በቁጥር (ከመጋቢት 24, 2010 እስከ ህዳር 3, 2014)1እነዚህ ቁጥሮች የሚያመለክቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደስልጣን ከመጡበት መጋቢት 24, 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገሪቱ መከሰታቸው የተዘገበ የግጭት ኩነቶችን ነው።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 2,204
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 12,698
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 5,816
በቁጥር (ከጥቅምት 27, 2014 እስከ ህዳር 3, 2014)2 በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተካተቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ቁጥሮች ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 47
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 140
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 38
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን እዚህ፣ ሁሉንም የአክሌድ ስራዎች ደግሞ እዚህ ጋር በመጫን ያገኛሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል ኦሮሞ ልዩ ዞን በትግራይ ህዝብ ነጻነት ግንባር (ትህነግ/ህወሃት) ሃይሎች እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መካከል ከፍተኛ ግጭት ቀጥሏል። በደዋ ጨፋ (ማጀቴ) እና በከሚሴ ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች ውጊያዎች ተካሂደዋል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነግ)-ሸኔ በመባልም ይታወቃል) ታጣቂዎች እንደነበሩ እና ከትህነግ ጎን በመሆን ከመንግስት ጋር እንደተዋጉ ተዘግቧል። ተጨማሪ ውጊያ በዋግ ሃምራ ዞን (ቆዘባ ቀበሌ) በትህነግ ሃይሎች እና የአማራ ክልል ልዩ ሃይሎች እና ታጣቂዎች ጋር ተካሂዷል።
ሳምንቱን ሙሉ በትህነግ ሃይሎች እና በአፋር ታጣቂዎች እና ልዩ ፖሊስ መካከል ውጊያ መካሄዱ ተዘግቧል። ስትራቴጂካዊ የሆነችው ሚሌ ከተማ መያዟ (ስህተት) የተወራ ቢሆንም ከባቲ ከተማ በስተምስራቅ በሚገኘው የካሳ ጊታ/ቡርቃ ግንባር ጦርነቱ ቀጥሏል (ኢቢሲ፣ ህዳር 5, 2014)። በአፋር ክልል ጦርነቱ በጭፍራ አካባቢ የቀጠለ ሲሆን በሁለቱም በኩል በግዛት ቁጥጥር ላይ ብዙም ለውጥ አላመጣም።
በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ማንዱራ ከተማ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ባልሆኑ ሰዎች ላይ ጥቃት በመሰንዘር አራት ሰዎች ሲገደሉ 6 ሰዎች አቁስለዋል። በምላሹ በተወሰደ የጸጥታ እርምጃ የ19 ሰዎች ህይወት ማለፉን ዘገባዎች ያሳያሉ። በቤንሻንጉል ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ በሚመራ አመጽ መሃል በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ ጥቃቶች እንዲሁም ውጊያዎች ተከስተዋል። እንደ መንግስት ምንጮች ከሆነ ባለፈው ሳምንት በአሶሳ ዞን ሸርቆሌ ወረዳ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ የቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል ልዩ ሃይል፣ እና የአካባቢ ታጣቂዎች ከቤንሻንጉል ህዝብ ነፃነት ንቅናቄ ጋር ተዋግተዋል (ኢቢሲ፣ ህዳር 3, 2014)። ግጭት ፈጥረው እንደነበር የመንግስት ምንጮች ገለፁ። የመንግስት ምንጮች ብዙ ጊዜ ታጣቂዎቹ በትህነግ እንደሚደገፉ ይገልጻሉ።
በምዕራብ ኦሮሚያ ባለፈው ሳምንት ውጊያ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በምስራቅ ወለጋ ምዕራብ ሸዋ ዞን (አቡነ ግንዴ በረት) እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ውጊያ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና አጋር የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይሎች እና በኦነግ-ሸኔ ሃይሎች መካከል የሚካሄደው ውጊያ ተጠናክሮ ቀጥሏል (ዲደብሊው አማርኛ፣ ህዳር 4, 2014)። በኦነግ-ሸኔ ሃይሎች እና በመንግስት ወታደሮች መካከል የተደረገውን ውጊያ ተከትሎ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ቀዬያቸውን ለቀው እየተሰደዱ ሲሆን ቤንሻንጉል/ጉሙዝ ውስጥ ተጠግተው ይገኛሉ (ኢቢሲ፣ ህዳር 4, 2014)።
በመላው ኢትዮጵያ ፀረ-ትህነግ የተቃውሞ ሰልፎች ሳምንቱን በሙሉ መካሄዳቸው የተዘገበ ሲሆን በቡሌ ሆራ (ኦሮሚያ)፣ ጅጅጋ (ሶማሌ)፣ አርባ ምንጭ (ደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል)፣ ወራቤ (ደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል)፣ አምቦ (ኦሮሚያ)፣ አሰላ (ኦሮሚያ)፣ ሃዋሳ (ሲዳማ)፣እና ቦንጋ (ደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል) ሰልፎች እንደነበሩ ተዘግቧል። ዋና ከተማዋ አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም ዋና ከተሞች ሊባል በሚቻል ሁኔታ ሳምንቱን ሙሉ ትልልቅ መንግስትን የሚደግፉ ሰልፎች ተካሂደዋል።
ሳምንታዊ ትኩረት: ግጭት እየተባባሰ ባለበት ወቅት በመላው ኢትዮጵያ የተመዘገቡ እስራቶች
በኢትዮጵያ ሰሜን እና ምዕራብ ክፍሎች ያለው ግጭት በተጠናከረበት ወቅት የኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ መሆን ሲጀምር የመንግስት የፖሊስ ሃይሎች ከትህነግ ወይም ኦነግ-ሸኔ ጋር ግንኙነት አላቸው በተባሉ ግለሰቦች ላይ ከፍተኛ እርምጃ ወስደዋል። በርካቶች የመንግስትን በመላ ሀገሪቱ ፀጥታ የማስከበር ስራዎችን አላማ ሲደግፉ ሌሎች ደግሞ መንግስት ግለሰቦችን በማንነታቸው ኢላማ አድርጓቸዋል እንዲሁም የፖለቲካ ልዩነቶችን የሚገልጹ ለጥቃት ሊጋለጡ ይችላሉ የሚል ስጋት አላቸው። የኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ባለሥልጣኖች ከ”አሸባሪ ቡድኖች” ጋር እንደሚተባበር “ምክንያታዊ ጥርጣሬ” ካለ ማንኛውንም ሰው ያለፍርድ ቤት ማዘዣ እንዲይዙ ይፈቅዳል (የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5/2014)። በአሁኑ ጊዜ ለስድስት ወራት ያህል የሚቆየው አዋጅ በሥራ ላይ እስካለ ድረስ ያለፍርድ ቤት ምልከታ ማሰር ይቻላል (የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5/2014)።
ባለፈው ሳምንት በሐረር ከተማ ከኦነግ-ሸኔ ወይም ትህነግ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የተጠረጠሩ 300 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል (ዲደብሊው አማርኛ፣ ህዳር 2, 2014)። በሀዋሳ (ሲዳማ)፣ ወላይታ (ደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል)፣ አርሲ ነገሌ (ኦሮሚያ)፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው እስራቶች ተፈፅመዋል (ኢቢሲ፣ ህዳር 4, 2014፤ ቦርከና፣ ህዳር 5, 2014፤፤ ኢቢሲ፣ ህዳር 7, 2014)። ለአለም የምግብ ፕሮግራም የሚሰሩ 72 አሽከርካሪዎች በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በቁጥጥር ስር ውለዋል (ቢቢሲ፣ ህዳር 1, 2014)። በአዲስ አበባ የትግራይ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ “በዘር ላይ የተመሰረተ የዘፈቀደ እስራት” አለ የሚል ክስ በአዲስ አበባ የፌዴራል ፖሊስ ላይ የቀረበ ሲሆን ፖሊስ ክሱን አጣጥሎታል (አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ህዳር 3, 2014፤ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ህዳር 3, 2014)።
በሚዲያ ኤጀንሲዎች ላይ እርምጃ መወሰዱም ተዘግቧል። በሶማሌ ክልል አራት የናባድ ቲቪ ጋዜጠኞች ቴሌቭዥን ጣቢያው በመንግስት ባለስልጣናት ተዘግቶ ብዙም ሳይቆይ መታሰራቸው ተነግሯል (ቢቢሲ አማርኛ፣ ህዳር 4, 2014)። ናባድ ቲቪ መጋቢት 2013 ላይ በተሾሙት የቀድሞዋ የሴቶች፣ ህጻናት፣ እና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትር ፊልሳን አብዱላሂ የተመሰረተ ነው። ፊልሳን መስከረም 2014 ላይ “የግል ጉዳዮችን” በመጥቀስ ከመንግስት ስራቸው ለቀዋል (አዲስ ስታንዳርድ፣ መስከረም 18, 2014)። የኢትዮጵያ ሚዲያ ኤጀንሲ ለፈው ሳምንት ለግል ሚዲያ ጋዜጠኞች ዘገባዎች በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያለውን አንድምታ እንዲያጤኑ ጠይቋል (አዲስ ስታንዳርድ፣ ህዳር 3, 2014)። ማስጠንቀቂያው የመጣው እንደ ከአሃዱ ሬዲዮ ያሉ ጋዜጠኞች ለሳምንታት በእስር ላይ ከሆኒ በኋላ ነው (ኢትዮጵያ ኢንዳይደር፣ ህዳር 3, 2014)።
በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሰረት የግለሰቦች እና ከመገናኛ ብዙሃን ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎች መታሰራቸው የፖለቲካ ምህዳሩ ላይ ያለውን አዲስ ጫና ያሳያል። በአንድ በኩል የኢትዮጵያ ፌደራል ባለስልጣናት ታጣቂዎች መንግስትን ለመገልበጥ የሚፈልጉ ታጣቂዎች ለፈጠሩት አደገኛ የጸጥታ ሁኔታ ምላሽ እየሰጡ ነው። በሌላ በኩል እንደዚህ አይነት ድርጊቶች የፌደራል መንግስቱን ለወደፊት የዲሞክራሲ ሂደቶች እንደ እውነተኛ አጋር የመታየት ችሎታ እስከመጨረሻው ሊያበላሹ ይችላሉ።