በቁጥር: ኢትዮጵያ, ከታህሳስ 1, 2014 –ከታህሳስ 28, 2015
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ብዛት: 1,320
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 7,404
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 3,303
በቁጥር: ኢትዮጵያ, ከታህሳስ 1-28, 20151በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ በመረጃ ቋታችን ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ብዛት: 53
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 153
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 88
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን በኢፒኦ የዳታ ፋይል እንዲሁም በዋናው የአክሌድ ኤክስፖርት መሳሪያ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ባለፉት አራት ሳምንታት ኦሮሚያ በሀገሪቱ ካሉ ክልሎች እጅግ በጣም ያልተረጋጋ ክልል ሆኖ የቀጠለ ሲሆን በትግራይ ክልል ደግሞ ሰብአዊ እርዳታ እና መሰረታዊ አገልግሎቶች መሻሻል አሳይተዋል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የትግራይ መከላከያ ሰራዊት በመባል የሚታወቁት የትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሓት) ሃይሎች ከፍተኛ አዛዦች ለሁለተኛ ጊዜ በኬንያ ናይሮቢ ተገናኝተው የጋራ ክትትል፣ ማረጋገጫ እና ተገዢነት ሜካኒዝም ማጣቀሻ ስነድን (Term of Reference of the Joint Monitoring, Verification and Compliance Mechanism) በታህሳስ 13 ቀን ከሁለት ቀናት የምክክር ስብሰባ በኃላ ፈርመዋል።2አፍሪካን ዩንኤን፣ ታህሳስ 13, 2015 የኬንያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት እና የአፍሪካ ህብረት አደራዳሪ ቡድን አባል ኡሁሩ ኬንያታ እንዳሉት በዚህ የስምምነት ስነድ ፓርቲዎቹ ለአፍሪካ ህብረት የክትትል እና የማረጋገጫ ቡድን ሁሉንም በሰላም ስምምነቱ የተዘረዘሩ ነገሮች መተግበራቸውን 360 ዲግሪ ለማያት የሚያስችል ሙሉ ፍቃድ ስጥተዋል።”3ሪፖርተር ኢትዮጵያ፣ ታህሳስ 15, 2015 ከፍተኛ አዛዦቹ ትጥቅ የማስፈታት፣ የማስወገድ እና የመልሶ ማቋቋም ሂደቶች አፈፃፀም ላይም ተወያይተዋል። ከእያንዳንዱ ተፋላሚ ወገን አንድ ተወካይ እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ተወካይ ያካተተ እና በአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ፓነል የሚመራ የጋራ ኮሚቴ አቋቁመዋል። ይህ የጋራ ኮሚቴ ትህነግ/ህወሓት የጦር መሳሪያዎች በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በተለዩ ቦታዎች እንዲከማቹ ፣የትህነግ/ህወሓት ትጥቅ መፍታት እንዲጠናቀቅ እና የትህነግ/ህወሓት ተዋጊዎች ምንም አይነት መሳሪያ እንዳይገዙ፣ እንደገና እንዳይኖራቸው እና እንዳያዘዋውሩ እንዲሁም ያልተፈቀደ ወታደራዊ መሳሪያ እንዳይንቀሳቀስ ዋስትና የመስጠት ኃላፊነት ተጥሎበታል።4ሪፖርተር ኢትዮጵያ፣ ታህሳስ 15, 2015
ይህን ስምምነት ተከትሎ ታህሳስ 17 ቀን የተለያዩ ሚኒስትሮችን እና የብሄራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላትን ያካተተ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ የተመራ የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ ተወካዮች የትግራይ ክልል ርዕሰ መዲና መቀሌን ጎብኝተዋል። በዚህ ጉብኝት ተወካዮቹ በጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም የተፈረመውን የሰላም ስምምነት አፈፃፀም ለመከታተል ከትህነግ/ህወሓት መሪዎች ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።5የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሪ፣ ታህሳስ 17, 2015 በታህሳስ 20 ቀን የአፍሪካ ህብረት አደራዳሪ ቡድን አባላት ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ እና ኡሁሩ ኬንያታ ከፍትህ ሚኒስትር፣ የኢጋድ ስራ አስፈፃሚ ፀሀፊ እና 32 የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር በመሆን መቀሌን ጎብኝተዋል። በዚህ ጉብኝት የሰላም ስምምነቱን አፈጻጸምን የገመገሙ ሲሆን የአፍሪካ ህብረት ክትትል፣ ማረጋገጫ እና ተገዢ ሚሽን (ኤዩ-ኤምቪሲኤም (AU Monitoring, Verification and Compliance Mission/AU-MVCM)) መቋቋሙን በመቀሌ አስታውቀዋል።6ቢቢሲ አማርኛ፣ ታህሳስ 20, 2015; አፍሪካ ዩንየን፣ ታህሳስ 20, 2015 የኤዩ-ኤምቪሲኤም ቡድን ታህሳስ 25 ቀን በመቀሌ ተስማርቷል።7አፍሪካ ዩንየን፣ ታህሳስ 26, 2015 ኤዩ-ኤምቪሲኤም የተቋቋመው ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም በተፈራረሙት ለዘለቄታዊ ሰላም ቋሚ የተኩስ አቁም ስምምነት አንቀጽ 11 መስረት ሲሆን ኃላፊነቱም የሰላም ስምምነቱን አፈፃፀም መከታተል ሲሆን ለጋራ ኮሚቴው ሪፖርት ያደርጋል።8የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሪ፣ ጥቅምት 25, 2015
ታህሳስ 20 ቀን የፌዴራል ፖሊስ አባላት የፌዴራል ተቋም የሆኑትን እንደ ኤርፖርት፣ ኢትዮ ቴሌኮም እና በከተማዋ የሚገኙ ባንኮችን ለመቆጣጠር መቀሌ ገብተዋል።9የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ፣ ታህሳስ 20, 2015 በታህሳስ 21, 2015 ዓ.ም የኤርትራ መከላከያ ሠራዊት ከባድ መሳሪያ እና ወታደሮቹን ከአክሱምና ከሽሬወደ ሁለቱ ሀገራት ድንበር ሲያወጣ መታየቱም ተዘግቧል።10ሮይተርስ፣ በታህሳስ 21, 2015; ቢቢሲ አማርኛ፤ በታህሳስ 21, 2015 ጥር 2, 2015 ዓ.ም በምስራቅ ትግራይ ዞን አጉላ አካባቢ የትህነግ/ህወሓት ኃይሎች ከባድ መሳሪያቸውን ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት እንዳስረከቡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የትህነግ/ህወሓት ምንጮች የገለጹ ሲሆን11የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት፣ ጥር 3, 2015; ትዊተር @ረዳ_ጌታቸው፣ ጥር 2, 2015 ሌላ ዘገባ ደግሞ ይህ የሆነው ታህሳስ 20, 2015 ዓ.ም መሆኑን አመልክቷል።12ኢኤምስ፣ ታህሳስ 20, 2015
በጦርነቱ ወቅት ሁሉ የኤርትራ ወታደሮች ዘረፋ እና በሰላማዊ ሰዎች ላይ እየፈጸሙ የነበረው ጥቃት አሳሳቢ ነበር።13ኤፒ ኒውስ፣ ግንቦት 20, 2014 ስምምነቱ ከተፈረመ በኃላም በትግራይ በታህሳስ ወር ላይ የኤርትራ ወታደሮች ቤቶችን እና የንግድ ድርጅቶችን እየዘረፉ እንደሚገኙ የሚገልጹ ዘገባዎች መውጣት ቀጥሏል።14ሮይተርስ፣ ህዳር 23, 2015 በታህሳስ 19 ቀን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፀጥታ አማካሪ ሬድዋን ሁሴን በሰሜኑ ግጭት ወቅት ኤርትራ ለኢትዮጵያ ፌዴራል ኃይሎች የምታደርገው ድጋፍ አሁንም እንደቀጠለ እንደሆነ እና ትህነግ/ህወሓት “ትጥቅ እስካልፈታ ድረስ” የኢትዮጵያ መንግስት እና የኤርትራ የጋራ ጠላት ነው ሲሉ ተናግረዋል። ሬድዋን ሁሴን የአድሎ (የተመረጠ) ጥሪ አድርገው የሚያዩትን የኤርትራን ኃይሎች ለቀው እንዲወጡ አጥብቀው የሚጠይቁትን “አካላት” ተቃውመዋል።15የኢትዮጵያ ሪፖርተር፣ ታህሳስ 23, 2015 ይህንን የገለጹት ከተለያዩ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ጋር የሰላም ስምምነቱ ላይ በተደረገው የምክክር መድረክ ላይ ነው።
ሰብአዊ እርዳታ በአፋር እና በአማራ ክልሎች በአራት ኮሪደሮች ለትግራይ ክልል መድረሱን ቀጥሏል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ከህዳር 6 እስከ ታህሳስ 21, 2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ “የኢትዮጵያ መንግስት እና የሰብአዊ እርዳታ አጋሮች 2,740 የጭነት መኪናዎች ወይም ከ101,700 ሜትሪክ ቶን በላይ ምግብ እና 309 የጭነት መኪናዎች ወይም 10,840 ሜትሪክ ቶን ምግብ-ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን አጓጉዘዋል።”16የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ፣ ታህሳስ 27, 2015 ሆኖም ግን በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ዞን አበርገሌ እና ፃግብጂ ወረዳዎች በግጭቱ የተጎዱ ነዋሪዎች አሁንም ሰብዓዊ እርዳታ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል። የአበርገሌ ወረዳ አስተዳዳሪ እንደገለፁት በወረዳው 37,000 ነዋሪዎች ተፈናቅለው ሰብአዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።17ዲደብሊው አማርኛ፣ ታህሳስ 20, 2015 በሁለቱም ወረዳዎች ከ67,000 በላይ ነዋሪዎች አፋጣኝ ሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው አንድ ዘገባ አመልክቷል።18የኢትዮጵያ ሪፖርተ፣ ታህሳስ 26, 2015 እነዚህ ወረዳዎች በትህነግ/ህወሓት ኃይሎች ቁጥጥር ስር መሆናቸው ተነግሯል።
በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች መሰረታዊ አገልግሎቶችም ወደ ነበሩበት ተመልሰዋል። አዲ አርቃይን፣ ቆቦን፣ አባላን፣ ውቅሮን፣ መቀሌን፣ ራማን፣ ሽሬን እና አክሱምን ጨምሮ በአፋር፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች የቴሌኮሙዩኒኬሽንና የመብራት አገልግሎት ወደ ነበረበት ተመልሷል።19ኢትዮ ቴሌኮም፣ ታህሳስ 19, 2015; ዲደብሊው አማርኛ፣ ታህሳስ 20, 2015 እንደ ኢትዮ ቴሌኮም ዘገባ በእነዚህ ሶስት ክልሎች ውስጥ በሚገኙ ከ50 በላይ ከተሞች የኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ወደ ነበረበት ተመልሷል።20 ኢትዮ ቴሌኮም፣ ታህሳስ 19, 2015 ታህሳስ 24, 2015 የግል ባንክ የሆነው ወጋገን ባንክ በመቀሌ ውስጥ የባንክ አገልግሎት በይፋ ጀመረ ሲሆን ለጊዜው ግን በቀን 2,000 ብር (ወደ 37 ዶላር አካባቢ) የማውጣት ገደብ ተጥሏል።21ኢትዮጵያ ኢንሳይደር፣ ታህሳስ 24, 2015; የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ፣ ታህሳስ 27, 2015 የመንግስት የሆነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሽሬ፣ አላማጣ እና ኮረም ከተሞች በታህሳስ 10, 2015 እንደገና ሥራ ጀምሯል።22የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ታህሳስ 10, 2015 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ወደ መቀሌ ታህሳስ 19, 2015 እና ወደ ሽሬ ታህሳስ 24 ቀን ከ18 ወራት በኋላ የመጀመሪያውን የንግድ በረራ ጀምሯል።23የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ታህሳስ 18, 2015; የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ታህሳስ 20, 2015; ፋና ቴሌቪዥን፣ ታህሳስ 25, 2015 በተጨማሪም በታህሳስ ወር የኢትዮጵያ ኢነርጂ ባለስልጣን ለ14 ነዳጅ አከፋፋዮች ነዳጅ ከጅቡቲ ወደብ በቀጥታ ወደ ትግራይ ክልል ለማጓጓዝ ፍቃድ ሰጥቷል።24ዲደብሊው አማርኛ፣ ታህሳስ 20, 2015 ቀደም ሲል ነዳጅ ወደ ክልሉ የሚያጓጉዘው በሰብአዊ እርዳታ ኤጀንሲዎች ነበር።
በኦሮሚያ ክልል የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ፣ የመንግስት ኃይሎች እና የአማራ ብሔር ታጣቂዎች የተሳተፉባቸው ውጊያዎች እንዲሁም በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች ቀጥለዋል። ከታህሳስ 1 እስከ ከታህሳስ 28, 2015 ዓ.ም ድረስ 24 የውጊያ ኩነቶች በክልሉ ውስጥ ተመዝግበዋል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። በኦነግ-ሸኔ እና በመንግስት ኃይሎች መካከል 23 ውጊያዎች በቦረና፣ ጉጂ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብ ሀረርጌ፣ ምዕራብ ሸዋ እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች ተመዝግበዋል። ኦነግ-ሸኔ በኦሮሚያ እና በአፋር ክልሎች አዋሳኝ አካባቢም በተፈጠረ ውጊያ ተሳታፊ ነበር። ኦነግ-ሸኔ ሁለት የአፋር ወጣቶች ላይ በአፋር እና ኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ ላይ በሚገኝ በአዋሽ ብሄራዊ ፓርክ ዙሪያ ጥይት በመተኮሳቸው ታህሳስ 15 እና 16 የኦነግ-ሸኔ እና የአፋር ብሔር ታጣቂዎች በዚህ ስፍራ ተዋግተዋል። ወጣቶቹ ድንበር አልፈው የገቡት ሁለት የጠፉ ግመሎችን ለመፈለግ ነበር። በእነዚህ ውጊያዎች ምክንያት አራት ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል። በታህሳስ ወር የመንግስት ኃይሎች በምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ ከኦነግ-ሸኔ አባላት ጋር ከተዋጉ በኃላ ቁጥራቸው በውል ያልተገለጸ ቀበሌዎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አስታውቀዋል። በተመሳሳይ በታህሳስ ወር መጨረሻ ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በደቡብ ኦሮሚያ በኦነግ-ሸኔ “ለአመታት” ተቆጣጥሯቸው የነበሩ ሰባት ቀበሌዎችን መልሶ መቆጣጠሩን ዘግቧል።25የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት፣ ታህሳስ 25, 2015
ባለፉት አራት ሳምንታት በአማራ ብሔር እና ፋኖ ታጣቂዎች እና በመንግስት ኃይሎች – የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና ኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል – መካከል አንድ የጦርነት ኩነት ብቻ በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ወለጋ ዞን ተመዝግቧል። በህዳር ወር ካለው ጊዜ ጋር ሲነፃፀር የአማራ ብሔረ ታጣቂዎች የተሳተፉባቸው የጦርነት ኩነቶች ቁጥር ቀንሷል። በታህሳስ 12, 2015 ዓ.ም አካባቢ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል ወደ 60 የሚጠጉ የአማራ ብሔር ተወላጆችን በምስራቅ ወለጋ ዞን በጊዳ አያና ወረዳ በጉቲን ከተማ በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው ሁከትና ብጥብጥ እጃቸው አለበት በማለት በቁጥጥር ስር አውሏል።
በክልሉ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃትም ቀጥሏል። ከታህሳስ 1 እስከ ከታህሳስ 28, 2015 ዓ.ም ድረስ በኦሮሚያ ክልል የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች፣ የኦነግ-ሸኔ፣ የአማራ ብሔር ታጣቂዎች እና ፋኖ ታጣቂዎች የተሳተፉባቸው 20 በሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሱ የጥቃት ኩነቶች ተመዝግበዋል። የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች – የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል እና የቀበሌ ታጣቂዎች – ከህግ አግባብ ውጪ ግድያ በአርሲ፣ በምስራቅ ሀረርጌ፣ በምስራቅ ሸዋ፣ በፊንፊኔ ልዩ፣ በኢሉ አባ ቦራ፣ በቄሌም ወለጋ፣ በምዕራብ ሸዋ እና በምዕራብ ወለጋ ዞኖች የፈጸሙ ሲሆን በዚህም ምክንያት 31 ሰዎች ለሞት መዳረጋቸው ተዘግቧል። የኦነግ-ሸኔ አባላት በምዕራብ ሸዋ ዞን በአንድ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሰ የጥቃት ኩነት ተሳትፈዋል። በአማራ ብሔር ታጣቂዎች እና በፋኖ ታጣቂዎች የተፈፀሙ አብዛኛው በሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሱ ጥቃቶች በምዕራብ ኦሮሚያ ማለትም በሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ በምስራቅ ወለጋ እና በሰሜን ሸዋ ዞኖች የተመዘገቡ ሲሆን በዚህም 23 ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል።
ከኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ ዓላማ መስቀል እና ክልላዊ መዝሙር መዘመር ጋር በተያያዘ ሰልፎች እና ግጭቶች በአዲስ አበባ እስከ ታህሣሥ አጋማሽ ድረስ ቀጥለዋል። ታህሳስ 3 ቀን በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በኮተቤ ወንድይራድ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በኦሮሞ ተማሪዎች እና ወላጆች እና በሌሎች ተማሪዎች እና ወላጆች መካከል የኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ አላማ መስቀል ጋር በተያየዘ አለመረጋጋት ተቀሰቅሷል። በተመሳሳይ ቀን በጉለሌ ክፍለ ከተማ ሽሮ ሜዳ አካባቢ በእንጦጦ አምባ ትምህርት ቤት ተመሳሳይ ሁከት ተነስቷል። ከሁለት ቀናት በኋላ ታህሳስ 6 ቀን በጉለሌ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ የቀለም ወርቅ ትምህርት ቤት የኦሮሞ ተማሪዎች ከሌሎች ተማሪዎች ጋር የኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ አላማ መስቀል ጋር በተያየዘ ግጭት ተፈጠሯል። በእነዚህ ግጭቶች እና የጸጥታ ኃይሎች ሁከቱን ለማስቆም ባደረጉት ሙከራ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች ቆስለዋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ከሁከቱ ጋር በተያያዘ 570 ተማሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ተነግሯል።26ኢሳት፣ ታህሳስ 12, 2015 ተማሪዎቹ በታህሳስ 12 ቀን ከእስር ተፈተዋል። ጥቂት ተማሪዎች ግን አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ።
በአማራ ክልል የባህልና የኃይማኖት አባቶች ከመንግስት ጋር የቅማንት ኮሚቴ ታጣቂዎች በሰላም እጃቸውን እንዲሰጡ እና የተሃድሶ ስልጠና ላይ እንዲሳተፉ ከተወያዩ በኃላ ታህሳስ 13 ቀን ከ300 የሚበልጡ የቅማንት ኮሚቴ ታጣቂዎች በሰላም እጃቸውን ለመንግስት ሰጥተዋል።27የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ታህሳስ 12, 2015 ከቀናት በፊት ታህሳስ 9 ቀን በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ በሚገኘው አባይ ወንዝ ድልድይ አካባቢ የኦነግ-ሸኔ አባላት 10 የአማራ ተወላጆችን በጥይት ተኩሰው ገድለዋል። ተጎጂዎቹ አያታቸውን ከኦሮሚያ ክልል ኪረሙ ወረዳ ወደ አማራ ክልል የህክምና ማዕከል ሲያጓጕዙ ከነበሩ 16 ሰዎች መካከል ናቸው።