በቁጥር: ኢትዮጵያ ከየካቲት 18, 2014 – የካቲት 24, 2015
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 1,196
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 6,416
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 2,694
በቁጥር: ኢትዮጵያ ከየካቲት 18 – 24, 20151በዚህ የጊዜ ገደብ የተካተቱት አንዳንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ቁጥሮች ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 7
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 33
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 10
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን ከኢፒኦ የመረጃ መዝገብ እንዲሁም በዋናው የአክሌድ ኤክስፖርት መሳሪያ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ምንም እንኳን በርካታ ዉጊያዎች፣ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች እና ተቃውሞዎች የተመዘገቡ ቢሆንም በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አጠቃላይ የግጭት ሁኔታ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ጋብ ብሎ ቀጥሏል።
በኦሮሚያ በቅርቡ በክልሉ ምክር ቤት ውሳኔ በተደረገው አስተዳደራዊ እርከን ማሻሸያን ተከትሎ በተመሠረተው አዲሱ የምሥራቅ ቦረና ዞን ጋር በተያይዘ የተነሣው ሕዝባዊ ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው። የተቃውሞ ሰልፍ የወጡ ሰዎች መንግሥት በተደረገው ለውጥ የተጎዱ ነዋሪዎችን ሳያማክር አዲስ የአስተዳደር ዞን ለመፍጠር መሰኑን አውግዘዋል።የዞኑ የሀገር ሽማግሌዎችና እና ተወካዮች ከኦሮሚያ ክልል እና ከፌዴራል መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር በተነጋገሩበት ወቅት ሕዝባዊ ተቃውሞው የቆመ ቢሆንም፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት አዲሱን ዞን የመመሥረት ዉሳኔ “የማይቀለበስ”[2] መሆኑን ካተናገሩ በኋላ እንደገና የማገርሸት እድሉ ሰፊ ነው። (በቅርቡ በጉጂ ስለተደረገው ተቃውሞ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘትኢፒኦ ሳምንታዊ: ከየካቲት 18–24, 2015ን ይመልከቱ)።
እንደውም በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ከውኃ ጉድጓድ ጋር ተያይዞ በተነሣ ውዝግብ በኦሮሞ ብሔር ተወላጆች ላይ ጥቃት መፈጸሙ ተዘግቧል። በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ ቦታዎች ግጭቶች በተደጋጋሚ የሚከሰቱ ሲሆን ከ2008 እስከ 2010[3] በነበረው ግጭት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ተገድለዋል። በጥር ወር የውኃ ጉድጓድ ቁፋሮን በመቃወም የኦሮሞ ታጣቂዎች ሶስት የሶማሌ ተወላጆችን መግደላቸውን ተከትሎ በአካባቢው ውጥረቱ ቀጥሏል። የመንግሥት ኃይሎች በምስራቅ ኦሮሚያ በምትገኘው ምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግደገላ ወረዳ በሳምንቱ ባደረጉት ወታደራዊ እርምጃ 20 የኦሮሞ ነጻነት ግንባር – ሸኔ (ኦነግ- ሻኔ) ታጣቂዎችን መግደላቸው ተዘግቧል።
በኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ የከተማ አስተዳደሩ ትራንስፖርት ቢሮ በተለምዶ ባጃጅ በመባል የሚታወቁት ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎች በዋና ዋና መንገዶች ላይ አገልግሎት እንዳይሰጡ ማገዱን ተከትሎ አሽከርካሪዎች ሁከት ያስከተለ የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል። የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ሰልፈኞችን ለመበተን ባደረጉት ጥረት ቁጥራቸው በውል ባልታወቁ አሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት አድርሰዋል።
በአማራ ክልል በክልሉ መንግሥት እና በዋግ ኽምራ ዞን በሚንቀሳቀሰው “የአገው ሸንጎ” ታጣቂ ቡድን መካከል የሰላም ውይይት ተካሂዷል። ታጣቂ ቡድኑ የተመሠረተው የአገው ብሔራዊ ሸንጎ በመባል የሚታወቀውና በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የተመዘገበ የፖለቲካ ፓርቲ የቀድሞ አባላት ነው። ታጣቂ ቡድኖቹ “የአገው ዴሞክራሲያው ንቅናቄ” እና “የአገው ነጻነት ግንባር” በሚሉ ስያሜዎች ነው የሚንቀሳቀሱት። ንቅናቄው የአገው ብሔርተኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ጋር የተቆራኘ እና በጥቅምት 2014 “የኢትዮጵያ መንግሥትን በኃይልም ሆነ በድርድር ፍጽሞ ለማስወገድ” ታስቦ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር – ሸኔ (ኦነግ- ሻኔ)ን ጨምሮ ዘጠኝ ተቃዋሚ የፖለቲካ ኃይሎች የመሠረቱት የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት እና ኮንፌደራሊስት ኃይሎች አንድነት ግንባር[4] አባል መሆኑ ነው። የሰላም ዉይይቲን ወሳኝ የሚያደርገው ሌላው ነገር የአገው ሸንጎ ታጣቂ ቡድን በሰሜን ጠርነት ወቅት ከአማራ ክልል በመጡ ኃይሎችና በፌዴራል ኃይሎች ላይ በርካታ ጥቃቶችን ሲነዝር መቆየቱ ነው። በቡድኑ ሽምቅ ዉጊያ ምክንያት የዋግ ኽምራ ዞን አንዳንድ ቦታዎች ከመንግሥት ቁጥጥር ውጪ ሆነው ቆይተዋል።[5] ከዚህም የተነሣ የዋግ ኽምራ ዞን በሰሜኑ ጦርነት ወቅት በሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽ ካልሆኑ አካባቢዎች አንዱ ሆኖ ቆይቷል (ስለ አገው ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ እና ታሪኩ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ኢፒኦ ወርሃዊ፣ ከጥቅምት 22, 2014 እስከ ኅዳር 21, 2014ን ይመልከቱ)።[6]
በትግራይ ክልል በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሠረት በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ባለሥልታናት አስታውቀዋል። ከየካቲት 23 – 25 በተደረገው የጊዜያዊ መንግሥት ምሥረታ ኮንፈረንስ ላይ በተደረሰው የሥልጣን መጋራት ስምምነት መሠረት የክልሉ የሥልጣን ቦታዎች በህወሓት፣ በወታደራዊ ክንፍ አባላት፣ በተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶችና በምኁራን እንዲያዙ ስምምነት ላይ መደረሱን የጊዜያዊ መንግሥት ምሥረታ ኮሚቴ ምክትል ኃላፊ ተናግረዋል።[7] የጊዜያዊ መንግሥት ምሥረታ ሂደቱ ሙሉ በሙሉ በህወሓት መመራቱ ቅቡልነቱን አጠያያቂ ያደርገዋል ያሉ በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ኮንፈረንሱ ላይ ሳይሳተፉ ቀርተዋል። የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በሚቀጥለው ሳምንት ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ሲሆን ከፌደራል መንግሥት ባለስልጣናት እና ከትግራይ ክልል ተወካዮች ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።[8]
[1] በዚህ የጊዜ ገደብ የተካተቱት አንዳንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ቁጥሮች ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
[2] ዶቼዌሌ አማርኛ፣ ‘የጉጂው ውዝግብና የተወካዮችና የባለስልጣናት ውይይት’፣ የካቲት 30፣ 2015
[3] ቢቢሲ፣ ‘ከኦሮሚያና ሱማሌ ክልሎች ድንበር ግጭት ጀርባ ያለው ነገር ምንድን ነው?’ ፣ መስከረም 8፣ 2010
[4] ዘ ጋርዲያን፣ ‘የኢትዮጵያ የተቃማዊ ፖለቲካ አንጃዎች ጥምረት መንግሥትን የመውደቅ አደጋ ላይ ጥሏል’፣ ጥቅምት 26, 2014
[5] ኢትዮጵያ ኢንሳይደር፣ ‘የአማራ ክልል መንግስት ከ“አገው ሸንጎ” ታጣቂ ቡድን ጋር የሰላም ንግግር እያደረገ መሆኑን አስታወቀ’፣ መጋቢት 1, 2015
[6] አዲስ ስታንዳርድ፣ ‘የሰብዓዊ እርዳታ ተሽከርካሪዎች ከአንድ ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋግ ኽምራ ዞን ደረሱ’፣ ሐምሌ 20, 2014
[8] ሮይተርስ፣ ‘ብሊንከን በሚቀጥለው ሳምንት ኢትዮጵያና ኒጀርን ሊጎበኙ ነው’፣ መጋቢት 2, 2015