በዚህ ዘገባ ውስጥ የተካተቱ
- ከሕዳር 22 እስከ ታህሳስ 22, 2015 በጨረፍታ
- አበይት ክንውኖች
- ከሕዳር 22 እስከ ታህሳስ 22, 2015 የተከሰቱ ቁልፍ ኩነቶች
- ወርሀዊ ትኩረት፡ በኦሮሚያ ክልል ግጭት መስፋፋት
ከሕዳር 22 እስከ ታህሳስ 22, 2015 በጨረፍታ
አበይት ክንውኖች
- አክሌድ ከሕዳር 22 እስከ ታህሳስ 22, 2015 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ 70 የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች እና 263 ሪፖርት የተደረጉ ሟቾች መዝግቧል።
- በፖለቲካዊ ግጭት ምክንያት ከፍተኛ የኩነት እና የሟቾች ቁጥር በኦሮሚያ ክልል ሪፖርት መደረጉ የቀጠለ ሲሆን 58 ኩነቶች እና 246 ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል።
- ከሕዳር 22 እስከ ታህሳስ 22, 2015 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ተደጋግመው የተከሰቱት የኩነት አይነትች ጦርነት እና በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶች ሲሆኑ 29 የጦርነት ኩነቶች እንዲሁም 29 በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸመ የጥቃቶች ተከስተዋል።
- አክሌድ በኦሮሚያ ክልል ከየካቲት 2013 በኃላ ከፍተኛ የሆነውን 20 ሰልፎችን ባለፈው ወሩ ውስጥ መዝግቧል።
ከሕዳር 22 እስከ ታህሳስ 22, 2015 የተከሰቱ ቁልፍ ኩነቶች
ወርሃዊ ትኩረት፡ በኦሮሚያ ክልል ግጭት መስፋፋት
ከሕዳር 22 እስከ ታህሳስ 22, 2015 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በኦሮሚያ ክልል ፖለቲካዊ ግጭት ከፍተኛ ሆኖ የቀጠለ ሲሆን በግጭት እና መፈናቀል የበለጠ የተጎዱት የአማራ ተወላጆች የሚኖሩባቸው አካባቢዎች ናቸው። በኦሮሚያ ውስጥ ብዙ የተለያዩ ብሔሮች በሰላም የሚኖሩ ቢሆንም ታሪካዊ የስደት እና የመሬት ፉክክር፣ በቦታ ይገባኛል ዙሪያ የሚነሱ አለመግባባት እና ብሔርን መሰረት ያደረገ የባለቤትነት ጥያቄዎች፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ሽምቅ ውጊያ እና የአማራ ብሔር ተወላጆች ወታደራዊ ኃይሎች መኖራቸውን ጨምሮ በበርካታ ምክንያቶች የኦሮሚያ ክልል ሰሜን ምዕራብ ለከፍተኛ ግጭት የተጋለጠ እንዲሆን አድርገውታል። በቅርቡ ወደ ምዕራብ እና ደቡብ የክልሉ ስፍራዎች ወታደሮች ማሰማራትን ጨምሮ የፌዴራል መንግስት ሁኔታውን ለማረጋጋት አንዳንድ ጥረቶች ቢያደርግም የአካባቢው ሁኔታ አሁንም የልተረጋጋ ነው። ወሩን በሙሉ የታጠቁ ቡድኖች ዘርን መሠረት ባደረከ መልኩ ሰላማዊ ሰዎችን ያጠቁ ሲሆን ይህም የመፈናቀል ማዕበል አስከትሏል።
በኦሮሚያ ክልል ኦነግ-ሸኔ በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘረ ዘጠኝ የጥቃት ኩነቶች ላይ የተሳተፈ ሲሆን የአማራ ብሔር ታጣቂዎች እና የፋኖ ታጣቂዎች በሰባት በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘረ የጥቃት ኩነቶች ላይ ተሳትፈዋል። በምስራቅ ወለጋ ዞን በኪረሙ እና አንገር ጉቲን አካባቢ የሚኖሩ አንዳንድ የአማራ ተወላጆች ኦነግ-ሸኔ እና የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል በአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እየፈፀሙ ነው ሲሉ የከሰሱ ሲሆን አንዳንድ ኦሮሞዎች ደግሞ የአማራ እና ፋኖ ታጣቂዎች በኦሮሞ ተወላጆች ላይ ጥቃት አድርሰዋል ሲሉ ከሰዋል።1ቪኦኤ አማርኛ፣ ሕዳር 28, 2015; ቢቢሲ አማርኛ፣ ሕዳር 26, 2015; ዲደብሊው አማርኛ፣ ሕዳር 26, 2015
በኦሮሚያ ክልል አንገር ጉቲን እና ኪረሙ አካባቢዎች የተፈጠረው ግጭት መሠረቱ ከአስርተ ዓመታት በላይ በቆየ የግዛት ውዝግብ ነው። ድንገተኛ እና በመንግስት የተደገፈ የአማራ ገበሬዎች የተሻለ መሬት እና የስራ እድል ፍለጋ ብዙ የአማራ ተወላጆች በአካባቢው እንዲሰፍሩ ተድርጓል፤ ይህም በመሬት ሃብት ምክንያት ከኦሮሞ ጎረቤቶቻቸው ጋር አልፎ አልፎ ግጭት አስከትሏል።2 ተፈራ፣ ግንቦት 10, 2002 ከሚያዚያ 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በአካባቢው ውጊያዎች እንደገና የተቀሰቀሱ ሲሆን በሕዳር እና ታህሳስ 2015 ዓ.ም. ውጊያው ተባብሷል።
በዚህም ምክንያት፣ በግጭቱ የተነሳ የተፈናቀሉ ሰዎች በአቅራቢያው ወደ ሚገኙት አማራ፣ ኦሮሚያ እና ቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል ከተሞች በመሸሻቸው በእነዚህ አካባቢ ላይ ጫና ፈጥረዋል። እስከ ታህሳስ 21 ቀን በኦሮሚያ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት እስከ 14,000 የሚደርሱ አዲስ ተፈናቃዮች ከኦሮሚያ ወደ አማራ ክልል ገብተዋል።3የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ፣ ታህሳስ 27, 2015 በሺህ የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆችም ተፈናቅለው በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል በሚገኙ ከተሞች ተሰደዋል።4አዲስ ስታንደርድ፣ ሕዳር 29, 2015 በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ የፌዴራል ባለስልጣናት ጉዳዩን ከወታደራዊ እርምጃ ባለፈ መፍትሄ እንዲሰጡ ተገደዋል።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) “ግጭቶች እና ጥቃቶች የሚደርሱባቸው አካባቢዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ በመሄዳቸው እንዲሁም የሰብአዊ መብት ቀውሱን አሳሳቢነት” ላይ በመመስረት “አፋጣኝ እርምጃ” እንዲወሰድ ጥሪ አቅርቧል።5የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ሕዳር 28, 2015 ከኢትዮጵያ መንግስት ጫና ነፃ ነው ተብሎ ከሚታሰበው ከኢሰመኮ6የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ 2015 በስተቀር የፌዴራል ባለስልጣናት በአንገር ጉቲን እና በኪረሙ አካባቢዎች የተፈጠረውን ውጊያ አስመልክቶ የሰጡት መግለጫ የለም። በቀጥታም ባይሆን ውጊያውን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ኢትዮጵያውያን “የግጭት እና የጥላቻ አጀንዳዎችን ባለማዳመጥ አጋርነታችንን እናጠናክር” ሲሉ ጠይቀዋል።7ቪኦኤ አማርኛ፣ ሕዳር 29, 2015
በኦሮሚያ ክልል ደቡብ እና ምዕራብ አካባቢ ለረጅም ጊዜ የቆየው ግጭት ላይ የክልሉ ሰሜን ምዕራብ አዲስ የግጭት ስፍራ ሲሆን በኦሮሚያ ያለው ግጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ እና ከቦታ ወደ ቦታ እየተስፋፋ ነው (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። ከነሃሴ 2014 አጋማሽ እስከ ጥቅምት 2015 አጋማሽ ከነበረው አንፃራዊ መረጋጋት በኋላ በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ ውጊያዎች እንደገና ማንሰራራት የጀመሩ ሲሆን አክሌድ ከጥቅምት 22 እስከ ታህሳስ 22, 2015 ዓ.ም. ድረስ 87 የውጊያ ኩነቶችን መዝግቧል። ውጊያዎቹ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን፣ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይልን፣ ኦነግ-ሸኔን እና የአማራ ብሔር ታጣቂዎችን ያሳተፉ ናቸው። ከሕዳር 22 እስከ ታህሳስ 22, 2015 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ተፋላሚዎች መካከል ውጊያዎች በምስራቅ ወለጋ፣ በሆሮ ጉዱሮ ወለጋ፣ በቄሌም ወለጋ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ በምዕራብ ሀረርጌ፣ በምዕራብ ሸዋ እና በምዕራብ ወለጋ ዞኖች ተመዝግበዋል። በውጊያው ቢያንስ 137 ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል። ነገር ግን በሪፖርት አቀራረብ ችግር እና አስተማማኝ መረጃ ባለማግኘት ምክንያት የሟቾች ቁጥር ግምት በአጠቃላይ ዝቅተኛ ሊሆን ይችላል።8 ዘ ኢኮኖሚስት፣ ግንቦት 11, 2015
በወሩ ውስጥ በግምት 38% የሚሆኑት የሟቾች ቁጥር የተመዘገበበት በጣም ከባድ ግጭት የተከሰተው በሕዳር ወር መጨረሻ ባሉት ስምንት ቀናት ውስጥ በአንገር ጉቲን እና በኪረሙ ነው። እነዚህ ከተሞች ከኦሮሚያ ነቀምቴ ከተማ በአማራ ክልል የሚግኘውን ቡሬ ከተማን በሚያገናኘው መንገድ 32 ላይ ይገኛሉ። በታህሳስ ወር የቀጠለው የኪረሙ ግጭቱ የጀመረው በሕዳር ወር ሲሆን ግጭቱ የተጀመረው የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል የአማራ ተወላጅ የሆኑ እስረኞችን ከምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ወደ ነቀምቴ ለክስ (ለፍርድ ቤት ጉዳይ) ሲያጓጉዙ በአማራ ብሔር ታጣቂዎች ጥቃት ከተፈፀመባቸው በኃላ ለአራት ቀናት የዘለቀ ከባድ ግጭት ከተቀሰቀሰ በኃላ ሲሆን የአማራ ሰላማዊ ሰዎችን ጨምሮ ቢያንስ 219 ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል (ለበለጠ ዝርዝር መረጃ ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከሕዳር 10-16, 2015 ይመልከቱ)። በሕዳር 24 ቀን የብዙ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የውጊያ ኩነት የተዘገበ ሲሆን ይህም በጉቲን ቢያንስ 34 ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ወታደሮች በሕዳር 26 ወደ ጉቲን የተሰማሩ ቢሆንም ጦርነቱን ግን ማስቆም አልቻሉም።9ዲደብሊው አማርኛ፣ ሕዳር 27, 2015 በሕዳር 29 ቀን በኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል እና በአማራ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ ዳግም መቀስቀሱ ተነግሯል። በተጨማሪም በታህሳስ 14 ቀን ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በአቅራቢያው በሚገኘው የሃሮ አዲስ አለም መንደር ከ10 እስከ 20 የሚጠጉ ሰዎችን መግደላቸው ተዘግቧል።
ተጨማሪ አካላት እና ውስብስብነት መጨመር
ግጭቱ ወደ አንገር ጉቲን እና ኪረሙ አካባቢዎች የተስፋፋው ተጨማሪ አካላት የህብረተሰቡ ግጭቶችን ወደ አገራዊ ግጭት በማስፋት ጣልቃ በገቡበት ወቅት ነው። በእርሻ መሬት ምክንያት ግጭት ውስጥ በሚገቡት የአካባቢው ሰዎች ብቻ ከመሆን ይልቅ በአሁኑ ጊዜ ውጊያው በኦሮሞ እና በአማራ በኩል ብሔርተኛ ኃይሎችንም ያካትታል።
የኦሮሞ ተወላጆች እና ባለስልጣናት ድርጊቱን የፈፀሙት ፋኖ በመባል የሚታወቁት የአማራ ታጣቂዎች ከአማራ ክልል ከቡሬ በመምጣት በአካባቢው በሚገኙ የኦሮሞ አስተዳዳሪዎች ላይ ጥቃት ማድረጋቸውን ገልፀዋል።10ቪኦኤ አማርኛ፣ ሕዳር 28, 2015 እንደዚሁም እንደ ኦነግ ያሉ የኦሮሞ ብሔርተኛ የፖለቲካ ድርጅቶች የአማራ ፓራሚሊተሪ (ታጣቂ) ኃይሎች በኦሮሞ ግዛት ውስጥ እየፈጸሙ ያሉትን ‘መስፋፋት’ አውግዘዋል።11አዲስ ስታንደርድ፣ ሕዳር 28, 2015 የኦሮሞ ነፃ አውጪ ጦር (ኦኤልኤ) በመባልም የሚታወቀው የኦነግ-ሸኔ ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ የኦነግ-ሸኔ ኃይሎች በአካባቢው በሚገኙ የአማራ ተወላጆች ላይ ጥቃት እያደረሱ ነው የሚለውን ክስ አስተባብለው የቡድኑ አባላት ግን በአማራ ፋኖ ታጣቂዎች ላይ በተደረገው ውጊያ እጃቸው እንዳለበት አረጋግጠዋል።12ቪኦኤ አማርኛ፣ ሕዳር 28, 2015
በኦሮሞ እና በአማራ ሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈፀመው ጥቃት እና መፈናቀል ዜና በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በመላ ሀገሪቱ ሰልፎችን ቀስቅሷል። ከሕዳር 22 እስከ ታህሳስ 22, 2015 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በአዲስ አበባ፣ በአማራ፣ በድሬዳዋ፣ በጋምቤላ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች፣ በሶማሌ እና በደቡብ ምዕራብ ክልሎች 35 የሰልፎ ኩነቶች ተመዝግበዋል። በኦሮሚያ የተቀሰቀሰው ሁከትም በመዲናይቱ አዲስ አበባ ውጥረት ፈጥሯል፤ አዲስ አበባ በመንግስት ትምህርት ቤቶች ከኦሮሚያ ክልል ባንዲራ መስቀል ጋር በተያያዘ በተማሪዎች፣ ወላጆች እና መምህራን መካከል ግጭት እንዲፈጠር አድርጓል።13አዲስ አበባ ፖሊስ፣ ሕዳር 29, 2015
ሃገራዊ ፖለቲካ እና ሰላም ግንባታ
ሕዳር 26 ቀን ኦሮሚያን የወከሉ የፓርላማ አባላት በትግራይ ክልል የተጀመረው የሰላም ሂደት በኦሮሚያ ክልልም እንዲደገም እና የፌዴራል መንግስት ከኦነግ-ሸኔ ኃይሎች ጋር እንዲደራደር ለፌዴራል መንግስት በደብዳቤ ጠይቀዋል።14ኦልአፍሪካ ሚዲያ፤ ታህሳስ 4, 2015; ኢትዮጵያ ኢንሳይደር፣ ሕዳር 29, 2015 የገዥው ብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ በሕዳር መጨረሻ ላይ ከኦነግ-ሸኔ ጋር የተፈጠረውን ግጭት ለመፍታት “ሰላማዊ ስልቶችን” መሞከሩን ነገር ግን “ቡድኑ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ማጥቃት ሲቀጥል” ወታደራዊ መፍትሄዎችን ማስቀደም መምረጡን ገልጿል።15አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ሕዳር 28, 2015
ይህ በእንዲህ እንዳለ የፌዴራል መንግስት በኦሮሚያ ክልል ጉጂ፣ ምዕራብ ጉጂ እና ቦረና ዞኖች አዳዲስ ወታደራዊ ስምሪት በማድረግ በኦነግ-ሸኔ ላይ ወታደራዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።16የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ታህሳስ 19, 2015; የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ታህሳስ 24, 2015 ይህ የሆነው የፌዴራል ባለስልጣናት ኦነግ-ሸኔ “አንድ ወጥ የፖለቲካ ተወካይ ወይም ወታደራዊ እዝ መዋቅር ስለሌለው” ከቡድኑ ጋር እንደማይደራደሩ ከገለፁ ከአንድ ወር በኋላ ነው።17የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ሕዳር 21, 2015; አዲስ ስታንደርድ፣ ሕዳር 20, 2015 ኦነግ-ሸኔ በተመሳሳይ መልኩ ከፌዴራል መንግስት ጋር በገለልተኛ እና በሶስተኛ ሀገር በኩል ብቻ እንደሚደራደር አስታውቆ የነበረ ሲሆን ሌላ አይነት ድርድር “ምንም አይነት የሽምግልና ማዕረግ ይዘው የገዥው አካል ካድሬዎች ቢመጡ እንደማይሰራ” አስታውቋል።18ቲዊተር @ኦዳተርቢደብሊውቢኦ፣ ሕዳር 20, 2015
በአንገር ጉቲን እና በኪረሙ የተከሰቱት ውጊያዎች የፌዴራል መንግስቱን አጣብቂኝ ውስጥ ከተውታል። ከኦሮሞ እና ከአማራ ክልል የተውጣጡ የፖለቲካ አካላት በኦሮሞ እና በአማራ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፎች መካከል የተፈጠረውን ስስ ሚዛን አደጋ ላይ በሚጥል መልኩ የፌዴራል መንግስት በስማቸው እንዲገባ ጠይቀዋል (በብልጽግና ፓርቲ ውስጥ እየጨመረ የመጣው አለመግባባት ላይ የበለጠ መረጃ ለማግኘት ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከመጋቢት 17, 2014 እስከ መጋቢት 23, 2014 ይመልከቱ)።
ኢትዮጵያ በተለይም ኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች እንደገና መንታ መንገድ ላይ ይገኛሉ። ተፋላሚ ወገኖች በሰላማዊ ስምምነቱ መሠረት የተለያዩ ተግባራትን እያደረጉ በመሆኑ በሰሜን ኢትዮጵያ ሰላምን ማስፈን ከባድ ስራ ቢሆንም ስላም የመስፋን እድሉ ከፍተኛ ነው። በኦሮሚያ ሰላም እንዴት ሊሰፍን የሚችልባቸው መንገዶች ግልጽ አይደሉም። ምንም እንኳን በምርጫው ሂደት ላይ ለህብረተሰቡ ግልጽነት ቢጎደለው የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽነሮች የተሳታፊዎችን እና አጀንዳዎችን ምርጫ በታኅሣሥ ወር ጀምረዋል። የፍትህ ጥያቄዎችን እና ሁሉንም የግጭት ተዋናዮች የፈፀሙት ጉዳቶች መፍታት ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ቁልፍ ይሆናል።