በቁጥር (ከመጋቢት 24, 2010 እስከ መስከረም 28, 2014)1 እነዚህ ቁጥሮች የሚያመለክቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደስልጣን ከመጡበት መጋቢት 24, 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገሪቱ የተከሰቱ የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶችን፣ በዚህ ምክንያት የደረሱ የሞት ጉዳቶች፣ እንዲሁም በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ የተቃጡ ጥቃቶችን ነው።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 2,045
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 12,123
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 5,621
በቁጥር (ከመስከረም 22, 2014 እስከ መስከረም 28, 2014)2በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተካተቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ቁጥሮች ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 9
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 12
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 0
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን እዚህ፣ ሁሉንም የአክሌድ ስራዎች ደግሞ እዚህ ጋር በመጫን ያገኛሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
በሰሜን ኢትዮጵያ ያሉት ውጊያዎች በመስከረም አጋማሽ አካባቢ ለአጭር ጊዜ ረገብ ካሉ በኋላ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ሕወሓት) መካከል ባለፈው ሳምንት በድጋሚ አገርሽቷል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። መስከረም 27 እና 28, 2014 ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ትህነግ በያዛቸው በሰሜን ወሎ ዞን ውርጌሳ ከተማ አቅራቢያ፣ በደቡብ ወሎ ዞን በወገልጤና (ሁለቱም በአማራ ክልል)፣ እና የአፋር ክልልን ከአማራ ክልል ጋር በሚያገናኘው መንገድ ላይ በርካታ የአየር ጥቃቶችን ፈጽሟል (ሮይተርስ፣ መስከረም 29, 2014)።
መስከረም 24, 2014 ላይ ግጭቶች እየጨመሩ በመሄዳቸው የአውሮፓ ፓርላማ በትግራይ ግጭት ላይ ባለ 17 ነጥብ የውሳኔ ሀሳብ አጽድቋል። በዚህ ውሳኔ ውስጥ ከሌሎች ጉዳዮች በተጨማሪ ፓርላማው የአውሮፓ ምክር ቤት “የጦር እና ሌሎች ወታደራዊ መሣሪያዎችን ለኢትዮጵያ እና ለኤርትራ ማዘዋወር እና መሸጥ የሚያስቆም የጦር መሣሪያ ማዕቀብ እንዲያሳልፍ” አሳስቧል (የአውሮፓ ፓርላማ፣ የአሰራር ሂደር: 2021/2902(RSP)፣ መስከረም 24, 2014)።
በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ጎሮ ዶላ ወረዳ አዳዲ ቀበሌ ሙጋዮ አካባቢ ውስጥ በኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ እና በመንግሥት ኃይሎች መካከል ውጊያ ቀጥሏል (ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት፣ መስከረም 27, 2014)። በተጨማሪም እምኞች ባለፈው ሳምንትም ኦነግ-ሸኔ በሆሮ ጉዱሩ ዞን አቤ ደንጎሮ ወረዳ 12 ቀበሌዎችን ተቆጣጥሮ እንደሚገኝ ገልጸዋል (ኢሳት፣ መስከረም 28, 2014)። ኦነግ-ሸኔ በእነዚህ ቦታዎች የአማራዎችን ንብረት እንደዘረፈ ተነግሯል። በዚህም ምክንያት ከነዚህ ቀበሌዎች የተፈናቀሉ ከ10,000 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በአቤ ደንጎሮ ወረዳ በቱሉ ዋዩ ከተማ መጠለያ ውስጥ ይገኛሉ (ኢሳት፣ መስከረም 28, 2014)። በተጨማሪም ኦነግ-ሸኔ በምዕራብ ወለጋ ዞን ደንቢ ደሎ ውስጥ ኤርቡ ገበያ ከሚገኙ ሦስት ቀበሌዎች በስተቀር ሁሉንም ይቆጣጠራል (ኢሳት፣ መስከረም 28, 2014)።
ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ በተካሄደው የኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ አንዳንድ ተሳታፊዎች ፀረ-መንግስት መፈክሮችን ያሰሙ ሲሆን የኦሮሞ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ጠይቀዋል (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር፣ መስከረም 22, 2014)። አንድ ጋዜጠኛን ጨምሮ አንዳንድ ሰልፈኞች ታስረዋል። የኢሬቻ በዓል በኦሮሞዎች ዘንድ በየዓመቱ የሚከበር የምስጋና በዓል ነው።
በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል የካማሺ ዞን ለሳምንታት በቤንሻንጉል ሕዝቦች ነፃነት ግንባር ቁጥጥር ከቆዩ በኋላ በቅርቡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወደ ዞኑ መግባቱን ተከትሎ በካማሺ ዞን ከሚገኙ ሁለት ቀበሌዎች ከ13,000 በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል (ዲደብሊው አማርኛ፣ መስከረም 26, 2014)። እንደክልሉ መንግስት ከሆነ በአሁኑ ወቅት በክልሉ ከ490,000 በላይ ተፈናቃዮች ይገኛሉ (ዲደብሊው አማርኛ፣ መስከረም 26, 2014)።
ሳምንታዊ ትኩረት: አዲሱ መንግስት የተጋረጡበት ችግሮች
መስከረም 24, 2014 ላይ፣ የተመረጡ እና የተሾሙ የአዲሱ መንድስት አባላት ወደ ስልጣን መጡ።
ሰኔ 2013 ላይ በተደረገው ምርጫ አርባ አምስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች እና 125 ነፃ እጩዎች ተሳትፈዋል። የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን (ኦነግ), ኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)፣ እና ኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) ጨምሮ አንዳንድ ፓርቲዎች ራሳቸውን ከምርጫው አግልለዋል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካሉ 5473ለቀሩት የተወሰኑ ወንበሮች ምርጫ መስከረም 20 2013 ላይ ተካሂዷል። በደህንነት ጉዳይ ምርጫ ባልተካሄደባቸው ቦታዎች ምርጫው መቼ እንደሚካሄድ ግልጽ አይደለም። ምርጫው የዘገየባቸው አካባቢዎች ትግራይ ክልልን፣ በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ካማሺ እና መተከል ዞኖች፣ እና በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ያሉ የተወሰኑ የምርጫ ክልሎችን ይጨምራሉ። መቀመጫዎች ለ436 ምርጫ ተካሂዷል። ከእነዚህ 436 መቀመጫዎች ውስጥ በአብይ አህመድ የሚመራው የብልጽግና ፓርቲ 410 መቀመጫዎችን አሸንፏል (የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ሃምሌ 5, 2013)። ሶስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች – የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)፣ እና የጌዲዮ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት- በቅደም ተከተል አምስት፣ አራት፣ እና ሁለት መቀመጫዎችን አሸንፈዋል። ገለልተኛ ተወዳዳሪዎች አራት መቀመጫዎችን አሸንፈዋል።
በሀረሪ እና ሶማሌ ክልሎች እንዲሁም በደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ክልሎች ባሉ አንዳንድ የምርጫ ክልሎች እስከ መስከረም 20, 2014 ዘግይተው ነበር። የእነዚህ ምርጫዎች ውጤት አዲሱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመጀመሪያውን ስብሰባ እስካካሄደበት እለት ድረስ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አልተገለጸም። በመሆኑም 425 አዲስ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ብቻ ተገኝተዋል።4በሃምሌ 2013 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአማራ ክልል ካሉ የምርጫ ክልሎች በአምስቱ እና በደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ካሉት ደግሞ በሶስቱ የምርጫ ክልሎች ውስጥ በሰኔ 2013 የተካሄደውን ምርጫ እንዲደገም ወሰነ። እነዚህ የድጋሚ ምርጫዎች መስከረም 20 2013 ላይ ተካሂደዋል። የምርጫዎቹ ውጤት ገና አልተገለጸም። በመሆኑም የቀሩት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወንበሮች አልተሟሉም።
ባለፈው ሳምንት በህገ-መንግስቱ መሰረት አዲሱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አብይ አህመድን በድጋሚ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው እንዲቀጥሉ መርጧል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሀለማርያም ደሳለኝ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ለሦስት ዓመታት የዘለቁ ተቃውሞዎችን ተከትሎ ከስልጣን በመልቀቃቸው ወደ ስልጣን የመጡት አብይ ለመጀመሪያ ጊዜ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሾሙት መጋቢት 24, 2010 ነበር። አብይ ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው በፊት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሙሉ በሙሉ በገዢው ጥምር ፓርቲ – የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) – ቁጥጥር ስር ነበር። የአሁኑ ሹመት ምርጫን ተከትሎ አብይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙበት የመጀመሪያ ጊዜ ነው።
መስከረም 25, 2014 ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ 22 የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን5በቀደመው ጊዜ 20 የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ነበሩ። በአብይ የተቋቋመው አዲሱ መንግስት እነዚህን መስሪያ ቤቶች ወደ 22 አሳድጓል። ከ22 ውስጥ አምስቱ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ማለትም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር፣ እና የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በአዲስ መልክ የተዋቀሩ ናቸው። በተጨማሪም የንግድ ሚኒስቴር ቀጠናዊ ትሥሥርን ይጨምራል። የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሎጂስቲክ ይጨምራል። የሴቶች፣ ህጻናት፣ እና ወጣቶች ሚኒስቴር አሁን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ተደርጓል። በተመሳሳይ የቀድሞው የፕላን ሚኒስቴር አሁን የፕላን ልማት ሚኒስቴር ተደርጓል። የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ፍትህ ሚኒስቴር ተብሎ ተሰይሟል። አሁንም በድሮ ስማቸው የሚጠሩት የግብርና ሚኒስቴር፣ የማዕድን ሚኒስቴር፣ የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የትምህርት ሚኒስቴር፣ የጤና ሚኒስቴር፣ የመከላከያ ሚኒስቴር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ እና የሰላም ሚኒስቴር ናቸው (ኢቢሲ፣ መስከረም 24, 2014)። አስተዋውቀዋል እንዲሁም ሚኒስትሮችን ሾመዋል። አዲስ ከተሾሙት ሚኒስትሮች ውስጥ ሦስቱ የተሾሙት ከተለያዩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ማለትም ከኦነግ፣ አብን፣ እና ኢዜማ ነው። የኢዜማ ሊቀመንበር የትምህርት ሚኒስትር ሆነው የተሾሙ ሲሆን የአብን ሊቀመንበር የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል። የኦነግ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል። በተመሳሳይ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት የተለያዩ የክልል መንግስታት ሲመሰረቱም ሹመቶች ተሰጥተዋቸዋል።
አብይ እነዚህን ሹመቶች ሲሰጡ ከብሔር ይልቅ በልምድ ላይ መመስረታቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም በእነዚህ ሹመቶች የእጩዎቹን “የትውልድ ቦታ” እና ሃይማኖት ለማብዛት እንደሞከሩ ገልጸዋል (ኢቢሲ፣ መስከረም 24, 2014)።
በአገሪቱ ሰላምና ፀጥታን ለማቀላጠፍ ሦስት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች አስፈላጊ ናቸው። እነዚህም የፍትህ ሚኒስቴር፣ የመከላከያ ሚኒስቴር፣ እና የሰላም ሚኒስቴር ናቸው። የፍትህ ሚኒስቴር በ2008 ከፈረሰ እና በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ከተተካ በኋላ አሁን እንደገና ተቋቁሟል። የመከላከያ ሚኒስቴር እንደገና ያልተዋቀረ ቢሆንም የመከላከያ ሚኒስትሩ ብሄር ጎልቶ የሚወጣ ነው – ከትግራይ የሆነ እና በህዳር 2013 የተቋቋመውን የትግራይ የሽግግር መንግሥት ላይ በመምራት ያገለገለ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ በ2010 አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከተሾሙ በኋላ የተቋቋመው የሰላም ሚኒስቴር ኃላፊነቶች እንደገና ተስተካክሏል። ሌሎቹ ጉልህ ለውጦች ዋና ዋና የመረጃ፣ ደህንነት፣ እና ገንዘብ ተቋማት አሁን ተጠሪነታቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት መሆኑ ነው (Aአዲስ ስታንዳርድ፣ መስከረም 26, 2014)።
ለአምስት አመታት እንዲመራ የሚጠበቀው ይህ መንግሥት የሕገ-መንግሥት አወቃቀር እና በመላ አገሪቱ የሥልጣን ክፍፍል ላይ ጉልህ ለውጦች ሊያመጣ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል። የአብይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ተሃድሶ ዋና ማዕቀፍ መደመር ሲሆን ይህም የኢህአዴግ ዘመን አብዮታዊ ዴሞክራሲ ምትክ ነው። አብዮታዊ ዴሞክራሲ ከማርክስ-ሌኒን-ማኦይ አስተሳሰብ የተወሰደ ፅንሰ-ሀሳብ ሲሆን (ዣን-ኒኮላስ ባች፣ 2003) ልሂቃን ብዙሃኑን ወደ አብዮት እና የሀገሪቱን የዴሞክራሲ ሂደት መምራት አለባቸው የሚል ነው። “የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦችን የጋራ መብቶችን ይጠብቃል” (ዣን-ኒኮላስ ባች፣ 2003)። በአንፃሩ የመደመር አላማ የኢትዩጵያ ብዝሃነት ላይ በመመስረት ያለፉ ስህተቶችን ማረም ነው (አብይ አህመድ፣ ጥቅምት 10, 2012)። የጽንሰ-ሐሳቡ ሶስት ምሰሶዎች ብሔራዊ አንድነት፣ የዜጎች ክብር፣ እና ብልጽግና ናቸው። ፅንሰ-ሀሳቡ በኢትዮጵያ ባህል፣ ንቃተ-ህሊና፣ እና አስተሳሰብ “የተቀረጸ” ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲን ይደግፋል (አብይ አህመድ፣ ጥቅምት 10, 2012)።
አብዮታዊ ዴሞክራሲ በአስተዳደራዊ ደረጃ ውድድሮችን ፈጥሯል እንዲሁም ተመሳሳይ ብሔረሰብ ካለባቸው አካባቢን ለሚወክሉ መደበኛ የመንግሥት የሥራ ቦታዎችን ሰጥቷል። ይህ የድንበር ውዝግቦችን፣ የስልጣን ሽኩቻዎችን፣ የመንግስት ጭቆናን፣ እና ድብልቅ ብሄረሰቦች ያሉባቸውን አካባቢዎች በአንድ ብሔር ለመቀየር ሙከራ አድርጓል። አብይ በአገር አቀፍ ደረጃ ሥልጣን እንዴት እንደሚደራጅ ፣ እንደሚከፋፈል፣ እንደሚሰጥ፣ ወይም እንደሚለወጥ ገና መግለጽ ይጠበቅበታል። ይህ የእርግጠኝነት መጥፋትን ያመጣ ሲሆን ማንኛውም ለውጥ ከመደረጉ በፊት ስልጣንን ለመጠየቅ እና ለመያዝ በአካባቢ ደረጃ ውድድርን እየፈጠረ ነው።
ግጭቱ በፌዴራሊዝም ዙሪያ እና የማዕከላዊ ስልጣን ከክልል ስልጣን ጋር ሲነጻጸር ካለው ቦታ ጋር ከተያያዘበት የትግራይ ክልል ውጭ በተቀረው ኢትዮጵያ ውስጥ የሚነሱ አብዛኛዎቹ ግጭቶች ከአከባቢ አስተዳደር እና የስልጣን ሽኩቻዎች ጋር የተያያዙ ናቸው። አንዳንድ ቡድኖች ራስን ማስተዳደርን ይጠይቃሉ፣ ሌሎች ደግሞ በአከባቢ አስተዳደር ደረጃ ውክልና ይጠይቃሉ። እንደነዚህ ያሉ አለመግባባቶችን የሚፈቱ ተቋማት ደካማ በመሆናቸው በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ግጭቶች ተደጋጋሚ የመሆን አዝማሚያ አላቸው። በመላው ኢትዮጵያ የሚነሱ ግጭቶች ብዙ ጊዜ አካባቢ ላይ ይጀምሩና ወደ ውጭ ያድጋሉ። የአካባቢ አስተዳደሮች ሁከቱን መቆጣጠር ቢኖርባቸውም ብዙውን ጊዜ ይህንን ለማድረግ አይችሉም ወይም በቀጥታ ለግጭቱ አስተዋፅኦ ያደርጋሉ።
የአስተዳደር ግጭት ምሳሌዎች ከሆኑት መካከል በሶማሌ እና አፋር ክልሎች ድንበር ላይ በሶማሌዎች እና አፋሮች መካከል በተደጋጋሚ የሚነሱት ግጭቶች ይጠቀሳሉ (የኢፒኦን አፋር-ሶማሌ ድንበር ግጭት ገጽ ይመልከቱ)። በሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልሎች ድንበርም ላይ ተደጋጋሚ ግጭቶች አሉ። ቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች እና በዋናነት በጉሙዝ ታጣቂ ቡድን እና በመንግስት ወታደሮች መካከል ያሉ ግጭቶች አስተናግዷል። እነዚህ ግጭቶች በከፊል የሚገናኙት ከአስተዳደራዊ ድንበሮች እና በመተከል ዞን ውስጥ ባለው የስነ-ሕዝብ አወቃቀር (አማራዎች በአካባቢው ስለሰፈሩ) ጋር ይዛመዳሉ። በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል በቤንች ሸኮ እና ሰገን አካባቢ ሕዝቦች ዞኖች ውስጥ ሁከቶች በተደጋጋሚ የሚነሱ ሲሆን በክልሉ ውስጥ አዳዲስ ዞኖች (ለምሳሌ ኮንሶ) ከተመሰረቱ በኋላ ጨምረዋል (የኢፒኦን ቤንች ሸኮ (ቤንች ማጂ ዞን) ግጭት እና ሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን ግጭት ገጾችን ይመልከቱ)። በሁለቱም አካባቢዎች የሚነሱ ግጭቶች ከአስተዳደር ጋር የተያያዙ እና ከሰፊ የራስ ገዝ አስተዳደር ጥያቄ ጋር የሚያያዙ ናቸው።
ጠንካራና እምነት የሚጣልባቸው የተቋማት ማዕቀፍ አለመኖር እና ከአካባቢያዊ ባለሥልጣናት ጋር ያለው ግንኙነት አዲሱ መንግስት ከሚጋረጡበት ችግሮች መካከል ይጠቀሳሉ። ምንም እንኳን በከፍተኛው ደረጃ ላይ አንዳንድ ለውጦች ቢደረጉም የታችኛው አስተዳደር አሁንም በ2010 እንደነበረው ነው። ኢህአዴግ ከተበተነ በኋላ የመንግስት እና የፓርቲው ግንኙነት እንዲሁም በፌደራል እና አካባቢ ደረጃ ውሳኔ እንዴት እንደሚተላለፍ ግልጽ አይደለም። ከ2010 ጀምሮ አንዳንድ የፌዴራል እና የክልል መንግስታት ተቋማት አመራሮች ሁከት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ሥራቸውን ባለመወጣታቸው ተይዘው ተከሰዋል። በታጣቂ ቡድኖች ተደጋጋሚ ጥቃቶች የተጎዱ ሰዎች የመንግሥት የፀጥታ ዘርፍ እነሱን መጠበቅ አለመቻሉ ላይ ጥያቄ ያነሳሉ። መንግስት በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ዜጎችን መጠበቅ አለመቻሉን ከቀጠለ ጥበቃ ፍለጋ ወደ ታጣቂ ቡድኖች ሊዞሩ የሚችሉበት ዕድል አለ።
አዲሱ መንግሥት ለውጡን በአካባቢ ደረጃ እንዴት እንደሚተገብርው ወይም በብሔራዊ ቀውስ ወቅት ጉልህ ሥልጣን ካለው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ካቢኔ ጋር ለሕገመንግሥታዊ ለውጦች እንዴት እንደሚገፋ ገና ግልፅ አይደለም። በከፍተኛው ደረጃ የታየው የለውጥ መንፈስ በመሬት ላይ በቀጥታ ከህዝብ ጋር የሚገናኙት የአከባቢ አስተዳደሮች ደረጃ አልታየም። አዲስ የተቋቋመው መንግሥት በፌዴራል ደረጃ የታዩትን ለውጦች እስከ ታችኛው የአስተዳደር ደረጃዎች ማድረስ አለበት። የፀጥታውን ዘርፍ ማሻሻል እና በግጭት አፈታት ተቋማት ላይ እምነት መገንባት አለበት። የኢትዮጵያ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በአካባቢ ደረጃ ዘላቂ ሰላም መኖርን ይጠይቃል።