የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የሚደረጉ ውጊያዎች ሲቀጥሉ በአፋር እና በሶማሊ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ዳግም ግጭት ተቀስቅሷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች መጪውን የምርጫ እንቅስቃሴ አስታውቋል።
በአማራ እና በኦሮሚያ የቀጠለው ውጊያ
በአማራ ክልል በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና ፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ የቀጠለ ሲሆን ይህም በክልሉ መጨረሻ የሌለው ግጭት ከጀመረ አንድ አመት መሙላቱን አመላክቷል። ባለፈው ሳምንት በምስራቅ ጎጃም፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜን ጎንደር እና ደቡብ ወሎ ዞኖች በእነዚህ ወገኖች መካከል ውጊያ መደረጉ ተዘግቧል። በምስራቅ ጎጃም በጎንቻ ሲሶ እንበሴ ወረዳ ባርጃኖ ቀበሌ ከፍተኛ ውጊያ መደረጉን እና የመንግስት ወታደሮች 20 የፋኖ ታጣቂዎችን መግደላቸውን የመንግስት ምንጮች ዘግበዋል።1የኢትዮጵያ ፌዴራል ዲሞክራቲክ ሪፕብሊክ መከላከያ ሠራዊት፣ ‘የምስራቅ ጎጃም ዞን ኮማንድፖስት በጽንፈኛው ከሰርጉ ላይ የታፈነ ሙሽራን አስለቀቀ፣’ ሚያዚያ 16, 2016
እንደ አማራ ክልል ሁሉ በኦሮሚያ ክልልም የሚደረጉ ውጊያዎች ያልተቋረጡ ሲሆን በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት — በመንግስት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር–ሸኔ እየተባለ የሚጠራው — እና በመንግስት ወታደሮች መካከል ጦርነት በአርሲ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ እና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች ተካሂዷል። በምስራቅ ወለጋ ዞን በባኮ ጥቤ ወረዳ እና ጉቶ ጊዳ ወረዳ በሁለቱ ወገኖች መካከል ከፍተኛ ውጊያ መደረጉ ተነግሯል።2የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ፣ ‘ኦኤልኤ/ኦነግ-ሸኔ ቡድን በአሸባሪነት ተግባራቱ በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ስለሌለው እና ወታደሮቹን ለማንቀሳቀስ አስቸጋሪ በመሆኑ እጅ እየሰጠ ነው፣’ ሚያዚያ 18, 2016፤ የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ አፋን ኦሮሞ፣ ‘ጉቶ ጋዳፊ እና ወዩ ቱካ የተደረገ የህግ ማስከበር ዘመቻ፣’ ሚያዚያ 17, 2016
በአፋር እና ሶማሊ ድንበር አካባቢ ዳግም የተቀሰቀሰው ውጊያ
በሶማሊ–አፋር አዋሳኝ አካባቢዎች በመንግስት እና በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የተመራ የሰላም ሂደት እየተካሄደ ባለበት ወቅት በሶማሊ–አፋር አዋሳኝ የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው አካባቢዎች ዳግም ውጊያ ተቀስቅሷል። ሚያዚያ 4 እና 5 በአፋር ክልል ገዋኔ እና ገላሉ ወረዳዎች እንዲሁም በሶማሊ ክልል በሲቲ ዞን ጋራኒ እና መዳኒ ከተሞች በአፋር እና በሶማሌ ብሔረሰብ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ መካሄዱ ታውቋል። ውጊያው የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው አካባቢዎች ከየካቲት ወር ጀምሮ በመካሄድ ላይ የነበረውን የሰላም ድርድር ያቋረጠ ነበር።3አዲስ ማለዳ፣ ‘በአፋርና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የሚገጥሙ ችግሮችን ለመፍታት የእርቅ ኮሚቴ ተቋቋመ፣’ የካቲት 30, 2016፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ፣ ‘ኢትዮጵያ – ሁኔታ ሪፖርት፣ ሚያዝያ 19, 2026፣’ ሚያዝያ 19, 2026 ግጭቱን ተከትሎ ሚያዝያ 10 ቀን የተኩስ አቁም ስምምነት የተደረሰ ሲሆን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሶማሊ እና የአፋር ክልሎች መንግስታት የተኩስ አቁምን በማፅናት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቋል።4አዲስ ማለዳ፣ ‘ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ የዘለቀው የአፋር እና ኢሳ ጎሳዎች ግጭትን ለመቋጨት የተኩስ አቁም ስምምነት ተደረገ፣’ ሚያዝያ 11, 2016፤ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ ‘የአፋር እና የሶማሊ ክልላዊ መንግሥታት ለሰላም ስምምነቱ ዘላቂነት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ፣’ ሚያዝያ 12, 2016
መጪ የምርጫ እንቅስቃሴዎች
ሚያዚያ 18 ቀን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 9 ቀን በአፋር፣ በቤንሻንጉል/ጉሙዝ፣ በሶማሊ እና በመካከለኛው ኢትዮጵያ ክልሎች አንዳንድ አካባቢዎች ድምጽ እንደሚሰጥ አስታውቋል። እንደ የምርጫ ወረቀቶች ህትመት ጋር በተያያዙ እና የፀጥታ ችግር በመሳሰሉ እንዳንድ ሁኔታዎች ምክንያቶች በ2013 በተካሄደው ስድስተኛው አጠቃላይ ምርጫ በእነዚህ ክልሎች ውስጥ ባሉ በርካታ የምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ ምርጫ ተሰርዟል።5ነጋሳ ደሳለኝ፣ ሸዋዬ ለገሠ እና አዜብ ታደሰ፣ ‘ምርጫ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣’ ሚያዝያ 18, 2016 በእነዚህ ጉዳዮች ምክንያት በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ምርጫ አልተካሄደም። ስለሆነም በክልሉ ምርጫ በመዘግየቱ ምክንያት እስከ አሁን በ2007 ዓ.ም በተመረጠ የክልል መንግስት እየተመራ ቆይቷል። በእዚህ ክልል በመጪው ምርጫ ስምንት ፓርቲዎች ይወዳደራሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ከነዚህም መካከል የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ፣ የጉሙዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉህዴን)፣ ቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ፣ እናት ፓርቲ እና ገዥው ፓርቲ ብልፅግና ፓርቲ ይገኙበታል።6ነጋሳ ደሳለኝ፣ ሸዋዬ ለገሠ እና አዜብ ታደሰ፣ ‘ምርጫ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣’ ሚያዝያ 18, 2016
በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል በክልሉ መንግስት እና በጉህዴን መካከል የሰላም ስምምነት ከተፈረመበት ከመስከረም 2015 ጀምሮ በክልሉ የነበረው ግጭት በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል። በታህሳስ 2015 መንግስት እና የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄም ስምምነት ተፈራርመዋል።7አዲስ ስታንዳርድ፣ ‘ዜና፡- የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሁለተኛው አማፂ ቡድን ጋር የሰላም ስምምነት ተፈራረመ፣ ስምምነቱ የተፈረመው በሱዳን ነው፣ ታህሳስ 3, 2015 የ2013ቱ ምርጫ በመላ አገሪቱ በነበረ ከፍተኛ ግጭት ወቅት የተደረገ ቢሆንም የምርጫ ጣቢያዎችን፣ መራጮችን ወይም የምርጫ ባለስልጣናትን ያነጣጠረ ጥቃት አነስተኛ ነበር። በቀሪ ምርጫ ጣቢያዎች የሚካሄደው መጪው ምርጫ ግጭት ያስነሳል ተብሎ አይጠበቅም።
ኢትዮጵያ በጨረፍታ
ሚያዚያ12-18, 2016
ይህ መረጃ/ዳታ ከሚያዚያ 12 እሰከ 18, 2016 ያለውን ጊዜ ይሸፍናል። አክሌድ መረጃን እንዴት እንደሚሰበስብ እና ኩነቶችን እንዴት እንደሚመድብ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የአክሌድን የኮድ መጽሐፍን ይመልከቱ። በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንዳንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በሚቀጥሉት ሳምንታት ዳታ ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
የኩነት አይነቶች
ውጊያዎች: 23 ኩነቶች
ፍንዳታዎች/ የርቀት ግጭት: 1 ኩነት
ሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሱ ጥቃቶች: 6 ኩነቶች
የአመፅ ግጭት: 0 ኩነት
ሰልፎች: 0 ኩነት
ግጭት ያለበት የተቃውሞ ሰልፍ: 0 ኩነት