ከህዳር 22, 2014 እስከ ታህሳስ 22, 2014 በጨረፍታ
ዋና ቁጥሮች
-
- አክሌድ ከህዳር 22, 2014 እስከ ታህሳስ 22, 2014 ድረስ 109 የተደራጁ የፖለቲካ የግጭት ኩነቶች የተመዘገቡ ሲሆን 754 ሟቾች ደግሞ ተመዝግበዋል።
- በወሩ ውስጥ በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት በተከሰቱ ግጭቶች ከፍተኛው የሟቾች ቁጥር የተመዘገበው በኦሮሚያ ክልል ሲሆን በክልሉ 402 ሟቾች ነበሩ። አማራ ክልል በ313 የተዘገቡ ሟቾች ቁጥር ይከተላሉ።
- ከህዳር 22, 2014 እስከ ታህሳስ 222, 2014 ባለው ጊዜ በተደጋጋሚ የተከሰተው የኩነት አይነት ውጊያ ሲሆን 60 የዚህ አይነት ኩነቶች እና 384 ሟቾች ተመዝግበዋል።
ዋና ሂደቶች
- በታህሳስ ወር ማገባደጃ ላይ በሰሜን ጎንደር ዞን (አማራ ክልል)፣ በዋግ ኽምራ ዞን (አማራ ክልል) እና በኪልባቲ ዞን 2 (አፋር ክልል) ከሚገኙ አንዳንድ ቦታዎች በስተቀር የፌደራል መንግስት በአፋር እና በአማራ ክልል የሚገኙትን አብዛኛዎቹን ክልሎች በቁጥጥሩ ስር አድርጓል።
- በትግራይ ክልል የፌደራል መንግስት ወሩን ሙሉ ባደረገው የአየር ድብደባ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎች ተገድለዋል።
- የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ ከኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይሎች፣ እና ከኦሮሚያ ታጣቂዎች ጋር ውጊያ ማድረጉን ቀጥሏል።
- በወሩ ውስጥ ብዙ ሰዎች ከትግራይ ህዝብ ነጻነት ግንባር እና ኦነግ-ሸኔ ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል ተጠርጥረው ታስረዋል።
በዚህ ሪፖርት ውስጥ
- የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
- ወርሃዊ ትኩረት:- የትህነግ መውጣት ያወጣቸው የአንድነት ጥንካሬዎች እና ድክመቶች
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
እስከ ታህሣሥ መጨረሻ ድረስ ከፌዴራል መንግሥት ጋር የሚተባበሩ ሃይሎች በመተባበር በአማራና በአፋር ክልሎች የሚገኙ በርካታ ቦታዎችን ተቆጣጥረዋል። የፌደራል ወታደሮች ወደ ሰሜን ሲጓዙ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ በጋሸና ዙሪያ በሚገኙ በርካታ አካባቢዎች ከትህነግ ሃይሎች ጋር ከፍተኛ ውጊያ ተደርጓል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። በዋግ ኽምራ ዞን (አማራ ክልል) እና ቂልባቲ-ዞን 2 (አፋር ክልል) የሚገኙ አንዳንድ ቦታዎች በትህነግ ቁጥጥር ስር ናቸው (ዲደብሊው አማርኛ፣ ር 13, 2014)።። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ “የመጀመሪያውን ኦፕሬሽን በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን” ተከትሎ ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋልሰዋል (የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት – ኢትዮጵያ፣ ህዳር 29, 2014)።
ትህነግ ጥር መጨረሻ ላይ ከፍተኛ ዘረፋና የንብረት ውድመት፣ ጾታዊ ጥቃቶችና፣ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ባልሆኑ ግለሰቦች ላይ ሌሎች ጥቃቶችን ፈጽሟል። የወሎ ዩኒቨርሲቲ፣ የላሊበላ አየር ማረፊያ፣ የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪያል ፓርክ፣ እና በርካታ ሆስፒታሎችና የጤና ኬላዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። የአማራ ክልል መንግስት ሰሞኑን ያወጣው ግምት እንደሚያመለክተው የትህነግ ሃይሎች የደቡብ ወሎ ዞን በወረሩበት ወቅት 548 በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ገድለዋል (ቪኦኤ፣ ጥር 10, 2014)።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ታህሣሥ ወር ውስጥ በኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች እና በመንግሥት ሃይሎች መካከል የሚካሄዱ ውጊያዎች ከባድ እየሆኑ የሄዱ ሲሆን አማፂ ቡድኑ ከዚህ ቀደም እንቅስቃሴው ውስን በሆነባቸው አካባቢዎች ለምሳሌ በሰሜን ሸዋ ዞን የሚያደርገውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ ቀጥሏል። ቡድኑ ባለፉት ወራት በምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ጨምሯል። በመላው ደቡባዊ እና ምዕራባዊ ኦሮሚያ በሚገኙ ገጠራማ አካባቢዎች ውጊያ የቀጠለ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተፈናቅለዋል (ዲደብሊው አማርኛ፣ ጥር 4, 2014)። ግጭቶች ወደ ምስራቅ ኦሮሚያ (መኢሶ) ተስፋፍቷልል። ኦነግ-ሸኔ ያለባቸው እየተጠናከሩ ያሉ እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከታህሳስ 2, 2014 እስከ ታህሳስ 29, 2014ን ይመልከቱ።
ትህነግ ከአፋርና አማራ ክልሎች ከወጣ በኋላ መንግስት በትግራይ ክልል የሚያደርገው የአየር ጥቃት ጨምሯል። በታህሳስ ወር በትግራይ ክልል ቢያንስ ስድስት የአየር ድብደባዎች መደረጋቸው የተዘገበ ሲሆን ይህም በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ባልሆኑ ግለሰቦች ላይ ሞት አስከትሏል (የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ፣ ታህሳስ 21, 2014)። በትግራይ ከግጭት ጋር ተያይዞ የሞቱ ሰዎችን ለማረጋገጥ አስቸጋሪ በመሆኑ በሁሉም የአየር ድብደባዎች ምን ያህል ሰዎች እንደሞቱ አይታወቅም። የኢትዮጵያ አየር ሃይል ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ የአየር ጥቃቱ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎችን ኢላማ እንዳላደረገ ገልጸው በምትኩ ትህነግ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ወደሚታወቁ ወታደራዊ ካምፖች እንዲጠለሉ አድርጓል ሲሉ ከሰዋል (የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት/እንግሊዘኛ፣ ጥር 14, 2014)።
በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ከህዳር 22, 2014 እስከ ታህሳስ 22, 2014 በነበረው ወቅት የግጭት መጠን ቀንሷል። በአጠቃላይ መቀነሱ እንዳለ ሆኖ ግን ታህሳስ 8 ላይ በጉሬ ሻምቦላ የስደተኞች ማቆያ (ማኦ ኮሞ ልዩ፣ ቤንሻንጉል/ጉሙዝ) ላይ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች የፈጸሙትን ጥቃት ጨምሮ የተወሰኑ ኩነቶች ተዘግበዋል (ራዲዮ ሚራያ፣ ታህሳስ 29, 2014)። የፌደራል የጸጥታ ሃይሎች ከሱዳን ጋር በሚያዋስነው ክልል ውስጥ ከትህነግ ጋር ግንኙነት ያላቸው ታጣቂዎች ቢያንስ ሁለት ላይ ውጊያዎች እንደነበሩ አአስታውቀዋል።
ወርሃዊ ትኩረት፡ የትህነግ መውጣት ያጋለጣቸው በጥምረቶች ውስጥ ያሉ ጥንካሬዎችን እና ድክመቶች
ትህነግ ለወራት ወደ አዲስ አበባ ከገሰገሰ በኋላ ዋና ከተማዋን የማጥቃት እቅዱን ትቶ ታጣቂዎቹን ወደ ትግራይ ክልል ወሰን መልሷል። መንግስት ትህነግ ሳይወድ ነው ወደ ኋላ ያፈገፈገው ላለው የቡድኑ መሪዎች “በድፍረት የወሰዱት እርምጃ” ለሰላም ያላቸውን ቦታ ማሳያ ነው ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። እርምጃው በአንዳንድ የአለም አቀፍ ማህበረሰብ አባላት በመልካም ተወስዷል (ዲደብሊው፣ ታህሳስ 1, 2014)። ነገር ግን በትግራይ ክልል አዋሳኝ እና በአፋር እና በአማራ ክልሎች የሚደረገው ጦርነት መቀጠሉ እና በቅርቡ የኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም በሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያ ሃይሎች በእርግጥም በድጋሚ ወደ ትግራይ እንደሚገቡ መግለጻቸው ድርድር እንደማይካሄድ እና ጦርነቱም ለሁለተኛ አመት እንደሚቀጥል ይጠቁማል (ኢቢሲ፣ ጥር 12, 2014)።
ምንም እንኳን ውጊያው በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚቆም ባይሆንም ትህነግ ወደ ደቡብ አቅጣጫ በተጓዘበት እና በኋላም ወደኋላ ባፈገፈገበት ወቅት ውጊያዎች መባባሳቸው የግጭቱን ሁኔታ በተለያዩ መንገዶች ለውጦታል። በከፍተኛ ሁኔታ የተጠናከረው ውጊያ በመጪዎቹ ወራት በግጭቱ ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩት የሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች ጥንካሬ እና ድክመቶች አሳይቷል።
ውጥረት ያለባቸው ጥምረቶች
ከሃምሌ 2013 እስከ ታህሣሥ 2014 ትህነግ ከትግራይ ክልል ገጠራማ አካባቢዎች በወሰደው ግስጋሴ የኢትዮጵያ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ የሆነ የመሳሪያ እና የሰው ኃይል ጉዳት በመድረሱ በመሸነፍ ላይ ነበር (Newኒው ዮርክ ታይምስ፣ ጥቅምት 2, 2014)። የነበረውን አደጋ በመጋፈጥ አቢይ ከተዳከመው የኢትዮያ መከላከያ ሰራዊት የተረፈውን በፍጥነት በማስወጣት ሳምንታትን ጦሩን በማዘመን እና እንደገና በመገንባት አሳልፈዋል (ሮይተርስ፣ ታህሳስ 13, 2014፤ ኢቢሲ፣ ጥር 14, 2014። የፌደራል ወታደሮች እንደገና ለመደራጀት ከቦታው በወጡበት ወቅት ከፍተኛ የሆነው ውጊያ ለአማራ እና አፋር ክልል ሃይሎች ተትቷል። የተዳከመው የኢትዮጵያ ጦር መቆጣጠር የቻለው በስተምስራቅ ወሳኙን የሚሌ ኮሪደር እና በስተምዕራብ በኩል የሑመራ ኮሪደርን ብቻ ሆኖ ለትህነግ በስተደቡብ አቅጣጫ ወደ አዲስ አበባ ለመስፋፋት ክፍተት ፈጥረው ነበር (ኢቢሲ፣ ጥር 13, 2014)።
ወደ ደቡብ እና ምስራቅ እየገሰገሰ ካለው ትህነግ ጥቃት የተጋረጠበት የአማራ ክልል ባለስልጣናት በ2014 መጀመሪያ የክልሉን ታጣቂዎች በፍጥነት አሰባስበው የአካባቢው ባለስልጣናት የምልመላ ዘመቻ እንዲያደርጉ እና ግለሰቦችን ወደ ጦር ግንባር እንዲያመሩ አበረታተዋል (ኢትዮጵያን ኢንሳይደር፣ ሃምሌ 18, 2013)። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በአማራ ክልል የታጣቂ አመራሮች ታጥቀው ሰልጥነው በማሰልጠን ከትህነግ ጋር በተደረገው ውጊያ ወቅት ወታደራዊ ልምድ ወስደዋል። የአፋር ባለስልጣናት የሚሌ ኮሪደርን ለመከላከል በሰመራ ከተሰባሰቡ የመከላከያ ሰራዊት ጋር በቅርበት ሰርተዋል።
በአማራ ክልል የሚገኙ ሁሉም ሀብቶች ከሐምሌ 2013 መጀመሪያ እስከ ታህሳስ 19, 2014 (የአማራ መንግስት አገልግሎት እንደመደበኛው የቀጠለበት ቀን) ድረስ ለጦርነቱ የዋሉ ሲሆን ለክልሉ መንግስት ታማኝ የሆኑ ሀይሎች ብዛት ሰፍቷል (ኢትዮጵያን ኢንሳይደር፣ ታህሳስ 19, 2014)። ምንም እንኳን መጀመሪያ ላይ ባይደራጁም ታጣቂዎቹ ህዳር 2014 ላይ እየገሰገሰ የነበረው ትህነግ ላይ ጠንካራ መከላከል ለማድረግ ችለዋል። የአማራ ክልል ታጣቂዎች ከቱርክ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ፣ እና ቻይና በቅርቡ በተገዙ ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና በራሳቸው በአቢይ በሚመራ የታደሰ ብሄራዊ ጦር በመታገዝ የትህነግ ሃይሎችን በመከላከል የደቡብ ግስጋሴያቸውን እንዲተዉ አስገድደዋቸዋል።
የትህነግ ታጣቂዎች በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከደብረ ሲና በስተሰሜን በሚገኙ አካባቢዎች መገታት እነዚህ በችኮላ የተደራጁ የአማራ ሃይሎችን ጥንካሬ ከማሳየት ባለፈ የኢትዮጵያ ሰራዊት የሎጂስቲክስ ጉዳዮችን እንዲያስተካክልና የአየር ሃይሉን ለማዘመን ጊዜ ሰጥቶታል (ኢቢሲ፣ ጥር 13, 2014)። ይህ ግን ከፖለቲካ ዋጋ ጋር የመጣ ነው። እነዚህ የተጠናከሩ እና ኢ-መደበኛ እንዲሁም መደበኛ የአማራ ታጣቂዎች ለአማራ ክልል መንግስት ታማኝ ሆነው በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ አማራዎችን ጥቅም ለማስከበር የሚጥሩ ናቸው – ይህ እንቅስቃሴ ማዕከላዊውን መንግስት አሳስቧል (ሌ ሞንዴ፣ ጥር 19, 2014)።
በአማራ ክልል የትህነግ ሃይሎች ያደረሱት ውድመት የአካባቢ መሠረተ ልማቶችን ውድመት አስከትሏል እንዲሁም የሺዎችን ህይወት ረብሿል (ፍራንስ24፣ ጥር 12, 2014)። ሰዎች መንግስት ከትህነግ ሊከላከላቸው ባለመቻሉ ተበሳጭተዋል፣ ስለፌዴራል ሰራዊቱ አቅም እንዲሳሳቱ እንደተደረጉ ያስባሉ፣ እንዲሁም ወራሪ የትህነግ ታጣቂዎች በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ባልሆኑ አማሮች ላይ በፈፀሙት ግፍ አዝነዋል (የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ፣ ጥቅምት 7, 2014)። በ2013 ጀምሮ በ2014 የቀጠለው ግጭት በአብይ የሚመራው ብልፅግና ፓርቲ ላይ እምነት ያጣ እና በከፍተኛ ደረጃ የታጠቀ እና ከፍተኛ የጦር ሃይል ያለው የአማራ ክልል እንዲኖር አድርጓል (ኢፒኦ ወርሀዊ:- ከመጋቢት 23, 2013 እስከ ሚያዚያ 22, 2013)።
በአማራ እና ኦሮሞ ክልል መንግስታት መካከል ያለው ውጥረትውጥረት ባለፈው አመት የይገባኛል ጥያቄ ባለባቸው በተከሰቱ ግጭቶች እና የአስተዳደር መብቶች ላይ ታይቷል። ከፍተኛ ጥበቃና የአስተዳደር ውክልና ከመጠየቅ ጋር ተያይዞ በኦሮሚያ ለም አካባቢዎች የሰፈሩ (ወይም በመንግስት የማስፈሪያ መርሃ ግብሮች በ1970ዎቹ የሰፈሩ) አማራዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከፍተኛ ጫና ውስጥ ገብተዋል። በመሬት ወረራ ወይም በህገ-ወጥ ሰፈራ የተከሰሱት በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ እነዚህ ማህበረሰቦች ባለፉት ሁለት ዓመታት እየጨመረ በመጣው የአካባቢ ግጭቶች የጥቃት ኢላማ ሆነዋል፤ በዚህም መቶዎች ሞተዋል እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቅለዋል (ዲደብሊው አማርኛ፣ ጥር 4, 2014)። በአማራ ክልል ከዘመድ ጋር ጠንካራ ግንኙነት ያላቸው ግለሰቦች በክልሉ እየጨመረ የመጣውን የጦር ሃይል በመጠቀም ስልጠና እና ትጥቅ ፈልገዋል።
በ2013 እና 2014 በአማራ ክልል ከትህነግ ጋር የሚደረገው ጦርነት አንድ አካል ተደርገው የሰለጠኑ እና የታጠቁ የአማራ ክልል ታጣቂዎች በሌሎች የኦሮሚያ አካባቢዎች በተደረጉ ሁከትና ብጥብጥ ውድድሮች ተሳትፈዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል (ኦቢኤን፣ ጥር 5, 2014፤ አዲስ ስታንዳርድ፣ ነሃሴ 20, 2013)። ይህ ተለዋዋጭነት በሌሎች በአማራ ክልል መንግስት አስተዳደር ስር ያልሆኑ ቦታዎችን የአማራ ናቸው በሚባልባቸው የኢትዮጵያ ክፍሎችም አለ። የአማራ ታጣቂዎች በትግራይ ምዕራብ እና ደቡብ ዞኖች፣ በቤንሻንጉል/ጉምዝ ክልል መተከል ዞን፣ እና በሱዳን ድንበር (አል ፋሻጋ) እእየተንቀሳቀሱ ነው።
የትህነግ ግስጋሴ እና ማፈግፈግ በትህነግ በሚመራው ጥምረት ውስጥ ያሉ መሰንጠቆችንም አጋልጧል። ጥቅምት መጨረሻ እና ህዳር መጀመሪያ ሳምንታት ላይ የትህነግ ሃይሎች በአማራ ክልል ደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች ላይ ቁጥጥር አጠናክረው ወደ ደቡብ አቅጣጫ ወደ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ሲዘዋወሩ በትህነግ እና ከነሃሴ 2013 ጀምሮ በይፋ በተጣመረው ኦነግ-ሸኔ መካከል የተወሰኑ ውጊያዎች ነበሩ (አልጀዚራ፣ ነሃሴ 5, 2013፤ ኢሳት፣ ታህሳስ 6, 2014)።።
አንዳንድ ፀረ-መንግስት ፓርቲዎችም ትህነግ ወደ አዲስ አበባ ካደረገው ጉዞ በኋላ ራሳቸውን ከቡድኑ አሽሽተዋል። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) “ትህነግ ወደ ኦሮሚያ ክልል የሚያደርገውን ግስጋሴ እንዲያቆም” ጥሪ አቅርቧል (ዲደብሊው አማርኛ፣ ጥቅምት 27, 2014)። ይህም ኦነግን የትህነግ ህጋዊ አጋር ከሆነው የቀድሞ ታጣቂ ቡድኑ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር በተቃራኒ ቦታ አስቀምጦታል (ኢፒኦ ወርሀዊ:- ከጥቅምት 22, 2014 እስከ ህዳር 21, 2014ን ይመልከቱ)። ሁለቱ ቡድኖች ሚያዚያ 2010 ላይ በይፋ ቢለያዩም በፖለቲካ ግባቸው ግን ጎን ለጎን ጸንተዋል። ይህ መግለጫ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ከትህነግ ጋር ጥምረት ለመፍጠር ያሳለፈውን አወዛጋቢ ውሳኔ በይፋ ካሳወቁት አንዱ ነው።
ብሄራዊ ውይይት
የፌደራል መንግስቱ እየተንቀሳቀሰ ያለው ግጭቱ እንዳበቃ ነው። ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ብሄራዊ ውይይት በማድረግ የሀገሪቱ የወደፊት እጣ ፈንታ ወደመወሰን መራመድ ይፈልጋል (ዲደብሊው፣ ታህሳስ 21, 2014)። የብሔራዊ ውይይቱ “የኢትዮጵያን ችግሮች ከጥቃት በፀዳ እና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት መንገዱን ማመቻቸትን” ተስፋ ያደረገ ነውነው (አፍሪካኒውስ፣ ጥር 3, 2014)።
የፌደራል መንግስት የትህነግ ሃይሎችን ከአማራና አፋር ክልሎች መውጣታቸውን ተከትሎ በታላቅ ህዝባዊ ድጋፍ ታጅቦ ወደ ብሄራዊ ውይይት ለመግባት ተስፋ አድርጓል። አቢይ ግዛቶችን መልሰው በመያዝ ሂደት ውስጥ እራሳቸው ወታደሮቻቸውን የመሩ ሲሆን በአዲስ አበባ በሚገኙ ደጋፊዎቻቸው አካባቢ ያለው ስሜት እንደአዲስ ተጠናክሯል (ኤኤ፣ ህዳር 29, 2014)። ሆኖም ግን ይህ ስሜት በመላ ሀገሪቱ ውስጥ አይንጸባረቅም፤ ብዙዎችም የመንግስትን የውይይት አካሄድ እውነተኝነት ይጠይቃሉ።
ጅማሮው ላይ ብዙ የአማራ ክልል ተወካዮች “አሸባሪ ድርጅቶች” (ትህነግ እና ኦነግ-ሸኔን የሚጠቁም ቃል) መካተት እንደሌለባቸው እና ለውይይቱ የሚደረገውን ዝግጅት አስቸኳይነት “አጠራጣሪ” ብለውታል (ኢትዮጵያን ኢንሳይደር፣ ታህሳስ 20, 2014)። በጦርነቱ ላይ ትኩረት እንዲደረግ ተከራክረዋል። እንደ የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) ያሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥርጣሬያቸውን ቢገልጹም ውይይቱ “የአሳታፊነት እና እውነተኛ ውክልና” ደረጃዎችን እስካሟላ ድረስ እንደሚሳተፉ አመልክተዋል (ኦብነግ፣ ጥር 14, 2014)።
አሁን ያሉት ሁሉም የውይይት ኮሚቴ ዕቅዶች ትህነግ በእነዚህ ንግግሮች ውስጥ እንደማይካተት ያመለክታሉ እንዲሁም የመንግስት ሃይሎች ሊፈጠሩ ለሚችሉ ውጊያዎች እየተዘጋጁ ነው (ኢቢሲ፣ ጥር 12, 2014)። ከትህነግ ጋር የሚደረጉ ውጊያዎች እየቀነሱ ሲመጡ የመንግስት ሃይሎች በኦሮሚያ ክልል በኦነግ-ሸኔ ላይ የሚያደርጉትን ዘመቻ አጠናክረው ቀጥለዋል (ኢቢሲ፣ ጥር 4, 2014)። ዓለም አቀፍ የዕቅዱ ተቺዎች እንደሚጠቁሙት አገራዊ ውይይቱ ሁሉንም ወገኖች ባያጠቃልልና በተለይም በኦሮሚያና ትግራይ ውጊያ ባለበት ወቅት ቢካሄድ ስኬት የመኖሩ እድል አነስተኛ ነው (አልጀዚራ፣ ጥር 1, 2014)።
ኢትዮጵያ ከአሜሪካ እና አውሮፓ ህብረት ጋር ያላት ግንኙነት
ኢትዮጵያ ከአሜሪካ፣ አውሮፓ ኅብረት፣ እና ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ጋር ያላት ዓለም አቀፍ ግንኙነት በጦርነቱ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ ተለውጧል። ታህሳስ 24, 2014 ላይ አሜሪካ “በኢትዮጵያ መንግስት እና በሌሎች ወገኖች በሰሜን ኢትዮጵያ እየተስፋፋ ባለው ግጭት ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ረገጣ በመፈጸም” በሚል ኢትዮጵያን ከአጎዋ አስወጥታለች (ፍራንስ 24፣ ታህሳስ 24, 2014)። አሜሪካ ቀደም ብላ ኢትዮጵያ ከቱርክ ስለገዛቻቸው ሰው አልባ አውሮፕላኖች ቅሬታዋን አቅርባ ነበር (ሮይተርስ፣ ታህሳስ 13, 2014)።
የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት በአውሮፓ ህብረት ጥያቄ መሰረት የጠራው ልዩ ስብሰባ ታህሳስ 8, 2014 ላይ የተካሄደ ሲሆን በዚህ ወቅት “[በትግራይ] ክልል ውስጥ ከሚገኙት 10 ሰዎች ዘጠኙ ሰብአዊ እርዳታ እንደሚፈልጉ” ለልዑካኑ ተነግሯቸዋልተነግሯቸዋል (ዩኤን ኒውስ፣ ታህሳስ 8, 2014)። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ልዩ ስብሰባውን አውግዞ የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤው “አንዳንዶች ፖለቲካዊ ዓላማቸውን ለማስፈጸም” እንደሚጠቀሙበት ገልጿል (የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ታህሳስ 8, 2014)።
ኢትዮጵያ ከአሜሪካ እና አውሮፓ ህብረት መራቋ መንግስትን ለደገፉት ቱርክ፣ ሩሲያ፣ ቻይና፣፣ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አዳዲስ እድሎችን ከፍቷል (ኤዥያ ታይምስ፣ ህዳር 27, 2014)።
በአገር ውስጥ በገዥው ፓርቲ ውስጥ እና ከቀድሞ ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር ያለው ግንኙነት ይበልጥ እየሻከረ በመጣበት ወቅት መንግሥት ብሄራዊ ውይይት ሀገሪቱን አሁን ካለችበት የፖለቲካ ቀውስ ያወጣል የሚል ቁርጠኝነት እያሳየ ነው። ውይይቱ የኢትዮጵያን ዘርፈ ብዙ ግጭቶችን መቅረፍ ይቻል ወይም አይቻል ወደፊት የሚታይ ይሆናል።