የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል እና በአዲስ አበባ በፋኖ ታጣቂዎች እና በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች መካከል ውጊያ የተደረገ ሲሆን በሙስሊም ሰላማዊ ሰዎች ላይ በአማራ ክልል በደረሰ ጥቃት ምክንያት የኃይማኖት ውጥረት መከሰቱ ተዘግቧል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በኦሮሚያ ክልል አንድ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከፍተኛ ባለስልጣን ተገድሏል። በአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ጥቃትም በክልሉ መፈፀሙ ተዘግቧል።
የኃይማኖት ውጥረት በአማራ ክልል
አማራ ክልል በአምስት ከተሞች በሙስሊም ሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች መፈፀማቸውን ተከትሎ ከ10 የማያንሱ ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል። መጋቢት 29 ቀን ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በክልሉ ዋና ከተማ ባህርዳር ከመስጊድ ሲመለሱ አምስት ሙስሊም ሰላማዊ ሰዎችን ተኩሰው ገድለዋል። በጎንደር ከተማ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በደረሰባቸው ጥቃት ሌሎች ሶስት ሙስሊም ሰላማዊ ሰዎችም ባለፈው ሳምንት ተገድለዋል። በሞጣ ከተማ ሚያዚያ 1 ቀን አንድ ሙስሊም ሰላማዊ ሰው ከሁለት ቀናት በፊት ለገንዝብ ታፍኖ ከተወሰደ በኃላ ተገድሏል። የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ ባለፉት ስምንት ወራት በክልሉ 80 ሙስሊም ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት እና ግድያ ተፈጽሟል።1የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት፣ ‘በአማራ ክልል ባለፉት 8 ወራትና መጋቢት 29/2016 በባህር ዳር ከተማ ሙስሊም ወንድሞች ላይ በተፈጠሩ ግድያ ላይ የተሰጠ መግለጫ፣’ መጋቢት 30, 2016
በኢትዮጵያ የኃይማኖት ግጭቶች በየጊዜው የሚከሰቱ ሲሆን በአማራ ክልል ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር በተያያዘ በሙስሊሞች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች በኢትዮጵያ የኃይማኖት ግጭቶች ከኃይማኖት አክራሪነት ጋር የተያያዙ ሳይሆን የፖለቲካ ውጥረት ውጤቶች መሆናቸውን የሚያሳይ ነው። ለምሳሌ በጎጃም የአማራ ማንነት ከኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጋር በእጅጉ የተሳሰረ ሲሆን ሙስሊሞች ከኦርቶዶክስ ወገኖቻቸው ጋር አንድ አይነት የፖለቲካ ፍላጎት የሌላቸው ተደርገው ይታያሉ።2ዮናስ ብሩ፣ ‘ፋኖ ከሌሎቹ የአማራ ነገድ መሬት በተለየ በጎጃም ለምን ጠነከረ?’ ቦርከና፣ መጋቢት 1, 2016 በሚያዚያ 2014 በጎንደር ከተማ የአንድ ሼኽ የቀብር ሥነ–ስርዓት ላይ በተገኙ ሰዎች ላይ ባነጣጠረ ሁከት 20 ሙስሊሞች ተገድለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በፋኖ ታጣቂዎች እና በመንግስት ኃይሎች መካከል የሚደረግው ውግያ የቀጠለ ሲሆን በሰሜን ሸዋ፣ ሰሜን ወሎ፣ ምዕራብ ጎጃም እና ሰሜን ጎንደር ዞኖች ውጊያ መደረጉ ታውቋል። በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ እና በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን ከተማ እና ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በተካሄደ ጦርነት በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል።
የኦነግ ባለስልጣን ግድያ በኦሮሚያ ክልል
በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሸዋ ዞን መቂ ከተማ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ የኦነግ ፓርቲ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑትን ባቴ ኡርጌሳን ያልታወቀ ታጣቂ ቡድን ሚያዝያ 1 ቀን ከለሊቱ ስድስት ሰአት ላይ አፍኖ በመውሰድ በጥይት ተኩሰው በመግደል አስከሬኑን ከከተማ ወጣ አርገው ጥለዋል። ኦነግ የመንግስትን የፀጥታ ኃይሎችን ተጠያቂ ያደረገ ሲሆን3ኤክስ@ኦኤልኤፍኤቢኦኤችኪው፣ ሚያዚያ 6, 2016 የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መግለጫ ግን ይህንን ክስ ውድቅ በማድረግ የፀጥታ ኃይሎች የተጎጂውን ቤተሰብ ጨምሮ 13 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አመልክቷል።4የአሜሪካ ድምፅ፣ ‘በኢትዮጵያ ውስጥ የኦሮሞ ተቃዋሚ በመገደልን ተከትሎ 13 ሰዎች ተያዙ፣’ ሚያዝያ 4, 2016፤ የኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ፣ ‘ከኦሮሚያ ክልል የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፣’ ሚያዝያ 2, 2016 የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን “አፋጣኝ፣ ገለልተኛ እና ሙሉ ምርመራ” እንዲደረግ ጠይቋል።5ኤክስ@ዳንኤልበቀለ፣ ሚያዝያ 2, 2016 ከግድያው ጋር በተያያዘ ባልታወቁ አካላት በታወጀ የስራ ማቆም አድማ ምክንያት በኦሮሚያ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች የትራፊክ እንቅስቃሴ መገደቡ ተነግሯል። በጥር ወር ላይ በኦሮሚያ ክልል የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች በምስራቅ ሸዋ ዞን በህዳር 2014 የሃገር ሸማግሌዎችን መገደላቸውን ጨምሮ ለተፈጸሙት በርካታ ከህግ አግባብ ውጪ ለተደረጉ ግድያዎች ‘ኮሬ ነገኛ (Koree Nageenya)’ የተባለ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች መሆናቸው ተገልጦ ነበር6ጁሊያ ፓራቪሲኒ፣ ‘በኢትዮጵያ ሚስጥራዊ ኮሚቴ አማፂያንን ለማስወገድ ግድያ እና እስራት ያዝዛል፣’ ሮይተርስ፣ የካቲት 15, 2016፤ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ‘በከረዩ የሚችሌ ገዳ የጅላ አባላት ግድያ ላይ የተደረገ የምርመራ ሪፖርት፣’ ጥር 25, 2014 (በምስራቅ ሸዋ ዞን በሃገር ሸማግሌዎች ላይ ስለደረሰው ግድያ የበለጠ መረጃ ለማግኘት የኢፒኦ ሳምንታዊ: መጋቢት 16-22, 2015 እና የኢፒኦ ሳምንታዊ: ከህዳር 18, 2014 እስከ ህዳር 24, 2014ን ይመልከቱ)።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ውስጥ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) — በመንግሥት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ተብሎ የሚጠራው — ታጣቂዎች የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጣልቃ ከመግባቱ በፊት በአማራ ተወላጆች ላይ ጥቃት በመሰንዘር 11 ሰዎች መግደላቸው ተዘግቧል። ባለፈው ሳምንት በምዕራብ ሸዋ፣ በምዕራብ ወለጋ፣ በቄለም ወለጋ፣ በጉጂ፣ በምስራቅ ወለጋ እና በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና በኦነሠ/ኦነግ–ሸኔ መካከል ተጨማሪ ውጊያዎች መደረጋቸው ታውቋል።
የፖሊስ እና የፋኖ ታጣቂዎች ውጊያ በአዲስ አበባ
ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ጥቃት ሚያዚያ 4 ቀን በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ በሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ የአዲስ አበባ እና የፌዴራል ፖሊስ ኃይሎች ከሶስት ፋኖ ታጣቂች ጋር ተዋግተዋል። የፋኖ ታጣቂችን ለማስመለጥ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በፋኖ ታጣቂች በጥይት ተመተው የተገደሉ የታክሲ ሹፌር እና ሁለት የፋኖ ታጣቂችን ጨምሮ የሶስት ሰዎች ህይወት አልፏል።7አዲስ አበባ ፖሊስ፣ ‘በፅንፈኛው የፋኖ አመራርና አባላት ላይ እርምጃ ተወሰደ፡፡ የፅንፈኛው አመራርና አንድ የቡድኑ አባል ሲገደሉ አንደኛው በቁጥጥር ስር ውሏል፣’ ሚያዚያ 4, 2016 የፋኖ ተወካዮች ሚያዚያ 5 ቀን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጥቃቱ የአገዢ ኃይሉን የማጥቃት ስትራቴጂ አንዱ አካል መሆኑን አረጋግጠዋል። ከበርካታ ግንባሮች የተውጣጡ የፋኖ ተወካዮች ባደረጉት ገለጻ በአዲስ አበባ የተካሄደው ዘመቻ የጋራ ተግባር መሆኑን ገልጸው በከተሞች የአገዢ ኃይሉ ላይ ጥቃት ለማድረግ የታቀደ የረጅም ጊዜ ስትራቴጂ አካል መሆኑን እና በአዲስ አበባ እና በሌሎች ከተሞች ተጨማሪ ኢላማዎችን ለመምታት መዘጋጀቱን ገልጸዋል።8በግል የግብዣ ብድህረ መረብ የመስመር ላይ የተላለፈ አጭር መግለጫን ተከትሎ በሚያዚያ 5 ቀን 2016 የአክሌድ ተመራማሪ ከፋኖ ተወካዮች ጋር ያደረጉት የደብዳቤ ልውውጥ የአዲስ አበባ ፖሊስ የተኩሱ የተከፈተው በከተማዋ ላይ ጥቃት ለማድረስ አቅደዋል ያላቸውን ተጠርጣሪዎች የፀጥታ ኃይሎች ለመያዝ ሙከራ ባደረጉበት ወቅት መሆኑን አስታውቋል።9አዲስ አበባ ፖሊስ፣ ‘በፅንፈኛው የፋኖ አመራርና አባላት ላይ እርምጃ ተወሰደ፡፡ የፅንፈኛው አመራርና አንድ የቡድኑ አባል ሲገደሉ አንደኛው በቁጥጥር ስር ውሏል፣’ ሚያዚያ 4, 2016
በኢትዮጵያ ዋና ከተማ ውስጥ በአማጺ ቡድኖች የሚደረግ ጥቃት ያልተለመደ ነው። ባለፈው ሳምንት የተከሰተው ውጊያ ለፋኖ ታጣቂዎች ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ ክስተት ቢሆንም ወደ ፊት በአዲስ አበባ የሚኖሩ የንቅናቄውን አላማ በሚያራምዱ ሰዎች ሊደገም የሚችል ነው። በመዲናዋ የባለቤትነት ጉዳይ ላይ የሚነሱ ጥያቂዎች ጽንፍ ረገጥ ሲሆኑ አሁን ያለው አስተዳደር ውስጥ ያለውን የኦሮሞ የበላይነት በሚቃወሙ በአማራ ብሔርተኛ እና በፋኖዎች ይህ ነጥብ ይነሳል። የባልደራስ ፓርቲ መስራች እና በኋላም የአማራ ህዝባዊ ግንባር — አሁን የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ኃይል እየተባለ የሚጠራው — እስክንድር ነጋ ከተማዋን ለቆ በአማራ ክልል ፀረ–መንግስት ታጣቂ ቡድን ከመስራቱ በፊት በአዲስ አበባ ዋና ተቃዋሚ ነበር።
ኢትዮጵያ በጨረፍታ
ከመጋቢት 28–ሚያዚያ 4, 2016
ይህ መረጃ/ዳታ ከመጋቢት 28 እስከ ሚያዚያ 4, 2016 ያለውን ጊዜ ይሸፍናል። አክሌድ መረጃን እንዴት እንደሚሰበስብ እና ኩነቶችን እንዴት እንደሚመድብ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የአክሌድን የኮድ መጽሐፍን ይመልከቱ። በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንዳንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በሚቀጥሉት ሳምንታት ዳታ ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
የኩነት አይነቶች
ውጊያዎች: 21 ኩነቶች
ፍንዳታዎች/ የርቀት ግጭት: 1 ኩነት
ሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሱ ጥቃቶች: 13 ኩነቶች
የአመፅ ግጭት: 0 ኩነት
ሰልፎች: 4 ኩነቶች
ግጭት ያለበት የተቃውሞ ሰልፍ: 0 ኩነት