የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
በአማራ ክልል ያለው ግጭት መባባሱን ተከትሎ አንድ የሰብአዊ እርዳታ ሠራተኛ እና አንድ ስደተኛ የተገደሉ ሲሆን እምብዛም ባልተለመደ ክስተት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለአንድ የውጭ ዜጋ ሞት ምክንያት ሆኗል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በትግራይ እና አፋር አዋሳኝ አካካቢ ላይ ጥቃቶች መፈፀማቸው ተዘግቧል።
ውጊያዎች በአማራ ክልል እንደገና ተባብሰዋል
ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የሚደረጉ ውጊያዎች የተባባሱ ሲሆን በምዕራብ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊ እና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች ውስጥ ውጊያዎች መደረጋቸው ተዘግበዋል። በአማራ ክልል ያለው ውጊያ ካለፉት የግንቦት ወር ሳምንታት ጋር ሲነፃፀር የባለፈው ሳምንት በእጥፍ ጨምሯል። ከውጊያ መጨመር ባሻገር ግንቦት 16 ቀን በጎንደር እና በመተማ ከተሞችመካከል ማንነታቸው ባልተገለፀ መሳሪያ በታጠቁ ሰዎች የሰብዓዊ እርዳታ ሰራተኞች ቡድን መኪና ላይ በተፈፀመ ጥቃት አንድ የሰብዓዊ እርዳታ ሰራተኛ በተተኮሰው ጥይት የተገደለ ሲሆን ሌሎች በርካታ የቡድኑ አባላት ቆስለዋል።1በውስጥ ፀሃፊ፣ ‘በኢትዯጵያ የእርዳታ ሠራተኛ ግድያ ምርመራ እንዲጀመር የሚደረጉ ጥሪዎች እንዲበራከቱ ምክንያት ሆኗል፣’ የኢስት አፍሪካ ሪቪው፣ ግንቦት 20, 2016 የጎንደር አካባቢ የፋኖ ተወካይ ጥቃቱ የተፈፀመበት አካባቢን የሚቆጣጠሩ የመንግሥት ኃይሎች መሆናቸውን በመጥቀስ ለጥቃቱ የመንግሥት ኃይሎችን ተጠያቂ አድርገዋል።2የአማራ ማህበር በአሜሪካ፣ ‘በጎንደር የአማራ ፋኖ በጎንደር የተፀመ አሳዛኝ የእርዳታ ሠራተኛ ግድያ ላይ የተሰጠ መግለጫ፣’ ግንቦት 18, 2016
የተመዘገቡ ውጊያዎች መጨመራቸው እንዳለ ሆነው የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ግንቦት 17 ቀን መንግሥት ከስምንት ወረዳዎች በስተቀር በአማራ ክልል በሚገኙ በ266 ወረዳዎች አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታውቀዋል።3አዲስ ስታንዳርድ፣ ‘በአማራ ክልል ከስምንት ወረዳዎች በስተቀር የመንግሥት አገልግሎት ጀመረናል አረጋ ከበደ፣ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት፣’ ግንቦት 17, 2016 በተለይም በሰሜን ወሎ ዞን የቱሪስት እና የባህል ከተማ በሆነችው በላሊበላ ከተማ እንደገና ግጭት አገርሽቷል። በጥቅምት 2016 መጨረሻ አካባቢ ከተማዋ ለአጭር ጊዜ በፋኖ ቁጥጥር ስር የገባች ሲሆን ይኽውም በታሪካዊ አብያተ ክርስትያናት አካባቢ ከባድ መሳሪያዎች እንዲተኮሱ ምክንያት ሆኗል። የትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት ነሐሴ 2013 የላሊበላ ከተማን የተቆጣጠረ ሲሆን ይኽውም በጦርነቱ ወቅት በሆቴሎች እና በአየር ማረፍያ ላይ ጉዳት እንዲደርስ ምክንያት ሆኗል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አሁንም በአማራ ክልል ከሰደተኞች ጋር የተያያዙ ጉዳዮች አሳሳቢ ሆነው ቀጥለዋል። ግንቦት 10 ቀን ማንነታቸው ያልተገለፀ መሳሪያ የታጠቁ ሰዎች አንድ የኤርትራ ስደተኛን ከአንድ ቀን በፊት ከአለምዋጭ የስደተኞች ካምፕ ጠልፈው ከወሰዱት በኃላ በሰሜን ጎንደር በዳባት ወረዳ ጭላ በተባለ ቦታ ተኩሰው ገድለዋል። በከፊል ከፋኖ ፀረ መንግስት እንቅስቃሴ ጋር የተያያዘው በአማራ ክልል የሚገኘው የደህንነት ችግር ባለፉት ጥቂት ወራት እየከፋ የመጣ ሲሆን ይኽውም ብዙ ሰዎችን አፍኖ የመውሰድ ክሰተቶች እንዲባባሱ ምክንያት ሆኗል። ሚያዝያ 23 ቀን በምዕራብ ጎንደር በሺዎች የሚቆጠሩ የሱዳን ስደተኞች ከአቅማቸው በላይ የሆነ የደህንነት ችግር የገጠማቸው መሆኑን በመጥቀስ ተቃውሞ በማሰማት የስደተኛ ካምፕ ለቀው ወጥተዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ በተፈጠረ የፀጥታ ችግር ምክንያት ከተገደሉት መካከል የእስፔን ዜጋ የሆነ ቱሪስት ይገኝበታል
ግንቦት 12 ቀን የሙርሲ ብሔር ታጣቂዎች መሆናቸው የተጠረጠሩ ታጣቂዎች ከአሪ ብሔር ታጣቂዎች ጋር ተዋግተዋል። በሁለቱ ወገኖች መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ሶሰት ኢትዮጵያዊያን እና አንድ የእስፔን ዜጋ ፎቶ አንሺ ተገድለዋል።4 አብዱሊ ሰይ፣ ‘ በኢትዮጵያ እስፔናዊ ቱሪስትን ጨምሮ አራት ሰዎች በተኩስ ልውውጥ ውስጥ ተገደሉ፣’ ኤፒኤ፣ ግንቦት 18, 2016 የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጣልቃ በመግባት በክስተቱ የተሳተፉ ብዙ ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል።
በኢትዮጵያ ቱሪስቶችን ያካተቱ የፀጥታ ችግሮች በጣም ውስን ናቸው። ይሁንና በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ወደ ሀገሪቷ የሚደረጉ ጉብኝቶች በከፍተኛ ደረጃ የቀነሱ ሲሆን ገና መልሶ አላንሰራሩም። በጦርነቱ ወቅት በትግራይ ክልል ቁልፍ የጎብኚዎች መዳረሻ የሆኑ ተዘግተው የቆዩ አንዳንድ ቦታዎች በታኅሣሥ ወር ውስጥ በመንግሥት ተነሳሽነት እንደገና ተከፍተዋል።5ፋና ብሮድካስቲንግ, ‘ቢሮው በትግራይ የቱሪዝም ዘርፉን መልሶ በመክፈት ላይ እየሰራ ይገኛል፣’ ታኅሣሥ 19, 2016 መንግሥታዊው የኢንቨስትመንት ኮሚሽን በቅርቡ ቱሪዝምን ለውጪ አልሚዎች አዋጭ ከሆኑ ዘርፎች መካከል አንዱ አድርጎ የለየ ቢሆንም6ፋና ብሮድካስቲንግ, ‘ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ በጣም አዋጭ የሆነ የኢንቨስትመንት እድሎችን አቀረበች ፣’ ሚያዝያ 29, 2016 በኦሮሚያ እና በአማራ እንዲሁም በአንዳንድ ደቡባዊ የሀገሪቷ ክፍል አካባቢዎች ያለው የፀጥታ ችግር ለዘርፉ እድገት ማነቆ ሆኖ ቀጥሏል።
በትግራይ ክልል የአርብቶ አደሮች ግድያ
በትግራይ ክልል ግንቦት 13 ቀን ማንነታቸው ያልተገለፀ ታጣቂ ቡድን ከአፋር ወደ ራያ አዘቦ ወረዳ በመሻገር ከብት የሚጠብቁ እረኞች ላይ በፈፀመው ጥቃት ቢያንስ ሰባት ሰዎች ተገድለዋል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የአፋር ክልል መንግሥት እና የፌዴራል ፖሊስ ጥቃት ፈፃሚዎችን ተከታትለው በመያዝ ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነትን እንዲያረጋግጡ ጥሪ አቅርቧል።7የትግራይ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ፣ ‘ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ፣’ ግንቦት 13, 2016
ራያ አዘቦ ወረዳ ከራያ አለማጣ ወረዳ በሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ የሚገኝ ሲሆን በታኅሣሥ ወር በአማራ እና በትግራይ ታጣቂዎች መካከል ከባድ ውጊያ የተተደረገበት ስፈራ ነው። በኢትዮጵያ አርብቶ አደሮችን ያሳተፈ ከወሰን ጋር የተያያዙ ውጊያዎች የተለመዱ ሲሆን ብዙ ጊዜ ግን ካለው አጠቃላይ የፖለቲካ ውጥረት ጋር ተያይዘው የሚባባሱ ናቸው። አክሌድ ከግንቦት 16, 2015 ጀምሮ 16 አርብቶ አደሮችን ያሳተፉ ክስተቶችን መዝግቧል።
ኢትዮጵያ በጨረፍታ
ግንቦት 10-16, 2016
ይህ መረጃ/ዳታ ከግንቦት 10 እስከ 16, 2016 ያለውን ጊዜ ይሸፍናል። አክሌድ መረጃን እንዴት እንደሚሰበስብ እና ኩነቶችን እንዴት እንደሚመድብ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የአክሌድን የኮድ መጽሐፍን ይመልከቱ። በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንዳንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በሚቀጥሉት ሳምንታት ዳታ ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
የኩነት አይነቶች
ውጊያዎች: 43 ኩነቶች
ፍንዳታዎች/ የርቀት ግጭት: 1 ኩነት
ሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሱ ጥቃቶች: 8 ኩነቶች
የአመፅ ግጭት: 0 ኩነት
ሰልፎች: 1 ኩነት
ግጭት ያለበት የተቃውሞ ሰልፍ: 1 ኩነት