በቁጥር (ከመጋቢት 24, 20101እነዚህ ቁጥሮች የሚያመለክቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደስልጣን ከመጡበት መጋቢት 24, 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገሪቱ የተከሰቱ የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶችን፣ በዚህ ምክንያት የደረሱ የሞት ጉዳቶች፣ እንዲሁም በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ የተቃጡ ጥቃቶችን ነው። እስከ ሃምሌ 23, 2013)2አክሌድ እስከ ነሀሴ መጨረሻ ድረስ የተመዘገቡ ኩነቶችን ህትመት ይገታል። ከሐምሌ 24, 2013 እስከ ነሀሴ 28, 2013 ያሉ መረጃዎች የኩነቶች ህትመት ጷጉሜ 1, 2013 ላይ በድጋሚ ሲጀምር የሚለቀቁ ይሆናል። በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን እንዲሁም ኢትዮጵያን የተመለከቱ ሁሉንም የአክሌድ መረጃዎች ማውረድ ይችላሉ።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 1,735
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 9,294
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 4,944
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን እዚህ፣ ሁሉንም የአክሌድ ስራዎች ደግሞ እዚህ ጋር በመጫን ያገኛሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ባለፈው ሳምንት በመላው ኢትዮጵያ በአፋር፣ አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ትግራይ፣ እና ሶማሌ ክልሎች ውጊያዎች ተዘግበዋል።
ነሐሴ 12, 2013 ላይ በኦሮሚያ ክልል የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ታጣቂዎች በጊዳ ኪራሙ (ምስራቅ ወለጋ፣ ኦሮሚያ) የሚገኝ የአማራዎች ሰፈራ ቦታን አጥቅተው ቢያንስ 150 ሰዎች ገድለዋል (የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ነሃሴ 20, 2013)። ምንም እንኳን የኦነግ-ሸኔን ተሳትፎ ጨምሮ በድርጊቱ ዙሪያ ያሉ ዝርዝሮች አከራካሪ ቢሆኑም አንዳንዶች የሟቾች ቁጥር ከዚህ በጣም ከፍ ያለ እንደሆነ ይገምታሉ። የኦነግ-ሸኔ ተወካዮች ኃይሎቻቸው በግጭት ውስጥ ተስታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን አጥቅተዋል የሚለውን ውድቅ አድርገው ይልቁንም ሞት የተከሰተው በአካባቢው ከሚገኙ የብሄር ታጣቂዎች ጋር በተደረገ ውጊያ እንደሆነ ገልጸዋል (የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መግለጫ፣ ነሃሴ 19, 2013)። ይህንን ተከትለው በነበሩ ውጊያዎች ተጨማሪ 60 ሰዎች ተገድለዋል (የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ነሃሴ 20, 2013)።
የሚንቀሳቀሱ በታጠቁ የጎሳ ሚሊሻዎች መካከል በተደረገው ከፍተኛ ውጊያ መካከል የሞት አደጋ ተከስቷል (የኦላ መግለጫ ፣ ነሐሴ 25 ቀን 2021)። በጊዳ ኪራሙ ከተከሰቱት ክስተቶች በኋላ ተከስተው ለተጨማሪ 60 ሰዎች ሞት ምክንያት ሆነ (የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ፣ ነሐሴ 26 ቀን 2021)።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የፌዴራል ኃይሎች በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች፣ እና ህዝቦች ክልል እና በጉጂ-ሞያሌ መንገድ በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው የምዕራብ ጉጂ ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ 40 የኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች ሲገደሉ ተጨማሪ 35 ማቁሰላቸውን ተናግረዋል (ቪኦኤ፣ ነሃሴ 22, 2013)። የኦነግ-ሸኔ ኃይሎች ከትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ሕወሓት) ጋር ጥምረት መፍጠራቸውን ካሳወቁ በኋላ አንዳንድ ከተሞችና መንደሮች መቆጣጠራቸውን ገልጸዋል። በደቡባዊ እና ምዕራባዊ ኦሮሚያ ስለጨመረው የኦነግ-ሸኔ እንቅስቃሴ የበለጠ መረጃ ለማግኘት ኢፒኦ ሳምንታዊ:- ከነሃሴ 8, 2013 እስከ ነሃሴ 14, 2013 ይመልከቱ።
በአማራ ክልል የመንግስት ሃይሎች ደብረ ዘቢጥ፣ ጨጨሆ፣ ነፋስ መውጫ፣ እና ጋይንትን ጨምሮ የተለያዩ ከተሞችን መልሰው መቆጣጠር ችለዋል። የትህነግ ሃይሎች ነፋስ መውጫን ጨምሮ የተለያዩ ከተሞችን ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ዘርፈዋል ተብሏል።
ከስር በዝርዝር እንደሚገለጸው የአፋር እና ሶማሌ ክልሎችን በሚያወዛግቡ ግዛቶች ላይ ያለው ግጭት ባለደው ሳምንት በድጋሚ ያገረሸ ሲሆን ኡንዱፎ ከተማ (አፋር ክልል) እና ጋርባ ሲሴ (ሶማሌ ክልል) አካባቢ ባሉ የገጠር አካባቢዎች ላይ ውጊያ እና ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሞት ተዘግቧል (ቪኦኤ፣ ነሃሴ 22, 2013)። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በአወዛጋቢዎቹ አካባቢዎች የሚገኙ 30 የምርጫ ጣቢያዎችን በግጭት ፍራቻ ከሰረዘ በኋላ ሚያዚያ 2013 ላይ በአካባቢው ውጊያ ነበረ (የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ፣ መጋቢት 15, 2013)።
ሳምንታዊ ትኩረት:- በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ሞት ያስከተሉ ኩነቶች ላይ ያሉ የሚጋጩ እይታዎች
ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ውስጥ በተከሰቱ በርካታ ሟች በተመዘገበባቸው ክስተቶች ዙሪያ ያሉ የሚጋጩ እይታዎች በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ የግጭት ቦታዎችን አስቸጋሪ እና የተክፋፈለ ሁኔታ የሚያሳይ ነው። በተለይም በምዕራብ ኦሮሚያ እና በሶማሌ/አፋር ድንበር ላይ ያሉ ሁለት ኩነቶች የተቃራኑ ታሪኮችን ብቅ ማለት ያንፀባርቃሉ።
በ1960 እና 1970ዎቹ ከአማራ/ኦሮሚያ ክልላዊ ድንበር በስተደቡብ የሰፈሩ አማራዎች በምዕራብ ኦሮሚያ ምስራቅ ወለጋ ዞን አልፎ አልፎ በመሬት እና በሀብት ዙሪያ ከአካባቢው የኦሮሞ ነዋሪዎች ጋር ይጋጫሉ (ዘላለም ተፈራ፣ ኢጄቢኢ 2010 (እኤአ))። ይህ ጉዳይ በክልሉ ውስጥ የፖለቲካ ስልጣንን ለኦሮሞ ባለሥልጣናት በሚሰጠው የኢትዮጵያ የብሔር-ፌደራሊዝም የአስተዳደር ሥርዓት ምክንያት ተባብሷል። በአካባቢው አናሳ የሆኑ ህዝቦች የአካባቢውን ባለስልጣናት በግጭት ወቅት ከታጣቂ ድርጅቶች ጋር በመወገን ይከሳሉ።
ከላይ እንደተገለፀው ነሐሴ 12, 2013 እና ቀጣይ ቀናት ላይ በእነዚህ የሰፈራ አካባቢዎች ግጭት ጨምሮ ነበር። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እንደገለጸው ከኦነግ-ሸኔ ጋር ግንኙነት ያላቸው ታጣቂዎች በምስራቅ ወለጋ ጊዳ ኪራሙ ነዋሪዎች ላይ ጥቃት አድርሰው 150 ሰዎችን “በብሔር ማንነታቸው ምክንያት” ገድለዋል (የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ነሃሴ 20, 2013)። ኮሚሽኑ ከመጀመሪያው ጭፍጨፋ በኋላ ባሉት ቀናት “የብሔር በቀልን” መሠረት በማድረግ ሌሎች 60 ግድያዎች መፈጸማቸውን ገልጿል (የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ነሃሴ 20, 2013)።
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በቃል አቀባዩ በኩል የኮሚሽኑን መግለጫ ወዲያውኑ ውድቅ አድርጓል። ይልቁንም ሞት የተከሰተው በኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች እና ወደ ክልሉ ድንበር አቋርጠው የኦሮሞ ገበሬዎችን ከአወዛጋቢ ግዛቶች ባፈናቀሉ የአማራ ታጣቂዎች መካከል በተደረገው ከባድ ውጊያ መሆኑን ገልጿል (የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መግለጫ፣ ነሃሴ 19, 2013)። መግለጫው ኦነግ-ሸኔ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን አጥቅቷል የሚለውን ክስ አልተቀበለም። በዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ፓርቲ በተመሳሳይ ሁኔታ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ያወጣውን መግለጫ የኮነነ ሲሆን ኮሚሽኑ ድርጊቱን ለማጣራት ያደረገው አካሄድ አድሎአዊ እና ሙያዊ ያልሆነ ነው የሚል ወቀሳ ሰንዝሯል (የኦሮሞ ነፃነት ግንባር፣ ነሃሴ 21, 2013)።
ሁለተኛው ከፍተኛ ሞት የተመዘገበበት ኩነት ባለፈው ሳምንት በሶማሌ እና አፋር ክልሎች መካከል በሚያወዛግቡ አካባቢዎች ላይ የተከሰተ ሲሆን የሟቾችን ቁጥር የተመለከቱ ዝርዝር መረጃዎች የተወሰኑ ናቸው። የአፋር ክልል ባለሥልጣናት የሶማሌ ታጣቂዎች በኡንዱፎ ከተማ ውስጥ የአፋር ተወላጆችን ማጥቃታቸው የአዲስ አበባ-ጅቡቲ አውራ ጎዳና እንዲዘጋ ምክንያት ሆኗል ብለዋል (ቪኦኤ፣ ነሃሴ 22, 2013)። የሶማሌ ክልል ባለሥልጣናት በተመሳሳይ በሳምንቱ ውስጥ ለተከሰተው ሁከት የአፋር ብሔረሰብ ታጣቂዎች እና ልዩ ሃይሎችን የከሰሱ ሲሆን ግጭቱ የተነሳው የሱማሌ ነዋሪዎችን ውዝግብ ካለባቸው አካባቢዎች ለመግፋት በተደረገው ጥረት ነው ብለዋል። በብሔረሰቦቹ መካከል ውጊያ የተከሰተው ጋርባ ሲሴ አቅራቢያ ቃላክሌ አካባቢ፣ በካንዱፎ ቀበሌ ቢርታድሄር እና ሮቱ አካባቢዎች፣ እና ካድዬቲ ከተማ በ40 ኪሜ ርቀት ላይ በሚገኙት ቢያካዴ እና ፉርታ ገላ አካባቢዎች ነው (ቢቢሲ ሶማሊኛ፣ ነሃሴ 22, 2013)።
ሁለቱም ክስተቶች ኢትዮጵያን በሚመለከት የግጭት መረጃ ውስጥ ከሚታወቅ አዝማሚያ ጋር ይጣጣማሉ። ከፍተኛ ሞት የሚመዘገብባቸው ክስተቶች የመንግስት ለውጥ በ2010 ከተደረገ ወዲህ እየጨመሩ ነው። ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንግስት የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ጋር ሲነፃፀር ባለፈው አመት ከፍተኛ የሞት አደጋ ክስተቶች ተዘግበዋል (ከዚህ በታች ያለውን ምስል ይመልከቱ)። በተለይ መንግስታዊ ባልሆኑ ታጣቂዎች የሚደረጉ የጅምላ ሞት ክስተቶች በዝተዋል እንዲሁም በመላ አገሪቱ ከአፋር እስከ ቤንሻንጉል/ጉሙዝ ድረስ ተስፋፍተዋል። ይህ ከቀድሞው አገዛዝ መውደቅ እና ከአብይ አገዛዝ ጀምሮ ያለው የተሻለ ዘገባ እና ተደራሽነት ውጤት ሊሆን ይችላል (ምንም እንኳን ይህ የተሻለ ተደራሽነት ካለፈው አንድ ዓመት ወዲህ እየወረደ ነው)። ሆኖም ግን የኃይል ፉክክር ከፍተኛ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎችን ሞት ያስከተለበት እድል ሰፊ ነው።
ቡድኖች ብዙውን ጊዜ በክልሉ ውስጥ ባሉ ሌሎች ታጣቂዎች እንደሃይለኛ ለመታየት በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ የጅምላ ግድያ ያካሂዳሉ (ራሌይ, 2012(እኤአ)ን ይመልከቱ)። በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ‘ዝቅተኛ ወጪ’ ያላቸው ዒላማ ሲሆኑ አዲስ ታጣቂ ቡድኖች ወይም በአዲስ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ዝናቸውን እና የመዋጋት/መግደል ችሎታቸውን ከመገንባታቸው በፊት ከጠንካራ ቡድን ጋር ለመዋጋት አይፈልጉም።
ሆኖም የኢትዮጵያ ጉዳይ በሌሎች አገሮች ከሚገኙት በሁለት ምክንያቶች ይለያል:- አንደኛ ማንኛውም ቡድን ለእነዚህ ግድያዎች ኃላፊነቱን መውሰድ አይፈልግም። አንዴ ከተቋቋመ በኋላ የታጠቁ ቡድኖች ‘ሕጋዊነታቸውን’ የሚገነቡ ሲሆን በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎችን መግደል ይህንን ያጠፋል። ብዙውን ጊዜ የተቋቋሙ ቡድኖች እነዚህን ግድያዎች ‘ላልታወቁ’ የታጠቁ ቡድኖች ‘ውል’ ያደርጋሉ ወይም ተሳትፎአቸውን ይክዳሉ። ሁለተኛ ትህነግ እና ኦነግ በግጭቱ አከባቢ ሊተኩዋቸው የሚፈልጓቸው ሌሎች መንግስት ያልሆኑ የታጠቁ ቡድኖች የሉም (ትህነግም ሆነ ኦነግ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ከፍተኛ ሞት የተከሰተባቸው ክስተቶች ላይ ተሳትፈዋል ተብለው የተከሰሱ መንግስት ያልሆኑ ቡድኖች ናቸው)።
በአጭሩ በአሁኗ ኢትዮጵያ ግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን በጋራ የሚያስጨፈጭፍ ግጭት የተቀላቀለበት ውድድር የለም። በዚህም ምክንያት መንግስት ባልሆኑ ታጣቂ ቡድኖች በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ባልሆኑ ግለሰቦች ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎች አንድን ቡድን በማሳተፋቸው እንደ ‘ቅጣት’ አልያም ግለሰቦች በአንድ የኢትዮጵያ አካባቢ መቆየት ከመረጡ የሚያጋጥማቸውን አደጋ ማሳወቂያ መንገድ ነው።
ከምርጫ ጋር የተያያዙ ክርክሮች ወቅታዊ ሁኔታ
ባለፈው ሳምንት ነሐሴ 21, 2013 ላይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ ባቀረበው የድህረ-ምርጫ ክርክር ላይ ውሳኔ ሰጥቷል። ሐምሌ 14, 2013 ኢዜማ በደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል በሚገኙ 28 የምርጫ ክልሎች ምርጫውን እንደገና እንዲካሄድ ጠይቆ ነበር። ፍርድ ቤቱ ሁሉንም ማስረጃዎች ከመረመረ እና ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ከሰማ በኋላ ከ28 የምርጫ ክልሎች ውስጥ በምርጫ ወረቀቱ ላይ የኢዜማ ፓርቲ ዕጩዎች ስሞች እና ምስሎች ባልተካተቱባቸው አራት የምርጫ ክልሎች ላይ ምርጫው በድጋሚ እንዲካሄድ ወስኗል (የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ነሃሴ 21, 2013)። አራት የምርጫ ክልሎች ላሳካ፣ ኩቻ ልዩ፣ ጉመር 2፣ እና ብርብር ናቸው። በምርጫ እና በድምጽ ቆጠራ ወቅት ‘ታዛቢዎች እንዲሳተፉ አልተፈቀደላቸውም’ በሚል ቅሬታ ምርጫው ድጋሚ እንዲካሄድ ጥያቄ የቀረበባቸውን 22 የምርጫ ክልሎች ፍርድ ቤቱ ፓርቲው ዝርዝር መረጃ አላቀረበም በሚል ምክንያት ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል (የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ነሃሴ 21, 2013)።
በተመሳሳይ የጋምቤላ ከተማ እና ጊዮሌ ልዩ የምርጫ ጣቢያዎችን በተመለከተ ጥያቄ የቀረበው የጊዜ ገደቡ ካለፈ በኋላ ነው በሚል ፍርድ ቤቱ ምርጫው በድጋሚ እንዲካሄድ የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል (የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ነሃሴ 21, 2013)። በምርጫ ደንቡ መሠረት ከምርጫ፣ ቆጠራ፣ እና ምርጫ ውጤቶች ጋር የተያያዙ አቤቱታዎች ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ መቅረብ ያለባቸው ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አቤቱታዎችን የተመለከተ ውሳኔ ባሳለፈ በ10 ቀናት ውስጥ ነው (የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና፣ የምርጫ ስነምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011፣ አንቀጽ 155)። ከምርጫ ጋር የተያያዙ አቤቱታዎች መጀመሪያ የሚቀርቡት ለምርጫ ቦርድ ሲሆን ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ የማለት እድል አለ።
የደቡብ–ምዕራብ ክልልን ለማቋቋም ሕዝበ ውሳኔን ጨምሮ ምርጫ በሐረሪ፣ ሶማሌ፣ እና ደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልሎች መስከረም 20, 2014 ይካሄዳል። መጀመሪያ ምርጫው ጷጉሜ 1, 2013 ላይ እንዲካሄድ ታቅዶ ነበር። ባለፈው ሳምንት ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ካደረገ በኋላ የምርጫውን ቀን ወደ መስከረም 20 እንዲዘዋወር ወስኗል (የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ነሃሴ 18, 2013)። ምንም እንኳን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ከመስከረም 20 ምርጫ በፊት የተሰጠ ቢሆንም ከላይ በተጠቀሱት አራት የምርጫ ክልሎች ውስጥ ምርጫው በመስከረም 20, 2014 መካሄዱ ግልፅ አይደለም።