በቁጥር (ከመጋቢት 24, 2010 እስከ ሰኔ 4, 2013)1 እነዚህ ቁጥሮች የሚያመለክቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደስልጣን ከመጡበት መጋቢት 24, 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገሪቱ የተከሰቱ የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶችን፣ በዚህ ምክንያት የደረሱ የሞት ጉዳቶች፣ እንዲሁም በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ የተቃጡ ጥቃቶችን ነው።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 1,582
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 7,941
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 4,288
በቁጥር (ከግንቦት 28, 2013 እስከ ሰኔ 4, 2013)2በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተካተቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ቁጥሮች ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 6
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 38
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 4
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን እዚህ፣ ሁሉንም የአክሌድ ስራዎች ደግሞ እዚህ ጋር በመጫን ያገኛሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ከመንግስት ወታደሮች ጋር ባደረገው ውጊያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሞት መከተሰቱን ተከትሎ በኦሮምያ ክልል ውስጥ የትጥቅ ውጊያዎች ባለፈው ሳምንት ተባብሰዋል። በዚሁ ወቅት ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል በአማሮ ልዩ ወረዳ እና ቤንች ሸኮ ዞን ነዋሪዎች ላይ የሚያደርሱት ጥቃት በመቀጠሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። ሳምንቱን በሙሉ በሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ ህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ (ህወሓት)ን የሚቃወሙ ሰልፎች የተመዘገቡ ሲሆን የአማራ ክልል እና የትግራይ ክልል ምዕራብ ትግራይ ዞን ነዋሪዎች ግጭቶችን እና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የውጭ ሀገራትን ጣልቃ ገብነትን አውግዘዋል።
በምዕራብ ትግራይ ዞን በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ህወሓትን እና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳዮች የውጭ ጣልቃ ገብነት በመቃወም የተካሄዱ (ከዚህ በታች ያለውን ምስል ይመልከቱ)። ተቃውሞውን ሴቶች ሰኔ 2, 2013 በሁመራ ከተማ ጀምረዋል (አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ሰኔ 2, 2013).። በቀጣዩ ቀን በምዕራብ ትግራይ ዞን በባዕከር ከተማ ቀጥለዋል (አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ሰኔ 3, 2013)። ሰኔ 3, 2013 ላይ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችውን ማእቀብ በመቃወም የብልፅግና ፓርቲ ሴት ደጋፊዎች በአማራ ክልል የደባርቅ ከተማ ተካሂዷል (አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ሰኔ 3, 2013)። ሰኔ 4, 2013 ላይ የተቃውሞ ሰልፎች ለሶስተኛ ቀን ቀጥለው የዋሉ ሲሆን በምዕራብ ትግራይ ዞን በማይካድራ ከተማ (ካድራወንዝ) ተካሂዷል (አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ሰኔ 4, 2013)።
በኦሮሚያ ክልል በኦነግ-ሸኔ እና በመንግስት ሀይሎች መካከል ውጊያዎች በምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ጉጂ፣ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች ቀጥለዋል (ኢፒኦ ሳምንታዊ:- ከሚያዚያ 20, 2013 እስከ ግንቦት 13, 2013፤ ኢፒኦ:- ከግንቦት 14, 2013 እስከ ግንቦት 20, 2013፤ ኢፒኦ ሳምንታዊ:- ከግንቦት 21, 2013 እስከ ግንቦት 27, 2013)። ሰኔ 3, 2013 የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ እና የኦነግ-ሸኔ አባላት በምዕራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ገርባ ከተማ ውስጥ ለአራት ሰዓታት ውጊያ አካሂደዋል። በተመሳሳይ ቀን የኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በጃርቴ ጃርደጋ ወረዳ በጃርደጋ ከተማ 27 የፌደራል ፖሊሶችን ሀይሎችን ሲገድሉ ተጨማሪ 10 ሰዎችን ደግሞ አቁስለዋል። ከታጣቂዎቹ ውስጥም አንዱ ተገድሏል (ኢትዮጵያን ኢንሳይደር፣ ሰኔ 4, 2013)። በተጨማሪም ሰኔ 3, 2013 እንደተዘገበው ከግንቦት 24, 2013 እስከ ግንቦት 27, 2013 የኦሮሞ ልዩ ፖሊስ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና ከሶማሌ ክልል ፖሊስ ጋር በመሆን በጉጂ እና ቦረና ዞኖች ከኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች ጋር የተዋጉ ሲሆን 95 ታጣቂዎችን ገድለው “ብዙዎች”ን ደግሞ አቁስለዋል (ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ሰኔ 3, 2013)። የኦነግ-ሸኔ ቃል አቀባይ እነዚህን ዘገባዎች ውድቅ አድርገው እንዲያውም የፌደራል ሀይሎች በጉጂም ሆነ ቦረና ዞኖች ውስጥ መሸነፋቸውን ገልፀዋል (ኦዳ ታርቢ፣ ግንቦት 26, 2013)።
በኦሮሚያ ክልል ግጭቱ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች በኦነግ-ሸኔ እና በመንግስት ኃይሎች መካከል በሚደረገው ውጊያ አሁንም እየተጎዱ ነው። በዚህም ምክንያት በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን በአሁኑ ወቅት 55,163 ተፈቃዮች (9,825 ቤተሰቦች) ይገኛሉ (አዲስ ስታንዳርድ፣ ሰኔ 3, 2013)። በተጨማሪም ግንቦት 29, 2013 ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ከተማ ላሎ አሳቢ ቀበሌ አንድን ወጣት ተኩሰው ገለዋል (ኦኤምኤን፣ ሰኔ 3, 2013)። ሰኔ 1, 2013 ላይ በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ዳራሚ ቱሉ ጉሌድ ውስጥ የኦሮሞ ታጣቂዎች የሶማሌ ነዋሪዎችን አጥቅተው አንድ ሰው ገለዋል (ሀልጋን ሚዲያ፣ ሰኔ 1, 2013)።
በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ሰኔ 2 2013 ላይ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በአማሮ ልዩ ወረዳ የሮ እና ዳኖ ቀበሌዎች ነዋሪዎችን በማጥቃት ሁለት ሰዎች ሲገሉ ሶስተኛው ደግሞ አቁስለዋል (ዲደብሊው አማርኛ፣ ሰኔ 3, 2013)። ሰኔ 3, 2013 ከቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ የተፈናቀሉ ግለሰቦች በሀዋሳ ከተማ በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል አስተዳደር ጽ/ቤት ፊት ለፊት በመሰባሰብ መንግስት እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀዋል። በቅርቡ ታጣቂዎች በጉራፈርዳ ወረዳ (ቤንች ሸኮ ዞን፣ደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል) ባደረሱት ጥቃት ስድስት ሰላም አስከባሪዎች ህይወታቸው አልፏል (ዲደብሊው አማርኛ፣ ግንቦት 30, 2013)። ይህንን ጥቃት ተከትሎ ወደ 4000 የሚጠጉ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ከአካባቢው ሸሽተዋል (ኢፒኦ:- ከግንቦት 14, 2013 እስከ ግንቦት 20, 2013፤ ኢፒኦ ሳምንታዊ:- ከግንቦት 21, 2013 እስከ ግንቦት 27, 2013)።
ወቅታዊ የትግራይ ግጭት ሁኔታ
በትግራይ ክልል ዋና ከተማ ሕይወት ወደ ቀድሞ ሁኔታው እየተመለሰ ይመስላል። በከተማዋ ያሉ ትምህርት ቤቶች ተከፍተዋል፣ መንግስት ደህንነትን ለማስጠበቅ ጥረት ያደረገ ሲሆን በዚህ ሳምንት ባካሄደው እንቅስቃሴ ወንጀለኞችን በተሳካ ሁኔታ ማሰር ችሏል (ኢቢሲ፣ ሰኔ 2, 2013; ኢቢሲ፣ ሰኔ 4, 2013)። መንግስት በክልሉ ውስጥ በአሁኑ ወቅት 55% የሚሆኑት ሆስፒታሎች እና 52% ጤና ጣቢያዎች ከ85% ሰራተኞች ጋር አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን አስታውቋል (ኢቢሲ፣ ሰኔ 2, 2013)። ሆኖም ግን በክልሉ ሰሜን-ምዕራባዊ፣ ማዕከላዊ፣ እና ምስራቃዊ ዞኖች ግጭቶች አሁንም እንደቀጠሉ ነው። ይህንን ተከትሎ ሰብአዊ ድርጅቶች በእነዚህ ዞኖች ሰብዓዊ ዕርዳታ በቀላሉ ማድረስ አልቻሉም (የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ፣ ሰኔ 3, 2013)፡፡ በተጨማሪም የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች ተደራሽነት መከልከላቸውን፣ የተለያዩ ቁሳቁሶች እንደተያዙባቸው፣ እና በተለያዩ የፍተሻ ጣቢያዎች የሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞች መያዛቸውን ዘግበዋል (የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ፣ ሰኔ 3, 2013)። መንግሥት “አንዳንዶች በሰብዓዊ ዕርዳታ ሽፋን ሽብርተኞችን ለማስታጠቅ መሣሪያዎችን ለማዘዋወር ሙከራ ስላደረጉ” ለደህንነት ሲባል እነዚህ ፍተሻዎች እንደሚያስፈልጉ አሳውቋል (የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ሰኔ 5, 2013)።
በተጨማሪም የኤርትራ ኃይሎች ከትግራይ ክልል መውጣት መጀመራቸውን መንግሥት አስታውቋል (ዲደብሊው አማርኛ፣ ሰኔ 3, 2013; ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት፣ ሰኔ 3, 2013). ወታደሮቹ መቼ መውጣት እንደጀመሩም ሆነ ምን ያክል የኤርትራ ኃይሎች ክልሉን ለቀው እንደወጡ ግልጽ አይደለም። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የኤርትራ ኃይሎች ከትግራይ ክልል እንዲወጡ ጥሪ ሲያቀርብ ቆይቷል (ቪኦኤ፣ መጋቢት 25, 2013፤ S.Res.97፣ ግንቦት 11, 2013፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንቶኒ ጄ ብሊንከን፣ ግንቦት 7, 2013)።
ሳምንታዊ ትኩረት: የምዕራብ ትግራይ አመራር
ባለፈው ሳምንት በትግራይ ክልል ያለው ግጭት ከጀመረ ወዲህ ለሁለተኛ ጊዜ በትግራይ ክልል ሰልፎች ተካሂደዋል። ምንም እንኳን በአንጻራዊ ሁኔታ መጠናቸው አነስተኛ እና ከፍተኛ ግጭት ባያስከትሉም እነዚህ ሰልፎች በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን የኃይል ለውጥ ያሳያሉ። በየካቲት ወር በምስራቃዊ ትግራይ አካባቢዎች ከተካሄዱት ሰልፎች እጅግ በተቃራኒው ባለፈው ሳምንት በምዕራብ ትግራይ የተካሄዱት የተቃውሞ ሰልፎች ሰላማዊ እና የፀጥታ ኃይሎች ያልተሳተፉባቸው ነበሩ።
ባለፈው ሳምንት የተቃውሞ ሰልፎች የተካሄዱባቸው አካባቢዎች በአማራ ክልል ልዩ ሀይል እና ከእነሱ ጋር ግንኙነት ያላቸው የብሔር ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ሲሆኑ እነዚህ ቡድኖች ቦታዎቹን የተቆጣጠሩት ከህወሃት ጋር ያለ ግጭት ጥቅምት 2013 ላይ ተጀመሮ ብዙም ሳይቆይ ነበር። አካባቢው ላይ የአማራ እና የትግራይ ብሔር ተወላጆች የሚኖሩበት ሲሆን አመራሩ ለረዥም አመታት አከራካሪ ሆኖ ቆይቷል። በዚህ አመት አጋማሽ በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች ከነበሩ አመፆች ጋር ሲነፃፀር ሰልፎቹ ሰላማዊ ነበሩ።
በየካቲት ወር በምስራቃዊ ትግራይ ሽሬ፣ አክሱም፣ መቀሌ፣ እና ውቅሮ ውስጥ ትላልቅ ግጭት የተቀላቀለባቸው ሰልፎች የተካሄዱ ሲሆን አመጽ ውስጥ የተሳተፉ ወጣቶች መንገዶችን በመዝጋት እና ጎማዎችን በማቃጠል ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን እና እሱን ተከትሎ ያጋጠመውን የምግብ እጥረት አውግዘዋ። ምንጮች በመቀሌ ከተማ አምስት ሰዎች በውቅሮ ደግሞ ሁለት ሰዎች በእነዚህ ሰልፎች ወቅት መሞታቸውን ገልፀዋል። በተጨማሪም ሰልፎች በትግራይ ክልል በአዲግራት ከተማ እደጋ ሀሙስ እና ፍሬወይኒ ውስጥ ተካሂደው ነበር (የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ፣ የካቲት 23, 2013)።
በእነዚህ ሁለት እንቅስቃሴዎች መካከል ላለው ልዩነት ምክንያት የሆነው ከአከባቢው የደህንነት አሰራር ጋር መጣጣም ነው። የምዕራብ ትግራይ ዞንን የሚተቆጣጠሩት የአማራ ብሔር ታጣቂዎች ሕወሓትን የሚቃወሙ ናቸው። በቅርቡ የአሜሪካ ባለስልጣናት በሀላፊዎቻቸው ላይ የጣሉትን ማእቀብ ተቃውመዋል (ኒውዮርክ ታይምስ፣ ግንቦት 16, 2013)። ስለሆነም በመቀሌ እና ሌሎች የምስራቃዊ ትግራይ ዞን አካባቢዎች ላይ የተካሄዱ ሰልፎች በኢትዮጵያ ወታደሮች ከፍተኛ አፈና የታየባቸው ሲሆን ፀረ-ህወሃት መፈክሮችን ያሰሙ እና የአሜሪካን ማዕቀብ ያወገዙ ሰልፈኞች የአከባቢው የአማራ ኃይሎች ጣልቃ ሳይገቡባቸው በሰላማዊ መንገድ አልፈዋል።
ህወሃት የምዕራብ ትግራይ ዞንን ከ1987 እስከ ጥቅምት 2013 በሚያስተዳደረበት ወቅት በአካባቢው የሚኖሩ የአማራ ብሔር ተወላጆች አድሎ እንደሚፈፀምባቸው እና መንግስት እንደዜጋ ያላቸውን መብቶች እንደሚነፍጋቸው ቅሬታ ያቀርቡ ነበር። በክልሉ ውስጥ በ2008፣ 2009፣ 2010 አማራዎች የሚያካሂዷቸው ሰልፎች በአብዛኛው ከህወሃት ጋር ግንኙነት ባላቸው ወታደሮች በሀይል ይታፈኑ ነበር። እነዚህ የመብት ጥሰቶች ናቸው የወልቃይት ማንነት ጥቃቄ ኮሚቴ እንዲመሰረት እና በኢትዮጵያ የአማራ ብሄርተኝነት እንቅስቃሴ እንዲጀመር ያደረጉት (ቦርከና፣ የካቲት 12, 2010)። በአሁኑ ወቅት የምዕራብ ትግራይ ዞንን የተቆጣጠሩት የፋኖ ታጣቂዎች እና የአማራ ክልል ልዩ ኃይሎች የተቋቋሙት ህወሃትን በሚቃወሙ አዛዦች ሲሆን ብዙውን ጊዜም የአማራ ብሄርተኝነት ሃሳቦችን ይደግፋሉ፤ ይህ ጉዳይ በመጪው የኢትዮጵያ ምርጫ ውስጥ በጣም ዋና ጉዳይ ነው። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከሌሎች መካከል ምዕራብ ትግራይን ማስመለስ የሚል የአማራ ብሄርተኛ ፓርቲ ሲሆን በመጪው ምርጫ በአማራ ክልል ከተማ አካባቢዎች እና በምዕራብ ትግራይ ዞን ውስጥ ጥሩ እድል እንደሚኖረው ይጠበቃል።
ምዕራብ ትግራይ ዞን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መፈናቀልና በኢላማ ጥቃት የሚደርስበት ቦታ ሆኗል። ምርመራዎች ቢያንስ 600 ሰው ተገድለውበታል ያሉትን ማይካድራ ጨምሮ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ህወሀት እና የአማራ ክልል ሀይሎች ገድለዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል (የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ህዳር 15, 2013)። በቅርቡ ሬውተርስ ያደረገው ምርመራ ከትግራይ እና አማራ ብሔረሰቦች ጋር ግንኙነት ያላቸው ቡደኖች በማይካድራ በግጭት ውስጥ ያልተሳተፉ ግለሰቦችን መግደላቸውን አሳውቋል። የሟቾች ቁጥርም ሊጨምር እንደሚችል ይገመታል (ሬውተርስ፣ ግንቦት 30, 2013)። የአማራ ክልል ሀይሎች የትግራይ ብሔር ተወላጆችን ከዞኑ አስወጥተዋል ተብለው ክስ ቀርቦባቸዋል ፤ የአሜሪካ ባለስልጣናት ይህ ድርጊት እንደ የዘር ማጥፋት እንደሚቆጠር ገልፀዋል (ኤፒ፣ መጋቢት 29, 2013)።
የምዕራብ ትግራይን አመራር ተከትሎ በአማራ ክልል መንግስት እና በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳዳሪዎች መካከል ውጥረት ተፈጥሯል (ቢቢሲ አማርኛ፣ መጋቢት 5, 2013)። እነዚህ ክርክሮች እንዴት እንደሚፈቱ ግልፅ አይደለም። ለአሁን ግን በህወሃት “በጉልበት የተወሰደው´´ አካባቢ በአማራ ክልል ሀይሎች “በጉልበት የተመለሰ“ ይመስላል (ብሉምበርግ፣ መጋቢት 7, 2013)።
ከምርጫ ጋር የተያያዙ ክርክሮች ወቅታዊ ሁኔታ
የአርጎባ ብሄረሰብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ፓርቲ ዕድሜያቸው ለምርጫ ያልደረሱ ሰዎች እና በአርጎባ ልዩ ወረዳ ውስጥ የማይኖሩ ሰዎች ለመምረጥ እየተመዘገቡ ነው ሲል ላቀረበው ቅሬታ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምላሽ መስጠት አልቻለም ብሏል (ዲደብሊው አማርኛ፣ ሰኔ 3, 2013)። በጉዳዩ ላይ ምርጫ ቦርድ ከምርጫ በፊት ምላሽ የማይደሰጥ ከሆነ ምርጫው ላይ እንዳይሳተፍ እንደሚገደድ ፓርቲው አሳውቋል።
ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14, 2013 ላይ ምርጫ ለማይካሄድባቸው አካባቢዎች ምርጫው ጳጉሜ 1, 2013 ላይ እንደሚካሄድ አሳውቋል። በጠቅላላ አጠቃላይ ምርጫው በተለያዩ ምክንያቶች በ64 የምርጫ ክልሎች አይካሄድም። ከእነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ የምርጫ ክልሎች የሚገኙት በሶማሌ ክልል ነው። በመሆኑም በሶማሌ ክልል ምርጫው ጳጉሜ 1, 2013 ይካሄዳል። የደህንነት ጉዳይ ከ63ቱ የምርጫ ክልሎች ውስጥ በ26ቱ ውስጥ ምርጫ እንዳይካሄድ ያደረገው ዋና ምክንያት መሆኑ ተገልጿል (ኢፒኦ ሳምንታዊ:- ከግንቦት 21, 2013 እስከ ግንቦት 27, 2013)።