በቁጥር: ኢትዮጵያ, ከሐምሌ 22, 2014-ሐምሌ 28, 2015
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 1,073
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 4,027
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 1,918
በቁጥር: ኢትዮጵያ, ከሐምሌ 22-28, 20151በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ በመረጃ ቋታችን ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 39
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 46
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 9
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን ከኢፒኦ የመረጃ መዝገብ እንዲሁም በዋናው የአክሌድ ኤክስፖርት መሳሪያ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
በፌዴራል መንግስት እና በትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሓት) መካከል የተደረገው የሰላም ስምምነት የሰሜን ግጭት እንዲቋጭ ካደረገ በኋላ ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል የፖለቲካ ግጭቶች ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ደርሰዋል።2አዲስ ማለዳ፣ ‘በአማራ ክልል ያጋጠመውን የጸጥታ መደፍረስ ለመቆጣጠር የፌደራል መንግሥት አስፈላጊውን የሕግ ማዕቀፍ እንዲተገብር የክልሉ መንግሥት ጠየቀ፣’ ሐምሌ 27, 2015 መንግስት በመጋቢት ወር መጨረሻ ላይ ሁሉም የክልል ልዩ ኃይሎች ወደ ተለያዩ የፀጥታ መዋቅሮች እንደሚቀላቀሉ ማሳወቁን ተከትሎ በአማራ ክልል በሚመዘገቡ በመንግስት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የሚደረጉ ተደጋጋሚ ውጊያዎች (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ) እና የሰልፍ ኩነቶች ምክንያት የአማራ ክልል በሀገሪቱ ካሉ ክልሎች በጣም መረጋጋት ከጎደላቸው ክልሎች አንዱ ሆኗል። ሚያዚያ 19 ቀን ማንነቱ ያልታወቀ ታጠቂ ቡድን የገዢውን የብልጽግና ፓርቲ የአማራ ቅርንጫፍ መሪን ከገደለ በኋላ የፌዴራል መንግስት “በጽንፈኛ ኃይሎች” ላይ እርምጃ ለመውሰድ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን ካሰማራ በኃላ የክልሉ አለመረጋጋት ተባብሷል።3ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት፣ ‘በአማራ ክልል ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን በማፍረስ ክልላዊ ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠር በሚጥሩ ጽንፈኛ ኃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ፣’ ሚያዝያ 20, 2015
ባለፈው ሳምንት አክሌድ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተደረጉ 28 የውጊያ ኩነቶችን የመዘገበ ሲሆን አብዛኛው ውጊያ የተከሰተው በሰሜን ወሎ እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች ነው። የፋኖ ታጣቂዎች አንዳንድ ከተሞችን በመቆጣጠር እስረኞችን ማስፈታት ችለዋል።4ኤፍቢሲ፣ ‘የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ እዝ ዋና ሰብሳቢ አቶ ተመስገን ጥሩነህ የአዋጁ ቀጣይ ስራዎችን በሚመለከት የሰጡት ማብራሪያ፣’ ሐምሌ 30, 2015 በክልሉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን እንቅስቃሴ ለመግታት በደብረ ማርቆስ፣ ደምበጫ፣ ቡሬ እና አማኑኤል ከተሞች ሰልፈኞች መንገዶችን በመዝጋታቸው በርካታ ግጭት የተቀላቀለባቸው ስልፎችም ተካሂደዋል። አንድ የአካባቢው ባለስልጣን በምስራቅ እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች ውጊያዎች የተቀሰቀሰው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ወደ ምስራቅ አማራ መንቀሳቀስ በጀመረበት ወቅት መሆኑን ተናግረዋል።5የኢትዮጵያ ሚዲያ ስርቪስ፣ ‘ኢኤምስ እለታዊ እሮብ ሐምሌ 26, 2015፣’ ሐምሌ 26, 2015
በተፈጠረው አለመረጋጋት የአማራ ክልል መንግስት በክልሉ የተፈጠረው የፀጥታ ችግር ከክልሉ የፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ውጪ በመሆኑ የፌዴራል መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል።6አዲስ ማለዳ፣ ‘በአማራ ክልል ያጋጠመውን የጸጥታ መደፍረስ ለመቆጣጠር የፌደራል መንግሥት አስፈላጊውን የሕግ ማዕቀፍ እንዲተገብር የክልሉ መንግሥት ጠየቀ፣’ ሐምሌ 27, 2015 በዚህም መሰረት ሐምሌ 28 ቀን የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአማራ ክልል ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል።7የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት-ኢትዮጵያ፣ ‘23ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች፣’ ሐምሌ 28, 2015፤ በኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት፣ ‘የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ 6/2015፣’ ሐምሌ 28, 2015፤ አዲስ ማለዳ፣ ‘በአማራ ክልል ያጋጠመውን የጸጥታ መደፍረስ ለመቆጣጠር የፌደራል መንግሥት አስፈላጊውን የሕግ ማዕቀፍ እንዲተገብር የክልሉ መንግሥት ጠየቀ፣’ ሐምሌ 27, 2015 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንደ ሰላማዊ ሰልፎችን ማድረግ በመከልከል እና ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ሰዎችን ማሰርን በመፍቀድ የተለያዩ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ላይ ገደቦችን ያቀፈ ነው።8በኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት፣ ‘የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ 6/2015፣’ ሐምሌ 28, 2015፤ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ‘በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስመልክቶ የተሰጠ ማብራሪያ ኢቢሲ | ኢቲቪ | ኢትዮጵያ | ዜና | ዕለታዊ ዜና፣’ ሐምሌ 28, 2015 የሀገሪቱ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስፈላጊ ከሆነ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎችም ሊተገበር እንደሚችል ጠቁመዋል።9የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ‘በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስመልክቶ የተሰጠ ማብራሪያ ኢቢሲ | ኢቲቪ | ኢትዮጵያ | ዜና | ዕለታዊ ዜና፣’ ሐምሌ 28, 2015
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቢታወጅም በዚህ ሳምንት በአማራ ክልል በፋኖ ታጣቂዎች እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል የሚደረጉ ውጊያዎች ቀጥለዋል።10የአክሌድ ዳታ (መረጃ) እና የኢፒኦ ሳምንታዊ ዘገባዎች እ.ኤ.አ በኦገስት 2023 የመጨረሻዎቹ ሶስት ሳምንታት ውስጥ የማይታተሙ ሲሆን እ.ኤ.አ ከኦገስት 5 እስከ ሴፕቴምበር 1 (ከሐምሌ 29 እስከ ነሐሴ 26) ያለውን ጊዜ የሚሸፍነው ዳታ(መረጃ) ሴፕቴምበር 4 ቀን (ነሐሴ 29 ቀን) ላይ ይወጣል፣ ከዚያ በኋላ መረጃዎች በመደበኛ ጊዜያቸው ይቀጥላሉ። ይህንን ጊዜ የሚሸፍን የኢፒኦ ዘገባ እ.ኤ.አ በሴፕቴምበር 6 ቀን (ጳጉሜ 1 ቀን) ላይ ይታተማል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አባል እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክሪስቲያን ታደለ እና የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል ዶ/ር ካሳ ተሻገርን ጨምሮ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ታዎቂ ሰዎች በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው ግጭት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ውለዋል።11 ቢቢሲ አማርኛ፣ ‘አቶ ክርስቲያን ታደለ በፀጥታ ኃይሎች መታሰራቸውን ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ፣’ ሐምሌ 29, 2015 ሐምሌ 29 ቀን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሳዊ ሪፐብሊክ (የኢፌዴሪ) የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ እንደገለፁት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀ በኋላ ከአማራ ክልል ጋር ካለው ሁኔታ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋል መጀመረቸውን ግልፀዋል።12በኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት፣ ‘የሚኒስትሮች ምክር ቤት በትናንትናው እለት ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ተቋቁሞ ሥራ መጀመሩን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ገለጹ፣’ ሐምሌ 29, 2015
የግጭቱ መሠረታዊ መንስኤዎች
የአማራ ክልል ከ30 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የሚኖርበት በህዝብ ቁጥር በኢትዮጵያ ሁለተኛ የሆነ ክልል ነው። የአማራ ህዝብ እና በአማራ የተመረጡ ተወካዮች ከ2010 ጀምሮ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ መንግስት ጠንካራ ደጋፊ ሆነው የቆዩ ሲሆን ከ2013 እስከ 2015 መጀመሪያ ድረስ – የትግራይ መከላከያ ሰራዊት ተብሎም ከሚታወቀው – ከትህነግ/ህወሓት ኃይሎች ጋር በተደረገው ጦርነት ወቅት ጠንካራ መከላከያ ሠራዊት አካል ነበሩ። በዚያን ጊዜ ፋኖ እና ሌሎች የአማራ ብሔር ታጣቂዎች ክልላቸውን ከትህነግ/ህወሀት ኃይሎች ለመከላከል ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጎን ተሰልፈው የተዋጉ ሲሆን በምዕራብ ትግራይ ዞን የሚገኙ አካባቢዎችን ጨምሮ ውዝግብ የሚነሳባቸውን ቦታዎች ተቆጣጥረዋል።
በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ወቅት እና በኋላ በአማራ እና በፌዴራል ኃይሎች መካከል ያለው ውጥረት በሁለት ዋና ጉዳዮች ምክንያት ተባብሷል። አንደኛው በይፋ በትግራይ ክልል ስር የሚገኙ ነገር ግን በአማራ ክልል ስር መተዳደር የሚፈልጉ የአማራ ተወላጆችን በያዙት የወልቃይት፡ ሁመራ፡ ጸለምት እና ራያ አከባቢዎች ያለው የፖለቲካ ቅራኔ ነው (በእነዚህ አካባቢዎች በቅርቡ ተነስተው ስለነበሩ ህዝባዊ ተቃውሞዎች ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከግንቦት 26-ሰኔ 2, 2015ን እና ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከሰኔ 10-16, 2015ን ይመልከቱ)። መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ ውሳኔ ለመስጠት በእነዚህ አካባቢዎች ህዝበ ውሳኔ ለማድረግ ፍላጎቱን አሳይቷል።13ኢትዮጵያ ኢንሳይደር፣ ሰኔ 29, 2015 ነገር ግን በ1980ዎቹ የትህነግ/ህወሓት መራሹ መንግስት እነዚህን አካባቢዎች በትግራይ ክልል ስር ከማካለሉ በፊት ከአካባቢው ህዝብ ጋር ምንም አይነት ምክክር አላደረገም በማለት የአማራ ተወላጆች ህዝበ ውሳኔ ማካሄድን የሚቃወሙ ሲሆን መንግስት እነዚህ አከባቢዎች በአማራ ክልል ስር እንዲተዳደሩ ፖለቲካዊ ውሳኔ እንዲሰጥ ይፈልጋሉ።14ቢቢስ አማርኛ፣ ‘ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ስለወልቃይት የወደፊት ዕጣ እና ስለሚቀርብባቸው ክስ ምን ይላሉ?’ ሰኔ 12, 2015፤ ጌታሁን አስናቀ፣ ‘በራያና ጠለምት ጉዳይ ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ሀሳብ በመቅረቡ የጠለምት ተወካዮች ስብሰባ ረግጠው ወጡ፣‘ ሐምሌ 27, 2015
ሁለተኛው ጉዳይ የአማራ ህዝብ አጠቃላይ ደህንነት ሁኔታ ነው። በሰሜን ኢትዮጵያ በተቀሰቀሰው ግጭት ወቅት በ2013 መጨረሻ እና በ2014 የትህነግ/ህወሓት ኃይሎች ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች ዘልቀው ገብተው አካባቢዎችን መቆጣጠር ሲጅምሩ እና አብዛኛው ጦርነት በእነዚህ ክልሎች ሲደረግ የመንግስት ኃይሎች በተከታታይ ከተሞችን ለቀው በመውጣት የትህነግ/ህወሓት ኃይሎች ቦታዎችን እንዳይቆጣጠሩ አልተከታተሉም። በዚህ ጦርነት ወቅት ሰላማዊ የአማራ ተወላጆች በትህነግ/ህወሓት ሃይሎች በደል የደርሰባቸው ሲሆን በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልሎች የሚገኙ የአማራ ተወላጆችም አልፎ አልፎ በሚፈፀሙ ጥቃቶች ሰለባ ሆነዋል (ከዚህ በታች ያለውን ግራፍ ይመልከቱ)። በቅርቡ የክልል ልዩ ኃይሎችን ለማስወገድ የተደረሰው ውሳኔ በአማራ ክልል የአማራ ህዝብ ከሌሎች ክልሎች የሚነሱ ኃይሎችን ለመከላከል አቅም እንዳይኖረው ለሚያደርግ ነው ተብሎ ተወስዷል (የፀረ–መንግስት እንቅስቃሴዎች ላይ የበለጠ መረጃ ለማግኘት የኢፒኦ ወርሀዊ:- ከመጋቢት 23, 2013 እስከ ሚያዚያ 22, 2013ን እና በኦሮሚያ ክልል ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶችን ተከትሎ ስለተደረጉ ፀረ–መንግስት ሰልፎች የበለጠ መረጃ ለማግኘት የኢፒኦ ወርሀዊ:- ከግንቦት 24 እስከ ሰኔ 23, 2014ን ይመልከቱ)። ፋኖ እና አማራዎች – የአማራ ክልል ልዩ ኃይልን ትጥቅ በማስፈታት አማራ ክልልን ተከላካይ አልባ በማድረግ – በአማራ ህዝብ ላይ ለሚደርሰው በደል ተጠያቂነትን በሚያስወግድ መልኩ ከትህነግ/ህወሃት እና ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር-ሸኔ ጋር መንግስት የሰላማዊ ድርድር አድርጓል ሲሉ ይወነጅላሉ።
በአማራ ክልል አሁን ባለው ውጊያ ውስጥ እነማን ተሳታፊ ናቸው እና ለምን?
በአሁኑ ሰአት የመንግስት ኃይሎች በተለይም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከፋኖ እና ከአማራ ብሔር ታጣቂዎች ጋር እየተዋጉ ነው። የፋኖ ታጣቂዎች የፌዴራል ወታደሮች ከክልሉ ለቀው እንዲወጡ ጠየቀዋል። የክልል እና የፌዴራል መንግስት በኦሮሞ ብሔር የበላይነት ስር ናቸው ሲሉም ይከሳሉ። ከዚህም በተጨማሪ ወልቃይት፣ ፀለምት፣ ሁመራ እና ራያ አካባቢዎች በይፋ የአማራ ክልል አካል እንዲሆኑ ይጠይቃሉ።
ምን ተለወጠ እና ለምን አስፈላጊ ነው?
ከዚህ በፊት የፖለቲካ ቅሬታ በአጠቃላይ በሰላማዊ መንገድ ይገለጽ ነበር (ለበለጠ መረጃ ኢፒኦ ወርሀዊ:- ከግንቦት 24 እስከ ሰኔ 23, 2014ን እና ኢፒኦ ሳምንታዊ : ከሚያዚያ 9, 2013 እስከ ሚያዚያ 15, 2013ን ይመልከቱ)። ነገር ግን ከመጋቢት 2015 ጀምሮ በፋኖ ታጣቂዎች እና በመንግስት ኃይሎች መካከል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ውጊያ የተመዘገበ ሲሆነ እነዚህ ውጊያዎች በአብዛኛው የተከሰቱት በሰሜን ወሎ እና በሰሜን ሸዋ ዞኖች ነው (ለበለጠ መረጃ ኢፒኦ ወርሀዊ፡ ከመጋቢት 23 እስከ ሚያዚያ 22, 2015ን ይመልከቱ)። እስካሁን በኦሮሚያ ልዩ ዞን በሁለቱ ወገኖች መካከል ምንም አይነት ውጊያ ያልተከሰተ ሲሆን በአዊ ዞን አንድ የውጊያ ኩነት ሰኔ 3 ቀን የተከሰተ ሲሆን ይህም ከምዕራብ ጎጃም ዞን የመጡ የፋኖ ታጣቂዎች በአዊ ዞን የሚገኙ የአካባቢውን ባለስልጣናት አፍነው ለመውሰድ ሲሞክሩ የተከሰተ ነበር። በተጨማሪም የፀጥታ ኃይሎችን ጨምሮ በአካባቢው ባለስልጣናት ላይ ከፍተኛ የጥቃቶች በክልሉ ተመዝግበዋል። ይህም አንዳንድ የአካባቢው ባለስልጣናት ቤታቸውን ጥለው እንዲሸሹ አድርጓል። የክልሉ ፖሊስ እና የቀበሌ ታጣቂዎች ከፋኖ ታጣቂዎች አላማ ጋር ሳይወግኑ እንዳልቀረ የሚያመለክት ዘገባም አለ።15ኢኤምኤስ፣ ‘ኢኤምኤስ መረጃ ሰኞ ሐምሌ 24, 2015፣’ ሐምሌ 24, 2015
የአማራ ክልል ለፌዴራል መንግስት ብቸኛ የተረጋጋ ክልላዊ አጋር ተደርጎ ስለሚወሰድ እና የአማራ ክልል ድጋፍ ለአብይ መንግስት የማዕዘን ድንጋይ በመሆኑ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታዩ ያሉ ለውጦች በኢትዮጵያ የፀጥታ ስጋት ናቸው። እንደ ኦሮሚያ ክልል ያሉ ሌሎች ጠንካራ የክልል አጋሮች ለረጅም ጊዜ መረጋጋት የጎደላቸው በመሆኑ በአማራ ክልል የተረጋጋ የመንግስት ድጋፍ ማጣት ለአብይ መንግስት ጥሩ አይሆንም። በአማራ ክልል እየታየ ያለው ግጭት የፌዴራል መንግስት የክልል አጋር ድርጅቶችን እና የአማራ ማህበረሰብን ያለስልጣን እና ውዝግብ ያለባቸውን ቦታዎች ሳይስጥ ከፍተኛ መስዋዕትነት እንዲከፍሉ መጠየቁን ይጠቁማሉ። ከትህነግ/ህወሀት ጋር የተደረገው የሰላም ስምምነት ዝም ላለው ሶስተኛ ዋና ተዋናይ (የአማራ ክልልን) በስምምነቱ ላይ ያላካተተ መሆኑን አመላካች ሲሆን ይህን ትልቅ ጉልህ ችግር ለመፍታት ውዝግብ ያለባቸውን ባታዎችን ለአማራ ክልል የሚያካትት ነው። ይህ በጣም ውስብስብ ችግር ሲሆን የፌዴራል መንግስት ምንም ጉዳት ሳይደርስበት ከዚህ ችግር መላቀቅ አይችልም። ይልቁንም አሁን ያለውን የአማራ አለመረጋጋት እና የፌዴራል መንግስትን ድጋፍ ከወደፊት የትግራይ አለመረጋጋት እና ከአማራ ክልል ለፌዴራል መንግስት ድጋፍ እንደማይጠበቅ ካለው ጋር ሚዛን መጠበቅ ይጠይቃል።
ተጨማሪ ንባቦች
- ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከሰኔ 24-30, 2015 በአማራ ክልል በአካባቢው የፀጥታ ኃላፊዎች ላይ የሚደርሰው ግድያ መቀጠሉ።
- ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከሰኔ 10-16, 2015 በትግራይ ክልል ውዝግብ ባለባቸው ቦታዎች በአማራ ተወላጆች የተደረገ ሰልፍ።
- ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከሰኔ 3-9, 2015 በአማራ ክልል መንግስት ‘በጽንፈኛ’ ኃይሎች ላይ እየወሰደ ካለው እርምጃ ጋር የተያያዘ የተዘገቡት የፖለቲካ ግጭቶች እና አለመረጋጋቶች።
- ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከግንቦት 26-ሰኔ 2, 2015 በትግራይ ምዕራብ ትግራይ ዞን ውዝግብ ባለብቸው ቦታዎች በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች የተካሄደ የተቃውሞ ሰልፎች።
- ኢፒኦ ከመጋቢት 23 እስከ ሚያዚያ 22, 2015 ወርሀዊ፡ የተቀረው የአገሪቱ ክፍል ሲረጋጋ በአማራ ክልል የተከሰተው አለመረጋጋት ይህ ዘገባ በአማራ ክልል የተቀሰቀሰውን የግጭት መሰረታዊ መንስኤ እና የቅርብ ጊዜ መንስኤ፣ የክልሉ ልዩ ኃይል እና የፋኖ ታጣቂዎች እንዴት እንደተመሠረቱ፣ የአማራ ብሔርተኝነት እና በአማራ ክልል ሊፈጠሩ የሚችሉ ግጭቶችን በዝርዝር ይተነትናል።
- ኢፒኦ ከግንቦት 24 እስከ ሰኔ 23, 2015 ወርሃዊ፡ በአማራ ክልል መንግስትን ያደረገውን ጫና ተከትሎ የፖለቲካ አመጽ እየቀነሰ መምጣቱ ምንም እንኳን ይህ ዘገባ ከግንቦት 24 እስከ ሰኔ 23 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በአማራ ክልል የፖለቲካ ግጭት እንደቀነስ ቢተነትንም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በክልሉ ውስጥ መገኘት እና ማንኛውንም የአመፅ ለማፈን መጣር ዘላቂ መፍትሄ እንደማይሆን እና ውጊያዎች እንደገና ሊከሰቱ እንደሚችሉ ይደመድማል።