በዚህ ዘገባ ውስጥ የተካተቱ
- ከታህሳስ 23 እስከ ጥር 23 በጨረፍታ
- አበይት ክንውኖች
- ከታህሳስ 23 እስከ ጥር 23 የተከሰቱ ቁልፍ ኩነቶች
- ወርሀዊ ትኩረት፡ የመረጃ ምህዳር በኢትዮጵያ
ከታህሳስ 23 እስከ ጥር 23 በጨረፍታ
አበይት ክንውኖች
- አክሌድ ከታህሳስ 23 እስከ ጥር 23 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ 92 የፖለቲካ ግጭት ኩነቶችን እና 236 ሪፖርት የተደረጉ ሟቾች መዝግቧል። ይህ ከሕዳር 22 እስከ ታህሳስ 22 ካለው ጊዜ ጋር ሲነፃፀር በ103% ከጨመረው ከጦርነት እና በ7% ከመጨመረው ከጦርነት ጋር የተያያዘ የሟቾች ቁጥር በስተቀር ሁሉም የኩነት ዓይነቶች ቀንሰዋል።
- በፖለቲካዊ ግጭት ምክንያት ከፍተኛው የኩነት መጠን በኦሮሚያ ክልል የተከሰተ ሲሆን 50 ኩነቶች ሲመዘገቡ በአማራ ክልል ከፍተኛው ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር ሲከሰት 142 ሪፖርት የተደረጉ ሟቾች ተመዝግበዋል። ይህ ባለፉት ሦስት ወራት ከነበረው ሁኔታ ጋር የሚፃረር ሲሆን ባለፉት ሦስት ወራት አብዛኛው ኩነቶች እና የሟቾች ቁጥር ይከሰት የነበረው በኦሮሚያ ውስጥ ነበር።
- ከታህሳስ 23 እስከ ጥር 23 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ተደጋግመው የተከሰቱት የኩነት አይነትች ጦርነት እና በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶች ሲሆኑ 65 የጦርነት ኩነቶች እንዲሁም 25 በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸ የጥቃት ኩነቶች ተከስተዋል።አብዛኛው ጦርነት በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ እና በመንግስት ኃይሎች መካከል መሆኑ በዚህ ወርም የቀጠለ ሲሆን 13% የሚሆነው ጦርነት ደግሞ በኦሮሞ ብሄር ታጣቂዎች እና በአማራ ክልል ልዩ ኃይሎች መካከል የተደረገ ነው።
ከታህሳስ 23 እስከ ጥር 23 የተከሰቱ ቁልፍ ኩነቶች
ወርሀዊ ትኩረት፡ የመረጃ ምህዳር በኢትዮጵያ
በ2010 ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተደረጉ ማሻሻያዎች (ለውጦች) በመጀመሪያ ከፍተኛ የፕሬስ ነፃነትን አስገኝተው ነበር ። አብይ ከ250 በላይ የሚዲያ ተቋማት ላይ ተጥሎ የነበረውን እገዳ በማስወገድ በደርዘን የሚቆጠሩ ጋዜጠኞችን ከእስር ፈትተዋል።1ማጊ ፊክ፣ ‘በአብይ ኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት አብቦ ከዚያ ፍርሃት ተመለሰ’ ሮይተርስ፣ ግንቦት 20, 2013 እንደ በዲያስፖራው ከሚተዳደረው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (ኦኤምኤን) እና የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ያሉ የተከለከሉ ሚዲያዎች በአቢይ በሚያከናውነው ለውጥ ያላቸውን እምነት በመግለፅ በአዲስ አበባ ቢሯቸውን ከፍተዋል።2ፍሪደም ሃውስ፣ ‘ነጻነት በአለም እ.ኤ.አ 2020፡ ኢትዮጵያ፣’ እ.ኤ.አ 2020; የኦኤምኤን እና የኢሳት እገዳን በተመለከተ ለበለጠ መረጃ አዲስ ፎርቹን ‘ኮማንድ ፖስት ኢሳትን፣ኦኤምኤን ማየት ከለከለ,’ ጥቅምት 8, 2009 ይመልከቱ።
ከዚያን በኃላ የተደረጉ የፖለቲካ ግጭቶች፣ አመፆች እና የአብይ መንግሥትን በመቃወም የሚደረጉ በርካታ የሽምቅ ውጊያዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩን የነጻነት አጀንዳ ተገዳድረዋል። በምላሹ የመንግስት ጫና፣ ጥግ የረገጡ አስተሳሳቦች መጨመር እና ግጭት የተከሰተባቸው አካባቢዎች ተደራሽ እንዳይሆኑ መገደብ የተለያዩ የመረጃ ምህዳር አስከትሏል። ይህ በጊዜ ሂደት እየጨመረ የመጣ ሲሆን በመላ ሀገሪቱ የተለያየ ሁኔታ አስከትሏል። ለምሳሌ እ.ኤ.አ ከ2019 ጀምሮ የተለያዩ የሚዲያ አውታሮች እና ምንጮች በአጠቃላይ ቀንሰዋል፤ ጋዜጠኞች ታስረዋል፣ ከሃገር ተባረዋል እና እንግልት ደርሶባቸዋል፤ በተጨማሪም በአገር ውስጥ እና በአለም አቀፍ ለሚገኙ ታዳሚዎች ያላቸው ሽፋን ውስን ነው፤ የመገናኛ ብዙኃን ከጊዜ ወደ ጊዜ የአድማጮቻቸውን ጥግ የረገጠ አመለካከት ማንፀባረቅ የጨመሩ ሲሆን ክስተቶች በሚዘገቡበት ጊዜ ወደ አንድ ወገን ያደሉ ዘገባዎች ጨምረዋል።3ዴክለን ዋልሽ፣ ‘ኢትዮጵያ የኒውዮርክ ታይምስ ሪፖርተርን አባረረች’፣ ኒው ዮርክ ታይምስ፣ ግንቦት 12, 2013; ኮሚቴ ቱ ፕሮቴክት ጆርናሊስትስ፣ ‘ኢትዮጵያ የኢኮኖሚስት ዘጋቢውን ቶም ጋርድነርን አባረረች’ ግንቦት 8, 2014 ይህ በእንዲህ እንዳለ አንዳንድ ክልሎች ተደራሽ የሆኑ የህዝብ ቻናሎች/ጣቢያዎች ሰለሌሏቸው ‘የሚዲያ/የመገናኛ ብዙኃን በረሃ’ ሆነዋል። በመገናኛ ብዙኃን፣ በኮሙዩኒኬሽን እና በመብራት መቆራረጥ እንዲሁም የኢትዮጵያን የግጭት ቀጠናዎችን ከመሸፈን ጋር ተያይዞ በሚከሰቱ ስጋቶች ምክንያት ግጭት ያለባቸውን ጨምሮ ሌሎች ክልሎች ከመረጃ ውጪ ሆነዋል።4አሶሼትድ ፕሬስ፣ ‘ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ያለው የግንኙነት መቋረጥ (blackout) የሚያበቃበት ቀን አልሰጠችም፣’ ህዳር 20, 2015
የዚህም ምክኛት አጠቃላይ ውጤቶቹ
(1) በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ስላለው የፖለቲካ ግጭጥ እና ብጥብጥ የተሟላ እና ትክክለኛ መረጃ የማግኘት እጥረት እንዲኖር አድርጓል። ይህም ስለ ግጭት ኩነቶች እና ተሳታፊ አካላት በቂ ያልሆነ መረጃ እንዲኖር አድርጓል።
(2) ብዙ ጊዜ ከግጭት ቀጠና አልፎ ከኢትዮጵያ ውጪ በሚገኙ ምንጮች የተዛባ፣ የተሳሳተ እና የሀሰት መረጃ መስፋፋትን አስከትሏል። ለአንድ ወገን ያደሉ የግጭት ዘገባዎች ‘ለሌላው ወገን’ ሊያደሉ (ሊያግዙ) የሚችሉ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ከመዘገብ ይቆጠባሉ። እነዚህ ምንጮች የመረጃ ክፍተቶችን የሚሞሉ ቢሆንም አሳሳች የሆነ አድሏዊ፣ የጥላቻ ንግግሮች እና ጠንካራ የሆነ የመረጃ ማጣራት አያደርጉም ተብሎ ስለሚታሰብ በመረጃ ላይ ሰፋ ያለ አለመተማመንን ይፈጥራሉ።
(3) አድልዎ የሌለው፣ ጠንካራ እና በደንብ የተመዘገቡ ክስተቶች ላይ የሚያተኩር የኢትዮጵያ የመረጃ ምህዳርን ለማሳደግ የሚደረገውን አንቅስቃሴ ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ አሳይቷል።
ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥርን የአክሌድ ተመራማሪዎች እንዴት አድርገው ኮድ ያደርጋሉ?
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረጉ የፖለቲካ ግጭት እና የሰልፍ ኩነቶችን ከሀገር ውስጥ ካሉ አጋሮች ከሚሰበሰቡት መረጃ በተጨማሪ የኢፒኦ ተመራማሪዎች በየሳምንቱ የእንግሊዝኛ፣ የአማርኛ፣ የሶማሊኛ፣ የትግርኛ እና የአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች የመረጃ ምንጮችን ይከታተላሉ። አክሌድ እና ኢፒኦ መረጃን ለመሰብሰብ የሚጠቀሙበት ዘዴ የማይለዋወጥ እና አክሌድ በዓለም አቀፍ ደረጃ መረጃ መሰብሰብን በተመለከተ ካለው አካሄድ ጋር ተመሳሳይ ነው።
በዚህ ዘዴ መሰረት በአክሌድ መረጃ ቋት (dataset) ኩነቶች ናቸው የሚካተቱት ማለትም መረጃ ስለ ጦርነቶች፣ ፍንዳታዎች እና የርቀት ግጭቶች፣ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች፣ ተቃውሞዎች፣ አመፆች እና ስልታዊ ጉዳዮች ከተለያዩ ምንጮች ይሰበሰባል (ከዚህ በታች ያለውን ግራፍ ይመልከቱ)። የፖለቲካ ጥቃት ፈፃሚዎችን የመንግስት ኃይሎች እና አጋሮቻቸው፣ አማፂ ቡድኖች፣ ታጣቂዎች፣ የውጭ ወይም የግል ኃይሎች እና ሁከት ፈጣሪዎችን ያካትታሉ። ለሟቾች ቁጥር አክሌድ በጣም ወግ አጥባቂ የሆነ ግምት የሚጠቀም ሲሆን የኩነቱ ምንጭ (ዘገባ) ሰለ ሞቱ ሰዋች ካልዘገበ/ካልጠቀሰ ምንም አይነት የሟቾች ቁጥር አይመዘገብም። ምንጩ/ዘገባው ቁጥራቸው ያልታወቀ ሟቾችን ከጠቀሰ ተመራማሪዎች ኩነቱ የት እንደተከሰተ እና እነ ማን እንደተሳተፉበት መሠረት በማድረግ እንደ ኩነቱ ሁኔታ 3 ወይም 10 የሟቾች ቁጥር ኮድ ይደረጋል። ለምሳሌ በጦርነት ቀጠና ውስጥ የተከሰተ ኩነት ከፍተኛ የሞት አደጋ ሊያስከትል የሚችልበት አጋጣሚ ከፍተኛ በመሆኑ ዘገባው ቁጥራቸው ያልታወቀ ሟቾችን ከጠቀሰ 10 ሰዎች መሞታቸው ይገመት እና 10 ኮድ ይደረጋል። ሁኔታዎች የሟቾች ቁጥር ከ10 በታች ሊሆን እንደሚችል በሚጠቁሙበት ዝቅተኛ ግጭት በሚከሰትበት ቀጠና ውስጥ ዝቅ ያለ የሟቾች ቁጥር 3 ኮድ ይደረጋል። ተጨባጭ መረጃ እስካልተገኘ ድረስ ምንጩ/ዘገባው የተለያዩ የሟቾች ቁጥር ከጠቀሰ ዝቅተኛው የሟቾች ቁጥር ይመዘገባል። አንድ ምንጭ/ዘገባ ለአንድ ኩነት ‘በመቶዎች’ የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸውን ከጠቀሰ እና ለዚህ ክስተት ምንም ተጨማሪ መረጃ ካልተካተተ ለዚህ ኩነት 100 ሰዎች መሞታቸው ይመዘገባል። አስተማማኝ ምንጭ በጦርነት ምክንያት የሞቱ ሰዎችን ከዚህ እስከ እዚህ ብሎ የሚያመለክት ከሆነ አማካዩ የሟቾች ቁጥር በእዚህ ጦርነት ለተመዘገቡ ኩነቶች ሊከፋፈል/ሊሰራጭ ይቻላል (ለበለጠ መረጃ፣ FAQs፡ ACLED Fatality Methodology/ተደጋግመው የሚነሱ ጥያቄዎች፡ የአክሌድ የሟቾች ቁጥር የመመዝገብያ ዘዴን ይመልከቱ)። ለምሳሌ በኃላ ላይ በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሄደው የሁለት ዓመት ውጊያ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች መሞታቸው ከተገለጸ ከዚህ ቀደም አስተማማኝ የሟቾች ቁጥር መረጃ ያልተገኘባቸው ወይም የሟቾች ቁጥር በግምት ኮድ የተደረገባቸው ኩነቶች ተለይተው ይህ አዲስ የተረጋገጠው የሟቾች ቁጥር ለነዚህ ኩነቶች ይከፋፈል/ይስራጭ እና ኩነቶቹ ይታረማሉ/ይሻሻላሉ። እነዚህ ማስተካካያዎች/ማሻሻያዎች በቀጥታ የሚደረጉት በኩነቶች መረጃ ቋት ላይ ሲሆን በይፋ ተጠቅሰው አዲስ ትንተና ይለቀቃል።
እያንዳንዱ በአክሌድ የተመዘገበ ኩነት ከታወቀ ምንጭ ጋር የተገናኘ ነው። እነዚያ ምንጮች በአብዛኛው የታወቁ፣ ይፋዊ እና ክፍት ሲሆኑ- አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ – የአካባቢ እና የግል ምንጮች ናቸው። አክሌድ ሰለፖለቲካ ረብሻ ኩነቶች ትክክለኛ ዝርዝር መረጃ ለመስጠት በእነዚህ ምንጮች ላይ የሚመረኮዝ ሲሆን ማንኛውንም አድሎ ለመለየት እና ለመቆጣጠር እንዲሁም ጠንካራ መረጃ ለማግኘት በምንጮቹ/ዘገባዋቹ ላይ አስቀድሞ በጠንካራ ግምገማ ያደርጋል። ግጭት የሚገኙባቸው ቀጠናዎች በጣም የተዛባ መረጃዎችን ማፍራት ቢችሉም ከእንደዚህ ዓይነት ምንጮች ጠቃሚ መረጃዎችን መርጦ በማውጣት መጀመሪያ የነበረውን የአድሏዊነት ተፅእኖ ለመቀነስ እና የኩነት መረጃን ሰብሰቦ ለማቆየት ይችላል (በግጭት መረጃ ላይ ያለውን አድልዎ አስመልክቶ በቅርብ ጊዜ ስላለው ውይይት የበለጠ መረጃ ለማግኘት በግጭት መረጃ/ዳታ ውስጥ ስላለው አድልዎ ለመቅረፍ የቀረበ አጀንዳን ይመልከቱ)።
‘በጣም አድሏዊነት’ የሚታይባቸውን ዘገባዎች ለመቆጣጠር የሚደረጉ የተለመዱ የቁጥጥር ደንቦች ብዙውን ጊዜ ያልተዘገበ የሞቾች ቁጥርን ያስከትላል። በኩነቶች ዳታ ውስጥ የሟቾች ቁጥር በጣም አድሏዊነት የሚታይበት ክፍል ሲሆኑ ለሚዲያ ጥቅም፣ ለጋዜጠኞች አድሏዊ ግምት እና ለመረጃ አድልዎ (ማለትም ምንጩ/መረጃው የመጣው ከየትኛው የግጭት ወገን ነው) ለሚሉት ወገንተኝነት የተጋለጠ ነው። ለምሳሌ ታሊባን በአፍጋኒስታን ውስጥ አማፂ ሆኖ በሚንቀሳቀስበት ወቅት ንቁ የሪፖርት ማቅረቢያ አገልግሎት ነበረው (ለተጨማሪ መረጃ ዓለም በታሊባን መሠረት፡ አዲስ ዳታ/መረጃ በአፍጋኒስታንን ይመልከቱ)። ይህ አገልግሎት ወሳኝ በሆኑ ኩነቶች እና ከመንግስት ኃይሎች ጋር የሚደረጉ ውጊያዎች እንዲሁም ያልተለመዱ ግጭቶች ላይ ከሌሎች የአፍጋኒስታን ምንጮች ጋር ተመሳሳይ የሆኑ መረጃዎችን ሪፖርት አድርጓል። ሆኖም ይህ ምንጭ በአብዛኛው በመንግስት ኃይሎች ላይ የደረሱ የተዛቡ የሟቾች ቁጥር ሪፖርት የማድረግ አዝማሚያ ነበረው። ስለዚህም የሟቾች መረጃው ወገንተኛ የነበር ሲሆን የኩነቶቹ መረጃ ግን አስተማማኝ ነበር።
አክሌድ እና ኢፒኦ አጠቃላይ የግጭት ሞትን እንዴት ይዘግባሉ?
በኢትዮጵያ ከግጭት ጋር በተያያዘ የሞቱት ሰዎች በቅርቡ የዓለም አቀፍ ሚዲያዎችን ‘በዓለም ላይ እጅግ ገዳይ ግጭት’ በማለት አርዕስተ ዜናዎች ተቆጣጥሯል።5ቦቢ ጎሽ፣ ‘የአለማችን ገዳዩ ጦርነት በዩክሬን ሳይሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ነው፣’ ዋሽንግተን ፖስት፣ መጋቢት 14, 2014 ከጥቅምት 2013 እስከ 2015 ባለው ጊዜ ውስጥ በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ግጭት ከ300,000 እስከ 800,000 የሚገመት የሰላማዊ ሰዎች ህይወት መጥፋቱ ይገመታል። ይህ የተለያየ የሟቾች ቁጥር በግጭት ምክንያት የሚከሰቱ የሟቾች ቁጥር ግምገማ ምሳሌ ነው። እንደነዚህ ያሉ ግምገማዎች በተለምዶ ለክርክር የተጋለጡ ናቸው።
ለውይይት ሲባል የሚከተሉትን ነጥቦች ማንሳት ያስፈልጋል፣
(1) አክሌድ ከአጠቃላይ ኩነቶች እና ሟቾች ቁጥር ተነስቶ ወደ ታች እያንዳንዱ ኩነት ጋር እየሄደ ሳይሆን የሚሰራው ይልቁንም ከኩነቶች (እና ከምንጩ/መረጃው) ተነስቶ ወደ ላይ ወደ አጠቃላይ ኩነቶች እና የሟቾች ቁጥር ይሰራል። ይህ ማለት መረጃዎች የሚፈለጉት እና የሚሰበሰቡት በኩነቶች ላይ ነው እንጂ አሁን ያለውን ከፍተኛ ቁጥር ለመደገፍ አይደለም። አጠቃላይ የተገመቱ የሟቾች ቁጥርን በኩነቶች እና በማስረጃዎች ማረጋገጥ በጣም ያልተለመደ ነው።
(2) በሰፊው የሚለያዩ ትላልቅ የሟቾች ቁጥር ግምቶች የብዙ ከባድ ጦርነቶች መገለጫ ናቸው። እነዚህ ግምቶች ከደካማ ሪፖርት ወይም ከዝቅተኛ የመረጃ ምህዳር ጋር የተቆራኙ አይደሉም። ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር የተለያዩ የቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆኑ ሞትን ያንፀባርቃል። ብዙውን ጊዜ በጋዜጠኞች፣ በሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና በሌሎች የምርምር አካላት የሚለቀቁ ዘገባዎች በፖለቲካ ግጭት ምክንያት በቀጥታ ከሚሞቱት ሰዎች በተጨማሪ በተዘዋዋሪ/ቀጥተኛ ባልሆኑ ምክንያቶች (በጤና እጦት፣ የተመጣጠነ ምግብ እጦት ወዘተ ጨምሮ) የሞቱ ሰዎችን ግምቶችን ይጨምራሉ።
ብዙን ጊዜ በፖለቲካ ግጭት ምክንያት ደረሱ ተብለው የሚገመቱ ጠቅላላ የቀጥተኛ ሟቾች ቁጥር ከተገመተው ቀጥተኛ ያልሆነ/ተዘዋዋሪ የሟቾች ቁጥር በእጅግ ያነሰ ነው። በበርካታ የጦርነት ቀጠናዎች ውስጥ በተከሰቱት የሟቾች ቁጥር ላይ የተደረጉ ጥናቶች በአደባባይ ከግጭቶች ጋር በተያያዘ ከሚጠቀሱት የሟቾች ቁጥር በጣም ያነሰ ግምቶችን ያካትታሉ፡ በአፍጋኒስታን እና በፓኪስታን (እ.አ.አ. 2001-21) በኢራቅ (እ.አ.አ. 2003-21)፣ ሶሪያ (እ.አ.አ. 2014-21)፣ የመን (እ.አ.አ. 2002-21) ጦርነቶች እና ተጨማሪ የድህረ-9/11 የጦርነት ቀጠናዎች ቀጥተኛ የሟቾች ቁጥር ጨምሮ በብራውን ዩኒቨርሲቲ ዋትሰን የአለም አቀፍ እና የህዝብ ጉዳዮች ኢንስቲትዩት የጦርነት ወጪ ፕሮጀክት መሰረት በድህረ-9/11 ጊዜ ውስጥ የተካሄዱ ጦርነቶችን ሂሳብ ግምት ውስጥ ያስገቡ። ይህም “በቀጥታ ጦርነት ምክንያት ይህም በግጭቶቹ በሁሉም ወገን ያሉ የታጠቁ ኃይሎች፣ ተቋራጮችን፣ ሰላማዊ ሰዎችን፣ ጋዜጠኞችን እና የእርዳታ ሠራተኞችን ጨምሮ ቢያንስ 929,000 ሰዎች ሞተዋል” ይላል።6ዋትሰን የአለም አቀፍ እና የህዝብ ጉዳዮች ተቋም፣ ‘የጦርነት ዋጋ’፣ እ.እ.እ. ሴፕቴምበር 2021፣ በተጨማሪም ዳንኤል ብራውን እና አዝሚ ሃሮን ‘የጉዳቱን መጠን የሚዘረዝረው ዘገባ እንዳለው በኢራቅ እና አፍጋኒስታን ውስጥ በተደረጉት ጦርነቶች በትንሹ 500,000 ሰዎችን ገድለዋል፣’ ቢዝነስ ኢንሳይደር፣ ነሐሴ 20, 2014ን ይመልከቱ በተጨማሪም በዩክሬን ግጭት ወቅት በውጫዊ ምንጮች ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር ግምት የሚቀርቡበትን የእውነተኛ ጊዜ ሰነዶችን እና ያለውን ክርክሮች ይመልከቱ።7ኦሊቪየር ኖክስ፣ ‘ሩሲያ በዩክሬን እስከ 80,000 ወታደሮች አጥታለች። ወይም 75,000። ወይስ 60,000 ነው?፣’ ዋሽንግተን ፖስት፣ ነሐሴ 3, 2014፤ በተጨማሪም ሄለን ኩፐር፣ ኤሪክ ሽሚት እና ቶማስ ጊቦንስ-ኔፍ፣ ‘የሞት መጠን መጨመር ስለሩሲያ ስልቶች አሳዛኝ ግንዛቤን ይሰጣል፣’ ኒው ዮርክ ታይምስ፣ ጥር 25, 2015 ይመልከቱ፣ እንደ ዩኤስ ባለስልጣናት ሁሉም የተጎጂዎች ቁጥር ግምት ከፍ ወይም ዝቅ ሊል የሚችል ነው። ተጨማሪ ክስተቶችም የሚያመላክቱት ውጊያ ባለባቸው አካባቢዎች ስለ ኩነቶች፣ ሰለሚያስከትሉት ውጤቶች እና የሞት አደጋዎች ግልጽ በሆነ ሁኔታ ለማስረዳት ሪፖርት ማድረግ አለመቻልን ያመለክታሉ።8ዳን ላሞቴ፣ ሊዝ ስሊ እና አናቤል ቲምሲት፣ ”ዩኤስ ከ100,000 በላይ የሩስያ ወታደሮች በዩክሬን ተገድለዋል ወይም ቆስለዋል’ አለች፣’ ዋሽንግተን ፖስት፣ ህዳር 1, 2015። *በዩክሬን ጦር እና በሩሲያ ጦር ውድቅ ተደረገ ከዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ እይታ አንጻር በዩክሬን የተከሰቱ የሟቾች ቁጥር ሪፖርቶች።
የግጭት ውጤት ብዙውን ጊዜ በጦርነቱ መጀመሪያ ላይ የተጋነነ ሲሆን በተግባር ግን በጦርነቱ ምክንያት በቀጥታ የሞቱ ሰዎችን ቁጥርን በተዘዋዋሪ ምክንያት ከሞርቱ ሰዎች ቁጥር ጋር መገምገም አስቸጋሪ ነው። በተጨማሪም ከግጭት ጋር የተያያዙ የሟቾች ቁጥርን እንደ ናሙና ከተወሰዱ የማህበረሰብ ቁጥሮች ተነሰቶ የሟቾች ቁጥር የሚገመትበት አሰራር9ባሩክ ፊሽሆፍ፣ ስኮት አትራን እና ኖአም ፊሽሆፍ፣ ‘ተጎጂዎችን መቁጠር፡ ለጠቃሚ መዝገቦች ማዕቀፍ፣’ የስጋት እና አለመተማመን ጆርናል፣ እ.አ.አ. 2007 አከራካሪ ሲሆን በአብዛኛው ጊዜ ማረጋገጥ ሆነ ውድቅ ማድረግ አይቻልም። ለምሳሌ የዓለም አቀፉ የነፍስ አድን ኮሚቴ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከቀጠለው ግጭት ጋር በተያያዘ እ.ኤ.አ. እስከ 2007 ድረስ 5.4 ሚሊዮን ‘ከልክ በላይ’ ለሞት መዳረጋቸውን ዘግቧል።10ቤንጃሚን ኮግላን፣ ፓስካል ንጎይ፣ ፍላቪን ሙሉምባ፣ ኮሊን ሃርዲ፣ ቫለሪ ንካምጋንግ ቤሞ፣ ቶኒ ስቱዋርት፣ ጄኒፈር ሉዊስ እና ሪቻርድ ብሬናን፣ ‘የሟቾች ቁጥር በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፡ የቀጠለው ቀውስ፣’ የአለምአቀፍ አድን ኮሚቴ፣ ሚያዚያ 23, 1999 ይህ ግምት እንደ ናሙና ከተወሰዱ የማህበረሰብ ቁጥሮች ላይ የተመሰረተ11በሀገሪቱ ውስጥ ሶስት ደረጃ እና ቤተሰብን መሰረት ያደረገ የክላስተር ናሙና ዘዴን በመጠቀም በሁለት እርከኖች ጥናቶች ተደርገው ነበር። ከክላስተር ናሙና ተነሰቶ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ግምት ተግኝቷል። ሲሆን እንደ ናሙና ከተወሰዱ የማህበረሰብ ቁጥሮች ላይ በተደረጉ ጥናቶች ከመጠን በላይ የሞቱ ሰዎች የተገመቱበት ተደርጎ ይታያል።12ቤንጃሚን ኮግላን፣ ፓስካል ንጎይ፣ ፍላቪን ሙሉምባ፣ ኮሊን ሃርዲ፣ ቫለሪ ንካምጋንግ ቤሞ፣ ቶኒ ስቱዋርት፣ ጄኒፈር ሉዊስ እና ሪቻርድ ብሬናን፣ ‘የሟቾች ቁጥር በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፡ የቀጠለው ቀውስ፣’ የአለምአቀፍ አድን ኮሚቴ፣ ሚያዚያ 23, 1999፤ ሪቻርድ ቺንግጋምብ ካፔንድ፣ ‘የጦር ግጭት እና ብጥብጥ ስነ-ሕዝብ፡ እ.አ.አ. ከ1998-2004 ዲ.አር.ኮንጎ ጦርነት ጋር የተያያዘውን የየሟቾች ቁጥር መገምገም፣’ የሳውዝሃምፕተን ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ቴሲስ፣ እ.አ.አ. 2014 ተጨማሪ ንባብ በሚደረግበት ጊዜም ከእነዚህ ከተጠቀሱት የሟቾች ቁጥር ውስጥ 10% የሚሆኑት የሟቾች ቁጥር ብቻ ከግጭት ጋር በማንኛውም መንገድ (በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ) የተገናኙ ሲሆኑ የተቀሩት አብዛኛዎቹ በጤንነት ምክንያት የተከሰቱ ናቸው። ሆኖም በግጭቶች ላይ የሚወጡ ሪፖርቶች አንዳንድ ጊዜ መከላከል የሚቻሉትን የሞት አደጋዎች በሙሉ ወደ ‘ከግጭት ጋር በተያያዙ የሟቾች ቁጥር’ ስለ ሚጠቃለሉ ከፍተኛ የሟቾች ቁጥርን ያስከትላሉ።
ባለፉት ሁለት አመታት 600,000 የትግራይ ሰላማዊ ሰዎች ሞተዋል?
ከፋይናንሺያል ታይምስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የአፍሪካ ህብረት ተወካይ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ በኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት አመታት በተፈጠረው የእርስ በርስ ጦርነት 600,000 ሰዎች ሊሞቱ እንደሚችሉ ገምተዋል።13ዴቪድ ፒሊንግ እና አንድሬስ ሺፓኒ፣ ‘በትግራይ ጦርነት 600,000 ሰዎችን ሳይገድል አልቀረም ሲል የሰላም አስታራቂ ተናግሯል፣’ ፋይናንሺያል ታይምስ፣ ጥር 6, 2015 ይህ የሟቾች ቁጥር እና ሌሎች በትግራይ ጦርነት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ትላልቅ ድምር ግምቶች በአክሌድ በተመዘገቡ ኩነቶች ላይ ከተገኙት ቁጥሮች ጋር ተመሳሳይ አይደሉም። አክሌድ ከጥቅምት 22, 2013 እስከ ጥር 23, 2015 ድረስ 1,905 የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች እና 9,861 ሪፖርት የተየደረጉ የሟቾች ቁጥር በትግራይ፣ አፋር እና አማራ ክልሎች መዝግቧል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። አክሌድ ከአራቱ ኢትዮጵያውያን አንዱ14ይህ ግምት የተወሰደው ከአክሌድ – የግጭት ተጋላጭነትን ለመወሰን ከዓለም ፖፕ ትብብር ነው። ከአራት አንዱ የሚለው ቁጥር የሚያመለክተው እ.ኤ.አ. በ2021 ቢያንስ ለአንድ ውጊያ፣ የተደራጀ የፖለቲካ ጥቃት በሚኖሩበት 5ኪሎ ሜትር ውስጥ የተጋለጡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ነው። ባለፈው አመት ለውጊያ፣ ለተደራጁ እና ገዳይ የፖለቲካ ጥቃቶች እንደተጋለጠ ይገምታል። ነገ ግን ይህ የአክሌድ ግምት በተለምዶ ከሚጠቀሰው 600,000+ ቁጥር ጋር አይቀራረብም። ይህ ለምን አልሆነም?
የጌንት ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ በሆኑት ፕሮፌሰር ጃን ኒሴን የተመራው ጥናት መሠረት ”እስከ ታህሳስ 22, 2015 በትግራይ የሞቱት አጠቃላይ የሰላማዊ ሰዎች ቁጥር ስሌት ግምት በአማካይ 518ሺ ሰላማዊ ሰዎች” ሲሆኑ ዝቅተኛው ግምት “311ሺ” እና ከፍተኛው ግምት “808ሺ” ነው። በተጨማሪም “በግምት 10 በመቶው የሚሆነው በጅምላ ጭፍጨፋ፣ በቦምብ እና በሌሎች ግድያዎች ምክንያት የሞተ ሲሆን፣ 30 በመቶው በጤና ስርዓቱ መፍረስ ምክንያት እና 60 በመቶው በረሃብ የሞተ ነው”።15ጃን ኒሴን፣ ‘የትግራይ ጦርነት የተጎዱትን ሰላማዊ ስዎች መመዝገብ፣’ በሮያል ሆሎውይ ማዕከል ለአለም አቀፍ ደህንነት እና ኤቭሪ ካዥዋሊት ካውንትስ ድርጅቶች የተዘጋጀ ወቢናር፣ ጥር 11, 2015፤ ጃን ኒሴን፣ ‘ወቢናር፡ በትግራይ ጦርነት የተጎዱትን ሰላማዊ ስዎች መመዝገብ፣’ ኤቭሪ ካዥዋሊት ካውንትስ፣ ጥር 11, 2015 በእነዚህ ግምቶች መሰረት 31,100-80,800 በጦርነቱ በቀጥታ የሞቱ ሲሆኑ የተቀሩት ደግሞ በተዘዋዋሪ/ቀጥተኛ ባልሆነ ምክንያት እንደሞቱ ይሳያል። እነዚህን ቁጥሮች ለመገመት የትኛው ዘዴን እንደተጠቀሙ አይታወቅም ምክንያቱም የአጠቃላይ የሟቾችን ቁጥርን ለመገመት የተለመዱት የመገመቻ ዘዴዎች እና ቴክኒኮች የጤና ጣቢያዎች፣ ካምፖች እና ሌሎች ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ናሙናዎች እና ሰርቬይ (የዳሰሳ ጥናቶች) ያስፈልጋሉ። ለእነዚህ ቁጥሮች እንደ ማስረጃ የሚታወቁ የዳሰሳ ጥናቶች ወይም ናሙናዎች አልተሰጡም። ይህ መረጃ ከክልላዊ፣ ብሄራዊ እና አለም አቀፍ ሃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች እና ጋዜጠኞች በተጨማሪ ከዜጎች ዘገባ እና ቁልፍ መረጃ ሰጭዎች፣ በከፊል የተዋቀሩ ቃለመጠይቆች እና ከጥቃት ከተረፉ ሰዎች ጋር የተደረገ የስልክ ቃለ ምልልስ እንደተገኘ ተጠቅሷል።16ጃን ኒሴን፣ ‘ወቢናር፡ በትግራይ ጦርነት የተጎዱትን ሰላማዊ ስዎች መመዝገብ፣’ ኤቭሪ ካዥዋሊት ካውንትስ፣ ጥር 11, 2015 ነገር ግን ከጌንት ቡድን ጋር በተደረገ ግንኙነት በተለይ ከጥቅምት 2013 ጀምሮ ከትግራይ መረጃ የማግኘት ወይም የማውጣት ችግር አኳያ መረጃው እንዴት እንደተሰበሰብ እና እንደተረጋገጠ አልተገለጸም።
በትግራይ ጦርነት የሚደርሰው ቀጥተኛ ሞት በኢትዮጵያ ትግራይ ጦርነት ድህረ ገጽ በኩል ኤቭሪ ካዥዋሊት ካውንትስ ፕሮጀክት ጋር የተያያዘ ነው።17 ጌንት ዩኒቨርሲቲ እና ኤቭሪ ካዥዋሊት ካውንትስ፣ ‘ኢትዮጵያ፡ የትግራይ ጦርነት፣ ስለ እኛ፣’ እ.አ.አ. 2023 ይህ ድህረ ገጽ ከማህበራዊ ሚዲያ፣ የሚዲያ ሪፖርቶች እና አድቮኬሲ (የጥብቅና/ተከራካሪ) ቡድን የተገኙ ዝርዝሮችን ጨምሮ ከተለያዩ ምንጮች/ዘገባዎች18ጌንት ዩኒቨርሲቲ እና ኤቭሪ ካዥዋሊት ካውንትስ፣ ‘ኢትዮጵያ፡ የትግራይ ጦርነት፣ ዘዴ፣’ እ.አ.አ. 2023 ከተሰበሰበው የተጎጂ ዳታቤዝ (የመረጃ ቋት) 435 ክስተቶችን እና በግምት 8,081-15,414 የሚገመቱ “ሟች ተጎጂዎችን” ከ445 ክስተቶች19ጌንት ዩኒቨርሲቲ እና ኤቭሪ ካዥዋሊት ካውንትስ፣ ‘ኢትዮጵያ፡ የትግራይ ጦርነት፣ ክስተቶች፣’ እ.አ.አ. 2023 መዝግቧል። ከዚህ ድረ-ገጽ መዛግብት የ31,100-80,800 በቀጥተኛ ጦርነት ምክንያት ሞተዋል ተብሎ የተገመተው የሰላማዊ ሰዎች ሞት የተረጋገጠ አይደለም፣ የ600,000+ የሟቾች ቁጥር ግምት ወይ አልተረጋገጠም ወይ ውድቅ አልተደረገም።
በተጨማሪም ከ600,000+ የሚገመተው የሟቾች ቁጥር የትግራይ ሰላማዊ ሰዎች ብቻ ሲሆኑ የትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሓት) ኃይሎች፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ የኤርትራ መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ እና የአፋር ታጣቂዎች እና የአማራ እና የአፋር ሰላማዊ ሰዎች ሞትን ሳይጨምር ነው። በአማራ እና አፋር ክልል የተከሰቱ የሰላምዊ ሰዎች ሞት ላይ ሪፖርት ማድረግ እንደ ትግራይ ገደብ አልተደረገበትም ነበር። መጠነ ሰፊ ጦርነት ከተካሄደ በኋላ ብዙም ሳይቆይ በተወሰኑት በክልሉ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የተደረጉ ዘገባዎችን ጨምሮ በርካታ ዘገባዎች የሰላማዊ ሰዎችን ህይወት መጥፋት ዘግበዋል።20አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ‘በአሸባሪው ሕወሃት ወረራ በአማራ ክልል የደረሰው ጉዳት በጥናት የተገኘው ውጤት ይፋ ሆነ’፣ መስከረም 19, 2015 እነዚህ ዘገባዎች በቀጥታ ሞት ላይ ያተኮሩ ነበሩ። ሆኖም ያለው ችግር ስለ ተዋጊ ኃይሎች (ተዋጊዎች) መረጃ አለመኖሩ ነው። አንዳንድ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ከ1998-99 በባድመ ዙሪያ ከነበረው የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ጦርነት ጋር ተመሳሳይ በሆነ መልኩ ለጠቅላላው ቀጥተኛ ሞት ወደ 80,000 ወይም 100,000 የሚጠጋ የሟቾች ቁጥር ያቀርባሉ።21ዴቪድ ፒሊንግ እና አንድሬስ ሺፓኒ፣ ‘በትግራይ ጦርነት 600,000 ሰዎችን ሳይገድል አልቀረም ሲል የሰላም አስታራቂ ተናግሯል፣’ ፋይናንሺያል ታይምስ፣ ጥር 6, 2015 ነገር ግን በጦርነቱ ወቅት ሁሉ የኤርትራዊያንን ሞት – ከኤርትራ መከላከያ ሠራዊት እና በኤርትራ መከላከያ ሠራዊት የተገደሉትን ሰላማዊ ሰዎች – የሚገመት፣ የሚገለጽ ወይም የሚያብራራ ምንም መረጃ እንደሌለ ይታወቃል።
ርዕዮት ሚዲያ ባሰራጨው ዘገባ መሰረት ለሁለት አመታት በዘለቀው ግጭት እስከ 254,000 የሚደርሱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ተዋጊዎች ተገድለዋል።22ርዕዮት ሚዲያ፣ ‘254ሺ ሠራዊት አልቆብናል›› ብርሃኑ ጁላ’ ጥር 19, 2015 በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጄኔራል ኢታማዦር ሹም ብርሃኑ ጁላ ተነግሯል የተባለው ይህ ቁጥር ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ያልተረጋገጠ ሲሆን እንደገና አጠቃላይ የቀጥታ የሟቾችን ቁጥር ይወክላል። በጦርነቱ ወቅት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና ከሠራዊቱ ጋር የተባበሩ ታጣቂዎች እና የትህነግ/ህወሓት ኃይሎች ላይ ከፍተኛውን የሞት አደጋ ሳያደርስባቸው አይቀርም። በታጠቁ ቡድኖች የተገደሉትን ሰዎች ቁጥር መለያት እና ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው።
በሰሜን የነበረው ጦርነት በሁሉም ቦታ የሚገኙ እና በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችን ጨምሮ ጦርነቱ ያስከተለውን ተፅእኖ የሚያጠኑ ያልተዛባ፣ ጠንካራ እና ጥልቅ የሆኑ ጥናቶችን ለመሰብሰብ እድሎች አሉ። ይህ የባለብዙ ቋንቋ ጥናት ቡድን፣ የተሻሻለ የአካባቢ ህዝብ ቁጥር ግምት፣ የሳተላይት ምስሎች ጥናት እና ከተጎዱት የሶስቱ ክልሎች አስተዳደሮች – ትግራይ፣ አማራ እና አፋር – እና የፌዴራል መንግስት ፍቃድ ይጠይቃል።
ሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎችስ?
ጥቅምት 2015 ጦርነቱን በዘላቂነት የሚያቆም ስምምነት ከተፈረመ በኃላ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ጦርነት ጋብ ያለ ሲሆን ትኩረት ወደ ኦሮሚያ ክልል ዞሯል። የሰሜን ኢትዮጵያ የነበረው ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦችን ያሳተፈ እና እንደ ታንኮች፣ መድፍ እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች ያሉ ከባድ ወታደራዊ መሳሪያዎች የተሳተፉበት ነበር። በአንፃሩ የኦነግ-ሸኔ (የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት በመባል የሚታወቀው) ሽምቅ በትንሽ ታጣቂዎች በተዋቀሩ ቡድኖች ሲዋጋ ቆይቷል፣ ውጊያውም መድፍ ወይም ሌላ ከባድ መሳሪያ እምብዛም አላሳተፈም። ሆኖም ይህ ግጭትም ገዳይ ነበር። በመጋቢት 2011 ቡድኑ ከኦነግ ከተገነጠለ በኋላ አክሌድ ከኦነግ-ሸኔ ጋር በተያያዙ ኩነቶች 5,741 ሪፖርት የተደረጉ የሟቾንን መዝግቧል።23ዳዊት እንደሻው፣ ‘የኦነግ ፖለቲካ፣ ወታደራዊ መገንጠል፣’ ሪፖርተር፣ መጋቢት 28, 2011
በኦሮሚያ ክልል ያለው የመረጃ ምህዳር ከትግራይ ክልል በእጅጉ የተለየ ነው። የኦሮሚያ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ በኢትዮጵያ መሃል ላይ በመሆኑ መረጃ የማገድ ሙከራዎች ውጤታማ አይደሉም። ይልቁንም አድሎአዊነት (ሚዛን የጎደለው መረጃ) በኦሮሚያ ባለው የመረጃ ምህዳር ይበልጥ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው። በአጠቃላይ በግጭት ወቅት የሟቾች ቁጥር በጣም የተዛባ መረጃ ቢሆንም በኦሮሚያ ውስጥ ለተከሰቱት ግጭቶች የተሳተፉ አካላት በሰፊው አከራካሪ ነው። በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ወለጋ ዞን እንዲሁም በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ እና ኦሮሚያ ልዩ ዞኖች የተከሰተውን ግጭት አስመልክቶ የተሰጡት የተለያዩ ምክንያቶች ለዚህ ዋና ማሳያ ምሳሌዎች ናቸው። በአማራ ክልል በጥር ወር ክርክር ካለባቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች አንዱ ውስጥ በኦሮሞ እና በአማራ ተወላጆች መካከል ግጭት ተቀስቅሷል። የአማራ ክልል ባለስልጣናት ለተፈጠረው ሁከት ‘ፀረ-ሰላም ቡድኖች’ን ተጠያቂ ሲያደርጉ24አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ‘ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ የተሰጠ መግለጫ’፣ ጥር 16, 2015 የአካባቢው የአማራ ተወላጆች ደግሞ ኦነግ-ሸኔ ድርጊቱን ፈጽሟል ብለዋል።25እሸቴ በቀለ፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ብቻ 98 አርሶ አደሮች መሞታቸውን የአካባቢው ባለሥልጣን ገለጹ’፣ ጥር 20, 2015 የኦነግ-ሸኔ ባለስልጣናት በአካባቢው ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳልነበራቸው በመግለፅ የአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሎችን “በወሎ ኦሮሞዎች ላይ የዘር ማጥፈት ሙከራ አድርገዋል” በማለት ከሰዋቸዋል26 የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ ‘በወሎ በኦሮሞ ሰላማዊ ሰዎች ላይ የዘር ማጥፈት እየተካሄደ ነው’ ጥር 17, 2015 (በጥር ወር በአማራ ክልል በነበረበት ግጭት ስለተነገሩ የተለያዩ ምክያቶች የበለጠ መረጃ ለማግኘት የኢፒኦ ሳምንታዊ: ከጥር 13-19, 2015ን ይመልከቱ)።
በኦሮሚያ ውስጥ የሚከሰቱ ግጭቶች ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን ለመለየት ያለው ችግር አንዱ ምክንያት በግጭቱ ውስጥ የሚሳተፉት የታጠቁ ቡድኖች የመለዋወጥ ባህሪ ነው። ኦነግ-ሸኔ በተገንጣይ ቡድን የተሞላ ነው። በአንዳንድ ሁኔታዎች የተገነጠሉ ቡድኖች፣ ወንጀለኛ ቡድኖች እና የኦሮሞ ተወላጅ ወጣቶች ከቡድኑ ጋር ይፋዊ ግንኙነት ሳይኖራቸው የኦነግ-ሸኔ አባላት ነን በማለት ሁከት ይፈጽማሉ። በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል ውስጥም በግጭት የሚሳተፉት የፋኖ ታጣቂዎች ይፋዊ የእዝ መዋቅር የሌላቸው እና የፋኖ ታጣቂዎችን ማንነት ለይቶ መግለፅ ፈታኝ ሊሆን ይችላል (በኦሮሚያ ክልል ስላሉ ተሳታፊ አካላት ተጨማሪ መረጃ ለማግኛት ኢፒኦ ከሕዳር 22 እስከ ታህሳስ 22, 2015፡ በኦሮሚያ ክልል ግጭት መስፋፋት ይመልከቱ)።
እነዚህን ጉዳዮች ለማቃለል የአክሌድ ተመራማሪዎች በተለያዩ ቋንቋዎች የሚለቀቁ ምንጮችን/ዘገባዎችን በመከታተል የኩነቶችን ሙሉ ዝርዝር ምስል ይገነባሉ። እንደ ፋኖ ታጣቂዎች ወይም እንደ ኦነግ-ሸኔ ያሉ አካላትን በተመለከተ በአማራ ክልል የኦሮሚያ ልዩ ዞን ውስጥ እንዳለው አይነት አንዳንድ አሻሚ ጉዳዮች ቢኖሩም የአንድ ኩነትን ሙሉ እና ትክክለኛ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የኩነቱን የተለያዩ ማዕዘኖች ከግምት ውስጥ ማስገባት ወሳኝ ነው።
በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል የመሰረተ ልማት እና የሚዲያ ሽፋን ባለመኖሩ እንዲሆን ክልሉ እምብዛም የፖለቲካ ተጽዕኖ ስለሌለው የመረጃ ምህዳሩ በከፍተኛ ሁኔታ የተገደበ ነው። በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ተወላጆች ከአካባቢው መስተዳድሮች ውክልና በተጨማሪ በአገራዊ ፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ያላቸው ተፅዕኖ አነስተኛ ነው።27ቶም ጋርድነር፣ ‘በኢትዮጵያ ምዕራባዊ ግንባር ሁሉም ዝም አላለም፣’ ፎሪን ፖሊሲ፣ ታህሳስ 28, 2014 ክልሉ ዳር የሚገኝ፣ በፖለቲካ የተገለለ እና በከፍተኛ ደረጃ ያላደገ ነው። በቅርቡ እየተጠናቀቀ ካለው ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በስተቀር ክልሉ ለሀገራዊ ኢኮኖሚ የሚያበረክተው አስተዋፅኦ አነስተኛ ነው።
በመሠረተ ልማት መጓደል ምክንያት በሚዲያ ሽፋን ላይ ካሉ ተግዳሮቶች በተጨማሪ የአድሎአዊነትም ችግር አለበት። በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የብሔር ተኮር ፌዴራሊዝም ሥርዓት ምክንያት በቤንሻንጉል/ጉሙዝ መተከል ዞን ውስጥ የሰፈሩ የአማራ ተወላጆች በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል ፖለቲካ ውስጥ የተገለሉ ናቸው።28ፀጋዬ ብርሃኑ፣ ‘ኢትዮጵያ፡ከትግራይ ቀጥሎ መተከል የጦርነት አውድማ ናትን’ አዋሽ ፖስት፣ ነሐሴ 18, 2013 በቤንሻንጉል/ጉሙዝ የአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች በአገሪቱ በሚገኙ የአማርኛ መገናኛ ብዙኃን በደንብ ተዘግቧል። በአገሬው ተወላጆች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች በሃገሪቱ ሚዲያዎች በደንብ ያልተሸፈኑ በመሆኑ የሪፖርት ሚዛን መዛባት እና ለበለጠ አድሎአዊነት ዕድል ፈጥሯል። አክሌድ በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል ከክልሉ ፖለቲካዊ አቋም ጋር በተያያዘ የሚታወቁ አድሎአዊ ድርጊቶችን ከግምት ውስጥ በማስገባት መረጃዎችን ይሰበስባል።
በአጠቃላይ አብዛኛው የግጭት አከባቢዎች አስቀድሞም ‘ዝቅተኛ መረጃ’ የሚገኝባቸው ቦታዎች ናቸው ምክንያቱም የአጥፊዎች ማንነት፣ የተጎጂዎች ማንነት እና የጥቃት መጠን እና መዘዞቹን በእውነተኛ ጊዜ በትክክል ለማወቅ አስቸጋሪ ናቸው። አክሌድ የኩነት እና የሟቾችን ብዛት (ድምር) ከተለዩ እና ከተናጥል ኩነቶች ተነስቶ ይገነባል። የክስተቶች መረጃ የሚመነጨው ከታወቁ እና ከታመኑ ምንጮች ነው ነገር ግን እንደዚያም ሆኖ ሁሉም ምንጮች የሚያቀርቡት መረጃ ትክክል ወይም ያለ አድልዎ ሊሆን አይችልም። በእነዚህ ጊዜ አክሌድ ተጨማሪ ማረጋገጫ መረጃዎችን እና ከሌሎች መረጃዎች ጋር ማመሳከር ያስፈልገዋል። ከእነዚህ ጥበቅ የመረጃ ማጣሪያዎች በተጨማሪ አክሌድ ወግ አጥባቂ የሆነ የሟቾች ቁጥርን ይጠቀማል፣ ምክንያቱም ወግ አጥባቂ ቁጥሮች በግጭቶች፣ ወቅቶች እና አገሮች ውስጥ ካሉ ትላልቅ የሟቾች ቁጥር ግምቶች ይልቅ ያነሰ አድሏዊ መሆናቸው በመረጋገጡ ነው።
የመረጃ ምህዳሮች በዝቅተኛ መረጃ ሊጎዱ ስለሚችሉ እንደ አካባቢ ምንጮች እና የተደራጀ የመረጃ መረቦችን ማሳደግ የመሳሰሉ አስተማማኝ አማራጮች መጠቀም እና ትክክለኛ ዘገባዎች ሲገኙ የተሰበሰበ መረጃን ማስተካከልን ይጠይቃሉ። የመረጃ ምህዳሮች በተዛባ/አድሏዊ በሆኑ ወይም እርስ በርሱ የሚጋጩ (ፕሮፓጋንዳ፣ የሀሰት መረጃ እና እውነታው የተገደበን ጨምሮ) ዘገባዎችም ሊጎዱ ይችላሉ። ከላይ እንደተጠቀሰው እንደዚህ ባሉ ሁኔታዎች ውስጥ እንኳን የተመረጡ መረጃ ጥቅም ላይ ማዋል እና መረጃዎችን ከሌሎች ምንጮ ጋር ማስተያየት እና ማረጋገጥ ይችላል። የሟቾች ቁጥር እና የትኛዎቹ አካላት ግጭቶችን እንዳነሳሱ ወይም ጉዳት እንደደረሰባቸው የሚያሳዩ መረጃዎች ከሁሉም ይበልጥ ወገንተኛ/አድሏዊ ይሆናሉ።
የኢትዮጵያ ሰሜናዊ ጦርነት ሀገሪቱን እ.አ.አ. በ2021 እና 2022 ከዓለማችን ከፍተኛው ግድያ ከተፈጸመባቸው ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ አድርጓታል (እ.አ.አ. በ2022 ኢትዮጵያ በ‘ሟቾች ቁጥር’ እና ‘አደጋ’ ላይ ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ለማየት የአክሌድ የግጭት ክብደት መረጃ ጠቋሚን ይመልከቱ)። ቢሆንም የጦርነቱ መጠን እና ቀጥተኛ ጉዳቶቹ እስካሁን በስፋት እና ሙሉ በሙሉ አልታወቁም። በሰሜን የሃገሪቷ ክፍል ውስጥ ባሉ ማህበረሰቦች ላይ የደረሰውን ጉዳት የሚገልፁ ተጨማሪ ሪፖርቶች/መረጃዎች ሲወጡ በአክሌድ በኮድ መፅሐፉ (Codebook) ላይ በተገለፀው መሰረት አክሌድ እነዚህን ሪፖርቶች/መረጃዎች ከተለያዩ መረጃዎች ጋር ካስተያየ በኃላ ክስተቶቹን እና ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር ያስተካክላል እንዲሆም ይመዘግባል።
የሚጨመሩ መረጃዎች/ዳታ
የአክሌድ ጊዜን የጠበቀ ሽፋን እና ትንተና የመረጃ ቋቱ (dataset) ዋና መለያ ባህሪ ቢሆንም እነዚህ መረጃዎች በየሳምንቱ እርማቶች እና ተጭማሪ መረጃዎች ይካተትባቸዋል። ተጨማሪ መረጃ ሲታተም እና ስለ ታሪካዊ ግጭት ኩነቶች እውነታዎች ሲታወቁ መደበኛ ግምገማዎች ይከናወናሉ። በትግራይ ክልል በጦርነቱ ወቅት የመረጃ መቆራረጥ ሰለነበረ መረጃ የመሰብሰብና የማረጋገጥ ስራን በጣም ከባድ አድርጎት ነበር። የመንግስት አገልግሎቶች ወደ ነበሩበት እየተመለሱ ባሉብት ሁኔታ፣ ተጨማሪ መረጃዎችን መመልከት፣ ማጣራት እና በታሪካዊ የመረጃ ቋት ውስጥ ይጨምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በኢትዮጵያ የመረጃ ምህዳር ውስጥ ያሉ ውስብስብ ነገሮች በኢትዮጵያ ስላሉ ግጭቶች ሙያዊ እና አድልዎ የሌለበት ሚዛናዊ ዘገባ ማቅረብ እንደሚያስፈልግ ያሳያሉ። ጋዜጠኞች እንዳይዘግቡ በመንግስታት እና በታጠቁ ቡድኖች የሚደረገው ማደናቀፍ ትክክለኛ መረጃን በማደናቅፍ በናሙና ላይ የተመሰረቱ ግምቶችን አበረታተዋል። ሙሉ እና አጠቃላይ መረጃዎችን በኩነቶች ላይ ለመሰብሰብ ይቻል ዘንድ የኢፒኦ ቡድን ለሚመለከታቸው ድርጅቶች ለትክክለኛነት ቅድሚያ እንዲሰጡ እና አድልዎ እንዲቀንስ ያሳስባል።