በቁጥር: ኢትዮጵያ, ከመጋቢት 24, 2010 – መስከረም 6, 20151እነዚህ ቁጥሮች የሚያመለክቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡበት መጋቢት 24, 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገሪቱ የተከሰቱ የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶችን፣ በዚህ ምክንያት የደረሱ የሞት ጉዳቶች፣ እንዲሁም በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተቃጡ ጥቃቶችን ነው።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ብዛት: 3,350
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 19,259
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 8,436
ቁጥር: ኢትዮጵያ, ጷጉሜ 5, 2014 – መስከረም 6, 20152በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ብዛት: 19
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 75
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 32
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን እዚህ፣ ሁሉንም የአክሌድ ስራዎች ደግሞ እዚህ ጋር በመጫን ያገኛሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
በአዲሱ የኢትዮጵያ አመት የመጀመሪያ ሳምንት በሰሜን ኢትዮጵያ በመንግስት ኃይሎች እና በትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሓት) ኃይሎች መካከል ውጊያዎች ቀጥለዋል። ይሁን እንጂ የተቀረው የአገሪቱ ክፍል በአንጻራዊ ሁኔታ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው የፖለቲካ አለመረጋጋት ሪፖርት በመደረጋቸው የተረጋጋ ነበር።
በኢትዮጵያ አዲስ ዓመት፣ መስከረም 1 ቀን ትህነግ/ህወሓት በአፍሪካ ኅብረት የሚመራውን ከፌዴራል መንግሥት ጋር የሚደረግ የሰላም ድርድር ተቀብሏል (ትዊተር @ትግራያኢኤኦ፣ መስከረም 1, 2015)። ከዚህ ቀደም ትህነግ/ህወሓት በድርድር ጠረጴዛ ላይ ከመቀመጡ በፊት በፌዴራል መንግስት ሊሟሉ የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎችን ዝርዝር አስቀምጦ ነበር (በትህነግ/ህወሓት ሰለተቀመጠው ቅድመ ሁኔታ የበለጠ መረጃ ለማግኘት ኢፒኦ ሳምንታዊ :- ከሰኔ 26, 2013 እስከ ሐምሌ 2, 2013 ይመልከቱ)። ከዚህም በተጨማሪ ትህነግ/ህወሓት ቀደም ሲል መንግሥት ያቀረበውን በአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ የሚመራውን የሰላም ድርድር ውድቅ አድርጓል (ዘ አፍሪካ ሪፖርት፣ ነሐሴ 16, 2014፤ ትግራይ ቲቪ፣ ነሐሴ 12, 2014) ።
ይህ የሰሞኑ የትህነግ/ህወሓት መግለጫ ቢኖርም ከመስከረም 1 እስከ 4 የትህነግ/ህወሓት ኃይሎች እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል እና የአማራ ታጣቂዎች በአማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር ዞን በመተማ ግንባር መዋጋታቸውን ቀጥለዋል። በእነዚህ ውጊያዎች የትህነግ/ህወሓት ኃይሎችን በመደገፍ የቅማንት እና የጉሙዝ ብሔረሰብ ታጣቂዎች የመንግስት ኃይሎችን ተዋግተዋል። አንድ ዘገባ እንደመላከተው የሱዳን ኃይሎችም ትህነግ/ህወሓት እየረዱ እንደነበር ተገልጿል። የትህነግ/ህወሓት ኃይሎች በሱዳን ግዛት ውስጥ በሚገኘው ቱመታ ሜዶቃ አካባቢ ሆነው በመዋጋታቸው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ድንበር ተሻግሮ ከትህነግ/ህወሓት ኃይሎች ጋር እንዳይዋጋ እንቅፋት ፈጥሮበታል (ኢኤምኤስ፣ መስከረም 4, 2015)። የኢትዮጵያ መንግስት አጋር የሆኑ ኃይሎች – የአማራ ክልል ልዩ ኃይል እና የአማራ እና የፋኖ ታጣቂዎች – የሱዳንን ድንበር ጥሰው መግባት አለመግባታቸው እስካሁን ግልፅ አይደለም።
መስከረም 5 ቀን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የትህነግ/ህወሓት ኃይሎች በትግራይ ክልል በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ዞን ማይ ፀምሪ ተዋግተዋል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። በተመሳሳይ ቀን የመንግስት ኃይሎች በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ዞን አዲ አግራይ፣ ዱጋሊ፣ አዲ ዳይሮ፣ አዲ ነብሪድ እና ጸአዴ አካባቢዎችን በድጋሚ መቆጣጠራቸውን ተነግሯል። በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ዞን ሸራሮ ላይም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የኤርትራ መከላከያ ሠራዊት ከትህነግ/ህወሓት ኃይሎች ጋር ተዋግተው ብዙም ሳይቆይ አካባቢውን መቆጣጠር ችለዋል (ትግራይ ቲቪ፣ መስከረም 3, 2015)። የትህነግ/ህወሓት ኃይሎች አዛዥ የኤርትራ መከላከያ ሠራዊት በአፋር ክልል በርሀሌ፣ ሳባ፣ ሻኢ ጉቢ እና ዋሴማ አካባቢዎችን እንደገና መቆጣጠሩን እንዲሁም የአፋር ኃይሎች በአፋር ክልል ዋልሁ፣ አባላ እና ካላ አካባቢዎችን እንደገና መቆጣጠራቸውን ተናግረዋል (ትግራይ ቲቪ፣ መስከረም 3, 2011)።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በመቀሌ በርካታ የድሮን ጥቃቶችን አድርጓል። ትህነግ/ህወሓት እነዚህ የአየር ድብደባዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ሲገልፅ ሌሎች ዘገባዎች ደግሞ የአየር ጥቃቱ የቡድኑን ወታደራዊ ማዕከላት እና የሚዲያ ማዕከል ደምጺ ወያኔ ላይ እንዳነጣጠረ አመላክተዋል (ትዊተር፣ @ረዳ_ጌታቸው፣ መስከረም 3, 2015፤ ትዊተር፣ @ረዳ_ጌታቸው፣ መስከረም 4, 2015፤ ትግራይ ቲቪ፣ መስከረም 4, 2015፤ ኢኤምኤስ፣ መስከረም 14, 2015)።
በኦሮሚያ ክልል ካለፉት ሳምንታት ጋር ሲነጻጸር ትንሽ ኩነቶች ተዘግበዋል። ባለፈው ሳምንት በምዕራብ ሸዋ ዞን ጊንጪ እና አምቦ መካከል በምትገኘው ሜቲ በምትባል ስፍራ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል እንደሆኑ የሚገመት የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ታስሮ የነበረን መምህር በጥይት ገድለውታል። መምህሩ ጷጉሜ 4 ቀን ከቡራዩ ወደ ጀልዱ በአውቶብስ ሲጓዝ “ያለ ምክንያት” በቁጥጥር ስር ውሎ ጊንጪ ማረሚያ ቤት ውስጥ ታስሮ እንደነበር ተነግሯል (ኦኤምኤን፣ መስከረም 6, 2015)።