አክሌድ ታዋቂ የአማፂ ቡድን ሃላፊዎች፣ የታጣቂ ቡድን አባል፣ የፖለቲካ ሰው፣ ወይም የማህበረሰብ አንቂ/እንቅስቃሴ መሪን ሲያካትቱ፣ ወይም እስራቱ በፖለቲካ ግጭት አሊያም የሰልፎች አዝማሚያዎች ላይ ተጽእኖ ሊኖረው የሚችል ከሆነ እስራቶችን ይመዘግባል። በአንድ ቦታ እና ጊዜ ከ25 በላይ ሰዎች የሚያዙበት የጅምላ እስራት እንዲሁም 100 እና ከዚያ በላይ ሰዎች ለረጅም ጊዜ በቁጥጥር ስር የሚቆዩባቸው ኩነቶችም ይመዘገባሉ። ይህ ክፍል በኢትዮጵያ ውስጥ ስለተፈጸሙ የእስር እና የጅምላ እስራቶች የያዙ ዘገባዎች ያካትታል።