በቁጥር (ከመጋቢት 24, 2010 እስከ ጥር 6, 2014)1እነዚህ ቁጥሮች የሚያመለክቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደስልጣን ከመጡበት መጋቢት 24, 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገሪቱ መከሰታቸው የተዘገበ የግጭት ኩነቶችን ነው።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 2,460
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 14,226
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 6,416
በቁጥር (ከታህሳስ 30, 2014 እስከ ጥር 6, 2014)2በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተካተቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ቁጥሮች ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 26
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 122
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 38
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን እዚህ፣ ሁሉንም የአክሌድ ስራዎች ደግሞ እዚህ ጋር በመጫን ያገኛሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ባለፈው ሳምንት በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ እና የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች መካከል ያለው ግጭት በመላ ኦሮሚያ ተባብሶ ቀጥሏል። በምዕራብ ሸዋ ዞን ጮቢ እና ኖኖ አካባቢዎች፣ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሆሮ ቡሉክ እና አቤ ዶንጎሮ ወረዳዎች፣ በጉጂ ዞን ዋደራ እና ጉራ ዶሌ ወረዳዎች ውጊያዎች እንደነበሩ ተዘግቧል። በታህሳስ 2014 ላይ በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል ያለው ግጭት ከተረጋጋ በኋላ የመንግስት ሃይሎች በአማፂያኑ ላይ የሚወስዱትን እርምጃ አጠናክረው ቀጥለዋል። በሳምንቱ ውስጥ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ጃል ኦዳ ከብሶ የሚባል የቡድኑን ክከፍተኛ አመራር ጨምሮ የኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎችን በሀረር እና በድሬዳዋ ከተሞች መያዛቸው ተዘግቧል።
በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል የመንግስት ምንጮች የድንበር ወረራ ሙከራ ሲሉ በገለጹት ሁኔታ ከትግራይ ህዝብ ነጻነት ግንባር (ትህነግ/ህወሀት) ጋር የተቆራኙ ሃይሎች በገመድ እና ሰዳል ወረዳ በሚገኙ አካባቢዎች ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና ከቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል ልዩ ሃይሎች ጋር ተዋግተዋል። የመንግስት ምንጮች ታጣቂዎቹ የትህነግ አካል እንደሆኑ ቢገልጹም ምናልባትም በቅርቡ በተቋቋመው የኢትዮጵያ ፌደራሊስት እና ኮንፌደራሊስት አንድነት ግንባር አካል የሆነው እና ከትህነግ ጋር ያበረው የቤንሻንጉል ሕዝብ ነፃ አውጪ ንቅናቄ (ቤሕዴን) ታጣቂዎች ሳይሆኑ አይቀርም። የቡድኑ ታጣቂዎች ብዙ ጊዜ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጋር በሱዳን ድንበር በኩል ወደ ኋላ እና ወደ ፊት ያቋርጣሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በትግራይ ክልል ባለው ግጭት ከፍተኛውን ቦታ የሚወስደውና በኢትዮጵያ መንግስት የሚወሰደው የአየር ጥቃት ቀጥሏል (ከዚህ በታች ያለውን ምስል ይመልከቱ)። በሳምንቱ ውስጥ ቢያንስ ሁለት የአየር ድብደባዎች በትግራይ ክልል መከሰታቸው ታውቋል። የመጀመሪያው ጥቃት በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ውስጥ በማይ ፀምሪ 17 በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎችን ገድሏል (ሮይተርስ፣ ጥር 3, 2014)። ሁለተኛው በመቀሌ በሚገኘውን የቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት በመምት ሶስት ሰዎችን ገድሏል (ፍራንስ 24፣ ጥር 6, 2014)።
ጥር 5 እና 6 ላይ የትህነግ ሃይሎች በአፋር ክልል በትግራይ ክልል አዋሳኝ ላይ የምትገኘውን አባላ ከተማን በከባድ መሳሪያ ደብድበዋል። በዋግ ኽምራ ዞን (አማራ ክልል) ሰቆጣ እና አበርገሌ ወረዳዎች በትህነግ እና የመንግስት ታጣቂዎች እንዲሁም ተባባሪ የአማራ ታጣቂዎች መካከል ተጨማሪ ውጊያዎች ተዘግበዋል። ስለ ግጭቶች ተጨማሪ መረጃ ከዚህ በታች ባለው ሳምንታዊ ትኩረት ውስጥ ይካተታል።
ሳምንታዊ ትኩረት፡ በትህነግ እና የኢትዮጵያ መንግስት መካከል የሚደረጉ ድርድሮችን የሚያደናቅፈው ምንድን ነው?
በትግራይ፣ አፋር፣ እና አማራ ክልሎች በሚገኙ አከራካሪ መሬቶች ላይ እየተካሄደ ያለው ጦርነት በኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት እና ትህነግ መካከል የሚደረጉ የውይይት አማራጮችን እያደናቀፉ ነው። ትህነግ ከአፋር እና ከአማራ ክልል “ለሰላም ወሳኝ መክፈቻ ነው” ብሎ እንደለቀቀ ቢገልጽም ሳምንቱን ሙሉ በዋግ ኽምራ ዞን አበርገሌ እና ሰቆጣ ወረዳዎች እንዲሁም በሰሜን ጎንደር ዞን አዲ አርቃይ ጦርነት ቀጥሏል (ዲደብሊው አማርኛ፣ ታህሳስ 1, 2014)። በተመሳሳይ የትህነግ ሃይሎች ባለፈው ሳምንት በአፋር ክልል አባላ ከተማን ቢያንስ ለሁለት ቀናት በከባድ መሳሪያ በመደብደብ በሰመራ -አባላ – መቀሌ መንገድ ወደ ትግራይ ክልል የሚጓዙ የሰብአዊ እርዳታ የያዙ መኪኖች እንዲዘገዩ አድርጓል (የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት፣ ጥር 5, 2014)።
የመንግስት ሃይሎችም እንዲሁ ጦርነቱ እንዲቆም ያደረጉት ነገር ትንሽ ነው። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወደ ትግራይ ክልል እንደማይዘልቅ ቢገለጽም እንዲሁም ብሔራዊ ውይይት እንደሚደረግ ቢነገርም በደቡብ ትግራይ ዞን ራያ አላማጣ በዋጃና ጥሙጋ አካባቢዎች ሳምንቱን ሙሉ ከመንግሥት ጋር የተገናኙ ኃይሎች ከትህነግ እየተዋጉ መሆኑ ታውቋል። ከላይ ባለው የሁኔታዎች አጭር መግለጫ እንደተጠቀሰው የኢትዮጵያ አየር ሃይል ከግንባሩ ርቀው በሚገኙ አካባቢዎች ቢያንስ ሁለት የአየር ድብደባዎች አድርጓል። በጥቅምት 2013 ጦርነቱ ሳይደመር በፊት በትግራይ ክልል ስር የነበረው የምዕራብ ትግራይ ዞን በአማራ ክልል መንግስት ሃይሎች ቁጥጥር ስር ይገኛል።
ማንኛውም አይነት ድርድር ወይም የሰላም ግንባታ ሂደት ከመጀመሩ በፊት የጦርነት ማቆም ስምምነት መመስረት እንዳለበት ባለሙያዎች ይስማማሉ (አል ጀዚራ፣ ጥር 1, 2014)። ይሁን እንጂ የትኛውም አካል ውዝግብ ያለበትን ግዛት በመቆጣጠር ወደ ድርድር ቢገባ በድርድር ወቅት የበላይነት ይኖረዋል የሚል ስሜት አለ። ስለሆነም በአሁኑ ወቅት የተራዘመው ግጭት ዋነኛው መንስኤ በዋነኛነት የግዛት ሲሆን ሁለቱም ወገኖች ወታደራዊ አቅም እስካላቸው ውጊያው ሊቀጥል ይችላል። የምዕራብ ትግራይ ክልል ጉዳይ በህዳር 2013 ጦርነት መጀመሪያ ላይ እንዳደረገው ሁሉ ዛሬም ግጭቱን እየገፋው ይገኛል። ግጭቱ ሲጀመር ምዕራብ ትግራይ ከአማራ ክልል በመጡ ሃይሎች የተወሰደ ሲሆን በትህነግ ቁጥጥር ስር ያለው የደቡብ ትግራይ ዞን የአማራ (ወሎ) የብሄረሰብ መገኛ ነው የተባለውን ግዛት (ራያ) ያጠቃልላል።
የህዝብ ድጋፍ ጉዳዮችም አሉ። ተይዘው የነበሩ አንዳንድ የትህነግ መሪዎች በይቅርታ መፈታት ይፋ ሲደረግ ውጊያው ከሃምሌ 2013 እስከ ታህሳስ 2014 ድረስ በአፋርና በአማራ ክልሎች በነበረበት ወቅት ለተፈፀሙ ወንጀሎች ፍትህ የሚፈልጉ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ቁጣ ቀስቅሷል (ዲደብሊው አማርኛ፣ ጥር 2, 2014)። የአማራ ክልል ህዝብ ባለፈው አመት ሚያዚያ ወር በአማራ ክልል በነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ ወቅት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ እምነት ማጣቱን ገልጿል፤ የመንግስት ባለስልጣናት ከትህነግ ጋር አከራካሪውን ግዛት በተመለከተ ከትህነግ ጋር መደራደር ቀድሞውንም ደካማ የሆነውን የብልፅግና ፓርቲ የአማራ እና ኦሮሞ ክንፎች ቁርኝት ሊያበላሽ እንደሚችል ያውቃሉ። በ2013 የፀደይ ወቅት ስለነበረው የአማራ ተቃውሞ እና በብልጽግና የኦሮሞ እና አማራ ክንፎች መካከል ያለውን ውጥረት እንዴት እንዳሳየ የበለጠ መረጃ ለማግኘት ኢፒኦ ወርሀዊ:- ከመጋቢት 23, 2013 እስከ ሚያዚያ 22, 2013ን ይመልከቱ።
በትግራይ ክልልም ተመሳሳይ ጉዳይ አለ። የኤርትራ ሃይሎች መውረር እና የኢትዮጵያ ወታደሮች ትግራይን ሲቆጣጠሩ የፈፀሟቸው ወንጀሎች ለትህነግ አላማ ድጋፍ እንዲፈራ እና ፀረ-መንግስት አስተሳሰብን ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ እንዲል አድርጓል። የትግራይ ህዝብ በጦርነቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ ለተፈፀሙ ወንጀሎች፣ ከምዕራብ ትግራይ ዞን ለተፈናቀሉ የትግራይ ተወላጆች፣ እና በመንግስት የአየር ድብደባ ለተገደሉ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ፍትህ ይፈልጋል። በትግራይ ውስጥ ይህንን ግብ እውን ማድረግ የሚችሉት ብቸኛ የፖለቲካ መንገዶች ትህነግና ታጣቂዎቹ ናቸው። መንግስት ትህነግን “አሸባሪ” ብሎ የፈረጀው በመሆኑ በቅርቡ በሚካሄደው አገራዊ ውይይት ላይ ይጋበዛል ተብሎ አይታሰብም።
አሜሪካ “የመንግስት ባለስልጣናት የአየር ድብደባውን እና ሌሎች ግጭቶችን በማስቆም አሁን ያለውን የሰላም ክፍተት እንዲጠቀሙ የሚያበረታታ” አዲስ ልዩ መልዕክተኛ ለአፍሪካ ቀንድ ልኳል (ሮይተርስ፣ ጥር 7, 2014)። ሆኖም ሁለቱም ወገኖች ጦርነት ቢያቆሙ እንኳን የደኅንነት ዋስትና በሌለበት ሁኔታ በመንግስትም ሆነ ትህነግ መካከል ያለው ውጊያ አንዱ ወገን በምዕራብ እና ደቡብ ትግራይ ዞኖች ላይ ያለምንም ውዝግብ የበላይነት እስከሚያገኝ ድረስ ሊቀጥል ይችላል። ሁለቱም ወገኖች ለጦርነቱ መቀጠል እኩል ተጠያቂዎች ናቸው እንዲሁም ምንም እንኳን ባለፉት ሳምንታት ውጊያዎች ጋብ ቢሉም ግጭቱ እስካሁን አልቆመም።