ኢትዮጵያ በቁጥር (ከመጋቢት 24, 2010 እስከ ሐምሌ 23, 2013)1 እነዚህ ቁጥሮች የሚያመለክቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደስልጣን ከመጡበት መጋቢት 24, 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገሪቱ የተከሰቱ የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶችን፣ በዚህ ምክንያት የደረሱ የሞት ጉዳቶች፣ እንዲሁም በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ የተቃጡ ጥቃቶችን ነው።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 1,735
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 9,294
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 4,944
ኢትዮጵያ በቁጥር (ከሐምሌ 17, 2013 እስከ ሐምሌ 23, 2013)2በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተካተቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ቁጥሮች ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ። በተለይም በወቅታዊ የትግራይ ሁኔታ ላይ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ጥቃት በተመለከተ ዘገባዎች ቀስ ብለው በሚቀጥሉት ሳምንታት ሊወጡ ይችላሉ።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 27
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 427
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 304
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን እዚህ፣ ሁሉንም የአክሌድ ስራዎች ደግሞ እዚህ ጋር በመጫን ያገኛሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ባለፈው ሳምንት በመንግሥት ኃይሎች እና በትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ሕወሓት) መካከል የሚደረጉ ውጊያዎቸ በሦስት ግንባሮች ማለትም፡- በአፋር ፋንቲ ራሱ-ዞን 4፣ በምዕራብ ትግራይ ዞን ወልቃይት ጠገዴ፣ እና በደቡብ ትግራይ ዞን/በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ቀጥለዋል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። አነስተኛ የመገናኛ ተደራሽነት ባለባችው የገጠር አካባቢዎች ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደ በመሆኑ የሟቾችን ቁጥር ለመገመት አዳጋቸ ነው። በተጨማሪም ትህነግ ባለፈው ሳምንት ከዚህ በታች የሚብራሩ አዲስ የጋራ የተኩስ አቁም ስምምነት ቅድመ-ሁኔታዎችን ሲሆን አውጥቷል።
ውጊያው እየተባባሰ እየሄደ ባለበት ወቅት በመላ አገሪቱ በሚገኙ አካባቢዎች የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን የሚደገፉና በትህነግ መፈፀም የቀጠለውን ወታደራዊ እርምጃ የሚያወግዙ ሰልፎች ተካሂደዋል። ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል በጎንደር ከተማ፣ በባህርዳር ከተማ፣ እና አንጾኪያ ገምዛ ከተማ የተቃውሞ ሰልፎች ተመዝግበዋል። እንዲሁም በአፋር ክልል ርዕሰ ከተማ ሰመራ እና በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን ተፈሪ ከተማ ውስጥ ተካሂደዋል። ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የመጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች “ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ“ በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን እየተቀላቀሉ ነው ተብሏል (ቪኦኤ አማርኛ፣ ሐምሌ 20, 2013)። ከትህነግ ጋር የሚደረገውን ጦርነት መንግስት ቀደም ሲል “የሕግ ማስከበር ተግባር” ብሎ ሲጠራው የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ “ኢትዮጵያን ለማዳን” የሚደረገ ጦርነት ተብሏል (ዋልታ ቲቪ፣ ሐምሌ 20, 2013)።
አዲስ አበባ ውስጥ የሚኖሩ በርካታ የኤርትራ ስደተኞች በቅርቡ በትግራይ ክልል የስደተኞች መጠለያ ካምፖች ላይ ተፈጽመዋል ለተባሉ የጥቃት ዜናዎቸ በአዲሰ አበባ በሚገኘወ የአለም አቀፍ የስደተኞቸ ጉዳይ ጽ/ቤት ፊት ለፊት በመሰበሰብ ምላሽ ሰጥተዋል (ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት፣ ሐምሌ 22, 2013)። ሰልፈኞቹ የአለም አቀፍ የስደተኞቸ ጉዳይ ጽ/ቤት በትግራይ ክልል የሚኖሩ ስደተኞችን እንዲጠብቅና ደህንነቱ ወደተጠበቀ አካባቢዎች እንዲያዘዋውር ጠይቀዋል። በትግራይ ክልል በስደተኞች መጠለያ ካምፕ ውስጥ የሰፈሩ የኤርትራ ስደተኞች በአሁኑ የትግራይ ግጭት የጥቃት ኢላማ መሆናቸውን የተለያዩ ዘገባዎች ያመለክታሉ (ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከሐምሌ 10, 2013 እስከ ሐምሌ 16, 2013፤ ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከሐምሌ 3, 2013 እስከ ሐምሌ 9, 2013 ይመልከቱ)።
በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ባለፈው ሳምንት ሁከት ቀጥሏል። ሐምሌ 19, 2013 አካባቢ በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ የፀጥታ ኃይሎች ማንነቱ ካልታወቀ የታጠቀ ቡድን ተዋግተወ እጃቸውን የሰጡ 25 ታጣቂዎችን በቁጥጥር ስር አውለዋል (ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት፣ ሐምሌ 19, 2013)። በተጨማሪም ሐምሌ 21, 2013 ላይ የጉሙዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ አባላት በአሶሳ ዞን በሸርኮሌ ወረዳ አወልበጉ ቀበሌ ውስጥ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል ኃይሎች ጋር ተዋግተዋል (የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ሐምሌ 21, 2013)። ከ100 በላይ የጉሙዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የመጡ ታጣቂዎች በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መገደላቸው ተዘግቧል። ከተገደሉት ታጣቂዎች አምስቱ የትህነግ አባላት እንደሆኑ ይታመናል። በሪፖርቱ መሰረት ቡድኑ ከሱዳን የመጣው በቤንሻንጉል/ጉሙዝ በመተከል ዞን አለመረጋጋትን ለመፍጠር ነው።
ከዚህ ባለፈም በዓመቱ መጀመሪያ አካባቢ ወታደራዊ ኮማንድ ፖስት ቢቋቋምም በመተከል ዞን በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ቀጥሏል። ሐምሌ 21, 2013 ላይ የጉሙዝ ታጣቂ ቡድን አባላት በመተከል ዞን በግልገል በለስ ከተማ ቢያንስ ሦስት በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎችን በጥይት ገድሏል። ይህንን ጥቃት ተከትሎ የጉሙዝ ታጣቂ ቡድኑ በግገልገል በለስ ከተማ ከዞኑ ኮማንድ ፖስት የፀጥታ ኃይሎች ጋር ተጋጭቷል (ኢሳት፣ ሐምሌ 22, 2013)።
ባለፈው ሳምንት የአፋር ክልል ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት በመቶዎቸ የሚቆጠሩ ሶማሌዎች ተገድለዋል። ሐምሌ 17, 2013 ላይ የአፋር ታጣቂዎቸ እና ከአፋር አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር (ኡጉጉማ) ጋር የተቆራኙ የአፋር ታጣቂዎች በአፋር ክልል ጋቢ ዞን 3 በጋዳማይቱ ከተማ ነዋሪ የሆኑ የሶማሌ ተወላጆች ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል (ሮይተርስ፣ ሐምሌ 20, 2013፤ ብሉምበርግ፣ ሐምሌ 20, 2013፤ ሶማሌ ኮሚኒኬሽን፣ ሐምሌ 19, 2013)። የሶማሌ ክልል ባለስልጣናት ከ350 በላይ ሰዎች ተገድለዋል ሲሉ የአፋር ክልል መንግስት ውድቅ አድርጎታል (ዲደብሊው አማርኛ፣ ሐምሌ 21, 2013)። ሐምሌ 20, 2013 እና ሐምሌ 21, 2013 ላይ በጋዳማቱ በሶማሌ ክልል ሀይሎች እና በአፋር ክልል ሀይሎች መካከል ሌላ ዙር ውጊያ መካሄዱ ተዘግቧል (ቪኦኤ አማርኛ፣ ሐምሌ 20, 2013፤ ቪኦኤ አማርኛ፣ ሐምሌ 21, 2013)። በአሁኑ ወቅት የትኛው ቡድን አካባቢውን እንደሚቆጣጠረው ግልፅ አይደለም። በአሚባራ ወረዳ ገዳማይቱ ቀበሌ እና በሚሌ ወረዳ ዓዳይቱ እና በገዋኔ ወረዳ ኡንዱፎ የተባሉ ሌሎች ሁለት ቀበሌዎች በአፋር-ሶማሌ ክልሎች ድንበር ላይ የሚገኙ የባልለቤትነት ጥያቄ ያለባቸው ቦታዎች ናቸው። እነዚህ አካባቢዎች ተደጋጋሚ ግጭት ይካሄድባቸዋል። ስለግጭቱ ምንጭ የበለጠ ለማወቅ የኢፒኦን አፋር-ሶማሌ የድንበር ግጭት ገጽን ይመልከቱ።
በጋዳማይቱ የተፈጸመው ጥቃት በመላው ሶማሌ ክልል እና ድሬዳዋ ከተማ የተቃውሞ ሰልፎችን አስነስቷል። ሰኔ 21, 2013 ላይ የተቆጡ የሶማሌ ወጣቶች በድሬዳዋ አቅራቢያ ያለ መንገድ እና የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመርን መንገድን ብዙ ቆሻሻ ወደ መንገዱ በመውሰድ የዘጉ ሲሆነ የጭነት መኪናዎች እንዳያልፉ ከልክለዋል (ብሉምበርግ፣ ሐምሌ 20, 2013)። በጋዳማይቱ ከተማ የሶማሌ ነዋሪዎች መገደልን የሚያወግዙ ሰላማዊ ተቃውሞዎች በሶማሌ ክልል በጅጅጋ፣ ቀብሪደሃር፣ ደጋሃቡር፣ ጎደይ፣ ሽንሌ፣ ሃርጌሌ፣ እና ፊልቱ ከተሞች እንዲሁም በድሬዳዋ ከተማ ተካሂደዋል (ቪኦኤ አማርኛ፣ ሐምሌ 20, 2013)።
በተጨማሪም ባለፈው ሳምንት ሐምሌ 21, 2013 የአልሸባብ አባላት ከሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ጋር በሶማሌ ክልል እንደተጋጩ ዘገባዎቸ ያመለክታሉ (ኢሳት፣ ሐምሌ 22, 2013)። የግጭቱ ትክክለኛ ቦታ ያልተጠቀሰ ቢሆንም ሟቾቸ እንደነበሩ ምንጮች ያመለክታሉ። በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ከአልሸባብ ጋር የሚካሄዱ ውጊያዎቸ የተለመዱ አይደሉም።
ሐምሌ 21, 2013 ላይ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን በአቡና ጊንዴ በረት ወረዳ የፀጥታ ኃይሎች አንድ ወጣት ከእስር ቤት አውጥተው በአደባባይ ገድለውታል ሲሉ የተቃዋሚ ሚዲያዎች ዘግበዋል (ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ፣ ሐምሌ 22, 2013)። ወጣቱ የታሰረው ከኦነግ-ሸኔ ኃይሎች ጋር ግንኙነት አለው ተብሎ ከተከሰሰ በኋላ ነበር።
ሳምንታዊ ትኩረት፡ የትግራይ ግጭት
የትህነግ ኃይሎች የተጠናከረ መከላከል ካጋጠማቸው በኋላ ቀደም ብለው በስተደቡብ ወደ ሰሜን ወሎ እና በስተምሥራቅ ወደ አፋር ክልል የሚሄዱበትን ፍጥነት የቀነሱ ይመስላል። በአፋር ክልል ዞን 4 ሳምንቱ በሙሉ በትህነግ ታጣቂዎቸ እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በሚደገፈው የአፋር ልዩ ሃይል መካከል ከፍተኛ ውጊያ የተካሄደ ሲሆን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ሰዎች ሞት አስከትሏል። በተመሳሳይ የአማራ ክልል ሀይሎች እና ግንኙነት ያላቸው ታጣቂዎች ትህነግ ስትራቴጂካዊ ቦታ የሆነውን የወልዲያ ከተማን መቆጣጠር እንዳይችል አድርገውታል (የወልድያ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ / ቤት፣ ሐምሌ 25, 2013)።
ምንም እንኳን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ያወጀውን የአንድ ወገን የተኩስ አቁም በይፋ ባያቋርጥም፣ የትህነግን እንቅስቃሴ ለመግታተ የፌዴራል ኃይሎች ከክልል ሀይሎች ጎን መሰለፋቸው ግልፅ ነው። በወልቃይት ግንባር እና በራያ ቆቦ የአየር ላይ ጥቃቶች መደረጋቸውን የሚያሳዩ አንዳንድ ተዓማኒ ዘገባዎች አሉ (ኢሳት፣ ሐምሌ 22, 2013፤ ኢሳት፣ ሐምሌ 23, 2013)። ትህነግ ትግራይ ክልልን ከሌሎች ክልሎች እንዲሁም እንደ ሱዳን እና ጅቡቲ ካሉ ጎረቤት አገራት የሚያገናኙ መንገዶችን መቆጣጠር ሰብዓዊ አቅርቦቶች ሳይስተጓጎሉ ወደ ትግራይ ክልል እንዲገቡ ይረዳል በማለት የቀጠለው ግጭት እና የግዛት ማስፋፋት ምክንያታዊ ነው ሲል ይከራከራል። በተጨማሪም የቀጠለውን ግጭት በፌዴራል መንግሥት ላይ የሁለትዮሽ የተኩስ አቁም ቅድመ-ሁኔታዎች ዝርዝርን እና የፖለቲካ ውይይት እንዲቀበል ጫና ለማሳደር እየተጠቀሙበት ነው (ቢቢሲ አማርኛ፣ ሐምሌ 26, 2013)።
ምንም እንኳ የትህነግ ግስጋሴ በዚህ ሳምንት የቀዘቀዘ ቢመስልም በአፋርም ሆነ በአማራ ክልላዊ ግዛቶች ያገኘው ቦታዎች በጦርነቱ ውስጥ ጉልህ ቦታ ያለው ነው። በአሁኑ ወቅት የትህነግ ታጣቂዎቸ ከትግራይ ህዝብ ጋር ታሪካዊ ትስስር ካላቸው አካባቢዎች ውጭ እየተዋጉ ነው። ትህነግ የተቋቋመው የኢትዮጵያን መንግሥት የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ዕውቅና ላይ መሠረት አድርጎ የማዋቀር ፖለቲካ ዓላማ ይዞ ነበር። የእነሱ ታሪካዊ ስኬት እና የአገሪቱ ቀጣይ አመራር በዚህ መርህ ላይ የተመሠረተውን የአሁኑን የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት አስገኝቷል (ሙሉጌታ በርሄ፣ “Laying the Past to Rest”፣ 2019 (እ.ኤ.አ.)፣ ገጽ 84)። በሚገርም ሁኔታ (የአሁኑ) የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት “ወደፊት ለሚካሄድ ማንኛውም ድርድር ብቸኛው መሠረት” እንዲሆን የሚለው ቅድመ-ሁኔታ ትህነግ አዲሰ ለጋራ የተኩስ አቁም የሚሆኑ ቅድመ-ሁኔታዎች ካወጣው ዝርዝር አልተካተተም (ጌታቸው ኬ ረዳ፣ ሐምሌ 22, 2013)።
ሐምሌ 22, 2013 ላይ ትህነግ ለማንኛውም የወደፊት የጋራ የተኩስ አቁም ድርድር የቅድመ-ሁኔታዎችን አዲስ ዝርዝር አውጥቷል። ትህነግ ያወጣው አዲስ የቅድመ-ሁኔታዎች ዝርዝር ላይ በመጀመሪያው ዝርዝር ውስጥ ከተካተቱት ውስጥ የተወሰኑት ተለውጠዋል ወይም ወጥተዋል። በመጀመሪያ ወደ ትግራይ ክልል ዓለምአቀፍ በረራዎች እንዲፈቀዱ የቀረበው ጥያቄ ውድቅ ተደርጓል። የፌዴራል መንግሥት ለዚህ ዓመት የክልሉን በጀት እንዲለቅ የጠየቀው ሁለተኛው ቅድመ ሁኔታ መጪው ዓመትን ጨምሮ የ2013 እና 2014 በሚል እንዲሰፋ ተደርጓል። የኢትዮጵያ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትህነግ ቁጥጥር ስር ያለውን የትግራይ ክልል ምክር ቤት እና ካቢኔ “ሕገ-ወጥ” መሆኑን በመግለፅ መስከረም 26, 2013 ላይ ፌዴራል መንግስቱ የወሰነውን ገንዘብ ሰርዟል (ኤኤፍፒ፣ መስከረም 27, 2013)።
የኤርትራ እና የአማራ ኃይሎች ከትግራይ ክልል ይውጡ የሚለው ጥያቄ ቢኖርም ትህነግ ይህንን የሁለትዮሽ የተኩስ አቁም ለማድረግ የሚያሰችል ድርድር ለመጀመር ከተቀመጠ ቅድመ-ሁኔታነት ሰርዞታል። የፌዴራል ወታደሮች ከትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ እንዲለቁ ያስቀመጠውን ጥያቄም በተመሳሳይ አስወግዷል። በተጨማሪም በቅርቡ በተለቀቀው የቅድመ-ሁኔታዎች ዝርዝር ውስጥ ትህነግ አንድ በትግራይ ሕዝብ ላይ የተፈጸመውን ኢፍትሐዊነት መርምሮ ወንጀለኞችን ወደ ዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት የሚያቀርብ እና ሌላ ደግሞ አፈፃፀሙን የሚከታተል በአጠቃላይ ሁለት ነፃ ዓለም አቀፍ ተቋማትን የማቋቋም ጥያቄን አላካተተም። ሆኖም ግን አዲሱ የቅድመ-ሁኔታዎች ዝርዝር ግን ቀደም ሲል የተጠቀሰውን “አገሪቱን እየጎዱ ያሉትን የፖለቲካ እና ሕገ-መንግስታዊ ችግሮችን ለመቅረፍ በማሰብ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ዋና ዋና የፖለቲካ ተዋንያን” ሁሉ ያካተተ ሁሉን አቀፍ የሽግግር ሂደት ማቋቋምን ያጠቃልላል (ጌታቸው ኬ ረዳ፣ ሐምሌ 22, 2013)።
ትህነግ ያስቀመጣቸው ቅድመ-ሁኔታዎች አሁን ካለው የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት ጋር የሕግ መወሳሰቦችን የሚፈጥሩ ይመስላሉ። የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ላይ ከመመሥረት በተጨማሪ የፌዴራል መንግሥት እንደ የአየር መዣ፣ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ክልሎችን የሚያገናኙ ዋና ዋና መንገዶች፣ እና የስልክ የመሳሰሉ የተለያዩ የሕዝብ ዕቃዎችን እንዲያስተዳድር ያዛል (የኢፌዴሪ ሕገመንግሥት፣ 1987፣ አንቀጽ 51)። በተጨማሪም የክልል መንግሥት ያለ ፌዴራል መንግሥት ተሳትፎ ሳይኖረው በቀጥታ ከውጭ አገሮች ጋር የመገናኘት ሥልጣን የላቸውም (የኢፌዴሪ ሕገመንግሥት፣ 1987፣ አንቀጽ 51-52)።
የኢትዮጵያ ፌደራል ባለሥልጣናት እስካሁን ድረስ ትህነግ ለጋራ የተኩስ አቁም ድርድር ላሰቀመጣቸው ቅድመ-ሁኔታዎች በይፋ ምላሽ አልሰጡም። የሆነ ሆኖ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሐምሌ 2, 2013 ከጋዜጠኞች ጋር ሲነጋገሩ ተግባራዊ ለማድረግ መጀመሪያ የተለቀቁትን ቅድመ-ሁኔታዎች “ለመፈፀም የማይቻሉ” ብለዋቸዋል (ዲደብሊው አማርኛ፣ ሐምሌ 2, 2013)። በተፋላሚዎቹ ወገኖች መካከል ያለውን ሊታለፍ የማይችል ክፍተት በማየት ሲታይ በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ያሉ ውጊያዎቸ በመጪዎቹ ሳምንታትም የሚቀጥሉ ይመስላል። ቀጣይ ግጭቶች ወደ ትግራይ ክልል የሚደረጉ የሰብዓዊ ዕርዳታ መጓጓዝ ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው። ሐምሌ 23, 2013 ላይ 200 አካባቢ የሰብዓዊ ዕርዳታን የጫኑ የዓለም የምግብ ፕሮግራም መኪኖች ወደ ትግራይ ክልል መጓዝ ጀምረዋል (ቢቢሲ አማርኛ፣ ሐምሌ 23, 2013)። በፋንቲ ራሱ-ዞን 4 በአምስት ወረዳዎች የተካሄደውን ከፍተኛ ውጊያ ተከትሎ እነዚህ መኪኖቸ በአፋር ክልል አውሲ ዞን 1 ሰመራ ከተማ ውስጥ ቆይተዋል።
ከምርጫ ጋር የተያያዙ ክርክሮች ወቅታዊ ሁኔታ
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ከድህረ-ምርጫ ጋር የተያያዘ የክርክር ጥያቄ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማቅረቡን እና አዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙት 23 የምርጫ ክልሎች ውስጥ በ21 ምርጫ ድጋሚ እንዲካሄድ መጠየቁን አስታውቋል (ዲደብሊው አማርኛ፣ ሐምሌ 23, 2013)። ፓርቲው ገዥው ፓርቲ ስድስተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር በመተባበር ‘መጥለፉን’ ገልጿል (ዲደብሊው አማርኛ፣ ሐምሌ 23, 2013)። አገሪቱ የተመጣጠነ የውክልና ሥርዓትን ብትከተል ፓርቲው በአዲስ አበባ ቦታን እንደሚያገኝ ፓርቲው ገልጿል። ስለዚህ ፓርቲው የአገሪቱን ቀላል የአብላጫ ሥርዓት ወደ ተመጣጣኝ የውክልና ሥርዓት እንዲቀየር ሐሳብ አቅርቧል።
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከምርጫ በኋላ ጋር የተያያዘ የክርክር ጥያቄ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበ ሁለተኛው ፓርቲ ነው። ሐምሌ 14, 2013 የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል በሚገኙ 28 የምርጫ ክልሎች ምርጫዎች እንደገና እንዲካሄዱ በመጠየቅ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከምርጫ ጋር የተያያዘ የክርክር ጥያቄ አቅርቧል (ኢዜማ፣ሐምሌ 15, 2013)።