በቁጥር: ኢትዮጵያ, ከግንቦት 19, 2014-ግንቦት 25, 2015
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 1,109
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 5,710
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 2,591
በቁጥር: ኢትዮጵያ, ከግንቦት 19-25, 20151 በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ በመረጃ ቋታችን ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 17
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 131
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 19
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን ከኢፒኦ የመረጃ መዝገብ እንዲሁም በዋናው የአክሌድ ኤክስፖርት መሳሪያ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
በሸገር ከተማ መስጊዶችን ከማፍረስ ጋር ተያይዞ የሚደረጉ ሰልፉች በአዲስ አበባ የቀጠሉ ሲሆን በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ፖለቲካዊ ጥቃቶች ማለትም ጦርነቶች፣ የርቀት ጥቃቶች እና በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ቀጥለዋል።
ባለፈው ሳምንት ግንቦት 25 ቀን ህዝበ ሙስሊሙ ከጁምዓ ሰላት በኋላ በአዲስ አበባ መርካቶ በሚገኘው ታላቁ አንዋር መስጊድ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ሮቤ፣ ሻሸመኔ እና ጅማ ከተሞች እና በሐረሪ ክልል ሐረር ከተማ በኦሮሚያ ክልል አዲስ በተቋቋመው ሸገር ከተማ በመንግስት እየተፈጸመ ያለውን መስጊዶችን ማፈረስ በማውገዝ ሰልፎች አድርገዋል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። ሰልፈኞቹ ባለፈው ሳምንት በሙስሊም ተቃዋሚዎች ላይ በመንግስት ኃይሎች የተፈጸመውን ግድያም አውግዘዋል። ግንቦት 18 ቀን የፀጥታ ኃይሎች ከጁምዓ ሰላት በኋላ በታላቁ አንዋር መስጊድ በተደረገው ሰልፍ ላይ ጥይት በመተኮሳቸው ሁለት ሰዎችን መግደላቸው እና ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ ተቃዋሚዎችን ማቁሰላቸው ተነግሯል (ለበለጠ መረጃ የኢፒኦ ሳምንታዊ: ከግንቦት 12-18, 2015 ይመልከቱ)። ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ እና በጅማ የመንግስት ኃይሎች ሰልፈኞችን ለመበተን የኃይል እርምጃ በመውሰዳቸው ጉዳት ደርሷል። በአዲስ አበባ የመንግስት ኃይሎች – የሪፐብሊካን ጋርድ፣ የፌዴራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ – የታላቁን አንዋር መስጊድ ቅጥር ግቢ ከበው በር በመዝጋት በህዝቡ ላይ አስለቃሽ ጭስ እና ጥይት በመተኮሳቸው በትንሹ ሦስት ሰዎች መሞታቸው እና ያልታወቁ ሰዎች መቁሰላቸው ተነግሯል። አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት የኃይል እርምጃ ስምንት ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል።2አዲስ ማለዳ፣ ‘በአንዋር መስጊድ በተከሠተ ግጭት እስከአሁን የስምንት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተነገረ፣’ ግንቦት 27, 2015 የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር ተነጋግሮ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች እንዲታከሙ እና ሌሎችም በሰላም ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ እሳካደረገበት ምሽት ድረስ በርካታ ሙስሊም ምዕመናን ከመስጊዱ መውጣት አቅቷቸው በመስጊዱ ለመቆየት ተገደው ነበር። ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ወደ 63 የሚጠጉ የፖሊስ አባላትም ቆስለዋል።3የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ‘ከፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል የተሰጠ መግለጫ፣’ ግንቦት 25, 2015 በተመሳሳይ የፌዴራል ፖሊስ እና የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ አባላት በጅማ ከተማ በተቃውሞ ሰልፈኞች ላይ ድብደባ እና አስለቃሽ ጭስ እና ጥይት መተኮሳቸው ታውቋል። በዚህም ሁለት ሰዎች ሲቆስሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ታስረዋል። በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ አዲስ በተቋቋመው ሸገር ከተማ እየተካሄደ ባለው የቤቶች እና መስጊዶች ፈረሳ ምክንያት ያለው ቁጣ እየጨመረ መጥቷል። እንደ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከሆነ በሸገር ከተማ ከ19 ያላነሱ መስጊዶች ፈርሰዋል።4ሪፖርተር፣ ‘በመስጊድ በመፍረሳቸው ምክንያት ከፍተኛ ተቃውሞ ተቀስቅሷል፣’ ግንቦት 19, 2015
የሸገር ከተማ ከተመሠረተ ጥር 2015 ዓ.ም ጀምሮ የከተማዋ ባለስልጣናት አስፈላጊ ወረቀት የሌላቸውን ቤቶች እንዲፈርሱ ትዕዛዝ ሲሰጡ የቆዩ ሲሆን ይህም የቤት ፈረሳው ኦሮሞ ባልሆኑ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ነው በሚሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ቅሬታ አስነስቷል።5 አዲስ ስታንዳርድ፣ ‘የዜና ትንተና፡ ቅሬታው እየጨመረ ቢመጣም የሸገር ከተማ ባለስልጣናት “ህገ-ወጥ ቤቶችን” ማፍረሱን ቀጥለዋል፣ ብሔርን መሰረት ያደረገ ነው የሚለውን ክስ አስተባብለዋል፣ የካቲት 27, 2015 የኦሮሚያ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊው የቤት ፈረሳውን በመደገፍ መስጊዶች ብቻ ሳይሆኑ ሁሉም ህገወጥ ህንፃዎች እየፈረሱ መሆኑን ጠቁመው ህዝበ ሙስሊሙ “በኃይማኖት ሽፋን የሚንቀሳቀሱትን የተደራጁ የውስጥ እና የውጭ ፅንፈኞችን” ችላ እንዲሉ አሳስበዋል።6አዲስ ስታንዳርድ፣ ‘ዜና፡ የኦሮሚያ ክልል ሕንፃዎችን ማፍረስ “ሕገ-መንግስታዊና ህጋዊ ነው” ሲል ጽንፈኞችን “ለሐሰት ፕሮፓጋንዳ” ወንጅሏል፣’ ግንቦት 27, 2015 እንደ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ያሉ ሌሎች ድርጅቶች የቤት ፈረሳ ዘመቻውን በማውገዝ አንዳንድ የፈረሱት ቤቶች የባለቤትነት ማረጋገጫ ዶክመንት አላቸው ሲሉም ተናግረዋል።7ቢቢሲ አማርኛ፣ ‘በአዲስ አበባ እና በሸገር ከተሞች ከ111 ሺህ በላይ ቤቶች መፍረሳቸውን ኢሰመጉ አስታወቀ፣’ ግንቦት 24, 2015
በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን በደብረ ኤልያስ ወረዳ በደጎልማ ቀበሌ በሚገኘው በደብረ ኤልያስ ብሔረ በፁአን መልካ ስላሴ አንድነት ገዳም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ማንነቱ ካልታወቀ ታጣቂ ቡድን ጋር ከግንቦት 18 እስከ 22 ቀን ድረስ ተዋግተዋል። መንግስት ቡድኑን የአማራ ህዝባዊ ግንባር ሲል የጠራ ሲሆን አንዳንድ እማኞች ግን እራሱን “የአለም ብርሃን” ብሎ የገለጸ ቡድን እንደሆነ ገልፀዋል።8የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ፣ ‘ከፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል የተሰጠ መግለጫ፣’ ግንቦት 25, 2015፤ የኢትዮጵያ ሚዲያ ሰርቪስ፣ ‘ኢኤምኤስ መረጃ አርብ ግንቦት 25, 2015፣’ ግንቦት 25, 2015፤ የደብረ ኤልያስ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት፣ ‘ከደብረ ኤልያስ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት የተላለፈ መልዕክት፣’ ግንቦት 23, 2015 የተለያዩ ምንጮች ሰለደረሰው ጉዳት የሚገምቱት የተለያየ ነው። በእነዚህ ግምቶች መሰረት በግጭቱ ቢያንስ 200 የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት ሲቆስሉ ሌሎች 10 ተገድለዋል። የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል በግንቦት 25 በለቀቀው መግለጫ የባልደራስ ፓርቲ ሊቀመንበር የነበሩትን እስክንድር ነጋን በዋነኛነት ተጠያቂ ያደረገ ሲሆን በ“ኦፕሬሽኑ” ወቅት 200 “ታጣቂዎቹ” ተገድለዋል ብሏል።9 የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ፣ ‘ከፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል የተሰጠ መግለጫ፣’ ግንቦት 25, 2015፤ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ‘በምሥራቅ ጎጃም ዞን፣ ደብረ ኤልያስ ወረዳ ሥላሴ ገዳም መሽገው መንግሥትን በትጥቅ ትግል ለመጣል ሲንቀሳቀሱ በነበሩት እስክንድር ነጋ እና ግብረዓበሮቹ ላይ በተወሰደው እርምጃ ክልሉን የማተራመስ ሴራቸው መክሸፉን የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ፣’ ግንቦት 26, 2015 የደብረ ኤልያስ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት እንደገለጸው ቡድኑ በገዳሙ ውስጥ ስልጠና ሲሰጥ እንደነበረ እና የኃይማኖት አባቶችን፣ የአካባቢውን የሀገር ሽማግሌዎች እና የአካባቢውን ባለስልጣናት በመግደል ተሳትፏል።10የደብረ ኤልያስ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት፣ ‘ከደብረ ኤልያስ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት የተላለፈ መልዕክት፣’ ግንቦት 23, 2015
በተጨማሪም ባለፈው ሳምንት ሁለት የእጅ ቦምቦ ጥቃቶች በክልሉ ውስጥ ተመዝግበዋል። ግንቦት 22 ቀን በደቡብ ወሎ ዞን ሳይንት ወረዳ አጅባር ከተማ የዞን፣ የወረዳና የቀበሌ የብልፅግና ፓርቲ አስተዳዳሪዎችን ያሳተፈ ስብሰባ እየተካሄደ ባለበት የኮንፈረንስ ማዕከል ማንነቱ ያልታወቀ ቡድን የእጅ ቦምብ ወርውሯል። በኮንፈረንስ ማዕከል ላይ ጉዳት ቢደርስም በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም። በማግስቱ በሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ ማንነቱ ያልታወቀ ቡድን አምስት የአካባቢውን ሚሊሻዎች ጨምሮ ስድስት የፀጥታ ኃይሎች ላይ የእጅ ቦምብ በመወርወር አቁስሏል። ጥቃቱን ተከትሎ በከተማዋ የተኩስ ድምጽ ተሰምቷል። ነገር ግን ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በዚህ የተኩስ እሩምታ ውስጥ ማን እንደተሳተፈ የታወቀ ነገር የለም። መንግስት የክልል ልዩ ኃይል ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ የፀጥታ አካላት እንዲዋሃዱ ከወሰነ ወዲህ አማራ ክልል በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ያልተረጋጋ ክልሎች አንዱ ሆኖ ቆይቷል (ለበለጠ መረጃ ኢፒኦ ከመጋቢት 23 እስከ ሚያዚያ 22, 2015 ወርሀዊ፡ የተቀረው የአገሪቱ ክፍል ሲረጋጋ በአማራ ክልል የተከሰተው አለመረጋጋት ይመልከቱ)።
በኦሮሚያ ክልል ባለፈው ሳምንት ውጊያዎች እና በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ቀጥሏል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና ኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ በምዕራብ ሸዋ ዞን በአቡና ግንዴ በረት ወረዳ በባዳ ጢኖ እና ኤሬሪ ኬሎ ቀበሌዎች እና በሽኩቴ በጀልዱ ወረዳ እንዲሁም በአርሲ ዞን ዶዶታ ወረዳ ሙዴ ላይ ተዋግተዋል። በተጨማሪም በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ ኦነግ-ሸኔ፣ ፋኖ ታጣቂ እና ማንነቱ ያልታወቀ የታጠቀ ቡድን የተፈጸሙ ቢያንስ 16 ሰዎች ህይወትን የቀጠፉ ስድስት በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈፀሙ ጥቃቶች በክልሉ ተዘግቧል።