ከሚያዚያ 23 እስከ ግንቦት 23, 2013 በጨረፍታ
ዋና ቁጥሮች
-
- አክሌድ 48 ኩነቶች እና 429 ሟቾች መዝግቧል።
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት በተከሰቱ ግጭቶች ከሞቱ ግለሰቦች ውስጥ ትልቁ የሟቾች ቁጥር የተመዘገበው በትግራይ ክልል ሲሆን ይህም 345 ነበር። ኦሮሚያ ክልል በ40 የሟቾች ቁጥር ይከተላል።
- በተደጋጋሚ የተከሰተው የኩነት አይነት በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ባልሆኑ ሰዎች ላይ የሚደርስ ጥቃት ነበር፤ 21 የኩነቶች እና 52 የሟቾች ቁጥር ተዘግቧል። በተለያዩ የሀገሪቷ አካባቢዎች 12 ሰልፎች ነበሩ። 11 የውጊያ ኩነቶች 370 ሰዎችን ለሞት ዳርጋዋል። ከጠቅላላው 370 የሟቾች ቁጥር ውስጥ 323 በትግራይ የተካሄዱ አራት ውጊያዎች የሞቱ ናቸው።
ዋና ሂደቶች
- በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች በታጠቁ ቡድኖች መካከል የሚደረጉ ውጊያዎች ጨምረዋል። በአማራ ክልል በጎንደር አቅራቢያ በሚገኙ አካባቢዎች በቅማንት ብሄርተኛ ቡድኖች እና በአማራ ክልል ኃይሎች መካከል ተደጋጋሚ ውጊያዎች ተደርገዋል። በኦሮሚያ ክልል በጉጂ እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች በኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ እና በክልሉ የፀጥታ ኃይሎች መካከል የሚደረጉ ውጊያዎች ጨምረዋል።
- ካለፉት ወራት ጋር ሲነፃፀር በዚህ ወር ከመንግስት ጋር ግንኙነት ያላቸው ግለሰቦች ግድያ ጨምሯል፤ አብዛኛዎቹ ግድያዎች የሚፈፀሙት በኦነግ-ሸኔ ነው
- በመላው አገሪቱ በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ በመቃወም ሰልፎች ተካሂደዋል።
በዚህ ሪፖርት ውስጥ
- ከሚያዚያ 23 እስከ ግንቦት 23,2013 (ሚያዚያ/ግንቦት) የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
- ወርሀዊ ትኩረት: ከምርጫ ጋር የተያያዙ ክርክሮች እና ግጭቶች
የሚያዚያ/ግንቦት ሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ (ህውሃት) እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ሽብርተኛ ድርጅቶች ተብለው እንዲፈረጁ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚያዚያ ወር መጨረሻ ላይ አፅድቋል። መንግስት ይህ ስያሜ መንግስት የሁለቱን ቡድኖች ድርጊቶች በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት እንዲከላከል እና እንዲያስቆም ያስችለዋል ብሏል (የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፣, ሚያዚያ 23, 2013)። ከዚህ ውሳኔ በኻላ በኋላ ኦነግ-ሸኔ (የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በመባልም ይታወቃል) “ሕገወጡን ቡድን ከስልጣን ለማስወገድ ጦርነት ውስጥ እንደሚገባ” አስታውቋል (የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ እዝ መግለጫ፣ ሚያዚያ 27, 2013)። ይህንን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ጉጂ፣ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች ውስጥ በኦነግ-ሸኔ እና የክልሉ የፀጥታ ኃይሎች መካከል ውጊያዎች የተደረጉ ሲሆን ቡድኑ በሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች ግጭት ጨምሯል። እነዚህ ውጊያዎች የተካሄዱባቸው ቦታዎች ገጠራማ መሆናቸው እና መረጃ የማግኝት እድል አነስተኛ መሆኑ የሟቾችን ቁጥር መገመት አስቸጋሪ ያደርገዋል።
በሚያዚያ/ግንቦት በኦሮሚያ ክልል የኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች በአንድ ጥቃት አራት ከመንግስት ጋር ግንኙነት ያላቸውን ባለስልጣናት ከነሹፌራቸው እና በሌላ ጥቃት ደግሞ ስምንት የፀጥታ ኃይሎችን ገድለዋል። በተጨማሪም በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በአቤ ዶንጎሮ ወረዳ ውስጥ የኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች እንደሆኑ የተጠረጠሩ ታጣቂዎች ሶስት በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ አማራዎችን ገድለዋል (ኢሳት፣ ግንቦት 11, 2013)
በአማራ ክልልም ውጊያዎች ተካሂደዋል። ግንቦት 15 እና 17, 2013 ላይ የሱዳን እና የኢትዮጵያ ታጣቂዎች በቱመንት መንዶቃ ቀበሌ የባለሀብቶችን ንብረት አጥቅተዋል (ቪኦኤ አማርኛ፣ ግንቦት 17, 2013; ዲደብሊው አማርኛ፣ ግንቦት 19, 2013)። በዲደብሊው ኣማርኛ ቃለመጠይቅ የተደረገላቸው ምስክር (ግንቦት 19, 2013) የሱዳን ታጣቂዎች በጉሙዝ ህዝቦች ነፃ አውጪ ንቅናቄ፣ ህዝበ ወያነ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት)፣ ቅማንት ብሄርተኛ ቡድን፣ እና የሳምሪ ወጣት ታጣቂዎች ይደገፋሉ ብለዋል። ግንቦት 18 እና 19, 2013 የአማራ ክልል ኃይሎች ባልታወቁ ታጣቂዎች በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ ውስጥ በሚገኙት የቁስቋም፣ በላጅግ ዳብሬካ፣ እና አዘዞ ሳይድ ሰፈሮች ውስጥ የደረሰውን ጥቃት በተሳካ ሁኔታ ተከላክለዋል (ዲደብሊው አማርኛ፣ ግንቦት 20, 2013)።
ባለፉት ጥቂት ወራት የጨመሩ ግጭቶች እና በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ አማራዎችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶች የክልሉ አመራሮች ላይ ጫና እያሳሩረ ነው። ሚያዚያ መጨረሻ ላይ የአማራ ክልል መንግስት ባለስልጣናት በክልሉ ውስጥ ለሚገኙ ተፈናቃዮች በቂ የሰብአዊ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል (የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ሚያዚያ 27, 2013፤ ኢቢሲ፣ ሚያዚያ 28, 2013፤ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ግንቦት 10, 2013፤ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ግንቦት 14, 2013)። በአማራ ክልላዊ መንግስት መረጃ መሠረት በአጣዬ እና አከባቢው የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ 246,818 ሰዎች ተፈናቅለዋል (የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ግንቦት 16, 2013; ኢፒኦ ሳምንታዊ:- ከሚያዚያ 2 2013 እስከ ሚያዚያ 8 2013 ይመልከቱ)። የአማራ ክልል መንግስት ከቤንሻንጉል/ጉሙዝ፣ ኦሮሚያ፣ እና ከደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልሎች የተፈናቀሉ ዜጎችን ጨምሮ 565,000 ተፈናቃዮችን እያስተናገደ መሆኑን ገልጿል (የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ግንቦት 10, 2013)።
በቤንሻንጉል/ጉሙዝ በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ተወካዮች እና በክልሉ የዳግም ውህደት ስልጠና በሚወስዱት የጉሙዝ ህዝቦች ዴሞክራሲ ንቅናቄ አባላት መካከል ስምምነት ተፈርሟል (ቢቢሲ አማርኛ፣ ግንቦት 11, 2013)። ምንም እንኳን እነዚህ ጥረቶች ቢኖሩም የጉሙዝ ህዝቦች ነፃ አውጪ ንቅናቄ እና ሌሎች የታጠቁ ኃይሎች ማድረስ በቀጠሉት ጥቃት ምክንያት ክልሉ አሁንም አልተረጋጋም (ኢሳት፣ 10 ግንቦት, 2021)። በክልሉ ውስጥ ባሉ አብዛኛዎቹ ዞኖች ውስጥ የድምፅ መስጫ ቀናት በፀጥታ ጉዳዮች ምክንያት እንዲዘገዩ ተደርገዋል (የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ግንቦት 24, 2013)።
በተጨማሪም ግንቦት 14, 2013 ላይ የጉሙዝ ህዝቦች የነፃነት ንቅናቄ አባላት እንደሆኑ የተጠረጠሩ ቤንሻንጉል/ጉሙዝ እና ኦሮሚያ ክልሎች መካከል ያለውን ድንበር በማቋረጥ ነጆ ወረዳ (ኦሮሚያ ክልል) ያምቤልጋራ ኦሊ ቀበሌ ውስጥ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል። ታጣቂ ቡድኑ ስድስት ሰዎችን ገድሏል፣ አንድ ሰው አቁቆስሏል፣ እንዲሁም ቤቶችን አቃጥሏል (ቪኦኤ አማርኛ፣ 16 ግንቦት 2013፣ ዲደብሊው አማርኛ፣ ግንቦት 17, 2013)።
በሶማሌ ክልል ግንቦት 12, 2013 ላይ የአፋር ታጣቂዎች ከሲቲ ዞን በስተምዕራብ ከቢርታ ድሂር መንደር እና ታራይኔ ላይ ጥቃት ካደረሱ በኋላ ከሶማሌ ታጣቂዎች ጋር ተዋግተዋል። ቢያንስ ስድስት ሰዎች ሲገደሉ 25 ሰዎች ቆስለዋል (ቮስ ቲቪ፣ ግንቦት 12, 2013)።
በሚያዚያ/ግንቦት የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ሁለት አካባቢዎች የፀጥታ ችግሮች አጋጥመዋቸዋል፡፡ ግንቦት 10, 2013 ላይ በቤንች ሸኮ ዞን በሸኮ ወረዳ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ዘጠኝ የፀጥታ ሀይሎችን ገድለው ሶስት አቁስለዋል። ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ ዞኑ ከፍተኛ የብሔር ግጭት የሚከሰተበት ቦታ ሆኗል (ቪኦኤ አማርኛ፣ ግንቦት 11, 2013) እየተባባሰ በመጣው ግጭት ምክንያት የቤንች ሸኮ ዞን አስተዳደር የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል እና የፌዴራል መንግስት ሰላምና ፀጥታን ለማስፈን ድጋፍ እንዲያደርጉ ግንቦት 16, 2013 ላይ ጠየቀ (የቤንች ሸኮ ዞን የመንግስት ኮምንኬሽን ጉዳዮች መምሪያ፣ ግንቦት 16, 2013; Sየደቡብ ሸኮ ወረዳ ኮምንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት፣ ግንቦት 18, 2013) በኦሮሚያ ክልል ከሚገኘው የምዕራብ ጉጂ ዞን ጋር አዋሳኝ የሆነው የአማሮ ልዩ ወረዳ በሚያዚያ/ግንቦት ሌላው ከፍተኛ ግጭት የተከሰተበት ስፍራ ነበር፡፡ ግንቦት, 4 2013 ላይ የደረሰ ጥዋት 3 በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎችን ሲገድል፣ 2 አቁስሎ፣ ከ6000 በላይ አፈናቅሏል (ዲደብሊው አማርኛ፣ ግንቦት 6, 2013)። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ በአካባቢው ባለው ከፍተኛ አለመረጋጋት ምክንያት የሰብአዊ እርዳታ ስራው የተገደበ ነው ብሏል (ሪሊፍዌብ፣ ሚያዚያ 22, 2013)።
በተመሳሳይም በማዕከላዊ፣ በሰሜን ምዕራባዊ፣ ምስራቃዊ፣ ደቡብ ምስራቃዊ፣ እና ደቡባዊ ትግራይ አሁንም የቀጠሉ ውጊያዎች የተራእዶ ድርጅቶች የተከሰቱ ግጭቶች በገጠራማው ትግራይ የሚገኙ እና እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ጋር እንዳይደርሱ እያደረጋቸው እንደሚገኝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ ዘግቧል (የተመድ የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ፣ ሚያዚያ 29, 2013; የተመድ የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ፣ ግንቦት 12, 2013; የተመድ የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ፣ ግንቦት 18, 2013)። በተለይ በሀውዜን አቅራቢያ ባሉ አካባቢዎች ውጊያዎቹ በጣም ከባድ የነበሩ ሲሆን ይህ አካባቢ እስከ ሚያዚያ 29, 2013 ድረስ ለህወሃት ታማኝ በሆኑ ኃይሎች ቁጥጥር ነበር (ኤፒ፣ ግንቦት 27, 2013)። መንግስት ወታደራዊ አጃቢዎችን በማቅረብ ተደራሽነትን ለማሻሻል ጥረት ቢያደርግም አሁን ተደራሽ የሆኑት አካባቢዎች የትኞቹ እንደሆኑ ዝርዝር መረጃዎች ወዲያው ግልፅ አልነበሩም (የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት-ኢትዮጵያ፣ ሚያዚያ 30, 2013)። የህወሃት ሀይሎች መንግስት በክልሉ መንግስት ለማቋቋም የሚያደርገውን ጥረት ማደናቀፍ ቀጥለዋል። ግንቦት 20, 2013 ላይ የህወሃት ታጣቂዎች የአዲግራት ከተማ ጊዜያዊ ከንቲባን በጥይት የገደሉ ሲሆን በጥቃቱም በኋላም በደረሰበት ጉዳት ህይወቱን ያጣ የአለምአቀፍ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሰራተኛን መተዋል (የተመድ የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ፣ ግንቦት 26, 2013)። ግጭቱ ከጀመረ አንስቶ 22 የጊዜያዊ አስተዳደሩ መንግሥት አባላት ተገድለዋል (ኤፒ፣ ግንቦት 18, 2013)።
ሰብአዊ መብት ጥሰቶች ላይ ባለው ስጋት እና በትግራይ ክልል በሚያስፈልገው አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ ምክንያት የአሜሪካ መንግስት በአሁን እና የቀድሞ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የአማራ ክልል ሃይሎችን ጨምሮ በፀጥታ ኃይል አባላት፣ እና የህወሃት አባላት ላይ የቪዛ ገደቦችን ጥሏል፡፡ አሜሪካ በተጨማሪም ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የገንዘብ እና ደህንነት እርዳታአ ያቋረጠች ሲሆን ሌሎች መንግስታትም ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቃለች (የቃል አቀባይ ጽ/ቤት፣ ግንቦት 15, 2013)። የአሜሪካ መንግስት ተኩስ በፍጥነት እንዲቆም፣ የኤርትራ እና የአማራ ክልል ሃይሎች ከትግራይ ክልል እንዲወጡ፣ እና የኢትዮጵያ መንግስት ከህወሃት ጋር ውይይት እንዲያደርግ ጠይቋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የአሜሪካ ተወካዮች ለሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተጠያቂ የሆኑ ሁሉ ተጠያቂ የማድረግ ጥረት እንዲጨምር ጠይቀዋል (የቃል አቀባይ ጽ/ቤት፣ ግንቦት 15, 2013; በተጨማሪም S.Res.97፣ ግንቦት 11, 2013 ይመልከቱ)። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ባልሆኑ ግለሰቦች ግድያ ጋር በተያያዘ 28 ወታደሮች እንዲሁም በፆታዊ ወንጀል የተጠረጠሩ 25 ወታደሮች ላይ ክስ መመስረቱን አስታውቋል (የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣ ግንቦት 13, 2021)።
የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ የጣለውን ማዕቀብ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ በዋና ከተማዋ እና አሶሳ፣ ድሬዳዋ፣ ጋምቤላ፣ ሀረር፣ ሆሳአና፣ ስልጤ፣ እና ወላይታ-ሶዶ ከተሞች በርካታ ሰልፎች ተካሂደዋል (የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ግንቦት 13, 2013፤ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት፣ ግንቦት 22, 2013; ቢቢሲ አማርኛ፣ ግንቦት 22, 2013፤ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ግንቦት 22, 2013ሀ፤ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ግንቦት 22, 2013ለ)።
ወርሀዊ ትኩረት: ከምርጫ ጋር የተያያዙ ክርክሮች እና ግጭቶች
በሀገሪቷ ውስጥ በጣም ተለዋዋጭ ሁኔታ ባለበት በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ለሶስተኛ ግዜ መራዘሙ ግንቦት 7, 2013 ላይ ይፋ ተደርጏል (ሮውተርስ፣ ግንቦት 7, 2013)። በትግራይ ያለው ውጊያ ወደ ቀጣይነት ያለው አመፅ ተቀይሯል፤ በምዕራብ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ከአማፂ ቡድኖች ጋር የሚደረጉ ውጊያዎች ተጠናክረዋል፣ እንዲሁም ሞት የሚመዘገብባቸው ግጭቶች በሶማሌ እና አፋር ክልሎች መካከል ተቀስቅሷል። የአማራ እና የቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልሎች የሆኑ በርካታ አካባቢዎች በፌደራል ኮማንድ ፖስት ቁጥጥር ስር ያሉ ሲሆን በአብዛኛው ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች የሚፈፀሙ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ግድያዎች አሁንም በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ውስጥ በሚገኙ አካባቢዎች ቀጥለዋል። ብዙዎች ምርጫው እንደዚህ ያለ የደህንነት ችግር ባለበት ሁኔታ ውስጥ መደረጉ ተጨማሪ ግጭቶችን በመቀስቀስ ኢትዮጵያን ወደባሰ ስርአተ አልበኝነት ውስጥ የሚገፋ ነው ብለው ይሰጋሉ።
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በ37 የምርጫ ክልሎች ምርጫ እንደማይካሄድ አስታውቋል፡፡ ከ37ቱ የምርጫ ክልሎች ውስጥ በ26 ምርጫው የማይካሄደው በደህንነት ችግር ምክንያት ነው (የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ግንቦት 24, 2013፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ግንቦት 14, 2013፤ ከታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። ከ26ቱ የምርጫ ክልሎች 4 በቤንሻንጉል/ጉሙዝ የሚገኙ የምርጫ ክልሎች ሲሆኑ በአማራ ክልል 8፣ እንዲሁም በኦሮሚያ እና በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች በእያንዳንዳቸው 7 የምርጫ ክልሎች አሉ (የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ግንቦት 24, 2013; የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ግንቦት 14, 2013)። በትግራይ ክልል በየትኛውም ክፍል የድምጽ መስጠት ሂደት አይካሄድም (ኤፒ፣ ግንቦት 12, 2013)። ምርጫው ይካሄድባቸዋል በተባሉ አካባቢዎች ያሉ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሀላፊዎች በዚህ ሁኔታ ውስጥ መካሄዱን እርግጠኛ አለመሆናቸውን አመላክተዋል።1 በምዕራብ ኦሮሚያ ከምርጫ ቦርድ ሰራተኛ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ፣ ሚያዚያ 2013
ግጭቶች የምረጡኝ ዘመቻዎችን አደናቅፈዋል። በርካታ እጩዎችን ኢላማ ያደረጉ ግድያዎች ተዘግበዋል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) እጩዎች በቢሾፍቱ ከተማ (ኦሮሚያ) እና አጣዬ (አማራ) የተገደሉ ሲሆን የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) እጩዎች ደግሞ በመተማ (አማራ) እና መተከል (ቤኒሻንጉል/ጉሙዝ) በጥይት ተገድለዋል።
ታዲያ ኢትዮጵያ በእንደዚህ ዓይነት ሁከት ውስጥ ለምን ብሄራዊ ምርጫ ታደርጋለች? ድምጽ መስጠት በአንፃራዊነት ሰላማዊ በሆኑ የሀገሪቱ ክፍሎች ውስጥ ግጭት እንዲነሳ ያደርጋል? ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት በሀገሪቱ ከፍተኛ መሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ውሳኔዎች የተቀረፀውን አሁን ያለውን ሁኔታ እንመረምራለን ፡፡
አብይ አህመድ ወደ ስልጣን የመጡት በኢትዮጵያ የአመራር ስርአት ውስጥ የህዝበ ወያነ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት)ን ቦታ ለአስርት አመታት የጠበቀው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዲግ) የሀይል ማሽቆልቆል ባጋጠመው ወቅት ነበር። በከፍታቸው ጊዜ የተበላሸ የአስተዳደር ስርዓት እና በጥቂት ልሂቃን የሚደረገውን ማጭበርበር አጋልጠዋል፤ ይህንን ክፍተት ወደስልጣን ሲመጡ ቢወርሱትም። ከዚህ ወዲህ ዙሪያቸው ጠባብ ሆኖ በታማኝነት፣ ልውውጥ ግንኙነቶች፣ እና ችግር ጊዜ ምላሽ አሰጣጥ ላይ የተመሰረተ ነው።
ከትግራይ ክልል ህወሃትን በማፍረስ እና በኦሮሚያ እንደ ጃዋር መሃመድ እና ዳውድ ኢብሳ ያሉ አማራጭ የኦሮሞ ፖለቲከኞችን ወደጎን በማድረግ አብይ ፓርቲያቸው ብልፅግና በመጪው ምርጫ በሰፊ ልዩነት እንደሚያሸንፍ አረጋግጠዋል። ኦሮሚያን እና ትግራይ ለብዙ ወራት በግጭት ሲናወጡ ቢቆይም የምርጫው ውጤት ቀድሞ እንደመታወቁ ምርጫውን ተንተርሶ ሁኔታዎች የመባባስ እድላቸው አነስተኛ ነው። በኦሮሚያ ትልልቅ እና ግጭት የተቀላቀለባቸው ሰልፎችን ያካሄዱ እንደ ቄሮ ያሉ ቡድኖች ከ2010 ወዲህ ወደመንግስት በመግባት እና በተፅእኖ በእጅጉ ተዳክመዋል (ኢትዮጵያን ኢንሳይደር፣ መጋቢት 29, 2013)። የእነዚህ ጥረቶች ውጤታማነት ቀደም ሲል ተረጋግጧል – በጥር 2013 በእስር በሚገኙ የኦሮሞ ፖለቲከኛ የረሃብ አድማ ዘመቻ ሲጀመር ሊደረግ የነበረ የተቃውሞ ሙከራ በጸጥታ ኃይሎች በፍጥነት ተበትኗል፤ በምርጫው ወቅትም ሊደገም የሚችል ነው (ኤፒ፣ የካቲት 29, 2013)።
ለአብይ የበለጠ አሳሳቢ የሚሆነው አማራ ክልል ነው፤ በክልሉ በኦሮሚያ ልዩ ዞን አካባቢ በአጣዬ ከተማ የተከሰቱ ግጭቶች በብዙ መራጮች እንደየመንግስት ብቃት ማነስ እና “የሕግ የበላይነትን ማስከበር ላይ ያለ ድክመት” ተደርገው መታየታቸው አብን ያለው ቦታ እየተጠናከረ እንዲመስል አድርገዋል (ቪኦኤ፣ ግንቦት 26, 2013)። ሚያዚያ አጋማሽ ላይ በባህር ዳር በተካሄደ ሰልፍ ላይ የአብን ደጋፊዎች የብልፅግናን ባነሮችን ሲያቃጥሉ እና ፀረ-ዐቢይ መፈክሮችን ሲያሰሙ ሰልፉ ወደግጭት ተቀይሯል (አዲስ ስታንዳርድ፣ ሚያዚያ 12, 2013)። የፖለቲካ እጣ ፈንታው ቀድሞ ከተወሰነው ከኦሮሚያ ክልል ጋር ሲነፃፀር በብልፅግናን እና አብን መካከል ያለው ውድድር ወደምርጫ መስጫው ክፍሎች የሚወሰድ ነው። አከራካሪ ውጤቶች የምርጫ ቀን ብጥብጥ ሊያስከትሉ ይችላሉ ፡፡
መጪው ምርጫ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን ውጥረቶችን እና የግጭት ደረጃዎችን በእርግጥም ከፍ አድርጎታል። ሆኖም በምርጫው መዳረሻ ያሉ ግጭቶች በአዳዲስ አካባቢዎችም ሆነ በአዲስ መንገድ እየተከሰቱ አይደለም፡፡ ይልቁንም የቆዩ ጉዳዮች የአካባቢ አስተዳዳሪዎች በአዲስ የተደራጀ የፖለቲካ ስርዓት ውስጥ ያልተረጋጋ የፖለቲካ ሁኔታ በሀብታቸው ወይም ድጋፍ መያዛቸው ላይ የሚያመጣውን አደጋ በመረዳታቸው እንደገና እየተነሱ ነው፡፡ በእርግጥም ይህ በመላ ሀገሪቷ በርካታ ቀውሶች ቢኖሩም እንኳን ምርጫው የሚቀጥልበት ምክንያት ነው። ምንም ዓይነት ችግር ቢኖር አብይ ይህንን ምርጫ ታማኞቻቸውን እና በአካባቢ ደረጃ የፓርቲያቸው ተወካዮች ሀይል ለመገንዘብ ነው፡፡ በዚህ እውቀት ላይ ተመስርተው የሚያደርጉት ነገር የኢትዮጵያን ብዙ አመታት መፃኢ እድል ይወስናል።