar-Somali regional border area this week. The conflict is still active and EPO is monitoring developments.
መጋቢት 29, 2013: በዚህ ሳምንት በአፋርና ሶማሌ ክልሎች ድንበር ላይ በተነሳ ግጭት 100 ሰዎች እንደሞቱ ሪፖርት ተደርጏል። ግጭቱ እስካሁን ያልበረደ ሲሆን፤ አክሌድም ሁኔታውን እየተከታተለ ነው።
Source: Al Jazeera
31 March 2021: “Overall, data collected by ACLED shows a 33% increase in the number of fatalities compared to the 2015–17 baseline. But a more nuanced picture emerges if one looks at disaggregated data related to each Ethiopian region.”
መጋቢት 22, 2014: “በጠቅላላው በአክሌድ የተሰበሰበው መረጃ ከ2007-2009 ከነበረው ጋር ሲነጻጸር የሟቾች ቁጥር የ33% ጭማሪ ያሳያል። ነገር ግን ከእያንዳንዱ የኢትዮጵያ ክልል ጋር የተያያዙ የተከፋፈሉ መረጃዎችን ከተመለከቱ የበለጠ ጥልቅ ሁኔታ ይታያል።”
Source: Tiziana Corda