በዚህ ዘገባ ውስጥ የተካተቱ
- ከግንቦት 24 እስከ ሰኔ 23 በጨረፍታ
- አበይት ክንውኖች
- ከግንቦት 24 እስከ ሰኔ 23 ድረስ የተከሰቱ ቁልፍ ኩነቶች
- ወርሃዊ ትኩረት፡ በአማራ ክልል መንግስት ያደረገውን ጫና ተከትሎ የፖለቲካ አመጽ እየቀነሰ መምጣቱ
ከግንቦት 24 እስከ ሰኔ 23 በጨረፍታ
አበይት ክንውኖች
- አክሌድ ከግንቦት 24 እስከ ሰኔ 23 ድረስ 78 የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች እና ቢያንስ 226 ሪፖርት የተደረጉ ሟቾች መዝግቧል።። ከእነዚህ ውስጥ 56ቱ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠሩ ኩነቶች ሲሆኑ ከሚያዚያ 23 እስከ ግንቦት 23 ድረስ ካለው ጊዜ ጋር ሲነጻጸር 40 ከመቶ ጭማሪ አሳይቷል።
- ከግንቦት 24 እስከ ሰኔ 23 ድረስ ከፍተኛ የሆነ ኩነቶች እና በፖለቲካ ግጭት ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ ሟቾች ቁጥር በኦሮሚያ ክልል የተዘገበ ሲሆን 55 ኩነቶች እና ቢያንስ 182 ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር ተመግቧል ። በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል በሀገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአካባቢ አስተዳዳሪዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት የተመዘገበ ሲሆን አብዛኞቹ – ከአምስቱ ሶስቱ – የተፈፀሙት በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ መሆኑ ተነግሯል።
- ከግንቦት 24 እስከ ሰኔ 23 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በጣም ተደጋግመው የተከሰቱት የኩነት ዓይነቶች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈፀሙ ጥቃቶች – 51 ኩነቶች – እና የተቃውሞ ሰልፎች – 32 ኩነቶች – ናቸው። በሀገሪቱ ከተመዘገቡት የተቃውሞ ሰልፎች ግማሹ የተከሰቱት በትግራይ ክልል ሲሆን ይህም በክልሉ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች የብሔር ማንነታቸው ካለው አስተዳደር ጋር እንዲታይ በመጠየቅ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የተቃውሞ ሰልፍ በማካሄዳቸው ነው።
አበይት ክንውኖች
ወርሃዊ ትኩረት፡ በአማራ ክልል መንግስት ያደረገውን ጫና ተከትሎ የፖለቲካ አመጽ እየቀነሰ መምጣቱ
በአማራ ክልል ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ የፖለቲካ ውጥረቱ እየጨመረ ቢመጣም ከግንቦት 24 እስከ ሰኔ 23 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ የተመዘገቡ የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች መቀነሳቸው ቀጥለዋል (ከዚህ በታች ያለውን ምስል ይመልከቱ)። ከአማራ ክልል ልዩ ኃይል ትጥቅ መፍታት ጋር ተያይዞ በመጋቢት ወር መጨረሻ ላይ በተከሰተው አለመረጋጋት እና በሚያዚያ ከአማራ ብሔር ታጣቂዎች ጋር ተያይዞ በተነሳ ግጭት ጋር ሲተያይ ከግንቦት 24 እስከ ሰኔ 23 ድረስ ውስን ግጭቶች እና አንዳንድ የተቃውሞ ሰልፎች ብቻ ታይተዋል። ጉልህ በሆነ መልኩ በአማራ ክልል በሀገሪቱ የፖለቲካ አቅጣጫ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ውጥረት እና በመንግስት ላይ የሚነሱ ቅሬታዎች ቢኖሩም በአጠቃላይ ሲታይ በክልሉ የሚታየው የግጭት መጠን ከኦሮሚያ ክልል ጋር ሲነፃፀሩ በጣም ዝቅተኛ ነው (ለበለጠ መረጃ የኢፒኦ ወርሃዊ፡ ከሚያዚያ 23 እስከ ግንቦት 23, 2015ን ይመልከቱ)።
መጋቢት 28 ቀን የኢትዮጵያ መንግስት የክልል ልዩ ኃይሎችን ወደ ተለያየ የፀጥታ መዋቅሮች ውስጥ ለማካተት ያለውን ፍላጎት አስታውቋል። ይህ አካሄድ በመላው አማራ ክልል ረብሻ እና ተቃውሞ አስነስቷል( ለተጨማሪ መረጃ ኢፒኦ ወርሃዊ፡ ከመጋቢት 23 እስከ ሚያዚያ 22, 2015ን ይመልከቱ )። ይህን አካሄድ የተቃወሙ ወገኖች “ጊዜውን ያልጠበቀ ነው” በማለት መንግስት የአማራ ክልልን ለጥቃት እንዲጋለጥ ትቶታል ሲሉ ተችዋል።1የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ ‘በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ፣’ ሚያዝያ 3, 2015 ይህ ስሜት የሰሜኑ ግጭት ወደ አማራ ክልል ተዛምቶ በመንግስትና በግል ንብረቶች ላይ ከፍተኛ ውድመት ካደረሰ በኋላ በክልሉ ውስጥ ያለውን ስጋት ያመለክታል። ሁኔታው በሚያዚያ ወር የአማራ ብልፅግና ፓርቲ መሪ ከመሃል ሜዳ ወደ ደብረ ብርሃን በመጓዝ ላይ እያሉ በመገደላቸው በክልሉ ያለው አለመረጋጋት ከፍተኛ ደረጃ ደርሷል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ወደ ተለያዩ የክልሉ ከተሞች በመሰማራቱ ከመጋቢት መጨረሻ እስከ ግንቦት ወር መጀመሪያ ድረስ በመከላከያ እና በአማራ ታጣቂዎች፣ ፋኖ እና የልዩ ኃይል አባላት መካከል የተደረገ 15 ውጊያዎች ቢያንስ በ12 ቦታዎች ተመዝግበዋል። በግንቦት ወር አጋማሽ ላይ በምስራቅ ጎጃም ዞን በደብረ ኤልያስ ወረዳ በደጎልማ ቀበሌ በሚገኘው የደብረ ኤልያስ ብሔረ ብጹአን መልካስላሴ አንድነት ገዳም ከመሸጉት ከአማራ ህዝባዊ ግንባር ታጣቂዎች ጋር የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አራት ቀናት የፈጀ ውጊያ አድርጓል። መንግስት የቀድሞ የባልደራስ ፓርቲ ሊቀመንበር እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በዋነኛነት ተጠያቂው መሆኑን ገልጾ 200 የአማራ ህዝባዊ ግንባር አባላት በዚህ ዘመቻ መገደላቸውን ተናግሯል2የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ‘በምሥራቅ ጎጃም ዞን፣ ደብረ ኤልያስ ወረዳ ሥላሴ ገዳም መሽገው መንግሥትን በትጥቅ ትግል ለመጣል ሲንቀሳቀሱ በነበሩት እስክንድር ነጋ እና ግብረዓበሮቹ ላይ በተወሰደው እርምጃ ክልሉን የማተራመስ ሴራቸው መክሸፉን የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ፣’ ግንቦት 26, 2015 (በደብረ ኤልያስ ስለተፈጠረው ክስተት የበለጠ መረጃ ለማግኘት የኢፒኦ ሳምንታዊ: ከግንቦት 19-25, 2015ን ይመልከቱ)።
በአማራ ክልል በአማራ ብሔርተኞች ላይ መንግስት እየወሰደ ያለው እርምጃ ፈጣን እና ወሳኝ የሆነ ይመስላል። በአማራ ክልል ከፌዴራል የፀጥታ ኃይሎች ጋር ተያይዞ በተለያዩ ቡድኖች እና ታጣቂዎች የሚነሱ ቅሬታዎች ወደ ከፋ አመጽ የመሸጋገር አቅም አላቸው። ይሁን እንጂ ከግንቦት 24 እስከ ሰኔ 23 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ የተስፋፋው የጦርነት ኩነቶች አለመኖራቸው መንግስት በሚያዝያ እና በግንቦት ወር በአማራ ብሔርተኞች ላይ የወሰደው ፈጣን እርምጃ በክልሉ ተጨማሪ ታጣቂዎችን በተሳካ ሁኔታ እንዳስቆመ ሊጠቁም ይችላል። የኦነግ-ሸኔ ብዙ አመታትን ካስቆጠረበት ኦሮሚያ ክልል ከሚገኘው የሸምቅ ውጊያ በተቃራኒ በአማራ ክልል ውስጥ ያሉ ፀረ-መንግስት ቡድኖች አዲስ እና ገና ያልበሰሉ በመሆናቸው ሰፊ ቅንጅት ይጎድላቸዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መሰማራቱ ግን በፓርላማ ውስጥ በሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እና በብዙ ከተሞች ተቃውሞዎችን አስነስቷል።
በአማራ ብሔርተኞች ላይ የመንግስት ጫና
የአማራ ብሔርተኝነት አዲስ ክስተት አይደለም። የዘመኑ የአማራ ብሔርተኞች መነሻው የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ መቋቋም ነው። ኮሚቴው በ2007 ዓ.ም. የተቋቋመ ሲሆን በትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሓት) በሚተዳደረው በትግራይ ክልል በሚገኘው በወልቃይት እና ፀገዴ አካባቢዎች የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች የብሔር መብት እንዲከበር ይሟገታል።3ዞንያ ጆን፣ ‘የኢትዮጵያ ዲሞክራሲ እምቅ: የወልቃይት ጥያቄ እንደሊትመስ ፈተና፣’ ጆርናል ኦፍ ኤዥያን ኤንድ አፍሪካን ስተዲስ፣ ሐምሌ 26, 2013 የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት የተለያዩ የአማራ ቡድኖች ወታደራዊ ልምድ እንዲቀስሙ፣ መሳሪያ እንዲያገኙ እና እንዲደራጁ እድል ፈጥሮላቸዋል። ግጭቱን ተከትሎ ሰለ ምዕራብ ትግራይ፣ ከትህነግ/ህወሓት ጋር ሰለሚደረገው የሰላም ድርድር እና የፋኖ ታጣዊዎችን ትጥቅ ማስፈታትን አስመልክቶ ከእነዚህ ቡድኖች የሚመጣው ጥያቄ የአማራ ብሔርተኝነትን የሚደግፉ ታጣቂዎች ከመንግስት ኃይሎች በተጻራሪ እንዲሆኑ አድርጓል።
የሰሜኑ ግጭት ማብቃቱን ተከትሎ መንግስት በክልሉ በሚገኙ በርካታ ከተሞች ወታደሩን ማስፈር እና እስራት መፈጸምን ጨምሮ ጠንካራ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል። ሰኔ 1, 2015 ዓ.ም. የፌዴራል መንግስት አብዛኛዎቹ የአማራ ብሔርተኝነትን የሚደግፉ እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ወደ አማራ ክልል መግባቱን የሚቃወሙ ታዋቂ የሚዲያ ሰዎችን ጨምሮ በ51 ግለሰቦች ላይ የሽብርተኝነት ክስ መመስረቱን አስታውቋል።4ኢትዮጵያ ኢንሳይደር፣ ‘ዐቃቤ ህግ በ51 ግለሰቦች ላይ የመሰረተው የሽብር ወንጀል ክስ ዝርዝር እና የተከሳሾች የፍርድ ቤት ውሎ፣’ ሰኔ 6, 2015 በእስር ላይ በሚገኙ በርካታ የፋኖ ታጣቂ አመራሮች ላይ ተጨማሪ ክስ ቀርቧል።5አዲስ ስታንዳርድ፣ ‘<ዜና> የፌደራል የጸጥታ ግብረ ሃይል በአማራ ክልል የተቀሰቀሰውን አዲስ ሽምቅ ሃይል አዳክመናል ሲል የፋኖ ታጣቂ መሪ የሆነው ዘመነ ካሴ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ አይደለም ሲል በነፃ አስናብቷል፣’ ሰኔ 5, 2015 በፌዴራል መንግስት የተወሰደው እርምጃም ሰዎችን አስገድዶ መሰወርንም ያካተተ መሆኑም ተነግሯል።6ኢሰመኮ፣ ‘በኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣው ሰዎችን አስገድዶ የመሰወር (Enforced Disappearance) ድርጊት በአፋጣኝ ሊቆም ይገባል’ ግንቦት 28, 2015 በገዢው የብልጽግና ፓርቲ የበላይነት የተያዘው የአማራ ክልል መንግስት ከፌዴራል መንግስት ጋር እንደሚሰለፍ እና የልዩ ኃይል ውህደት እና ህብረተሰቡ ቢቃወም ከትህነግ/ህወሓት ጋር የሚደረገው የሰላም ሂደት ማስቀጠልን ጨምሮ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ስሚሰጡ መመሪያዎችን መፈጸም ቀጥሏል። ሰኔ 4 ቀን የትህነግ/ህወሓት ልኡካን ቡድን ባህር ዳርን የጎበኙ ሲሆን ከአማራ ክልል ባለስልጣናት ጋር በትግራይ እና በአማራ ክልሎች መካከል ስላለው የወደፊት ሰላም ተወያይተዋል።7ቪኦኤ አማርኛ፣ ‘የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳዳሪዎች ባህር ዳር ገቡ፣’ ሰኔ 4, 2015፣ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬን፣ ‘”ውይይቱ በሁለቱ ክልሎች መካከል ሰላምን ለማስፈን መሰረት የጣለ ነው” አቶ ግዛቸው ሙሉነህ፣’ ሰኔ 7, 2015
በአማራ ክልል የመንግስት ጫና እና የህዝቡ ምላሽ
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በአማራ ክልል መስፈር ከፍተኛ ተቃውሞ ቀስቅሷል። ማህበረሰቡ የሠራዊቱን በክልሉ መግባት የተቃወመ ሲሆን ቅሬታው የፋኖ አመራሮች በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች የመታሰራቸውን ሂደት በግጭት የታጀበ አድርጎታል። በህገ መንግስቱ መሰረት የፌዴራል ኃይሎች ወደ ክልል መግባት የሚችሉት የክልሉ የፀጥታ ሁኔታ ከክልሉ የፀጥታ ኃይሎች አቅም በላይ ሲሆን እና በክልሉ መንግስት ግብዣ ብቻ ነው።8የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አዋጅ ቁጥር 1/1987፣ 1987፣ አንቀጽ 51 (14) በዚህ ጉዳይ ላይ የአማራ ክልላዊ መንግስት የፌዴራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ በይፋ ጥሪ አላቀረበም። ሚያዚያ 20 ቀን የተለያዩ የፌዴራል የፀጥታ አካላትን ያቀፈው የጋራ የሰላምና ፀጥታ ግብረ ኃይል የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በአማራ ክልል መሰማራትን የክልሉን ስልጣን በኃይል ለመያዝ እየሞከሩ ያሉትን “ጽንፈኛ ኃይሎች” ላይ ያነጣጠር ነው ሲል መግለጫ አውጥቷል።9የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ፣ ‘በአማራ ክልል ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን በማፍረስ ክልላዊ ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠር በሚጥሩ ጽንፈኛ ኃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ፣’ ሚያዝያ 20, 201 የክልሉ መንግስት የመከላከያ ሠራዊት መግባትን በመደገፍ መግባታቸውን በመቃውም የሚያሰራጩ “የሐሰት ትርክቶችን” አውግዟል።10የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ‘ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሰላምና ጸጥታ ቢሮ በወቅታዊ ጉዳዮች የተሰጠ መግለጫ፣’ ግንቦት 2, 2015 ሰኔ 1 ቀን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የፓርላማ አባላት የፌዴራል መንግስት የፌዴራል ወታደሮችን ከክልሉ እንዲያስወጣ ጠይቀዋል።11ቪኦኤ አማርኛ፣ ‘በህግ አስከባሪ ስም ወደ አማራ ክልል የገባው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እንዲመለስ ተጠየቀ፣’ ግንቦት 30, 2015 ሰኔ 2 ቀን የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሃገር አቀፍ ጥምረት በሀገሪቱ ያለውን የፀጥታ ሁኔታ በማውገዝ በተለይም የአማራ ክልልን በመጥቀስ መንግስት ሁኔታውን ለማሻሻል የእርምት እርምጃዎችን እንዲወስድ ጠይቀዋል።12ዶይቸ ቬለ አማርኛ፣ ‘የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጥሪ፣’ ሰኔ 2, 2015
በተለያዩ ቦታዎች የተካሄዱ ጦርነቶች እና ሰልፎችን ጨምሮ የፌዴራል መንግስት በአማራ ብሔርተኞች እና ድርጅቶች ላይ እየወሰደ ያለው እርምጃ በክልሉ ላለው አለመረጋጋት ምክንያት ሆኗል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። ሰኔ 5 ቀን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እስክንድር ነጋን ፍለጋ ደምበጫ ከተማ በገቡበት ወቅት የፌዴራል ጦር በከተማዋ መገኘቱን በመቃወም ግጭት የተቀላቀለበት የተቀቃውሞ ሰልፍ እንዲቀሰቀስ ምክንያት ሆኗል። በሰልፈኞቹ ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ወታደሮች ተኩስ በመክፈታቸው ሁለት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላትን እና ሶስት ሰልፈኞችን ጨምሮ አምስት ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል። በተመሳሳይ በሰሜን ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ ሰኔ 14 ቀን ከፌዴራል ወታደሮቹ መካከል አንዱ ሴት ልጅ ደፍሯል የሚል ውንጀላ ከተሰራጨ በኋላ ስልፍ የተደረገ ሲሆን የፌዴራል ወታደሮች ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር ተዋግተዋል፡፡
ባለፈው ወር በመንግስት እና በገዥው የብልጽግና ፓርቲ ላይ ያለው ቅሬታም መገለጹ የቀጠለ ሲሆን በክልሉ የሚገኙ አርሶ አደሮች ከግንቦት 24 እስከ ሰኔ 23 ባለው ጊዜ ውስጥ በክልሉ ዋና ከተማ ተከታታይ ሰልፎች በማድረግ መንግስት የማዳበሪያ አቅርቦትን ከልክሏል ሲሉ ከሰዋል።13ዲደብሊው አማርኛ፣ ‘በአማራ ክልል የተከሰተውን የማዳበሪያ እጥረት ተከትሎ በምዕራብ ጎጃም ዞን ይልማና ዴንሳ ወረዳ ደብረማዊ ቀበሌ አካባቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮች በባህር ዳር ከተማ ጅራፍ እያጮሁ ነው፣” ግንቦት 24, 2015 የኦነግ-ሸኔ አባላት በርካታ ከአማኤኤል ከተማ የሆኑ አሽከርካሪዎችን ካገቱ በኋላ የአማኑኤል ከተማ ነዋሪዎች ሰኔ 12 ቀን አውራ ጎዳናዎችን በመዝጋት መንግስት በኦሮሚያ ክልል እየወሰደ ያለውን ልል የፀጥታ እርምጃ አውግዘዋል። የአማራ ክልል ፖሊስ በህዝቡ ላይ ጥይት በመተኮሱ አንድ ሰው ሲሞት አራት ሰዎች ቆስለዋል።
ያለው ቅሬታ ከፍተኛ ቢሆንም በአማራ ክልል የሚገኙት ፀረ-መንግስት ታጣቂዎች በበቂ ሁኔታ የተደራጁ ባለመሆናቸው እና የተከፈፈሉ በመሆኑ በመንግስት ላይ በቂ ተግዳሮት ለመፍጠር የሚችሉ አይመስሉም። በኦሮሚያ ክልል የኦነግ ቅርንጫፍ ከሆነው እና የኦሮሞ ብሔርተኞችን ስልጣን ከወረሰው የኦነግ-ሸኔ ሽምቅ ተዋጊዎች በተለየ መልኩ የአማራ ክልል ጠንካራ የሽምቅ ታሪክ የሌለው ሲሆን የአካባቢ ታጣቂዎች ጠንካራ ቅንጅት የላቸውም። እነዚህ ሁኔታዎች ብዙ ቅሬታዎች ቢኖሩም ከፌዴራል መንግስት ፈጣን ምላሽ ጋር ተዳምሮ የተዘገበው የፖለቲካ ግጭት በአጠቃላይ ለምን ዝቅ ያለ እንደሆነ ሊያብራሩ ይችላሉ።
መንግስት በአማራ ክልል የወሰደው እርምጃ በአማራ ብሔርተኞች ላይ ውጤታማ እና ከባድ ምላሽ ነው። መንግስት የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ ምንም እንኳን አለመረጋጋት እና አንዳንድ ውስን ውጊያዎች ቢኖሩም በአማራ ክልል ያለው ሁኔታ የተረጋጋ ሲሆን በሰኔ ወር የተከሰቱ ግጭቶች ከሚያዝያ እና ግንቦት ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ነው። እስራቶች፣ ውጊያዎች እና የፌዴራል ወታደሮች መሰማራት በክልሉ የተዘገቡ የግጭት ክስተቶች አነስተኛ እንዲሆኑ አድርገዋል። ነገር ግን በአማራ ክልል ቅሬታዎች አሁንም ያሉ ሲሆን በአብዛኛው ማህበረሰብ ተቀባይነት ሳይኖረው የፌዴራል ጦር በክልሉ መስፈሩ ያለው ቅሬታ እንዲጨምር አድርጎታል። ልክ እንደ አማራ ማህበር በአሜሪካ ያሉ የአማራ ዲያስፖራ ድርጅቶች መንግስት በክልሉ እየወሰደ ያለውን እርምጃ ያወገዙ ሲሆን ተጠያቂነትንም ጠይቀዋል።14ኤኤኤ፣ ‘በደምበጫ፣ ጅጋ እና ፍኖተ ሰላም ከተሞች (በምእራብ ጎጃም ዞን፣ አማራ ክልል፣ ኢትዮጵያ) በሰኔ 4 እና 5, 2015 ኦሮሞ በሚበዛበት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በንፁሃን ሰዎች ላይ የተፈጸመው ግድያ እና የአካል ጉዳት፣’ ሰኔ 20, 2015 የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በክልሉ ውስጥ መገኘት ማንኛውንም ሰፊ የአመፅ ስርጭት ለጊዜው አዘግይቶ ሊሆን ቢችልም ዘላቂ መፍትሄ አይደለም በመሆኑም ውጊያዎች እንደገና ሊከሰቱ ይችላሉ።