በቁጥር: ኢትዮጵያ ከመጋቢት 2፣ 2014 – መጋቢት 8፣2015
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 1,169
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 6,347
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 2,671
በቁጥር: ኢትዮጵያ ከመጋቢት 9 – 15፣ 20151በዚህ የጊዜ ገደብ የተካተቱት አንዳንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ቁጥሮች ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 3
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 4
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 4
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን ከኢፒኦ የመረጃ መዝገብ እንዲሁም በዋናው የአክሌድ ኤክስፖርት መሣሪያ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ሕግ አውጭዎች የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይን (ህወሓት) የአሸባሪነት ስያሜ እንዲሰረዝ ድምጽ በመስጠታቸው በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ሂደት ቀጥሏል። በተጨማሪም በቤኒሻንጉል/ጉሙዝ ክልል የሰላም ሂደት ቀጥሎ የቀድሞ አማጺያን ባለፈው ሳምንት ከእስር የተፈቱ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል ደግሞ ጥቂት ግችቶች ተመዝግበዋል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)።
በትግራይ ክልል መጋቢት 21 በጦርነት የቆሰሉ እና ለአካል ጉዳት የተዳረጉ የቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎች (የትግራይ መከላከያ ሠራዊት በመባልም ይታወቃሉ) በቂ የምግብ፣ ሕክምና፣ መድኃነት እና ሎሎች መሠርታዊ እንክብካቤዎች እጦትን በመቃወም በክልሉ ርዕሰ መዲና መቐለ ሰልፍ አድርገዋል። ወታደራዊ እና የፖሊሶች ኃይሎች የተቃውሞ ሰልፉን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ ተኩሰውባቸዋል። ተቃውሞው ከጥቅምት 6፣ 2014 ወዲህ በመቐለ የተካሄደ፣ እንዲሁም አዲስ በተመሠረተው ጊዜያዊ አስተዳደር ላይ የተደረገ የመጀመሪያው ሰላማዊ ሰልፍ ነው። የህወሓት ቃል አቀባይ ሆነው ያገለገሉት አቶ ጌታቸው ረዳ ባለፈው ሳምንት በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሆነው መሾማቸው ይታወሳል። አቶ ጌታቸው ረዳ “በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎችን ውክልና የሚያረጋግጥ ሁሉንም ያካተተ አስተዳደር” የማቋቋም ኃላፊነት ተጥሎበታል2ሮይተርስ፣ ‘ኢትዮጵያ በሰላም ስምመነቱ አንድ አካል የሆነውን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አቋቋመች’፣ መጋቢት 14፣ 2015።
ባለፈው ሳምንት ህወሓት ከአሸባሪ ድርጅቶች ዝርዝር ውስጥ የተሰረዘ ሲሆን ይህም የተለያዩ ግብረመልሶችን አስተናግዷል። አብዛኛዎቹ የፓርላማ አባላት የህወሓት የሽብርተኝነት ስያሜ እንዲሰረዝ ድምጽ ሲሰጡ፣ የተቃዋሚው አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባላትን ጨምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የፓርላማ አባላት ውሳኔውን ተቃውመዋል። አብን ባወጣው መግለጫ ህወሓት ለሌላ ዙር ጦርነት እየተዘጋ እንጂ በስምምነቱ መሠረት ትጥቁንም አልፈታም ሲሉ የፓርላማውን ውሳኔ አውግዘዋል3የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ ‘የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ፣’ መጋቢት 14 ቀን 2015። በሌላ በኩልም የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ፓርቲ አባላትም ውሳኔውን “ከተጠያቂነት ለማምለጥ የሚደረግ ጥረት” ነው ብሏል4 አዲስ ስታንዳርድ፣ ‘ዜና፡- የሕወሃት ከአሸባሪነት መውጣቱ “የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር መመሥረትን ያፋጥናል”፣ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል፣ መጋቢት 14፣ 2025። በደቡብ ትግራይ ዞን አላማጣ ከተማ የሚኖሩ የአማራ ብሔር ተወላጆች ህወሓት ተመልሶ አንዳይመጣ (እንዳያስተዳድራቸው) መንግሥት የበለጠ እንዲሠራ ጠይቀዋል። አንዳንድ የሰልፉ ተካፋዮች የአካባቢውን ታሪካዊ የአማራ ባለቤትነት የሚገልጹ ባነሮች በመያዝ በትግራይ ክልል ባለሥልጣናት ሥር መተዳደራቸው በይፋ እንዲቀር የሚጠይቁ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል5የአሜሪካ ድምፅ አማርኛ፣ “የራያ የማንነት ጥያቄ ምላሽ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄዷል”፣ መጋቢት 11፣ 2025። በአሁኑ ወቅት ደቡብ ትግራይ ዞን በይፋ የሚተዳደረው በትግራይ ክልል ቢሆንም፣ ግጭቱ በተጀመረበት ወቅት የአማራ ኃይሎች አካባቢውን ከያዙ ወዲህ የተወሰኑ አካባቢዎች በአማራ ክልል ባለስልጣናት ሲተዳደር ቆይቷል (ለበለጠ መረጃ የኢፕኦ ትግራይ ክልል ገፅን ይመልከቱ)። ይህ አካባቢ፣ እንዲሁም በምዕራብ ትግራይ ዞን ወልቃይት አካባቢ የትግራይ ተወላጆች እና የአማራ ተወላጆች የሚኖሩበት እና በሁለቱም ክልሎች የባለቤትነት ጥያቄ የሚነሣበት ሲሆን ከጥቅምት 2013 ጀምሮ ለሰሜኑ ጦርነት እንደ ቁልፍ የግጭት መንሥዔ ጉዳይ ሲነሣ ቆይቷል።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰላም ሂደት ቀጥሏል። ባለፈው ሳምንት የሁለቱም አማጺያን ቡድን መሪዎች ማለትም የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉሕዴን) እና የቤኒሻንጉል ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ (ቤሕነን) ከእስር ተፈተዋል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከመጋቢት 2014 ጀምሮ በክልሉ በተጀመረው የሰላም ሂደት እና የጸጥታ ኃይሎች በብዛት በሥፍራው በመኖራቸው በክልሉ የነበረው ግጭት በእጅጉ ቀንሷል።
በኦሮሚያ ክልል መጋቢት 14 ቀን በሰሜን ሸዋ ዞን ጉንዶ መስቀል ከተማ የፌደራል ፖሊስና የአካባቢው የቀበሌ ሚሊሻ መካከል ግጭት መፈጠሩ ታውቋል። የግጭቱ መንሥዔ የፌዴራል ፖሊስ አባላት የቀበሌ ሚሊሻ አዛዥን ትጥቅ ለማስፈታት እና በቁጥጥር ስር ለማዋል ሙከራ ማደረጉ ነው። ኅዳር 2021 የኦሮሞ ነጻነት ግንባር-ሼኔ ተዋጊዎች ከተማዋን ለአጭር ጊዜ በተቆጣጠሩ ጊዜ ከቀበሌው ሚሊሻዎች ጋር በተደጋጋሚ ሲዋጉ፣ የአካባባኢውን ባለሥልጣናትና ሰላማዊ ሰዎችን አፍኖ በመውሰድ እና ለመልቀቅ የቤዛ ገንዘብ ሲቀበሉ ነበር። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በርካታ የፖለቲካ ግጭቶች የነበሩ ሲሆን በከተማዋ ውስጥ በሰላማዊ ሰዎች እና በመንግሥት ባለስልጣናት ላይ የሚፈጸሙ በርካታ ጉዳቶች ተዘግቧል።
በመጨረሻም በአዲስ አበባ መጋቢት 14 ቀን አንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህን ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ በሚገኘው ሆርሲሳ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አገልግለው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ በድንጋይ ተወግረው ተገድለዋል። በካህኑ ግድያ ዙሪያ ያሉት ዝርዝር መረጃ አልተገኘም። ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ በቤተክርስቲያኒቱ እና በተለያዩ የአገሪቱ የፖለቲካ ቡድኖች መካከል ውጥረት ነግሦ ቆይቷል። (ለበለጠ መረጃ ኢፒኦ ወርሃዊ፣ የካቲት 2015፣ የሃይማኖት አለመግባባቶች እና የመንግሥት ጣልቃ ገብነትን ይመልከቱ)።