በቁጥር (ከመጋቢት 24, 2010 እስከ ሃምሌ 23, 2013) 1እነዚህ ቁጥሮች የሚያመለክቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደስልጣን ከመጡበት መጋቢት 24, 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገሪቱ የተከሰቱ የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶችን፣ በዚህ ምክንያት የደረሱ የሞት ጉዳቶች፣ እንዲሁም በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ የተቃጡ ጥቃቶችን ነው። እስከ ሃምሌ 23, 20132አክሌድ እስከ ነሀሴ መጨረሻ ድረስ የተመዘገቡ ኩነቶችን ህትመት ይገታል። ከሐምሌ 24, 2013 እስከ ነሀሴ 28, 2013 ያሉ መረጃዎች የኩነቶች ህትመት ጷጉሜ 1, 2013 ላይ በድጋሚ ሲጀምር የሚለቀቁ ይሆናል። በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን እንዲሁም ኢትዮጵያን የተመለከቱ ሁሉንም የአክሌድ መረጃዎች ማውረድ ይችላሉ።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 1,735
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 9,294
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 4,944
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን እዚህ፣ ሁሉንም የአክሌድ ስራዎች ደግሞ እዚህ ጋር በመጫን ያገኛሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
በትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሃት) እና በክልል ልዩ ሃይሎች እና ታጣቂዎች በታጀበው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአማራ ክልል እና በትግራይ ክልል ምዕራብ ትግራይ ዞን የቀጠለ ሲሆን በአፋር ክልል ቀንሷል።
በትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ ትግራይ ዞን ማይ ፀምሪ እና ምዕራብ ትግራይ ዞን ወልቃይት ውስጥ ትህነግ ከአማራ ክልል ልዩ ሃይል እና ከአማራ ታጣዎች ተዋግቷል። ከጥቅምት 2013 ጀምሮ ምዕራባዊ ትግራይ ዞን በአማራ ክልላዊ መንግስት ቁጥጥር ስር ነው (ስለ ምዕራብ ትግራይ ዞን አስተዳደር የበለጠ ዝርዝር ለማግኘት ኢፒኦ ሳምንታዊ :- ከግንቦት 28, 2013 እስከ ሰኔ 4, 2013 ይመልከቱ)።
ባለፈው ሳምንት የፀረ-ትህነግ ኃይሎች የሆኑት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስ ኃይሎች፣ የአማራ ክልል ልዩ ኃይሎች፣ የፋኖ ታጣቂዎች፣ እና የአካባቢ ታጣቂዎች በአማራ ክልል የግዛት ድል ያስመዘገቡ ሲሆን በሰሜን ወሎ ዞን ጋሸና፣ አርሴማ ተራሮች፣ እስታይሽ፣ ቀበሮ ሜዳ፣ አሁንተገኝ፣ ሃሙሲት፣ አርቢት፣ ኮን፣ እና መርሳን እንዲሁም በደቡብ ጎንደር ዞን ሀገረ ገነትን እንደገና ለመቆጣጠር ችለዋል (አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ነሃሴ 13, 2013)። ውጊያዎች በተጠቀሱት ቦታዎች ሁሉ ባለፈው ሳምንት የተካቄዱ ሲሆን አሁንም ቀጠለዋል።
በአማራ ክልል በአማራ ክልል ልዩ ሃይል እና በአማራ ታጣቂዎች ትዕዛዝ ስር ያልሆኑ አርሶ አደሮች እና ጠመንጃ የሚይዙ ወጣቶች የትህነግ ታጣቂዎች መንደርና ከተማ ውስጥ ሲዘዋወሩ ጥቃት መሰንዘር ጀምረዋል። እነዚህ ጥቃቶች የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ሁሉም ሰው ወደማህበረሰቡ/ቧ የሚገባን የትህነግ ሃይሎችን ‘‘እንዲታገሉ’’ ጥሪ ካቀረቡ እና በውጊያ ወቅት የሚያዙ ማናቸውን መሳሪያዎች በግለሰቦቹ እንዲወሰዱ ከገለጹ በኋላ ጨምረዋል (አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ነሃሴ 10, 2013፤ አዲስ ስታንዳርድ፣ ነሃሴ 12, 2013)።
የትህነግ ኃይሎች በአማራ ክልል ውስጥ ሰላማዊ ሰዎችን በመግደል፣ የአማራ ሴቶችን በመድፈር፣ ንብረቶችን በማውደም እና በመዝረፍ ተከሰዋል (አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ነሃሴ 10, 2013፤ ቴሌግራፍ፣ ነሃሴ 11, 2013)። ነሃሴ 13, 2013 ላይ የትህነግ ሃይሎች አማራ ክልል ውስጥ የሚገኘውን ደብረታቦር ከተማ በከባድ መሳሪያ ደብድበው አምስት ሰዎች ገድለዋል (ቢቢሲ አማርኛ፣ ነሃሴ 14, 2013)። ትህነግ እነዚህን ውንጀላዎች ክዶ ገለልተኛ ማጣራት በተባበሩት መንግስታት እንዲደረግ ጠይቋል (ቪኦኤ አማርኛ፣ ነሃሴ 17, 2013)።
ባለፈው ሳምንት ነሐሴ 9 እና 10, 2013 ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአማራ ክልል ወልቃይት ግንባር ከቅማንት ኮሚቴ ታጣቂዎች ጋር ተጋጭቷል (ኢሳት፣ ነሃሴ 11፣ 2013)። የቅማንት ኮሚቴ በአማራ ክልል ለሚገኘው የቅማንት ብሔረሰብ የበለጠ ራስን በራስ የማስተዳደር ነፃነት ጥያቄ ይጠይቃል። ሚያዝያ 2013 ላይ ከቅማንት ጋር ግንኙነት ያላቸው ታጣቂዎች በሰሜን ጎንደር ዞን ከአማራ ክልል ልዩ ሃይል ጋር ተዋግተዋል። የአማራ ክልል መንግስት ይህ ቡድን ከትህነግ ጋር ግንኙነት አለው ሲል ይከሳል (ግጭቱን በተመለከተ ለበለጠ ዝርዝር ለማግኘት የኢፒኦን የቅማንት ግጭት ገጽ ይመልከቱ)።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙት የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይል እና የኦሮሚያ ታጣቂዎች ጋር የተዋጋ ሲሆን አንዳአንድ አካባቢዎችን ተቆጣጥሯል። ባለው ግጭት ምክንያት በጊምቢ እና ናጆ፣ ጊምቢ እና ደንቢ ዶሎ፣ እንዲሁም ጊዳሚ እና አሶሳ መካከል ያሉ መንገዶች መዘጋታቸው ተዘግቧል (ቢቢሲ አማርኛ፣ ነሃሴ 8, 2013)። ዝርዝሩ ከዚህ በታች ይብራራል።
እንዲሁም ኦነግ-ሸኔ እና ትህነግን የሚያወግዙ ሰላማዊ ሰልፎች በኦሮሚያ ክልል አምቦ፣ ዱከም፣ አሰላ፣ ገላን፣ ሆለታ፣ ሸኖ፣ እና አዳማ ከተሞች ውስጥ ተካሂደዋል። ሰልፎች በተመሳሳይ ሲዳማ ክልል ሐዋሳ ከተማ ተካሂደዋል። ነሃሴ 5, 2013 ላይ ኦነግ-ሸኔ እና ትህነግ ‘የአብይን መንግስት ለማስወገድ’ አብረው ለመስራት ጥምረት መፍጠራቸውን አሳውቀዋል። ነሐሴ 11 ቀን 2021 ኦነግ-ሻኔ እና ህወሓት “የአብይን መንግስት ለማስወገድ” በጋራ ለመስራት ህብረት እንደሚሰሩ አስታወቁ (ኤፒ፣ ነሃሴ 5, 2013፤ ሮይተርስ፤ ነሃሴ 5, 2013)።
ነሐሴ 8, 2013 ላይ እንደተዘገበው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከፌዴራል ፖሊስ እና የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና፣ ሕዝቦች፤ ሲዳማ፤ እና ጋምቤላ ክልሎች ልዩ ኃይሎች ጋር በመሆን በቤንሻንጉል/ጉሙዝ መተከል በሚገኘው ጉባ ወረዳ ከማይታወቅ ታጣቂ ቡድን ጋር ተዋግቶ ከ170 በላይ የቡድኑን አባላት መግደሉ ተዘግቧል (የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ነሃሴ 8, 2013፤ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ነሃሴ 8, 2013)። ከሱዳን የመጣው ታጣቂ ቡድን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እየተገነባ በሚገኝበት የጉባ ወረዳ ውስጥ ሁከት ለመፍጠር አስቦ ነበር። ከተገደሉት ውስጥ 16 የትህነግ አባላት እንደሆኑ ይታመናል። በተጨማሪም 32 ከትህነግ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች ከሱዳን ወደ ክልሉ ለመግባት ሲሞክሩ በአሶሳ ዞን ኩርሙክ ወረዳ በቁጥጥር ስር ውለዋል (የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ነሃሴ 11, 2013)።
በመጨረሻም ነሐሴ 9, 2013 ላይ በደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ኮንሶ ዞን ሰገን ከተማ በሚገኝ አንድ ምግብ ቤት ላይ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ጥቃት ማድረሳቸው ተዘግቧል። በጥቃቱ ሦስት ሰዎች ሲሞቱ አምስት ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር፣ ነሃሴ 10, 2013)።
ሳምንታዊ ትኩረት:- የኦነግ-ሸኔ እንቅስቃሴ ከትህነግ ጋር ህብረት ከመሰረተ በኋላ
ኦነግ-ሸኔ ተብሎ የሚጠራው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በ2010 ከኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦነግ) ተገነጠለ። ከህዳር 2012 ጀምሮ በመላው ደቡባዊ እና ምዕራባዊ ኦሮሚያ ከፌዴራል እና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ኃይሎች ጋር ግጭት ጀመረ (ከዚህ በታች ያለውን ካርታው ይመልከቱ)። የቡድኑ መሪ ጃል ማሮ (ኩምሳ ድሪባ) ነሃሴ 5, 2013 ላይ ቡድኑ ከትህነግ ጋር ትብብር መፍጠሩን ካሳወቀበት ጊዜ ጀምሮ ኦነግ-ሸኔ የሚሳተፍባቸው እንቅስቃሴዎች ጨምረዋል (ቪኦኤ፣ ነሃሴ 5, 2013)። በደቡብ ኦሮሚያ ነገሌ ከተማ አቅራቢያ ባሉ አካባቢዎች ውጊያዎች የተባባሱ ሲሆን በአቅራቢያው በሚገኘው ጉሚ ኤልዳሎ ወረዳ ውስጥ የኦነግ-ሸኔ ኃይሎች አንዳንድ ቦታዎችን ተቆጣጥረዋል። ባለፈው ሳምንት በምዕራብ ወለጋ ዞንም ግጭቶችም የተጠናከሩ ሲሆን ታጣቂዎች ለአጭር ጊዜ መንገዶችን ተቆጣጥረው መንገድ መዝጋታቸው ተዘግቧል (ቢቢሲ አማርኛ፣ ነሃሴ 8, 2013)። ቡድኑ በወለጋ ዞን ሆሮ ጉድሩ ከፌደራል እና የኦሮሚያ ክልላዊ ሀይሎችን ጋር ከተዋጋ በኋላ በአባይ ጮመን አቅራቢያ ያለውን የፊንጫ ስኳር ፋብሪካን ተቆጣጥሬያለሁ ብሏል (የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መግለጫ፣ ነሃሴ 16, 2013) ባለፈው ሳምንት 22 የኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች ቡድኑ ከዚህ ቀደም እንቅስቃሴ ባልነበረበት ሐዋሳ (ሲዳማ ክልል) ውስጥ በቁጥጥር ስር ውለዋል (ቪኦኤ አማርኛ፣ ነሃሴ 11, 2013፤ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ነሃሴ 16, 2013)። ሐዋሳ በአዲስ አበባ-ሞያሌ መንገድ በኩል የምዕራብ አርሲ እና ምዕራብ ጉጂ/ጉጂ የኦሮሚያ ዞኖችን የሚያገናኝ መንገድ ላይ ያለ ከተማ ነው።
ኦነግ-ሸኔ የተቆጣጠራቸው ቦታዎች ቡድኑ በቀደምት ግዜያት ከሚያደርገው አጥቅቶ ወደ ጥልቅ የኦሮሚያ ጫካዎች የመሄድ ልምድ እንደተላቀቀ ያሳያሉ። ኦነግ-ሸኔ የትህነግን ግዛት ይዞ የመቆየት የጦርነት ስልት ለመተግበር በላው ፍላጎት የተጠናከረ ይመስላል። የኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች ግዛት ይዘው መቆየት መቻላቸው በሚቀጥሉት ሳምንታት የሚፈተን ይሆናል።
ኦነግ-ሸኔ እና ትህነግ ወሰን በሚጋሩ ክልሎች ውስጥ አለመንቀሳቀሳቸው አዲስ የተመሰረተው ትብብር ያለው ጥቅም ግልጽ እንዳይሆን አድርጎታል። ትህነግ ማንኛውንም አይነት የጦር መሳሪያም ሆነ ልምድ አነስተኛ መሣሪያ ላላቸው የኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች ጋር እንዲያካፍል መንግሥት በሚቆጣጠረው ክልል ውስጥ ማለፍን ይጠይቃል። በቡድኖች መካከል ያለውን የታሪካዊ ልዩነት ከግምት ውስጥ በማስገባት የጥምረቱን ጎጂ ውጤቶች ለመተንተን ቀላል ነው። በትህነግ አገዛዝ ወቅት በኦሮሚያ ውስጥ ጭቆና እና ከፍተኛ የፀጥታ አፈና ለደረሰባቸው ግለሰቦች ከማዕከላዊ መንግስት ጋር በሚደረገው ውጊያ ትህነግን የሚጠቅም አጋር አድርጎ ማሳየት ከባድ ስራ ይሆናል።
የአማጽያኑን ትብብር ተከትሎ በመንግስት በኩልም እንቅስቃሴዎች እንደአዲስ ተጀምረዋል። በሃዋሳ ከታሰሩት 22 ታጣቂዎች በተጨማሪ መንግስት በመላው ሃገሪቷ ከኦነግ-ሸኔ እና ትህነግ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በብዛት አስሯል፣ ንግዶችንም ዘግቷል። በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ባለፈው ሳምንት 117 ንግዶች ተዘግተዋል (ቪኦኤ አማርኛ፣ ነሃሴ 13, 2013)። 93 ግለሰቦች በጋምቤላ ታስረዋል (የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ነሃሴ 7, 2013)። ፀረ-መንግስት ከሆኑ ቡድኖች ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የተጠረጠሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ባለፈው ሳምንት በቤንሻንጉል/ጉሙዝ መታሰራቸው ተዘግቧል። በተመሳሳይ መልኩ እስሮች በሶማሌ ክልልም ተካሂደዋል (ዲደብሊው አማርኛ፣ ነሃሴ 13, 2013)። ተመሳሳይ እስሮች እንዲሁም የጋዜጠኞች መታፈን የመቀጠል እድሉ ሰፊ ነው።
የኢትዮጵያ መንግስት ፌስቡክ፣ ትዊተር፣ እና ዋትስአፕን የሚተኩ ሃገራዊ የማህበራዊ ድህረ-ገጾችን የመፍጠር ፍላጎት እንዳለው ገልጿል (ሮይተርስ፣ ነሃሴ 17, 2013)። የመንግስት ሃላፊዎች ለረዥም ግዜ የድህረ-ገጽ ድርጅቶችን የውሸት መረጃ እና ፀረ-መንግስት የሆኑ መልእክቶች እንዲስፋፉ በማድረግ ሲከሱ ቆይተዋል።
በተያያዘ መንግስት ማንኛዉም አቅም ያለው እና የሚችል ግለሰብ መከላከያን እንዲቀላቀል ጥሪ ማቅረቡን ቀጥሏል (ኒው ዮርክ ታይምስ፣ ነሃሴ 16, 2013)። በመላው ሃገሪቷ የሚካሄዱ ምልመላዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን ለጦርነት አደራጅተዋል። ትህነግን ለመታገል ያለው ዝግጁነት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ የክልል ልዩ ሃይሎች፣ እንዲሁም ታጣቂዎች መስጠት በሚችሉት ስልጠና ይወሰናል። በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ትግራይ፣ እና ቤንሻንጉል/ጉሙዝ ያሉ አመጾች ሲጨምሩ መንግስት የደህንነት ሁኔታዎች ላይ ያለው የቁጥጥር አቅም መፈተኑን ይቀጥላል።