በቁጥር (ከመጋቢት 24, 20101እነዚህ ቁጥሮች የሚያመለክቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደስልጣን ከመጡበት መጋቢት 24, 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገሪቱ የተከሰቱ የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶችን፣ በዚህ ምክንያት የደረሱ የሞት ጉዳቶች፣ እንዲሁም በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ የተቃጡ ጥቃቶችን ነው። እስከ ሐምሌ 23, 2013)2አክሌድ እስከ ነሀሴ መጨረሻ ድረስ የተመዘገቡ ኩነቶችን ህትመት ይገታል። ከሐምሌ 24, 2013 እስከ ነሀሴ 28, 2013 ያሉ መረጃዎች የኩነቶች ህትመት ጷጉሜ 1, 2013 ላይ በድጋሚ ሲጀምር የሚለቀቁ ይሆናል። በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን እንዲሁም ኢትዮጵያን የተመለከቱ ሁሉንም የአክሌድ መረጃዎች ማውረድ ይችላሉ።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 1,735
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 9,294
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 4,944
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን እዚህ፣ ሁሉንም የአክሌድ ስራዎች ደግሞ እዚህ ጋር በመጫን ያገኛሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
የትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሃት) ታጣቂዎች ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ፣ ዋግ ሃምራ እና አፋር ክልል ውስጥ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ አማራ ክልል ልዩ ኃይል፣ እና አካባቢ ታጣቂዎች ጋር ከተዋጉ በዃላ መግፋታቸውን ቀጥለዋል። ባለፈው ሳምንት የነበረው ቁልፍ ለውጥ የአካባቢ ቁጥጥር ላይ ሲሆን እነዚህም የትህነግ ሃይሎች በስተደቡብ ወደ ደቡብ ጎንደር ዞን አካባቢዎች በመስፋፋታቸው እና ከአማራ ክልል ልዩ ሃይሎች እና ታጣቂዎች ጋር ከነፋስ መውጫ ሰሜን-ምዕራብ አቅጣጫ ባሉት አካባቢዎች በመዋጋታቸው ነው። ዋና ከተሞች የሆኑትን የደብረታቦር እና ወልዲያ የሚያገናኘው መንገድ የአማራ ክልልን ምስራቅና ምዕራባዊ ክፍሎችን የሚያገናኝ ዋና መሠረተ ልማት ነው።
በተለይ በሰሜን ወሎ የሚገኘው የወልዲያ ከተማ የረዥም ጊዜ ውጊያ ሲካሄድበት የቆየ ሲሆን የመንግሥት ኃይሎችና የትህነግ ታጣቂዎች ሳምንቱን ሙሉ አንዱ በሌላው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ሲናገሩ ቆይተዋል። እንደወልድያ ከተማ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ከሆነ የትህነግ ታጣቂዎች ነሐሴ 3, 2013 ላይ ከተማውን ደብድበዋል (ወልዲያ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት፣ ነሐሴ 3, 2013)። የትህነግ ሃይሎች ወደ ሰሜን ከማፈግፈጋቸው በፊት ወደ ከተማው ደቡባዊ ክፍል በመግፋት መርሳ ከተማን ለአጭር ግዜ ተቆጣጥረው ነበር (ዲደብሊው አማርኛ፣ ነሐሴ 2, 2013)። በምስራቅ የአማራ ክፍሎች የሚካሄደው ውጊያ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን አፈናቅሏል (ቢቢሲ አማርኛ፣ ነሐሴ 8, 2013)።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን አልፎ አልፎ ሁከት መከሰቱ የቀጠለ ሲሆን ባለፈው ሳምንት ሰባት ሰዎች ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች አውቶቡሳቸው ላይ ጥቃት በፈጸሙባቸው ጥቃት ተገድለዋል። እንደዘገባዎች ከሆነ አውቶብሱ በአንድ ወቅት በሺዎች ለሚቆጠሩ ከመተከል ግጭት ለተፈናቀሉ ግለሰቦች ማረፊያ ቦታዎች ከነበሩባት የአማራ ክልል ድንበር ላይ ከምትገኘው ቻግኒ ወደ መተከል ዞን የአስተዳደር ማዕከል ወደሆነችው ግልገል በለስ እያቀና ነበር። ምንም እንኳን የፌደራል ወታደሮች በአካባቢው ቢገኙም መተከል ዞን ውስጥ አሁንም ድረስ በአገሪቱ ከፍተኛ ግጭት ካለባቸው ቦታዎች አንዱ ነው።
ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ ክልል ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ጋር ግንኙነት ያላቸው ታጣቂዎች ከኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይል ጋር በምዕራብ ኦሮሚያ መዋጋት የቀጠሉ ሲሆን በርካታ ትንንሽ ከተማዎችን መቆጣጥቅራቸውን ተናግረዋል። ቡድኑ ዋና ዋና የመንገድ መስመሮችን መቆጣጠሩንም ተናግሯል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ቡድኑ ለአጭር ጊዜ የነጆ-ጊምቢ-ደምቢ ዶሎ መንገድን፣ የደምቢ ዶሎ-አሶሳ መንገድን እንዲሁም የነቀምት-ባህር ዳርን መንገድ መዝጋቱን አረጋግጠዋል። የአካባቢው ባለሥልጣን የታጣቂዎቹን እንቅስቃሴ አረጋግጠው የፀጥታ ኃይሎች ግን ሁኔታውን ፈተዋል ብለዋል (ቢቢሲ አማርኛ፣ ነሃሴ 8, 2013)። ኦነግ-ሸኔ በቅርቡ ከትህነግ ጋር ያደረገው ወታደራዊ ትብብር ከዚህ በታች በዝርዝር ይብራራል።
የኦነግ-ሸኔ ሃይሎች ባለፈው ሳምንት ከኦሮሚያ ክልል ውጪም እየተንቀሳቀሱ እንደነበረ የተዘገበ ሲሆን የጋምቤላ የደህንነት ሀይሎች ከትህነግ እና ኦነግ-ሸኔ ጋር ግንኙነት አላቸው ያሏቸውን 93 ግለሰቦች በጋምቤላ ከተማ ዋንታ ዋር እና ላሬ ወረዳዎች ይዘዋቸዋል (የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሸን፣ ነሃሴ 7, 2013)።
ሳምንታዊ ትኩረት: በትግራይ ግጭት አዳዲስ ላይ የተፈጠሩ አዳዲስ ለውጦች
ባለፈው ሳምንት ከትግራይ ግጭት ጋር የተያያዙ ሁለት ዋና ዋና ለውጦች ነበሩ። የመጀመሪያው ነሐሴ 4, 2013 የኢትዮጵያ መንግስት ትህነግ የፈጠረውን ‘ውድመት’ ለማስቆም ሁሉንም ሀይል እንደሚያሳትፍ አሳውቋል (የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፣ ነሃሴ 4, 2013)። ይህም ሰኔ መጨረሻ የታወጀው የአንድ ወገን የተኩስ አቁም ውሳኔ መጨረሻ ይመስላል።
ሁለተኛው የመንግስት ተቃዋሚ የሆኑት የኦነግ-ሸኔ እና ትህነግ ታጣቂዎች ባላፈው ሳምንት ‘’የአብይን መንግስት ለማውረድ’’ አብረው ለመስራት ተስማምተዋል (ኤፒ፣ ነሃሴ 5, 2103፤ ሮይተርስ፣ ነሃሴ 5, 2013)። ምንም እንኳን ለተወሰነ ጊዜ አብረው ይሰራሉ ይባል የነበረ ቢሆንም ይህ ግን ቡድኖቹ አብረው መስራታቸውን በይፋ ያመኑበት የመጀመሪያ ጊዜ ነው። ይህ ክፍል እነዚህ ለውጦች ለትግራይ ግጭትም ሆነ ለአጠቃላይ ሀገሪቱ ያለውን እንድምታ ያብራራል።
የመንግስት ከመከላከል ወደ ማጥቃት መሸጋገር
መንግስት በሰኔ ወር መጨረሻ ላይ የአንድ ወገን የተኩስ አቁም ውሳኔ ካሳለፈ ጀምሮ የመንግሥት ምንጮች የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የመከላከል ሥራዎችን ብቻ እያካሄደ ነበር (የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት-ኢትዮጵያ፣ ሐምሌ 21, 2013)። በቅርቡ የፌደራል መንግስት የሰጠው መግለጫ የተኩስ አቁም ውሳኔው ሊቋረጥ እንደሚችል እና የፌዴራል ወታደሮች እንደገና የማጥቃት ሥራዎችን እንደሚሠሩ ያመለክታል።
ሐምሌ 2013 ላይ የትህነግ ኃይሎች ለጋራ የተኩስ አቁም ድርድር ያስፈልጋሉ ያሏቸው ቅድመ ሁኔታዎች የተካተቱባቸው ሁለት ዝርዝሮች አወጡ (ለዝርዝሩ ኢፒኦ ሳምንታዊ :- ከሰኔ 26, 2013 እስከ ሐምሌ 2, 2013 እና ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከሐምሌ 17, 2013 እስከ ሐምሌ 23, 2013 ይመልከቱ)። ቡድኑ የፌዴራል መንግሥት ቅድመ-ሁኔታዎቹን እስኪቀበል እና ትግራይ ክልል ላይ ያደረገውን መዝጋት እስኪያነሳ ትግሉን እንደሚቀጥል ቃል ገብቷል። በዚህ መሠረት ባለፈው አንድ ወር የትህነግ ኃይሎች በአምስት ግንባሮች ማለትም በምዕራባዊ ትግራይ ዞን (ትግራይ)፣ ሰሜን ጎንደር ዞን (አማራ)፣ ደቡብ ትግራይ ዞን (ትግራይ)፣ ሰሜን ወሎ ዞን (አማራ)፣ እና ፋንቲ ራሱ- ዞን 4 (አፋር) ላይ ውጊያ ቀጥለዋል። ቡድኑ ከክልል ኃይሎችም ሆነ ከመከላከያ ሰራዊት ምንም አይነት መከላከል ሳይደረግበት እንደ አላማጣ እና ላሊበላ ያሉ አንዳንድ አካባቢዎችን ለመቆጣጠር ችሏል። ይህ በእንዲህ እንዳለ እንደ ወልድያ እና አዲ ዓርቃይ ባሉ ሌሎች ቦታዎች ከአማራ ኃይሎች (አማራ ክልል ልዩ ሃይል እና የአካባቢ ታጣቂዎች) ጋር ከባድ ውጊያ አካሂደዋል። ቡድኑ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ከትግራይ ዋና ከተማ መቀሌ 338 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን የምትገኘው ጋሸና ደርሷል። እንዲሁም ከመቀሌ 445 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን የምትገኘው ጋይንት ደርሰዋል።
መንግስት ለክልል ኃይሎች፣ ለታጣቂዎች፣ እና ለመከላከያ ሰራዊት የትህነግን “ጥፋት ለማቆም” እርምጃ እንዲወስዱ ትእዛዝ ከሰጠ በኋላ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ ግንባሮች ውጊያዎች ተጠናክረዋል (የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት-ኢትዮጵያ፣ ነሐሴ 4, 2013)። መንግሥት በእነዚህ ግንባሮች ላይ የተካሄደውን አዲስ ጥቃት ተከትሎ ብዙ የትህነግ ሃይሎች መገደላቸውን አልያም ከቦታቸው መፈናቀላቸውን አስታውቋል (ኢሳት፣ ነሐሴ 5, 2013፤ የኢፌደሪ መከላከያ ሰራዊት፣ ነሐሴ 7, 2013)። ትህነግ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሚመራውን የፌዴራል መንግሥት ለማስወገድ የአፋርና የአማራ ሕዝብ የትህነግን እንቅስቃሴ እየደገፈ መሆኑን ዘግቧል (ትግራይ ሚዲያ ሃውስ፣ ነሐሴ 5, 2013)።
በአማራ ክልል በዋግ ሃምራ፣ ሰሜን ጎንደር፣ ደቡብ ጎንደር ዞን፣ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች በትህነግ እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ክልል ልዩ ሃይሎች እና የአማራ ታጣቂዎች መካከል ከፍተኛ ውጊያ ተመዝግቧል። የትህነግ ሃይሎች ከአማራ ክልል ልዩ ሃይሎች እና የአማራ ታጣቂዎች ጋር በአማራ ክልል ዋግ ሃምራ ዞን ሰቆጣ ከተማ ውስጥ ከነሐሴ 1, 2013 ጀምሮ ለአምስት ቀናት የዘለቀ ውጊያ አድርገዋል። ነሐሴ 3, 2013 ላይ የትህነግ ሃይሎች ወልዲያ ከተማን በከባድ መሳሪያ በመደብደብ ሁለት በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ሲገድሉ የከተማውን ስታዲየም ጨምሮ ንብረት አውድመዋል። ከነሐሴ 3 እስከ 5, 2013 በነበረው ውጊያ መከላከያ ሰራዊት በትህነግ ሃይሎች ላይ የአየር ላይ ጥቃት ፈጽሟል።
ባለፈው ሳምንት መንግስት ከጎረቤት ሀገራት ወደ ሀገሪቱ የገቡ በርካታ ከትህነግ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ታጣቂዎች መያዙን አስታውቋል። ነሐሴ 3, 2013 እና 4, 2013 ላይ ከትህነግ ጋር ግንኙነት ያለው የሳምሪ ቡድን ከመከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ክልል ልዩ ሃይሎች፣ እና የአማራ ታጣቂዎች ጋር በምዕራብ ትግራይ ሁመታ ባህረ-ሰላም አካባቢ ተዋግቷል። ቡድኑ አገሪቱ ከሱዳን ጋር በምትዋሰንበት ምስራቃዊ ድንበር ወደትግራይ ክልል ለመግባት ሞክሮ ነበር። ከ1,500 በላይ የሚሆኑ የቡድኑ አባላት በመከላከያ ሰራዊት አባላት መያዛቸው ተዘግቧል (ኢሳት፣ ነሐሴ 5, 2013ሀ፤ ኢሳት፣ ነሐሴ 5, 2013ለ)። የሳምሪ ቡድን በምዕራብ ትግራይ ማይካድራ ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተገደሉበት የህዳር 2013 እልቂት ተሳትሪ ነው ተብሎ ይታመናል (የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ህዳር 15, 2013)። የቡድኑ አባላት መንግስት ከተማዋን በህዳር 2013 በተቆጣጠረበት ወቅት ወደ ሱዳን እንደሸሹ ይታመናል።
በተመሳሳይ የቤንሻንጉል/ጉሙዝ መንግስት በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ 12 የትህነግ አባላትን ጨምሮ ከ170 በላይ ማንነቱ ያልታወቀ የትጥቅ ቡድን አባላት በፀጥታ ኃይሎች መገደላቸውን ገልጿል። ቡድኑ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እየተገነባ በሚገኝበት ጉባ ወረዳ ውስጥ ሁከት ለመፍጠር በሱዳን ድንበር በኩል ወደ ወረዳው መግባቱ ተዘግቧል (የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ነሐሴ 8, 2013)። እንዲሁም በሁኔታዎች አጭር መግለጫ ማጠቃለያ እንደተገለጸው የጋምቤላ ክልል መንግሥት በጋምቤላ ከተማ በዋንታ ዋር እና ላሬ ወረዳዎች ውስጥ ከትህነግ እና ኦነግ-ሽኔ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የታመኑ 93 ሰዎችን የክልሉ ፀጥታ ሃይሎች መያዛቸውን ዘግበዋል (የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት፣ ነሐሴ 7, 2013)። በመሆኑም መከላከያ ሰራዊት እየወሰደ ያለውን የማጥቃት ዘመቻ ተከትሎ ግልፅ የሆነ የውጊያዎች መጨመር ቢኖርም የትህነግ ኃይሎች ተጨማሪ ቦታዎችን መቆጣጠራቸውን እና የግጭቱ አዝማሚያዎች ላይ ተጽዕኖ ማሳደራቸን ቀጥለዋል።
በኦነግ-ሸኔ እና ትህነግ መካከል የተፈጠረውን ወታደራዊ ጥምረት መረዳት
ሌላው ባለፈው ሳምንት የተከሰተው ቁልፍ ለውጥ በኦነግ-ሸኔ እና በትህነግ መካከል የተፈጠረው ወታደራዊ ጥምረት ነው (ኤፒ፣ ነሃሴ 5, 2013፤ ሮይተርስ፣ ነሃሴ 5, 2013)። ትህነግ ከሌሎች ቡድኖች ጋር ተመሳሳይ ጥምረት ለመፍጠር እየተወያየ መሆኑንም አመልክቷል። የእነዚህ ጥምረቶች ዘገባዎች ይፋ የሆኑት መንግስት ሁሉንም የሀገሪቱ ኃይሎች ትህነግን ለማስቆም አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ ትእዛዝ ካስተላለፈ ከአንድ ቀን በኋላ ነው።
መንግስት ሁለቱን ቡድኖች “አሸባሪ” ብሎ ከሰየመበት ግንቦት 2013 ጀምሮ አክሌድ በኦሮሚያ ክልል ኃይሎች እና በኦነግ-ሽኔ መካከል 14 ውጊያዎችን መዝግቧል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። በሁኔታዎች አጭር መግለጫ ላይ እንደተብራራው ቡድኑ በደቡብ እና ምዕራብ ኦሮሚያ ባሉ አካባቢዎች እንቅስቃሴው እየጨመረ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ትንንሽ ከተማዎችን ይዧለሁ ብሏል። ቡድኑ ከፀጥታ ሀይሎች ጋር የሚያካሂደው ውጊያ መጨመሩ እንዳለ ሆኖ የቡድኑ ተፅእኖ ባለባቸው አካባቢዎች ላይ በተደጋጋሚ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎችን በተለይም አማራዎችን በማጥቃት ይከሰሳል።
መንግሥት ይህንን ጥምረት “አያስገርምም” ብሏል (የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት-ኢትዮጵያ፣ ነሐሴ 6, 2013)። መንግሥት የጥምረቱን ይፋ መደረግ ቡድኖቹን “አሸባሪ” ብሎ ያሳለፈውን ውሳኔ ትክክለኛነት የሚያሳይ እና መንግስት ትህነግ ሀገሪቷን ለማተራመስ ከተለያዩ ቡድኖች ጋር ይተባበራል ማለቱን የሚደግፍ አድርጎ ያየዋል። ከላይ እንደተገለፀው መንግስት በቤንሻንጉል/ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች ውስጥ የህወሓት አባላትን ጨምሮ ማንነቱ ያልታወቀ የትጥቅ ቡድን አባላትን በቁጥጥር ስር ማዋሉንው አልያም መግደሉን ባለፈው ሳምንት አሳውቋል (የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ነሐሴ 8, 2013)።
ይህ አዲስ ጥምረት ኦነግ-ሸኔ ላይ ምን አይነት ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ግልፅ አይደለም። ከ1980ዎቹ ጀምሮ ሰፊ ራስ-ገዝ አስተዳደር የጠየቁ የፖለቲካ ንቃት ያላቸው ኦሮሞዎች ከኦነግ ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል ትህነግ በሚመራው መንግስት ታስረዋል፣ ተሰቃይተዋል፣ እንዲሁም ተገድለዋል። ከ2006-2010 የነበረውን ስብስብ በመፍጠር በመጨረሻ ትህነግ የሚመራውን መንግስት በማውረድ አብይን ወደ ስልጣን ማምጣት የቻሉት በኦሮሚያ የነበሩት የመንግስት ተቃዋሚ የሆኑ የወጣቶች ቡድኖች (ቄሮ) አሁን ተከፋፍለዋል። የተወሰኑት ኦነግ-ሸኔን ሲቀላቀሉ ሌሎቹ ደግሞ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይል አባል ሆነው ከመንግሥት ኃይሎች ጋር ተቀላቅለዋል። ኦነግ-ሸኔ ከትህነግ ጋር ጥምረት ለመፍጠር መወሰኑ ከክልሉ በጠቅላላ ድጋፍ ለማግኘት የሚያደርጉትን ጥረት ያወሳስበዋል።
ከምርጫ ጋር የተያያዙ ክርክሮች ወቅታዊ ሁኔታ
ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሁለት ከድህረ-ምርጫ ጋር የተያያዙ አቤቱታዎች ላይ ውሳኔ አስተላልፏል። ሐምሌ 23, 2013 ላይ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የድህረ-ምርጫ አቤቱታ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ማቅረቡን ያሳወቀ ሲሆን በዚህም በአዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙት 23 የምርጫ ክልሎች በ21 ምርጫው በድጋሚ እንዲካሄድ ጠይቋል (ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከሐምሌ 17, 2013 እስከ ሐምሌ 23, 2013 ይመልከቱ)። የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታው የቀረበው ከጊዜ ገደቡ በዃላ በመሆኑ ጥያቄውን እንደማይቀበል ወስኗል (የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ነሃሴ 7, 2013)። የምርጫ ሕጎቹ መሠረት ማንኛውም ከምርጫ፣ ቆጠራ፣ እና የምርጫ ውጤቶች ጋር የተያያዙ ቅሬታዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በይገባኛል ጥያቄዎች ላይ ውሳኔ ካሳለፈ በ10 ቀናት ውስጥ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት መቅረብ እንዳለባቸው ይጠቅሳሉ (የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና፣ የምርጫ ሥነምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011፣ አንቀጽ 155)። በአብዛኛው ከምርጫ ጋር ተዛማጅነት ያላቸው የይገባኛል ጥያቄዎች መጀመሪያ ለምርጫ ቦርድ የሚቀርቡ ሲሆን የምርጫ ቦርድ ውሳኔን ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማለት ይቻላል። ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የይገባኛል ጥያቄውን ያቀረበው ምርጫ ቦርድ በድህረ-ምርጫ አቤቱታዎች ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ካሳለፈ ከ17 ቀናት በኋላ ነበር (የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ነሃሴ 7, 2013)።
በተመሳሳይ ፍርድ ቤቱ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ያቀረበውን የድህረ-ምርጫ አቤቱታ የይግባኝ ጊዜው ካለፈ በኋላ የቀረበ በመሆኑ ውድቅ አድርጎታል (የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ነሃሴ 10,2013)። አብን ጥያቄውን ያቀረበው በአማራ ክልል ከሚገኙት የደብረ ማርቆስ፣ ጎንጂ፣ እና ፍኖተ ሰላም የምርጫ ክልሎች ጋር በተያያዘ ነው።
በአጠቃላይ 74 ከምርጫ ጋር የተያያዙ አቤቱታዎች ለፍርድ ቤቱ ቀርበዋል። ከነዚህ 74 ጥያቄዎች ውስጥ 13 በድህረ-ምርጫው፣ 57 በቅድመ-ምርጫው፣ እንዲሁም 4 በምርጫው ወቅት የቀረቡ ናቸው (ሪፖርተር፣ ነሃሴ 9, 2013)።