በቁጥር: ኢትዮጵያ, ከጥር 20, 2014 –ጥር 26, 2015
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 1,253
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 6,660
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 2,658
በቁጥር: ኢትዮጵያ, ከጥር 20-26, 20151በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ በመረጃ ቋታችን ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 17
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 169
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 16
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን ከኢፒኦ የመረጃ መዝገብ እንዲሁም በዋናው የአክሌድ ኤክስፖርት መሳሪያ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
የኦሮሚያ ክልል በአገሪቱ ካሉ ክልሎች በጣም ያልተረጋጋ ክልል ሆኖ ቀጥሏል። ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ 10 የውጊያ ኩነቶች እና ስድስት በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸሙ የጥቃት ኩነቶች ተመዝግበዋል። አብዛኛው የውጊያ ኩነቶች በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ እና በመንግስት ኃይሎች – በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ በኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል፣ በማረሚያ ቤት ፖሊስ እና በቀበሌ ታጣቂዎች – መካከል በምስራቅ ወለጋ ዞን በአኖ ቀበሌ እና በስሬ ከተማ፣ በቄለም ወለጋ ዞን ደምቢ ዶሎ ከተማ፣ በምዕራብ ጉጂ ዞን ዶጎ/ማጋዳ ቀበሌ እና ገላና ወረዳ እና በምዕራብ ሸዋ ዞን የጎዳ ገላን/ቢቲሌ ቀበሌ እና ባኮ አቅራቢያ በሚገኘው ጊቤ ወንዝ አካባቢ የተፈፀሙ ናቸው (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። በምስራቅ ወለጋ ዞን ጎቡ ስዮ ከተማ ባለፈው ሳምንት የኦነግ-ሸኔ እና የኦሮሞ ብሄር ታጣቂዎች አራት የጥበቃ ሠራተኞችን ከገደሉ በኋላ ባንኮች መዘረፋቸውም ተነግሯል።
ኦነግ-ሸኔ፣ ማንነቱ ያልታወቀ ታጣቂ ቡድን እና የመንግስት ኃይሎች ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ በሰላማዊ ሰዎች ላይ በደረሱ ጥቃቶች ተሳትፈዋልl። ጥር 20 ቀን የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል አባላት በምዕራብ ሀረርጌ ዞን ጭሮ ከተማ እና በምዕራብ ሸዋ ዞን ስናን ለኩ ቀበሌ ከኦነግ-ሸኔ ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል በትንሹ አምስት ሰላማዊ ሰዎችን ተኩሰው መግደላቸው ተነግሯል። በተመሳሳይ የቀበሌ ታጣቂዎች በምዕራብ ሸዋ ዞን አቡና ግንደ በረት ወረዳ ጉዱሩ ቀበሌ የኦነግ-ሸኔ ደጋፊዎች ናቸው በማለት ሁለት ሰዎችን በጥይት ተኩሰው ገድለዋል። ኦነግ-ሸኔ ባለፈው ሳምንትም በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት መሰንዘሩ ተዘግቧል። ጥር 21 ቀን የኦነግ-ሸኔ አባላት በምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ ቶሬ አካባቢ በሚገኝ ደን አቅራቢያ ተሽከርካሪ ላይ ተኩስ ከፍተው አንዲት ነፍሰ ጡር ሴትን ጨምሮ ሁለት ሰላማዊ ሰዎችን ገድለው ሌሎች አራት ሰላማዊ ሰዎችን አቁስለዋል። ተሽከርካሪው ከቡርጂ ልዩ ወረዳ ወደ ዲላ ከተማ እየተጓዘ ነበር። ከአንድ ቀን በኋላ ጥር 22 ቀን በሰሜን ሸዋ ዞን ኩዩ ወረዳ ገብረ ጉራቻ ከተማ ዘጠኝ ቻይናውያን ባረፉበት ሀበሽ ሆቴል ውስጥ የኦነግ-ሸኔ አባላት እንደሆኑ የተገመቱ ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው አንድ ቻይናዊ ገድለው አንድ ኢትዮጵያዊ አግተው ወስደዋል።2ንጋቱ ረጋሳ፣ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ራዲዮ፣ ጥር 24, 2015 በመጨረሻም ጥር 24 ቀን ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በአርሲ ዞን መርቲ ወረዳ ጎልጎታ ቀበሌ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት በማድረስ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች የገደሉ ሲሆን በንብረት ላይም ጉዳት አድርሰዋል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን የተከሰተውን መከፋፋል ተከትሎ ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ ግጭት ተቀስቅሷል። በኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ያለው አለመግባባት እየሰፋ ሲሆን መንግሥት ጣልቃ በመግባቱ ውጥረቱ እየጨመረ መጥቷል። ጥር 14 ቀን የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሊቀነ ጳጳስ አቡነ ሳዊሮስ ከሌሎች ሁለት ሊቀነ ጳጳሳት ጋር በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ወሊሶ ከተማ በሚገኘው የሀሮ በዓለ ወልድ ቤተ-ክርስቲያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሲኖዶስ ሳያውቀው 26 ጳጳሳትን ሾመው “ሁሉን ያሳተፈ ቅዱስ ሲኖዶስ” መቋቋሙን አስታውቀዋል።3ኦቢኤስቲቪ፣ ‘በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ’፣ ጥር 14, 2015 አቡነ ሳዊሮስ ምእመናን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው መገልገል ባለመቻላቸው በቤተ-ክርስቲያኒቱ ውስጥ ለረዥም ጊዜ ሳይፈታ የቆየውን ችግር ለመፍታት እነዚህን ሹመቶች አስፈላጊ እንደሆኑ አስረድተዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሲኖዶስ አመራሩን በአብዛኛው “ከአንድ ቡድን” በመሾም ሁሉንም ያሳተፈ መሆን አልቻለም ሲሉ ከሰዋል።4ኦቢኤስቲቪ፣ ‘በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ’፣ ጥር 14, 2015 በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሲኖዶስ በአቡነ ሳዊሮስ የተመራውን ሁሉንም ያሳተፈ ነው የተባለውን ሲኖዶስ ሹመት “ሕገወጥ” በማለት ሦስቱን ሊቃነ ጳጳሳት እና የተሾሙትን 25 ጳጳሳት አውግዘው ከቤተ-ክርስቲያን አግደዋል።5ከተሾሙት 26 ጳጳሳት መካከል አንዱ 26 ጳጳስ በአቡነ ሳዊሮስ የሚመራውን ቡድን ትቶ ለበኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ፓትራያርክ የይቅርታ ደብዳቤ ከስጋባና ይቅርታ ከጠየቀ በኃላ ወደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሲኖዶስ ተመልሷል፤ የኢኦተቤ ቲቪ፣ ‘አባ ጸጋዘአብ አዱኛ ይቅርታ ጠየቁ’፣ ጥር 17, 2015 ይመልከቱ ሲኖዶሱ በአቡነ ሳዊሮስ ከሚመራው ቡድን ጋር መደራደር “በተዘዋዋሪ የቤተ-ክርስቲያናችንን ህግና ስርዓት መጣሰ ነው” ብሏል።6 የኢኦተቤ ቲቪ፣ ‘የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ’፣ ጥር 18, 2015 ሲኖዶሱ መንግሥት ቤተ-ክርስቲያንን እንዲጠብቅም ጠይቋል።
ባለፈው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ችግሩ በውይይት ሊፈታ እንደሚገባ ተናግረዋል። በቤተ-ክርስቲያኗ በተከሰተው አለመግባባት (ችግር) መንግስት ጣልቃ እንደማይገባ አረጋግጠው ካቢኔያቸውንም ጣልቃ እንዳይገቡ ጠይቀዋል።7ፌስቡክ @አብይ አህመድ አሊ፣ ጥር 23, 2015 ነገር ግን የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ኃይሎች የኦርቶዶክስ አብያተ-ክርስቲያናትን አቡነ ሳዊሮስ ለሚመራው ሁሉን ያሳተፈ ነው ለተባለው ሲኖዶስ ቡድን አንሰጥም በማለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያንን የደግፉ ሊቃነ ጳጳሳትን፣ ጳጳሳትን እና ምእመናንን ማሰር ሲጀምሩ ሁኔታው ወደ ግጭጥ ተለውጧል። እነዚህ ድርጊቶች ውዝግቡን በማባባስ ውጥረቱ እንዲጨምር ያደረጉ ሲሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሲኖዶስ እና አማኞች ጠቅላይ ሚኒስትሩን እና መንግስትን ህገ-መንግስቱን በመጣስ በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ እየገቡ እና ከቤተ-ክርስትያን “የታገደውን” ሌላኛውን ወገን ይደግፋሉ ሲሉ ከሰዋል።8የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት፣ ‘ጠቅላይ ሚንስትሩ በሰጡት ማብራሪያ የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ’፣ ጥር 24, 2015 ጥር 27 ቀን በሻሸመኔ ከተማ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ላይ ባደረሰው ጥቃት ቢያንስ ሦስት ሰዎች ተገድለዋል።9ቪኦኤ፣ በአንድ ሪፖርት መሰረት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ላይ በደረሰ ጥቃት ሶስት ሰዎች ተገደሉ፣ ጥር 27, 2015፤ ይህ ክስተት በሚቀጥለው ሳምንት ዳታ ውስጥ ይካተታል ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሲኖዶስ ከጥር 29 ጀምሮ ለሶስት ቀናት የጾም፣ የጸሎት እና የእምነቱ ተከታዮች ጥቁር ልብስ እንዲለብሱ ያወጀ ሲሆን የካቲት 5 ቀን በሀገር ውስጥ እና በውጪ በሚገኙ አብያተ-ክርስቲያናትን ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል።10 የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የታወጀ አዋጅ፣ ጥር 27, 2015 የኢፒኦ ተመራማሪዎች ይህንን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተሉ ነው።
በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ከጀመረ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር ተደራዳሪ ቡድን ጋር ተገናኝተዋል። በዚህ ስብሰባ በጥቅምት 2015 የተፈረመውን የሰላም ስምምነት አፈፃፀም የገመገሙ ሲሆን በትግራይ ክልል የቀሩትን የኤርትራ ወታደሮች፣ የባንክ አገልግሎት፣ መንገዶችን መክፈት፣ በጀት ማውጣት እና በትግራይ የሽግግር መንግስት መመስረትን ጨምሮ ሌሎች ተጨማሪ እርምጃዎችን የሚሹ ጉዳዮችን ለይተዋል።11የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ‘የፌዴራል መንግሥት እና የህወሓት የሰላም ስምምነት ኮሚቴ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ለመጀመሪያ ጊዜ ተገናኙ’፣ ጥር 26, 2015፤ ኢቢሲ፣ ‘የፌደራል መንግሥትና የህወሓት የሰላም ድርድር ኮሚቴ አባላት ውይይት’፣ ጥር 27, 2015፤ ኢቢሲ፣ ‘አቶ ጌታቸው ረዳ ከኢቢሲ ጋር’፣ ጥር 26, 2015፤ ኢቢሲ፣ ‘”የሰላም ስምምነት ውይይቶች መተማመንን የገነቡ ናቸው”- አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን’፣ ጥር 26, 2015፤ ቢቢሲ አማርኛ፣ ‘አቶ ጌታቸው ረዳ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ስለነበራቸው ውይይት ምን አሉ?’፣ ጥር 30, 2015 ከዚያም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ትግራይ ክልል ርዕሰ መዲና መቀሌ የሚደረጉ በረራዎች ቁጥር እንዲጨምሩ እና የባንክ ስርዓቱን አቅም ለማሳደግ ወስነዋል።12ቲዊተር @ሬድዋን ሁሴን፣ ጥር 26, 2015 የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አቶ ሬድዋን ሁሴን እንዳሉት፣ ብሔራዊ ባንክ ከጥር 29 ጀምሮ 5 ቢሊዮን ብር (93 ሚሊዮን ዩኤስ ዶላር) ወደ መቀሌ መላክ የጀመረ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደግሞ በሳምንት ወደ መቀሌ የሚያደርገውን በረራ ከሦስት ወደ አምስት አሳድጎል።13ቲዊተር @ሬድዋን ሁሴን፣ ጥር 27, 2015