በዚህ ዘገባ ውስጥ የተካተቱ
- ከጥር 24 እስከ የካቲት 21 በጨረፍታ
- አበይት ክንውኖች
- ከጥር 24 እስከ የካቲት 21 ድረስ የተከሰቱ ቁልፍ ኩነቶች
- ወርሀዊ ትኩረት፡ የኃይማኖት አለመግባባቶች እና የመንግስት ጣልቃ ገብነት በኢትዮጵያ
ከጥር 24 እስከ የካቲት 21 በጨረፍታ
አበይት ክንውኖች
- አክሌድ ከጥር 24 እስከ የካቲት 21 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ 41 የፖለቲካ ግጭት ኩነቶችን እና 268 ሪፖርት የተደረጉ ሟቾች መዝግቧል። ከባለፈው ወር ማለትም ከታህሳስ 23 እስከ ጥር 23 ካለው ጊዜ ጋር ሲነፃፀር ከተቃውሞ ስልፍ ኩነቶች በስተቀር የተመዘገቡ ሁሉም የኩነቶች ዓይነቶች ቁጥር ቀንሷል።
- ከጥር 24 እስከ የካቲት 21 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በፖለቲካ ግጭት ምክንያት ከፍተኛው የኩነት መጠን በኦሮሚያ ክልል የተከሰተ ሲሆን 31 ኩነቶች ሲመዘገቡ በአማራ እና በጋምቤላ ክልሎች በእያንዳንዳቸው ሦስት ኩነቶች በመመዝገብ የኦሮሚያ ክልልን ይከተላሉ። ከታህሳስ 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ኦሮሚያ በኢትዮጵያ በፖለቲካ ግጭት ምክንያት ከፍተኛውን የኩነት መጠን እያስመዘገበ ይገኛል።
- ከጥር 24 እስከ የካቲት 21 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ተደጋግመው የተከሰቱት የኩነት አይነትች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈፀሙ ጥቃቶች እና ጦርነት ሲሆኑ 22 በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈፀመ የጥቃት ኩነቶች እንዲሁም 17 የጦርነት ኩነቶች ተከስተዋል። ከባለፈው ወር ማለትም ከታህሳስ 23 እስከ ጥር 23 ካለው ጊዜ ጋር ሲነፃፀር የውጊያ ኩነቶች ቁጥር በ74% ቀንሷል። አብዛኛው በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈፀመ የጥቃት ኩነቶች በኦሮሚያ ክልል የተመዘገበ ሲሆን በኦሮሚያ ልዩ ኃይል የተፈፀሙ ናቸው ።
ከጥር 24 እስከ የካቲት 21 ድረስ የተከሰቱ ቁልፍ ኩነቶች
ወርሀዊ ትኩረት፡ የኃይማኖት አለመግባባቶች እና የመንግስት ጣልቃ ገብነት በኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ በኃይማኖት ውስጥ በሚከሰቱ አለመግባባቶች ምክንያት አለመረጋጋት እየጨመረ መጥቷል። ከጥር 24 እስከ የካቲት 21 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ አክሌድ የተለያዩ የኃይማኖት አካላት የተሳተፉበት 13 የግርግር ኩነቶችን መዝግቧል። አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ሲሆን ቀጥሎ ደግሞ ሙስሊም ነው። ከእነዚህ ኃይማኖቶች ጋር በተያያዘ በቅርቡ የተከስቱ ግጭቶች መንግሥት በኃይማኖት ጉዳዮች ላይ ጣልቃ መግባቱ ከኃይማኖት ጋር የተያያዙ አለመግባባቶችን ከመፍታት ይልቅ እንዴት የበለጠ እንደሚያቀጣጥለው ያሳያል። ይህ ሪፖርት መንግስት በኃይማኖት ጉዳዮች ላይ ያለውን ጣልቃ ገብነት እና ግጭቶቹ ሊባባሱ የሚችሉበት ሁኔታዎችን ጨምሮ የእነዚህ አለመግባባቶች ዋና መንስኤዎችን የተነትናል።
ባለፈው ወር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን (ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ) ውስጥ የተፈጠረውን የውስጥ አለመግባባት ተከትሎ በሀገሪቱ የኃይማኖት ውጥረት ነግሶ ነበር። አለመግባባቱ የጀመረው ጥር 14 ቀን ሲሆን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሳዊሮስ ከሌሎች ሁለት ሊቀነ ጳጳሳት ጋር በመሆን በኦሮሚያ ክልል በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ወሊሶ ከተማ በሚገኘው ሐሮ በዓለ-ወልድ ቤተ-ክርስቲያን 26 ጳጳሳትን በመሾም ከኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሲኖዶስ እውቅና ውጪ ‘የኦሮሚያ እና ብሔር ብሔረሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስ’ መቋቋሙን ይፋ ባደረጉበት ወቅት ነው።1የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ አገልግሎት ቲቪ፣ ‘በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ’፣ ጥር 14, 2015 ምእመናንን በቤተ-ክርስቲያን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በማገልገል ረገድ የነበረውን የቆየ ችግር ለመፍታት እነዚህ ሹመቶች አስፈላጊ መሆናቸውን አዲሱ ቡድን አስታውቋል። አዲሱ ሲኖዶስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሲኖዶስ አመራሩን በአብዛኛው “ከአንድ ቡድን” በመሾም ሁሉንም ያሳተፈ መሆን አልቻለም ሲልም ከሷል።2ኦቢኤስቲቪ፣ ‘በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ’፣ ጥር 14, 2015 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሲኖዶስ በበኩሉ አዲሱን ሲኖዶስ የቤተ-ክርስቲያኒቱን ቀኖና አልተከተለም ሲል የከሰሰው ሲሆን የኦሮሚያ እና ብሔር ብሔረሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስን “ህገ-ወጥ” በማለት ሦስቱን ሊቃነ ጳጳሳት እና 25ቱን ጳጳሳት አግዷል።3የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ቲቪ፣ ‘የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ’፣ ጥር 18, 2015፤ ከተሾሙት 26 ጳጳሳት መካከል አንዱ 26 ጳጳስ በአቡነ ሳዊሮስ የሚመራውን ቡድን ትቶ ለበኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ፓትራያርክ የይቅርታ ደብዳቤ ከስጋባና ይቅርታ ከጠየቀ በኃላ ወደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሲኖዶስ ተመልሷል፤ የኢኦተቤ ቲቪ፣ ‘አባ ጸጋዘአብ አዱኛ ይቅርታ ጠየቁ’፣ ጥር 17, 2015 ይመልከቱ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሲኖዶስ በአቡነ ሳዊሮስ ከሚመራው ቡድን ጋር የሚደረግ ድርድርን “በተዘዋዋሪ የቤተ-ክርስቲያናችንን ቀኖና መጣስ ነው” በሚል ድርድርን ህገ-ወጥ አድርጓል።4የኢኦተቤ ቲቪ፣ ‘የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ’፣ ጥር 18, 2015
መንግስት በዚህ ጉዳይ ጣልቃ በገባበት ወቅት በሀገሪቱ ውስጥ ያለው ውጥረት ይበልጥ ጨምሯል። የፀጥታ ኃይሎች በኦሮሚያ የሚገኙ የኦርቶዶክስ አብያተ-ክርስቲያናትን አዲስ ለተቋቋመው የኦሮሚያ እና ብሔር ብሔረሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስ ለማስረከብ ፈቃደኛ ያልሆኑትን ሊቀነ ጳጳሳት፣ ጳጳሳት እና ምእመናን ማሰር ሲጀምሩ ሁኔታው ወደ ግጭት ተቀይሯል። በክልሉ የሚገኙ አብያተ-ክርስቲያናትን ለመቆጣጠር በተለያዩት ሲኖዶሶች መካከል በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ ስምንት ሰዎች መሞታቸውና በርካቶች መቁሰላቸው ተነግሯል (ለተጨማሪ መረጃ ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከጥር 20-26, 2015፤ ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከጥር 27–የካቲት 3, 2015፤ ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከየካቲት 4–10, 2015 ይመልከቱ)።
የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት መንግሥት በኃይማኖት ጉዳዮች ወይም በፖለቲካ ጉዳዮች ውስጥ የኃይማኖት አባቶች ጣልቃ እንዳይገቡ በመከልከል መንግሥትና ኃይማኖት የተለያዩ እንደሆኑ ይደነግጋል።5የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 11፣ 1987 ሆኖም በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የተለያዩ መንግስታት በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ እና በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የውስጥ ጉዳዮች ላይ ጣልቃ ገብተዋል። በቅርቡ በኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን የውስጥ አለመግባባት ውስጥ የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ኃይሎች ከኦሮምያ እና ብሔሮች ብሔረሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስ ጎን በመቆም የወሰዱት የኃይል እርምጃ በመላ ሀገሪቱ የብሔር ተኮር ፖለቲካ ውጥረቶችን ሊያሰፋፋ ይችላል። በኢትዮጵያ ውስጥ ብሔረተኝነት እየጨመረ በመጣ ቁጥር የበርካታ ኃይማኖታዊ ቡድኖች ግንኙነት ከተለያየ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየጠነከረ መጥቷል። ይህ በተለይ በአማራ ብሔር ውስጥ ጎልቶ የሚታይ ሲሆን እየጨመረ የመጣው የአማራ ብሔርተኝነት የኢትዮጵያ ክርስቲያናዊ ኢምፓየር ቅርሶችን ከኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ጋር ያገናኙታል።6አንድሪው ዴኮርት፣ ‘የክርስቲያን ብሔርተኝነት ኢትዮጵያን እየከፈለ ነው፣’ ፎሪን ፖሊሲ፣ ሰኔ 11, 2015 ይህንን ነጥብ ለማስረዳት የኃይማኖት ድርጅቶች የፖለቲካ ጫናዎችን ከመቋቋም ይልቅ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተፈጠሩ ያሉ ግጭቶች በኃይማኖት ድርጅቶች ውስጥ መከፋፈል እንዲፈጠር ምክንያት መሆናቸውን እንደ ምሳሌ ማንሳት ያስፈልጋል (ለበለጠ መረጃ ኢፒኦ ወርሀዊ: ከመጋቢት 23 እስከ ግንቦት 23, 2014ን ይመልከቱ)። ይህ በ2010 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ቃል ከገቡት “የሃገሪቱን ህግጋትን የማክበር አስፈላጊነትን” በሚጻረር መልኩ የክልል ባለስልጣናት የሚወስዱት እርምጃ የፌዴራል መንግስቱን አጣብቂኝ ውስጥ ይከተዋል።7ፋና ቴሌቪዥን፣ ጠቅላይ ሚኒስትርዶ/ር አብይ አህመድ በፓርላማ ያቀረቡት ሙሉ ንግግር፣ መጋቢት 25, 2015
ከኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የውስጥ አለመግባባት ጋር በተያያዘ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ሁለቱ አካላት ልዩነቶቻቸውን በውይይት እንዲፈቱ በማበረታታት እና “በኦሮሚያ ውስጥ በኦሮምኛ ቋንቋ አገልግሎት ይስጠኝ ብሎ የሚጠይቅን ምዕመን አይስጥህም ልለው አይችልም እኔ” ብለዋል።8ፌስቡክ @አብይ አህመድ አሊ፣ ‘ሰላምና ሃይማኖታዊ ጉዳዮች፣’ ጥር 23, 2015 መንግሥት በዚህ ባለመግባባቱ ውስጥ ጣልቃ እንደማይገባ አረጋግጠው ካቢኔያቸውንም ጣልቃ እንዳይገቡ ጠይቀዋል።9ፌስቡክ @አብይ አህመድ አሊ፣ ‘ሰላምና ሃይማኖታዊ ጉዳዮች፣’ ጥር 23, 2015 የኢትዮጵያ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን ደግፎ የኦሮሚያ እና ብሔሮች ብሔረሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ወደ የትኛውም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ደብር ወይም ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ የሚከለክል የእግድ ትዕዛዝ ሰጥቷል።10የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የብሮድካስቲንግ አገልግሎት ኤጀንሲ፣ የካቲት 3, 2015
በቤተ-ክርስቲያን አገልግሎት ቋንቋ ወይም በቤተ-ክርስቲያን ጉዳይ ላይ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ጋር ተያይዞ የሚነሳ ውጥረት ለኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አዲስ አይደለም። እ.ኤ.አ. በ2019 (2011/2012) የኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን አገልግሎት በአፋን ኦሮሞ (በኦሮምኛ ቋንቋ) እንዲሆን የፈለጉ በቀሲስ በላይ መኮንን በመመራት ‘የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያንን’ ለማቋቋም ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ተጀምሮ ነበር።11ቦርከና፣ ‘አክራሪ ብሔርተኞች የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያንን ለመመስረት ሲሉ የኢትዮጵያን ቤተ-ክርስቲያን ለመክፈል መንቀሳቀስ፣ የኢትዮጵያ ቤተ-ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምላሽ ሰጠ፣’ ነሐሴ 25, 2011 ምንም እንኳን አንዳንድ ያልተፈቱ ጉዳዮች ባለፈው ወር ከአቡነ ሳዊሮስ ጋር ዳግም ቢነሱም በቀሲስ በላይ መኮንን እና በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መካከል የነበረው አለመግባባት እ.ኤ.አ. 2020 (2012/2013) በእርቅ ተፈቷል።12ቢቢሲ አማርኛ፣ ‘”በእርቅ ውስጥ ሁሉም አሸናፊ ነው”- ቀሲስ በላይ፣’ ጥቅምት 13, 2012 በትግራይ በነበረው ጦርነት ወቅት የትግራይ ሊቀነ ጳጳሳት የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሲኖዶስ መገንጠሉን አስታውቀው ነበር።13 ደስታ ሄሊሶ፣ ‘የመከፋፈል ቀውስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣’ ሪሊጅን አንፕላግድ፣ ጥር 27, 2015 በቅርቡ የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ ከኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሲኖዶስ የቀረበለትን “የእርቅና መደበኛ የግንኙነት” ጥሪን የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ “የዘር ማጥፈት ጦርነቱን” ድግፋለች ብለው በመክሰስ ውድቅ አድርገዋል።14መድሃኔ እቁበሚካኤል፣ ‘ትንተና፡ የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሲኖዶስ ግንኙታቸው ወደ መደበኛው እንዲስተካከል የቀረበለትን ጥሪ ውድቅ አደረገው፣ ሲኖዶሱን በትግራይ ሕዝብ ላይ “የዘር ማጥፋት ጦርነት”ን በመደገፍ ወቅሳለች። ቀጥሎስ?’ አዲስ ስታንዳርድ፣ የካቲት 14, 2015 በጦርነቱ ወቅት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ይፋዊ መግለጫ አልሰጠችም። ነገር ግን በግንቦት 2013 የትግራይ ተወላጅ የሆኑት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሲኖዶስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ውጊያውን በትግራይ ተወላጆች ላይ የተሰነዘረ “ዘር ማጥፋት” ሲሉ ገልፀውት ነበር።15ሮይተርስ፣ ‘የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን የበላይ በትግራይ የዘር ማጥፋት እየተፈጸመ ነው አሉ፣’ ግንቦት 1, 2015፤ የአሜሪካ ድምፅ፣ ‘የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ፓትርያርክ በትግራይ ‘ዘር ማጥፋት’ አሉ፣’ ግንቦት 1, 2015 ብዙ ሰዎች የኃይማኖት መሪውን በሀገሪቱ በሙሉ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰውን ግፍና በደል ከማውገዝ ይልቅ ወደ አንድ ወገን አድልተዋል በማለት ተችተዋቸዋል።
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ እና የኦሮሚያ ብሔር ብሔረሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እና ሽማግሌዎች ጋር በመመካከር በ10 ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ ከደረሱ በኋላ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ እና የኦሮሚያ ብሔር ብሔረሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስ አለመግባባት ጋብ ብሏል።16የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ‘በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል የነበረውን አለመግባባት ለመፍታት የተዘጋጀ የውይይት መርሐ ግብር ኢቲቪ | ኢትዮጵያ | ዜና፣’ የካቲት 9, 2015፤ ኢቢሲ፣ ‘በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል የነበረውን አለመግባባት ለመፍታት የተዘጋጀ የውይይት ክፍል-2 ኢቲቪ | ኢትዮጵያ | ዜና፣’ የካቲት 10, 2015 ስምምነቱ የቤተ-ክርስቲያኒቱን አገልግሎት በአፋን ኦሮሞ ማጠናከር እና የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የተባረሩትን ሦስቱን ሊቀነ ጳጳሳት እና 25ቱን ጳጳሳትን ወደ ነበሩበት ቦታ መመለስን ያጠቃልላል።17 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ብሮድካስቲንግ አገልግሎት ኤጀንሲ፣ ‘ቅዱስ ሲኖዶስ እና በሕገ ወጥ መልኩ ሣመት በፈጸሙት አባቶች መካከል የተደረሰው ስምምነት፤’ የካቲት 8, 2015 ሆኖም ከተሾሙት ጳጳሳት መካከል የተወሰኑት በኦሮሚያ የሚገኙ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አብያተ-ክርስቲያናትን በፀጥታ ኃይሎች በመደገፍ መቆጣጠር መቀጠላቸው ተነግሯል።18የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ብሮድካስቲንግ አገልግሎት ኤጀንሲ፣ ‘በሻሸመኔ ደብረ ስብሃት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅነት ተመድቤአለሁ የሚል ግለሰብ መምጣቱ ተገለጸ፣’ የካቲት 27, 2015፤ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ብሮድካስቲንግ አገልግሎት ኤጀንሲ፣ ‘ቅዱስ ሲኖዶስ ከብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ እና ከብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ጋር ውይይት አካሄደ፣’ የካቲት 21, 2015 ይመልከቱ ቢሆንም እስከ የካቲት 17 ድረስ ከግጭቱ ጋር በተያያዘ የቤተክርስቲያን አመራር አባላትን ጨምሮ የታሰሩ ሰዎች አሁንም በእስር ላይ ናቸው።19እሱባለው ጋሻው፣ ‘ብፁአን አባቶች በአዋሽ ሰባት የታሰሩ ወጣቶችን ሊጎበኙ ነው፣’ የካቲት 17, 2015
ከጥር 24 እስከ የካቲት 21 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብም ከአመራሩ ጋር በተያያዘ አንዳንድ አለመረጋጋት አጋጥሞት ነበር። በየካቲት አጋማሽ አካባቢ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (በተለምዶ መጅሊስ እየተባለ የሚጠራው) ሹመት ጋር በተገናኘ ያለው ውስጣዊ አለመግባባት በሀገሪቱ የሚገኙ ሙስሊሞች ላይ የመከፋፈል አደጋ ፈጥሯል። የካቲት 12 ቀን አንድ የሙስሊሞች ቡድን በኦሮሚያ ክልል ነቀምት በሚገኘው ፈቲህ መስጊድ በመግባት አዲስ የተሾሙ የመጅሊስ አባላት የሶላት ንግግር እንዳያደርጉ በማድረግ ቡድኑ በመስጊዱ የተገኙትን በመደብደብ እና መስኮቶችን በመስበር ጉዳት አድርሷል። ከዚህ በፊት የካቲት 3 ቀን በከተማዋ የሚገኘውን ትልቁን መስጊድ ለአዲሱ መጅሊስ ለማስረከብ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሰባት ሙስሊም የሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት ሙሁራን ታስረው ነበር። በነቀምት የሚኖሩ የሱፊ ሙስሊሞች አዲሱን መጅሊስ ብጥብጥ በመቀስቀስ የወነጀሉ ሲሆን መጅሊሱ “በወሃቢ ቡድን የበላይነት የተያዘ ነው” ሲሉም ወቅሰዋል።20አዲስ ማለዳ፣ ‘የነቀምት ሙስሊሞች ምን ገጠማቸው? የቤት ፈረሳን የተቃወሙ የሱሉልታ ወጣቶች መታሰር፣ የአሜሪካ ከፍተኛ ልዑክ በአዲስ አበባ!’ የካቲት 8, 2015 በአዲስ አበባ፣ በሐረር፣ በኢሉ አባ ቦራ፣ በጅማ እና በአዳማ ተመሳሳይ አለመግባባቶች በሙስሊሙ ማህበረሰብ ውስጥ እንደሚገኝ ተዘግቧል።21አዲስ ማለዳ፣ ‘የነቀምት ሙስሊሞች ምን ገጠማቸው? የቤት ፈረሳን የተቃወሙ የሱሉልታ ወጣቶች መታሰር፣ የአሜሪካ ከፍተኛ ልዑክ በአዲስ አበባ!’ የካቲት 8, 2015 በተጨማሪም በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን የኮምቦልቻ ከተማ ሙስሊም ነዋሪዎች “መጅሊሱ በህገወጥ መንገድ በወሃቢ ቡድን መወሰዱን” በኮምቦልቻ ከተማ አውግዘው ስላማዊ ተቃውሞ አድርገዋል። ሰልፈኞቹ “መሪያችን ሃጅ ኡመር ኢድሪስ ናቸው”፣ “እስልምና አይሸጥም”፣ “መጅሊስ የሙስሊም እንጂ የውሃብያ ተቋም አይደለም” የሚሉ ጨምሮ የተለያዩ መፈክሮችን አሰምተዋል።22አዲስ ማለዳ፣ ‘በነቀምት ከተማ መስጊድ ውስጥ በተፈጠረ ችግር ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል ተባለ፣’ የካቲት 14, 2015
ከመጅሊስ ጋር ተያይዞ የተነሳው ውዝግብ የጀመረው በጅማ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው በአሰንዳቦ እና ኦሞ ናዳ አካባቢዎች የተከሰተውን ኃይማኖትን መሠረት ያደረገ ጥቃትን ተከትሎ በ2004 መንግስት አል–አበሽ (የኢትዮጵያ) – እንዲሁም የእስልምና በጎ አድራጎት ፕሮጄክቶች ማህበር – በመባል የሚታወቀውን አስተምሮ በአገር ውስጥ ማስተማር በጀመረበት ወቅት ነበር።23አዲስ ስታንዳርድ፣ ‘የኃይማኖት ውጥረት በኢትዮጵያ፣’ መጋቢት 18, 2005፤ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ‘እ.ኤ.አ. 2011 ስለ ሽብርተኝነት ዘገባዎች፣ ምዕራፍ 2 የአገር ዘገባዎች፡ የአፍሪካ አጠቃላይ ዳሰሳ፣’ ሐምሌ 24, 2004፤ ዊልያም ዴቪሰን፣ ‘ሙስሊሞች የኢትዮጵያ መንግስት በመስጊድ ውስጥ ጣልቃ እየገባ ነው ሲሉ ይከሳሉ፣’ ዘ ክርስትያን ሳይንስ ሞኒተር፣ ግንቦት 23, 2004 እ.ኤ.አ. በ1980ዎቹ በሼክ አብዱላህ አል-ሀረሪ የተመሰረተው የአል–አህባሽ ትምህርት እጅግ በጣም ወግ አጥባቂ አስተሳሰብን ይቃወማል። የእምነቱ መርሆች ከሱኒ እና ሱፊ እስልምና ትርጓሜ የተወሰደ ነው። መንግስት ይህን ትምህርት ኃይለኛ ጽንፈኝነትን ለመመከት ሲል አበረታቶታል። በታሪክ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሱፊዝምን የሚከተሉ ቢሆንም ከጎልፍ አካባቢ ባለው ተፅዕኖ እ.ኤ.አ. ከ1990ዎቹ ጀምሮ የሳለፊዝምን ስርዓት በስፋት ተቀባይነት እንዲኖረው አድርጓል።24 ቴሪ ኦስቴቦ፣ ‘የአካባቢው ተሐድሶ አራማጆች እና ዕድል ፍለጋ፡ የሰልፊዝም መነሳት በባሌ፣ ኢትዮጵያ፣’ አፍሪካ፣ ጥቅምት 2, 2004
የስርአተ ትምህርት ለውጥ እና በታህሳስ 2004 በአወሊያ የኃይማኖት ትምህርት ቤት 50 መምህራንን ከስራ መባረርን ተከትሎ በኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ በ2004 ዓ.ም ህዝባዊ ሰልፎች ተካሂደዋል።25 ዘ ኒው ሁማኒተሪያን፣ ‘የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቃውሞ፣’ ህዳር 6, 2005፤ ፍራንስ 24፣ ‘የኢትዮጵያ ሙስሊሞች “በአሸባሪነት መፈረጃቸውን” ተቃወሙ፣’ ሐምሌ 18, 2004 ሰልፈኞቹ መንግስትን የአል–አህበሽ የበላይነት ያለው መጅሊስ ለመመስረት ሲል የመጅሊስ አመራሮች ምርጫ ተቆጣጥሯል ሲሉ ከሰዋል።26አሮን ማአሾ፣ ‘ተቃዋሚዎች፡ የኢትዮጵያ መስጊድ ውስጥ የተደረገው የመቀመጥ አድማ ሞት፣ እስራት አስከተለ፣’ ሮይተርስ፣ ሐምሌ 8፣ 2004፤ ፍራንስ 24፣ ‘የኢትዮጵያ ሙስሊሞች “በአሸባሪነት መፈረጃቸውን” ተቃወሙ፣’ ሐምሌ 18, 2004 የሙስሊሙን ሃሳብ ለመወከል እና በጉዳዩ ላይ ከመንግስት ጋር ለመወያየት 17 ታዋቂ አመራሮችን ያቀፈ የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ በ2004 ዓ.ም ተቋቁሟል። ነገር ግን መንግስት የተቃውሞ ሰልፉን መሪዎች ረዘም ላለ ጊዜ ቢያስራቸውም27ሂዩማን ራይትስ ዎች፣ ‘ኢትዮጵያ፡ ተቃውሞውን ለማብረድ የታሰሩ ታዋቂ ሙስሊሞች፣’ ነሐሴ 9, 2004፤ ኮሚቴ ቱ ፕሮቴክት ጆርናሊስትስ፣ ‘የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በሙስሊሙ ፕሬስ ላይ እርምጃ ወስደዋል፣’ ነሐሴ 10 ቀን 2012 የተቃውሞ ስልፉ “ድምጻችን ይሰማ” በሚል መሪ ቃል በሃገሪቱ ቀጥሏል።28ቦርከና፣ ‘የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በእስር ላይ የሚገኙትን የኮሚቴ አባላትን ለመደገፍ ሰልፍ አደረጉ፣’ ግንቦት 22, 2006፤ ፊሊፕ ሳንድነር፣ ‘የሙስሊሞች ተቃውሞ በኢትዮጵያ፣’ ዶይቸ ቬለ፣ ነሐሴ 3, 2005 በህዳር 2005 የአል–አበሽ ተከታዮችን በብዛት ያቀፈ አዲስ መጅሊስ ተቋቁሟል።29 ዘ ኒው ሁማኒተሪያን፣ ‘የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቃውሞ፣’ ህዳር 6, 2005፤ የአሜሪካ ድምፅ፣ ‘ኢትዮጵያ አዲስ እስላማዊ ምክር ቤት አቀረበች፣’ ጥቅምት 26, 2005 ከዓመታት በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ስልጣን ሲመጡ ታዋቂ የሙስሊም መሪዎችን እና አክቲቪስቶችን ከእስር ፈተዋል። በ2011 አብይ የመጅሊሱን አስራር ለማሻሻል አላማ ያደረገ ከ2004ቱ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ፣ ከመጅሊስ፣ ሽማግሌዎች እና ከኃይማኖት ምሁራን የተውጣጡ ዘጠኝ የኃይማኖት አባቶችን ያቀፈ ኮሚቴ አቋቁመዋል።30ቦርከና፣ ‘አብይ አህመድ በኢትዮጵያውያ ሙስሊም ማህበረሰብ መካከል ያሉ ተቀናቃኝ ቡድኖችን እንዲነጋገሩ አደረጉ፣’ ሰኔ 27, 2010
ሐምሌ 11, 2014 ወሃብያ እንደሆኑ በተነግሩት በሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የሚመራ አዲስ መጅሊስ ተቋቁሟል። ምንም እንኳን መንግስት ይህንን መጅሊስ የመላው ሙስሊም ማህበረሰብን ፍላጎት የሚወክል ነው ብሎ ቢያስተዋውቅም አንዳንድ ሙስሊሞች ግን አዲስ የተቋቋመውን መጅሊስ ያልተቀበሉት ሲሆን መንግስት ጣልቃ ገብቷል በማለት ከሰዋል። ስለሆነም የዚህ መጅሊስ አባላት አዲሱን መዋቅር ተግባራዊ ለማድረግ እና መስጊዶችን ለመረከብ ሲሞክሩ በሱፊ ሙስሊሞች በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ነቀምት እና በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ረብሻ እና ተቃውሞ ገጥሟቸዋል (ለተጨማሪ መረጃ ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከየካቲት 11–17, 2015 ይመልከቱ)።
በመንግስት እና በኃይማኖት መካከል ልዩነት አለመኖሩ ሌላው በሀገሪቱ የሁከት መንስኤ እየሆነ ነው። የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክም ሆነ አንዳንድ ሙስሊሞች መንግስት በውስጥ ጉዳያቸው ጣልቃ ገብቷል ሲሉ ይከሳሉ። ኃይማኖትን መሠረት ያደረጉ ግጭቶች የሚከሰቱበት ፍጥነት እየጨመረ ነው። እ.ኤ.አ. በ2022 (ከታህሳስ 2014- ታህሳስ 2015) አክሌድ ከተለያዩ የኃይማኖት አካላት ጋር የተያያዙ 25 የአለመረጋጋት ኩነቶችን መዝግቧል፣ ከእነዚህ ኩነቶች አብዛኛዎቹ ማለትም 86%ቱ በሚያዝያ ወር በጎንደር ከተከሰተው ክስተት ጋር ተያይዘው የተከሰቱ ናቸው (ለበለጠ መረጃ ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከሚያዚያ 15, 2014 እስከ ሚያዚያ 28, 2014 ይመልከቱ)። ይህ እ.ኤ.አ. ከ2021 (ከታህሳስ 2013- ታህሳስ 2014) ጋር ሲነፃፀር የ39% ጭማሪ ያሳያል –እ.ኤ.አ. ከ2021 (ከታህሳስ 2013- ታህሳስ 2014) ከተለያዩ የኃይማኖት አካላት ጋር የተያያዙ 18 የአለመረጋጋት ኩነቶች ተመዝግበዋል። ከዚህ በፊት የኃይማኖት አካላትን ያካትቱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የአለመረጋጋት ኩነቶች የተመዘገቡት እ.ኤ.አ. በ2012 (ከታህሳስ 2004- ታህሳስ 2005) እና በ2019 (ከታህሳስ 2011- ታህሳስ 2012) ነበር (ከዚህ በታች ያለውን ግራፍ ይመልከቱ)። እ.ኤ.አ. በ2012 (ከታህሳስ 2004- ታህሳስ 2005) ሁሉም ከኃይማኖት ጋር የተያያዙ የአለመረጋጋት ኩነቶች ሙስሊሞችን ያካተቱ ሲሆን ይህም ከላይ ከተገለጹት ምክንያቶች ጋር የተያያዘ ነው። እ.ኤ.አ. በ2019 (ከታህሳስ 2011- ታህሳስ 2012) የደረሰው ከኃይማኖት ጋር የተያያዙ የአለመረጋጋት ኩነቶች ከአንድ ታዋቂ የማህበራዊ ሚዲያ አክቲቪስት መታሰር ጋር በተያያዘ በኦሮሚያ በሚገኙ የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ኢላማ ከመደረጋቸው እና በመቀጠልም በአማራ ክልል መስጊዶች ላይ በደረስ የበቀል ጥቃቶች ጋር የተያያዘ ነው። በ2015 ከጥር 24 እስከ የካቲት 21 ባለው ጊዜ ብቻ አክሌድ የተለያቱ የኃይማኖት አካላትን ያካተቱ 13 የአለመረጋጋት ኩነቶችን መዝግቧል።
የኢትዮጵያ ህዝብ ኃይማኖተኛ ሲሆን በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ እና በሙስሊም ማህበረሰቦች ውስጥ የሚከሰቱ መከፋፈሎች ብዙ የሀገሪቱን ነዋሪዎች የሚነካ ስሜታዊ ጉዳይ ነው። በቅርቡ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ውስጥ በተነሳው አለመግባባት እና ግጭት ብዙ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ቤተ-ክርስቲያንን እየጠበቁ ‘እንደ ቅዱሳን’ ለመሞት መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።31 የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት፣ ‘ኦርቶዶክሳውያን አቋመቸውን እየገለጹ ነው፣’ ጥር 27, 2015፤ በተጨማሪም ከዚህ ፖስት ስር ያሉትን አስተያየቶች ይመልከቱ የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት፣ ‘“ሰማዕታት የዚችን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ፤ ደማቸውን ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ፤ ስለ መንግሥተ ሰማያት መራራ ሞትን ታገሱ፣”’ ጥር 29, 2015 የተገነጠለው ቤተ-ክርስቲያን ደጋፊዎችም ለአቡነ ሳዊሮስ ያላቸውን ጥልቅ ቁርጠኝነት ገልጸዋል።32አዲስ ስታንዳርድ፣ ‘ዜና፡ የተገነጠለው ሊቃነ ጳጳስ መጀመሪያ የቤተ ክርስቲያን መከፈል ወደ ተነገረበት ሀገረ ስብከት ተመለሱ፣’ የካቲት 2, 2015 ከ2010 በፊት ከነበረው ኢትዮጵያ ጋር ሲነጻጸር የኃይማኖት ግጭቶች እየተለመደና ገዳይ እየሆነ መጥቷል። በኢትዮጵያ ውስጥ በኃይማኖት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት እንዲባባስ የፖለቲካ ተጽዕኖ እና ኃይማኖትን እንደ ፖለቲካ መሳሪያነት መጠቀም አስተዋጽኦ አድርገዋል።33መሐመድ ግርማ፣ ‘ኃይማኖት እና ማህበራዊ ቃል ኪዳን በኢትዮጵያ፡ እምነት በትግራይ ግጭት፣’ በርክሌይ የኃይማኖት፣ የሰላም እና የዓለም ጉዳዮች ማዕከል፣ ሐምሌ 12, 2013 እንደ ኢትዮጵያዊው ኤክስፐርት ጃን አቢንክ “የፖለቲካ ጣልቃገብነት እና ኃይማኖትን ለፖለቲካ መሳሪያነት መጠቀም ሲቻል ብቻ የተወሰነ ግጭት ይፈጠራል።”34 አለምነው መኮንን እና ቤኒታ ቫን ኢሰን፣ ‘የሃይማኖቶች ውጥረት በኢትዮጵያ ነግሷል፣’ ዶይቸ ቬለ፣ ሚያዚያ 18, 2014 የተለያዩ አካላት ኃይማኖትን እንደመሳሪያ በሚጠቀሙበት የፖለቲካ ምኅዳሩ እየተካረረ በሄደበት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ምኅዳር የኃይማኖት አካላትን ያሳተፈ ተጨማሪ ግጭት መነሳቱ አይቀሬ ነው።