በቁጥር: ኢትዮጵያ, ከመጋቢት 24, 2010 –ጥቅምት 18, 20151እነዚህ ቁጥሮች የሚያመለክቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡበት መጋቢት 24, 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገሪቱ የተከሰቱ የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶችን፣ በዚህ ምክንያት የደረሱ የሞት ጉዳቶች፣ እንዲሁም በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተቃጡ ጥቃቶችን ነው።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ብዛት: 3,546
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 20,271
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 8,979
በቁጥር: ኢትዮጵያ, ከጥቅምት 12- 18, 20152በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ብዛት: 29
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 107
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 15
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን እዚህ፣ ሁሉንም የአክሌድ ስራዎች ደግሞ እዚህ ጋር በመጫን ያገኛሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ባለፈው ሳምንት በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ትላልቅ መንግስትን የሚደግፉ ሰልፎች ተካሂደዋል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። ሰልፈኞቹ “ለኢትዮጵያ እቆማለሁ ድምፄን አሰማለው” በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የምዕራባውያንን ጣልቃ ገብነትን አውግዘዋል። የተቃውሞ ሰልፎቹ በከተማ አስተዳደር አካላት የተዘጋጁ ሲሆን በሕዝብ መሰብሰቢያ ስፈራዎች ተካሂደዋል (ኤፒ ኒውስ፣ ጥቅምት 12, 2015፣ የኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ፣ ጥቅምት 12, 2015)። በሳምንቱ መገባደጃ ላይ የፌዴራል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት “በኢትዮጵያ ላይ በተለያዩ ምዕራባውያን አካላት ስም የሚያጠፋ ውሸት እየተሰራጩ ነው” በማለት ይህንን የሚያወግዝ ይፋዊ መግለጫ አውጥቷል (የኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት፣ ጥቅምት 18, 2015)። በትግራይ ክልል “የከፋ የዘር ማጥፋት አደጋ” ስጋትን ለገለፀው ለዩኤስ ሆሎኮስት መታሰቢያ ሙዚየምን ጨምሮ መግለጫው እና ተቃውሞ ለብዙ ቡድኖች ምላሽ ነው (ዩኤስ ሆሎኮስት መታሰቢያ ሙዚየም፣ ጥቅምት 15, 2015)። በጥቅምት ወር መጀመሪያ ላይ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለአየርላንድ መንግስት በፃፉት ደብዳቤ የኢትዮጵያን “ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት” አደጋ ላይ በመጣል ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን እንደሚያቋርጡ ስፈራርተው ነበር (አዲስ ስታንዳርድ፣ ጥቅምት 4, 2015)።
በትግራይ ክልል የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና ከአማራ ክልል የተውጣጡ አጋር ኃይሎች በአንድ በኩል እና በሌላ በኩል የትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሓት) ደጋፊ ወታደሮች መካከል የሚደረገው ውጊያው ቀጥሏል። የመንግስት ኃይሎች አድዋን፣ አክሱምን፣ ብዘትን፣ እንትጮን፣ እዳጋ ሀሙስን፣ ቆላ ተምቤን፣ ሳምረን፣ የችላይን እና አዲግራትን በመቆጣጠራቸው ወደ ክልሉ ርዕሰ መዲና መቀሌ ለመግፉት ቦታዎችን ይዘዋል (ኤፒ ኒዊስ፣ ጥቅምት 15, 2015፤ ኢኤምኤስ፣ ጥቅምት 15, 2015)። በከተሞች የሚደረጉ ውጊያዎችን ለማስቀረት ጥረት ቢደረግም ሰላማዊ ሰዎች ግን በውጊያው እየተጎዱ ይገኛሉ። ጥቅምት 18 ቀን የአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ሰራተኛ የሆነ አንድ የአምቡላንስ ሹፌር የተጎዱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እንደሆኑ የተገመቱ ወታደሮችን ከአድዋ ወደ አዲረመጽ ሆስፒታል ሲያጓጉዝ የትህነግ/ህወሓት ኃይሎች እንደሆኑ በተጠረጠሩ ኃይሎች መገደላቸው ተሰምቷ (የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር፣ ጥቅምት 18, 2015)። አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባለፈው ሳምንት ያወጣው ዘገባ እንደሚያመለክተው ከጳጉሜ 1, 2014 እስከ መስከረም 2, 2015 በሸራሮ ከተማ ኤርትራውያን ስደተኞችን ጨምሮ ቢያንስ 40 ሰዎች በኤርትራ ወታደሮች መገደላቸውን አመልክቷል (አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ጥቅምት 14, 2015)። በደቡብ አፍሪካ በተፋላሚ ወገኖች መካከል እየተካሄደ ያለው የሰላም ድርድር በዚህ ሳምንት ተራዘመ ቢሆንም ጦርነቱ እንደሚቆም የሚያሳይ ምልክት ግን የለም (ፈራንስ24፣ 21, 2015፣ በመንግስት እና በትህነግ/ህወሓት መካከል በሚደረገው ድርድር ላይ ሊነሱ ስለሚችሉ ጉዳዮች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ኢፒኦ ወርሀዊ: ነሐሴ 26, 2014 እስከ መስከረም 20, 2015 ይመልከቱ)።
በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ፣ በምስራቅ ወለጋ እና በምስራቅ ሸዋ ዞኖች በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ተደጋጋሚ የአየር ድብደባዎች መደረጋቸው ተዘግቧል። በምዕራብ ሸዋ ዞን ጮቢ ወረዳ በጥቅምት 13 እና 14 በተደረገ የአየር ድብደባ በትንሹ 60 ሰዎች መሞታቸውና በርካቶች መቁሰላቸው ተነግሯል (አዲስ ስታንዳርድ፣ ጥቅምት 15, 2015)። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ መንግስት ትምህርት ቤቶችን እና የሰላማሳዊ ሰዎችን ስብሰባዎችን ኢላማ አድርጓል ሲል መንግስትን በመክሰስ ይፋዊ መግለጫ አውጥቷል (ኦነግ-ኦኤልኤ ከፍተኛ እዝ፣ ጥቅምት 15, 2015)። ከጥቂት ቀናት በፊት በዚሁ አካባቢ የኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ያነጣጠረ የአየር ድብደባ እንደነበር ተነግሮ ነበር (ስለእነዚህ የአየር ጥቃቶች የበለጠ መረጃ ለማግኘት ኢፒኦ ሳምንታዊ: ጥቅምት 5-ጥቅምት 11, 2015 ይመልከቱ)።
በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል በመንግስት ኃይሎች ከህግ አግባብ ውጭ የሚፈፀሙ ግድያዎች ቀጥለዋል። ባለፈው ሳምንት በቡኖ በደሌ፣ በጉጂ፣ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በምዕራብ ሀረርጌ እና በምዕራብ ሸዋ ዞኖች በመንግስት ኃይሎች ማለትም በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ እና የቀበሌ ታጣቂዎች የተፈፀሙ ሰባት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያደረሱት የጥቃት ኩነቶች ተመዝግበዋል። በእነዚህ ጥቃቶች በአጠቃላይ 13 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል። ከእነዚህ ጥቃቶች አብዛኛዎቹ የተፈፀሙት በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሲሆን አብዛኞቹ ተጎጂዎች ከኦነግ-ሸኔ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው ነበር።
በሶማሌ ክልል የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አባል በጅግጅጋ ጋራዲ ዊልዋል አየር ማረፊያ በአንድ ፌዴራል ፖሊስ መገደላቸውን ተከትሎ በክልሉ ርዕሰ መዲና ጅግጅጋ ተቃውሞ ተቀሰቅሶ ነበር (ሬድዮ ሪሳላ፣ ጥቅምት 16, 2015)። በተኩሱ የሟች እህት እና ሌላ የክልሉ ምክር ቤት አባልን ጨምሮ ሌሎች አራት ሰላማዊ ሰዎች ቆስለዋል። ድርጊቱን ተከትሎ ድርጊቱን የፈፀመው ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውሏል (ኢቢሲ፣ ጥቅምት 16, 2015)። የፌዴራል ፖሊሱ ተኩስ ከመክፈቱ በፊት ከአየር መንገዱ አስተዳዳሪ እና ከተጎጂዎች ጋር ፎቶ ሲያነሱ ለምን እሱን እንዳካተቱት ሲከራከሩ መታየታቸውን የዓይን እማኞች ተናግረዋል (ቢቢሲ አማርኛ፣ ጥቅምት 16, 2015)።
በመጨረሻም በጋምቤላ ክልል ጥቅምት 17 ቀን ከደቡብ ሱዳን የመጡ የሙርሌ ብሔረሰብ ታጣቂዎች ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ጥሰው ከገቡ በኋላ በአግኝዋክ ዞን ዲማ ወረዳ ከቀበሌ ታጣቂዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርገዋል። የተኩስ ልውውጡን ተከትሎ አንድ የሙርሌ ብሔረሰብ ታጣቂ ሲገደል አራቱ አምልጠዋል።