በቁጥር: ኢትዮጵያ, ከታህሳስ 29, 2014 –ጥር 5, 2015
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ብዛት: 1,266
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 6,651
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 2,786
በቁጥር: ኢትዮጵያ, ከታህሳስ 29-ጥር 5, 20151በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ በመረጃ ቋታችን ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ብዛት: 15
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 29
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 7
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን በኢፒኦ የዳታ ፋይል እንዲሁም በዋናው የአክሌድ ኤክስፖርት መሳሪያ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ባለፈው ሳምንት የትግራይ የሰላም ስምምነት ፈራሚዎች በጥቅምት 23, 2015 ዓ.ም. የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ በርካታ እርምጃዎችን ወስደዋል። በሌላ በኩል በኦሮሚያ ክልል ፖለቲካዊ ግጭት ቀጥሏል።
ጥር 2 ቀን የትግራይ መከላከያ ሠራዊት በመባል የሚታወቀው የትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሓት) ኃይሎች በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ትግራይ ዞን አጉላ በሚገኘው ካምፕ ውስጥ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከባድ መሳሪያዎችን ማስረከብ ጀምረዋል።2ትግራይ ቲቪ፣ ጥር 2, 2015; ትግራይ ቲቪ፣ ጥር 2, 2015 የአፍሪካ ህብረት ክትትል፣ ማረጋገጫ እና ተገዢ ተልዕኮ አባላት ለዘለቄታዊ ሰላም ቋሚ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ በተገለፀው መሰረት የጦር መሳሪያ መፍታት ሂደትን ምስክር የመሆን ሚናቸውን ለመወጣት በስፍራው ተገኝተዋል።3 ትግራይ ቲቪ፣ ጥር 2, 2015; የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሪ፣ ጥቅምት 25, 2015 በትግራይ ክልል የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ያልሆኑ ኃይሎች ከትግራይ ክልል ለቀው እንዲወጡ በተደረገው ስምምነት መሰረት ከአንድ ቀን በኋላ ጥር 3 ቀን የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አባላት ከትግራይ ክልል በሰሜን ምዕራብ ዞን ከምትገኘው ሽሬ ከተማ እና አካባቢው ለቀው ወጥተዋል። የኤርትራ ኃይሎች ከትግራይ ክልል ለቀው እየወጡ እንደሆን ቢዘገብም የተወሰኑ ወታደሮች በድንበር አካባቢዎች ትገኛሉ።4ሮይተርስ፣ በታህሳስ 21, 2015; ቢቢሲ አማርኛ፤ በታህሳስ 21, 2015
በኦሮሚያ ክልል ውጊያ እና በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ባለፈው ሳምንትም ቀጥሏል። በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) -ሸኔ እና በመንግስት ኃይሎች – የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል እና የማረሚያ ቤት ጠባቂዎች መካከል የተደረጉ ዘጠኝ ውጊያዎች በምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብ ሀረርጌ እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች የተመዘገቡ ሲሆን አብዛኞቹ ውጊያዎች የተፈፀሙት በምዕራብ ሸዋ ነው (ከታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)።
ባለፈው ሳምንት አራት በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተሰነዘሩ ጥቃቶች በምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋ እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች ተመዝግበዋል። በእነዚህ ድርጊቶች የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል እና የፋኖ ታጣቂዎች ተሳትፈዋል። በምስራቅ ወለጋ ዞን በኪረሙ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ቀጥሏል (በኪረሙ አካባቢ ስላለው ግጭት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የ ኢፒኦ ከሕዳር 22 እስከ ታህሳስ 22, 2015 ዘገባን ይመልከቱ)። ጥር 3 ቀን ማንነቱ ያልታወቀ ታጣቂ ቡድን በኪረሙ ወረዳ ሃሮ አዲስ አለም በተባለ ቦታ ባብዛኛው የአማራ ተወላጆች የሆኑ ስላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ፈጽሟል። ጥር 3 አካባቢ የፋኖ ታጣቂዎች አባይ ወንዝን ተሻግረው ወደ ኦሮሚያ ክልል ከገቡ በኋላ በኪረሙ ወረዳ በቡርቃ ሶሬማ ተኩስ ከፍተው ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ ሰላማዊ ሰዎችን መግደላቸው ተዝግቧል።
በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ጥር 1 ቀን አራት እስረኞች ከፍርድ ቤት ወደ አላባ ማረሚያ ቤት እየተመለሱ ሳሉ የደቡብ ክልል ማረሚያ ቤት ጥበቃዎች ላይ በርበሬ በመበተን ለማምለጥ ሲሞክሩ የደቡብ ክልል ማረሚያ ቤት ጥበቃዎች አንድ እስረኛ ተኩሰው የገደሉ ሲሆን ሌላ ሁለትኛ እስረኛን አቁስለዋል። ሌሎቹ ሁለቱ እስረኞች ሊያመልጡ ችለዋል።
በጥር 5 ቀን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ክልል በኦሮሚያ ልዩ ዞን 109 የፋኖ ታጣቂዎችን እና 107 የኦነግ-ሸኔ አባላትን ጨምሮ 371 ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል። እስረኞቹ ታህሳስ 29 ቀን በተከበረው የኢትዮጵያ የገና በዓል አከባበር ላይ “በአካባቢው በብሄር ለማጋጨት እና ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር” በማቀድ ተጠርጥረው ታስረዋል።5የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ፣ ጥር 6, 2015
አንዳንድ ከአዲሱ ከተማ ወሰን አደራጃጀት ውጪ የሆኑ ማህበረሰቦች ተቃውሞ ቢያደርጉም በኦሮሚያ ክልል ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ውስጥ የሚገኙ ከተሞችን፣ ወረዳዎችን እና አንዳንድ መንደሮችን በማዋሃድ “ሸገር ከተማ” የተባለ አዲስ አስተዳደር ተቋቁሟል።6አዲስ ስታንዳርድ፣ ጥር 1, 2015 እርምጃው በኦሮሚያ ክልል ትልቅ ለውጥ ያስመዘገበ ሲሆን የኢፒኦ ቡድን አዲሱን ከተማ በተመለከተ የሚወጡ አዳዲስ መረጃዎች በቅርብ ይከታተላል።