በቁጥር፡ ኢትዮጵያ, ኀዳር 1-7, 20161በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ በመረጃ ቋታችን ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት፡ 21
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር፡ 91
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር፡ 73
በቁጥር፡ ኢትዮጵያ, ኀዳር 2, 2015 -ኀዳር 7, 2016
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት፡ 1,214
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር፡ 3,769
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር፡ 1,362
ኢትዮጵያን የሚመለከቱ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን ከኢፒኦ የመረጃ መዝገብ እንዲሁም በዋናው የአክሌድ ኤክስፖርት መሳሪያ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች በአማፂ ቡድኖች እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል የሚደረጉ ውጊያዎች የቀጠሉ ሲሆን በትግራይ ክልል ሰዎች የተገደሉበት አመጽ ተዘግቧል።
በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (በመንግስት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ተብሎ የሚጠራው) እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል የሰላም ንግግር እየተደረገ ያለ ቢሆንም በኦሮሚያ ክልል የተወሰኑ ውጊያዎች ተዘግበዋል። ባለፈው ሳምንት በክልሉ ስምንት የጦርነት ኩነቶች የተመዘገቡ ሲሆን ከእነዚህ መካከል አብዛኞቹ – ከስምንቱ ሰባቱ – በሰሜን ሸዋ ዞን ተመዝግበዋል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። በሰሜን ሸዋ ዞን የተከሰቱ አብዛኞቹ ውጊያዎች በኦነግ-ሸኔ እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል የተደረጉ ናቸው። በሰሜን ሸዋ ዞን ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ በተከታታይ ውጊያዎች እየተከሰቱ ሲሆን ከእነዚህ ውጊያዎች መካከል አብዛኞቹ ዞኑ ከአማራ ክልል ጋር በአባይ ወንዝ በሚዋሰንበት በሰሜናዊ የዞኑ ክፍል የተመዘገቡ ናቸው። በዚህ ዞን ያለው አለመረጋጋት አልፎ አልፎ አዲስ አበባን የአማራ ክልል ዋና ከተማ ከሆነችው ከባህርዳር ጋር በሚያገናኘው መንገድ ላይ የሚደረጉ ጉዞዎችን አስተጓግሏል2ሃሚድ አወል፣ ‘በአባይ ድልድልይ አቅራቢያ ታጣቂዎች በሰነዘሩት ጥቃት ተዘግቶ የነበረው አውራ ጎዳና ለአገልግሎት ክፍት ሆነ፣’ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር፣ የካቲት 2, 2014 (ለተጨማሪ መረጃ የኢፒኦ ሳምንታዊ፡ ጥር 28-የካቲት 4, 2014ን ይመልከቱ)።
በአማራ ክልል በፋኖ ታጣቂዎች እና በመከላከያ ሠራዊት መካከል የሚደረጉ ውጊያዎች እንደቀጠሉ ሲሆን ባለፈው ሳምንት በደቡብ ወሎ እና በምዕራብ ጎጃም ዞኖች ውጊያዎች ተዘግበዋል። እየተካሄዱ ያሉ ውጊያዎች መንገዶች እንዲዘጉ እያደረጉ ሲሆን በዚህም ቢያንስ አንድ የቀይ መስቀል የእርዳታ ጭነት መኪና የዋግ ኽምራ ዞን ህዝብ ዘንድ እንዳይደርስ እንቅፋት ሆኗል።3ቪኦኤ አማርኛ፣ ‘ቀይ መስቀል ወደ ዋግ ኽምራ የላከው እርዳታ መድረስ አልቻለም፣’ ኅዳር 7, 2016 በተጨማሪም የፋኖ ታጣቂዎች ጥቅምት 30 ቀን በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ ላይ በሚገኘው በቡሬ ወረዳ ሳንቶም እና ቤኮ ቶቦ ቀበሌዎች ውስጥ ቢያንስ አምስት የኦሮሞ ሰላማዊ ሰዎችን ባልታወቀ ምክንያት ተኩሰው መግደላቸው ሪፖርት ተደርጓል። ይህንን ጥቃት ተከትሎ አብዛኞቹ የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ የሆኑ ከ3000 በላይ ነዋሪዎች ወደ አጎራባች የኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ተሰደዋል። የአካባቢው የፋኖ ታጣቂዎች መሪ ድርጊቱን ቡድኑ አለመፈፀሙን በመግለጽ በምትኩ ለድርጊቱ ከመንግስት ጋር ግንኙነት ያላቸው ታጣቂዎችን ተጠያቂ አድርጓል።4ናኮር መልካ፣ ‘በቡሬ ወረዳ በታጣቂዎች ተፈጸመ በተባለ ጥቃት ሰዎች እንደተገደሉ ተገለጸ፣’ ቪኦኤ አማርኛ፣ ኅዳር 4, 2016
በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል የጉሙዝ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉሕዲን) ተዋጊዎች ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጋር በገነተ ማሪያም ከተማ ስምምነት ተፈራርመዋል። ይህንንም ተከትሎ የጉህዲን አባላት መሳሪያቸውን በማስረከብ ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል። ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ትጥቅ የማስፈታት ጥረቶች የነበሩ ቢሆንም ተዋጊዎቹ አልፎ አልፎ እንደገና ወደ ውጊያ ተመልሰዋል (ለተጨማሪ መረጃ የኢፒኦ ሳምንታዊ፡ መጋቢት 1-8, 2015 እና የኢፒኦ ሳምንታዊ፡ ሐምሌ 8-14, 2015ን ይመልከቱ)።
በትግራይ ክልል ኅዳር 1 ቀን ቢያንስ 125 የሚሆኑ የመቐለ ዞን ማረሚያ ቤት(ሮማናት ተብሎ የሚታወቀው) ታራሚዎች ከደረጃ በታች የሆነ የኑሮ ሁኔታን በመቃወም አምፀዋል። ታራሚዎቹ ከማረሚያ ቤቱ ጠባቂዎች እና ፖሊሶች ጋር በመጋጨታቸው የማረሚያ ቤቱ ጠባቂዎቹ እርምጃ ወስደዋል፡፡ የማረሚያ ቤቱ ጠባቂዎች ከማረሚያ ቤቱ ለማምለጥ በመሞከር ላይ የነበሩ አራት ታራሚዎችን ተኩሰው የገደሉ ሲሆን ሌሎች ዘጠኝ ታራሚዎችን አቁስለዋል። ሰባት የጥበቃ ሠራተኞችም ጉዳት ደርሶባቸዋል። በተጨማሪም የመቐለ ከተማ የታክሲ ሾፌሮች እና ባለንብረቶች መንግስት ለታሪፍ ማሻሸያ ጥያቄያቸው ምላሽ ባለመስጠቱ ምክንያት ከኅዳር 3 ቀን ጅምሮ ለአራት ቀናት የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት አቁመው ነበር።
በመጨረሻም ኅዳር 4 ቀን የኢትዮጵያ መንግስት እና የሰብአዊ እርዳታ አጋሮች ተግባራዊ ያደረጉትን “ሁለገብ ማሻሻያ” ተከትሎ ዩኤስኤድ በመላው ኢትዮጵያ ለ“አንድ አመት የሙከራ ጊዜ” የምግብ እርዳት እንደገና ማስጀመሩን አስታውቋል።5ዩኤስኤድ፣ ‘ሁለገብ ማሻሸያ ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ ዩኤስኤድ በመላው ኢትዮጵያ ለሚገኙ ሰዎች የምግብ እርዳታ እንደገና ጀመረ፣’ ኅዳር 4, 2016 ዩኤስኤድ በሰኔ ወር ውስጥ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናትን እርዳታን ለተዋጊዎች በመስጠት እና ወደ ውጭ ሀገር በመላክ መልሶ በመሸጥ ከሶ ነበር።6ካትሪን ሁረልድ፣ ‘በመንግሰት ላይ የቀረበ ከፍተኛ የስርቆት ክስን ተከትሎ ዩኤስኤድ በሚሊዮን ለሚቀጠሩ ኢትዮጵያኖች የሚሰጠውን የምግብ እርዳታ አቋረጠ፣’ ዋሽንግተን ፖስት፣ ሰኔ 1, 2015