ኢፒኦ ሳምንታዊ፡ 19-25 መስከረም 2016
…
Read more
በኢትዮጵያ የሚገኙ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎች ብዙ ጊዜ በተለያዩ ቡድኖች የተለያዩ አይነት አደጋዎች ይጋረጡባቸዋል። በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎችን ኢላማ የሚያደርጉ ጥቃቶች አብዛኛውን ጊዜ ሁለት አይነት ናቸው። በአንድ በኩል በኢትዮጵያ የሚገኙ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎች የፖለቲካ ቡድንን ይደግፋሉ (ወይም አይደግፉም) ተብለው ከተከሰሱ በኋላ ብዙ ጊዜ የጥቃት ኢላማ ይደረጋሉ። ይህ በተለይ መንግስትም ሆነ ፀረ-መንግስት ሃይሎች በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ባልሆኑ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጫና በሚፈጥሩባቸው የጦርነት ቀጠናዎች ባሉባቸው እንደ ትግራይ ወይም ኦሮሚያ ባሉ ክልሎች የተለመደ ነው። ሁለተኛ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎች በአብዛኛው በብሄር ላይ የተመሰረቱ እና ለማፈናቀል በማሰብ የሚደረጉ ጥቃቶች ሰለባዎች ናቸው። ይህ ክፍል በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ባልሆኑ ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን የሚያካትቱ ዘገባዎችን ይዟል።