ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከሰኔ 25 እስከ ሐምሌ 1, 2014
…
Read more
ኦሮሚያ በሃገሪቷ ከሚገኙ ክልሎች ትልቁ ሲሆን በቁጥር ከፍተኛ የሆነውን የኦሮሞ ብሄረሰብም ያቀፈ ነው። ክልሉ አለም አቀፍ ድንበር ከኬንያ እንዲሁም የውስጥ ድንበሮች ከስድስት ክልሎች እና ከድሬዳዋ መስተዳድር ጋር ይጋራል። በተጨማሪም አዲስ አበባ ከተማ እና ሀረሪ ክልል በኦሮሚያ ክልል ተከበው ይገኛሉ። ክልሉ ለብዙ አመታት ፀረ-መንግስት ተቃውሞዎች እና አመጾች ሲካሄዱበት ቆይቷል። ከ2006 እስከ 2010 ባሉት አመታት በክልሉ የተካሄዱ ህዝባዊ ሰልፎች የወቅቱን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ወደ ስልጣን እንዲመጡ ትልቅ አስተዋፆ አድርገዋል። ከ2010 ጀምሮ በክልሉ ውስጥ ዘርን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች እና ውጊያዎችን ጨምሮ የተለያዩ የፖለቲካ ግጭቶች ተመዝግበዋል። ይህ ክፍል በዚህ ክልል ላይ የተሰሩ ዘገባዎችን ያካትታል።