በቁጥር: ኢትዮጵያ, ከመጋቢት 23, 2014-መጋቢት 29, 2015
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 1,150
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 6,195
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 2,624
በቁጥር: ኢትዮጵያ, ከመጋቢት 23-29, 20151 በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ በመረጃ ቋታችን ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 8
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 4
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 2
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን ከኢፒኦ የመረጃ መዝገብ እንዲሁም በዋናው የአክሌድ ኤክስፖርት መሳሪያ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፈው ሳምንት ውጥረት ነግሶ ነበር። ላለፉት ሳምንታት አንጻራዊ ሰላም የነበረ ቢሆንም ባለፈው ሳምንት ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጋር ሲነጻጸር ቁጥሩ ከፍ ያለ ያለመረጋጋት ኩነቶች የተመዘገቡ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ በርካታ ዋና ዋና ኩነቶች መንግስት የክልል ልዩ ኃይልን ወደ ኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ ፌዴራል ፖሊስ ወይም የክልል ፖሊስ ጋር ለማዋሃድ ካቀደው እቅድ ጋር የተያይዙ ናቸው።
የመጋቢት ወር አቢይ አህመድ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ከተሾሙ አምስት አመታትን እንደሆነ ያመላክታል። ይህ ሹመት የተከናወነው በሀገሪቱ በተለይም በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች በትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሓት) የሚመራው መንግስት ስልጣን እንዲለቅ እና በሀገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ ለውጥ እንዲደረግ የሚጠይቁ ከ1,000 በላይ ሰልፎች በተመዘገቡበት ለአምስት ዓመታት የዘለቀውን አለመረጋጋት ተከትሎ ነው። በዓለ ሹመቱ በሚከበርበት መጋቢት 24 ቀን በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ተቃራኒ ሁኔታዎች ተስተውለዋል። በኦሮሚያ ክልል መንግስትን እና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን የሚደግፍ ሰልፎች “በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች” ተካሂደዋል።2 የኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ፣ ‘”የኦሮሞ ህዝብ ኢትዮጵያን እንድነት እውን ለማድረግ የሚደረገውን ጉዞ በሽምቅ ተዋጊዎች ጩኸት ሊደናቀፍ እንደማይችል አሳይቷል።” ሃይሉ አዱኛ፣ የኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ፣’ መጋቢት 24, 2015፤ ሥዩም ጌቱ እና እሸቴ በቀለ፣ ‘ዐቢይ ሥልጣን የያዙበትን አምስተኛ ዓመት ለመዘከር በተካሔደው ሰልፍ ምን ተባለ?’ ዶይቸ ቬለ አማርኛ፣ መጋቢት 24, 2015 በሌላ በኩል በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ እና በምዕራብ ጎጃም ዞን መራዊ፣ ደንበጫ እና ጅጋ ከተሞች መንግስትን የሚቃወም ስልፎች መደረጋቸው ተዘግቧል። ለተቃውሞ ሰልፍ የወጡ ሰዎች መንግስት “በአማራዎች ላይ እየደረሰ ያለውን በደል” እንዲያቆም እና የታሰሩትን እንዲፈታ ጠይቀዋል።3ዓለምነው መኮንን፣ አዜብ ታደሰ እና ማንተጋፍቶት ስለሺ፣ ‘መንግሥት በአማሮች ላይ የሚደርሰዉን እንግልትና መዋከብ እንዲያስቆ መጠየቁ፣’ ዶይቸ ቬለ አማርኛ፣ መጋቢት 25, 2015 በትግራይ ደቡባዊ ትግራይ ዞን ራያ አላማጣ ዞንም ተመሳሳይ ተቃውሞ መደረጉ ታውቋል። በዚህ አካባቢ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች በአማራ ክልል ስር መተዳደር ይፈልጋሉ። በዕለቱ በደቡብ ትግራይ ዞን የኦፍላ ወረዳ፣ ኮረም ከተማ እና ዛታ ወረዳ ነዋሪዎች በአማራ ክልል ስር እንዲተዳደሩ እና “ማንነታችን ይከበር” ሲሉ ጠይቀዋል።4የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ‘የወፍላ፣ ዛታ እና ኮረም ነዋሪዎች የማንነት ጥያቄ፣’ መጋቢት 24, 2015
ባለፈው አመት በገዥው ፓርቲ ብልፅግና ፓርቲ ውስጥ በአማራ ብልፅግና ፓርቲ እና በኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ መካከል አለመግባባት ተስተውሏል (በብልጽግና ፓርቲ ውስጥ እየጨመረ ስላለው አለመግባባት የበለጠ መረጃ ለማግኘት ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከመጋቢት 17, 2014 እስከ መጋቢት 23, 2014ን ይመልከቱ)። ላለፉት ጥቂት አመታት በአማራ ክልል በገዢው መንግስት ላይ በተለይም በኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ላይ ያለው ቁጣ እየጨመረ መጥቷል። ይህ የተፈጠረው በኦሮሚያ ክልል በአማራ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ካለው ግድያ፣ አማራ ክልልን በኦሮሚያ ክልል አቋርጦ ከዋና ከተማዋ አዲስ አበባ የሚያገናኘው ዋና መንገድ በየጊዜው መዘጋት እና ቀደም ሲል የፊንፊኔ ልዩ ዞን ተብሎ ይጠራ በነበረው በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል በተቋቋመው ሸገር ከተማ የመኖሪያ ቤቶች መፍረስ ጋር የተያያዘ ነው (በኦሮሚያ ክልል በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰው የጥቃት አዝማሚያ ላይ ለበለጠ መረጃ ለማግኛት ኢፒኦ ወርሀዊ:- ከግንቦት 24 እስከ ሰኔ 23, 2014ን፤ በቅርብ ጊዜ ስለተዘጉት መንገዶች ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከየካቲት 4–10, 2015ን ይመልከቱ)።
መጋቢት 28 ቀን በሰሜን ወሎ ዞን በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና በአማራ ክልል ልዩ ኃይል መካከል ውጊያ መከሰቱ ከዘገበ በኋላ በክልሉ በገዥው ፓርቲ ላይ ያለው ቅሬታ ተባብሷል። በሁለቱ ወገኖች መካከል ውጊያ በጎቢዬ መደረጉ ተዘግቧል። በራያ ቆቦ ወረዳ ቃሊም እና በላጎ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ መደረጉም ተነግሯል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። በተጨማሪም በጎማጣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከአማራ ክልል ልዩ ኃይል እና ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር ተዋግቷል። እነዚህ ውጊያዎች የተቀሰቀሱት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የክልሉ ልዩ ኃይል አባላትን “ትጥቅ ለማስፈታት” ሲሞክር እንደነበር ተነግሯል።5የኢትዮጵያ ሚዲያ ሰርቪስ፣ ‘ኢኤምኤስ እለታዊ ሐሙስ መጋቢት 28, 2015፣’ መጋቢት 28, 2015፤ አል አይን ኒውስ፣ ‘ልዩ ኃይል እንዲፈርስ መወሰኑን ተከትሎ በአማራ ክልል ተቃውሞ ተቀሰቀሰ፣’ መጋቢት 29, 2015
የኢትዮጵያ መንግስት መጋቢት 8 ቀን በሰሜን ወሎ ዞን ውጊያ መከሰቱ ከተዘገበ በኋላ በሁሉም የሀገሪቱ ክልል የሚገኙ የክልል ልዩ ኃይሎችን ወደ ተለያዩ የፀጥታ መዋቀሮች ውስጥ “እንዲገቡ” ማቀዱን በይፋ አስታውቋል።6የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት፣ ‘በወቅታዊ ጉዳይ ከመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ፣’ መጋቢት 28, 2015 በሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ የክልሉ ልዩ ኃይል “ትጥቅ እንዲፈታ” መወሰኑን በመቃወም ሰልፎች ተካሂደዋል።7አል አይን ኒውስ፣ ‘ልዩ ኃይል እንዲፈርስ መወሰኑን ተከትሎ በአማራ ክልል ተቃውሞ ተቀሰቀሰ፣’ መጋቢት 29, 2015 ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ የአማራ ልዩ ኃይሎች ወታደራዊ ካምፖችን ለቀው ዋናውን መንገድ ከዘጉ ሰልፈኞች ጋር መቀላቀላቸው ተነግሯል። በማግስቱ መጋቢት 9 ቀን በምስራቅ ጎጃም ዞን የደጀን ከተማ ነዋሪዎች የአማራ ክልል ርዕሰ መዲና ባህርዳርን ከዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ጋር የሚያገናኘውን ዋና መንገድ በድንጋይ ዘግተዋል። የፌዴራል ፖሊስ ንብረት የሆነ መኪናም አቃጥለዋል። በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት እና ሌሎች የንግድ ተቋማት እስከ ሚቀጥለው ቀን ተዘግተው ቆይተዋል። መንገዱ ግን ሚያዚያ 3 ቀን እንደገና ለመንገደኞች ክፍት ሆኗል።8አማኑኤል ይልቃል፣ ‘በተቃውሞ ሳቢያ ተዘግቶ የነበረው የደጀን መንገድ፤ ዛሬ ለሀገር አቋራጭ ትራንስፖርት አገልግሎት ክፍት ሆነ፣’ ኢትዮጵያ ኢንሳደር፣ ሚያዚያ 3, 2015
ከዚህ ቀደም በዚህ ዕቅድ ላይ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የክልል ልዩ ኃይሎችን እና ታጣቂዎችን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ተጠባባቂ ኃይል ለማድረግ ጥናት እየተደረገ መሆኑን በማመላከት ከሰጡት መግለጫ ውጭ ምንም አይነት ይፋዊ ሪፖርት/መግለጫ አልነበረም። ይህ ጥናት በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ወቅት የክልል ልዩ ኃይሎች እና ታጣቂዎች በነበራቸው ሚና ላይ የተመሰረተ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዋ ጠቁመዋል።9ሲሳይ ሳህሉ፣ ‘የክልሎች ልዩ ኃይልና ሚሊሻ በመከላከያ ሠራዊት ተጠባባቂ ኃይል እንዲካተቱ ጥናት እየተደረገ ነው፣’ ሪፖርተር፣ የካቲት 12, 2015 ነገር ግን ከሦስት ሳምንት በፊት አካባቢ የክልሉ ልዩ ኃይል ትጥቅ ለማስፈታት ተወስኗል የሚል ወሬ በተለይም የአማራ ክልል ልዩ ኃይል መኖር ከሌሎች በፌደራል መንግስት ስር ካሉ የፀጥታ ኃይሎች በላይ ለአማራ ክልል ደህንነት እና ጥቅም አስፈላጊ ነው በሚሉ የአማራ ብሔርተኞች መድረኮች ላይ ይናፈስ ነበር።10የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ ‘በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ፣’ ሚያዚያ 3, 2015፤ አዲስ ማለዳ፣ ‘ህወሓት በርካታ ታጣቂዎችን ወደ አማራ ክልል እያስጠጋ ነው፣ ቤንዚን 200 ብር!፣ ‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ፈጽሟል››’ መጋቢት 12, 2015
በየካቲት ወር የፌዴራል መንግስት ለክልሉ ልዩ ኃይል ማሰልጠን እንዲያቆም መጠየቁን ተከትሎ በአማራ ክልል እና በፌዴራል መንግስታት መካከል አለመግባባት መፈጠሩን አንድ ዘገባ አመልክቶ ነበር። የክልሉ መንግስት የትህነግ/ህወሓት ኃይሎች በክልሉ ላይ ጥቃት ሊሰነዝሩ እንደሚችሉ ያሚያሳዩ ምልክቶችን በመጥቀስ ይህንን ውሳኔ ውድቅ አድርጎታል ተብሏል።11አንከር ኢትዮጵያ፣ ‘አንከር ሚዲያ ዜና፡ የአማራ ብልጽግና መግለጪያው የወጣበት ምክንያት፥ የወልቂጤው የቤት ውስጥ አድማ፥ በሸገር ከተማ የቀጠለው ማፈናቀል፣’ የካቲት 12, 2015 ከዚህም አልፎ በአማራ ክልል የሚገኙ አንዳንድ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ይህ በክልሉ ልዩ ኃይል ላይ የሚወሰደው እርምጃ በአማራ ክልል ብቻ እየተተገበረ ነው ሲሉ12 አብን፣ ‘በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ፣’ ሚያዚያ 3, 2015 መንግስት ግን በተመሳሳይ ጊዜ በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች እየተተገበረ ነው ሲል አፅኖት ስጥቷል።13ፌስቡክ @አብይ አህመድ አሊ፣ ‘“ከጊዜያዊ መፍትሄ ዘላቂ ጥቅም አይገኝም!”’ ሚያዚያ 1, 2015፤ አሚኮ፣ ‘”የአማራ ልዩ ኃይልን በተለየ መንገድ ትጥቅ ለማስፈታት እና ለመበተን የተወሰነ ውሳኔ የለም” ርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)፣’ ሚያዚያ 1, 2015፤ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ‘ከጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተደረገ ቆይታ፣’ መጋቢት 29, 2015 ይህንን ሊያረጋግጡ የሚችሉ ምንም ተጨማሪ ዘገባዎች የሉም። ሆኖም በሚያዝያ 2 ቀን የሶማሌ ክልል ካቢኔ የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን ጨምሮ ወደ ተለያዩ የፀጥታ መዋቀሮች እንዲቀላቀል የተላለፈውን ውሳኔ አጽድቋል።14አዲስ ስታንደርድ፣ ‘ኒውስ አለርት፡ የሶማሌ ክልል ካቢኔ የመንግስትን የክልል ልዩ ኃይል የመበተን የመቀላቀል እቅድን በሙሉ ድምፅ አፀደቀ፣’ ሚያዚያ 2, 2015
በመርህ ደረጃ አብዛኛው ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች የክልል ልዩ ኃይሎችን ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና ከሌሎች የፀጥታ መዋቅሮች ጋር የማዋሃድ ሃሳብን ይቀበሉታል። ነገር ግን የአማራ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይህ ውሳኔ ሊፈፀምበት የታቀደበትን ወቅት እና ይህ ውሳኔ በሌሎች ክልሎችም በተመሳሳይ ተፈፃሚ መሆኑን ጥርጣሬ አድሮባቸዋል።15ሥዩም ጌቱ፣ ማንተጋፍቶት ስለሺ እና ታምራት ዲንሳ፣ ‘ውዝግብ ያስነሳው የክልሎች ልዩ ኃይሎች ጉዳይ፣’ ዶይቸ ቬለ አማርኛ፣ ሚያዚያ 2, 2015 የፌዴራል መንግስት የክልሉን ልዩ ኃይል ለማዋሃድ የሚያደርገውን ጥረት ተከትሎ የአሜሪካ የአማራ ማህበር በሌሎች 47 የዲያስፖራ ድርጅቶች በተፈረመ መግለጫ “የአማራ ህዝብ ለህዝባዊ ትግል እንዲነሳ” ጥሪ አቅርቧል።16ኤኤኤ፣ ‘መግለጫ፣’ መጋቢት 30, 2015
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ውሳኔውን ሊቃወሙ በሚችሉት ላይ የኃይል እርምጃ እንደሚወስዱ ማስጠንቀቂያ ቢሰጡም17ፌስቡክ @አብይ አህመድ አሊ፣ ‘“ከጊዜያዊ መፍትሄ ዘላቂ ጥቅም አይገኝም!”’ ሚያዚያ 1, 2015 የአማራ ክልል መንግስት ባለስልጣናት ውሳኔው በአማራ ክልል ብቻ ሳይሆን በአገር አቀፍ ደረጃ እንደሚተገበር ቢያረጋግጡም18አሚኮ፣ ‘”የአማራ ልዩ ኃይልን በተለየ መንገድ ትጥቅ ለማስፈታት እና ለመበተን የተወሰነ ውሳኔ የለም” ርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)፣’ ሚያዚያ 1, 2015 ሰልፎች እንዲሁም ውጊያዎች ባለፈው ሳምንት መጨረሻ እና በዚህ ሳምንት ቀጥለዋል።19ለምሳሌ ካትሪን ሁሬልድ፣ ‘የኢትዮጵያ የክልል ሃይሎችን ትጥቅ የማስፈታት እቅድ በአማራ ተቃውሞ ተቀስቅሷል፣’ ዋሽንግተን ፖስት፣ ሚያዝያ 2, 2015፤ ዳዊት እንደሻው፣ ‘የክልል ኃይሎችን ትጥቅ ለማስፈታት የታቀደው ዕቅድ በኢትዮጵያ የአማራ ክልል ተኩስ፣ ተቃውሞ አስነሳ፣’ ሮይተርስ፣ ሚያዝያ 1, 2015 ይመልከቱ በመሆኑም ጎንደር፣ ደሴ እና ደብረ ብርሃን ከተሞችን ጨምሮ በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሰዓት እላፊ ገደብ ተጥሏል።20 ዋዜማ ሬዲዮ፣ ‘ለቸኮለ ማለዳ! ማክሰኞ ሚያዝያ 3/2015 ዓ.ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች፣’ ሚያዚያ 3, 2015፤ ዋዜማ ሬዲዮ፣ ‘ኒውስ አለርት፣’ ሚያዚያ 3, 2015፤ አዲስ ማለዳ፣ ‘በጎንደር ከተማ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስን ጨምሮ የተለያዩ ክልከላዎች ተጣሉ፣’ ሚያዚያ 2, 2015 የኢፒኦ ተመራማሪዎች እነዚህን ኩነቶች በቅርበት እየተከታተሉ ሲሆን እነዚህን ሰልፎች እና ውጊያዎችን የሚዳስስ ዘገባ በሚቀጥለው ሳምንት ይታተማል።
በሌላ በኩል በኦሮሚያ ክልል አፈና እና በሸገር ከተማ የቤታቸውን መፍረስ በተቃወሙ ሰዎች ላይ ከመጠን ያለፈ ኃይል መጠቀም እንደቀጠለ ነው። መጋቢት 25 ቀን በምስራቅ ሸዋ ዞን ወለንጪቲ ከተማ አቅራቢያ በአሪቦና አካባቢ ማንነታቸው ያልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች 15 የከባድ ጭነት መኪና አሽከርካሪዎች መኪናቸውን ካቆሙ በኋላ አግተው ወስደዋቸዋል። ከታፈኑት ውስጥ አምስቱ በተመሳሳይ ዕለት ተለቀዋል። መጋቢት 26 ቀን የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ኃይሎች በሸገር ከተማ በገፈርሳ ኖኖ ሴና አካባቢ የቤታቸውን መፍረስ የተቃወሙ ሰዎችን በኃይል ለመበተን ሞክሯል። በዚህ ምክንያት የተቀሰቀሰው አለመረጋጋት ወደ አጎራባች አዲስ አበባ ኮልፌ ኮምፕሬሲቭ አካባቢ ተስፋፍቷል። ተማሪዎች እና ሴቶችን ጨምሮ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች መቁሰላቸው ተነግሯል። ከዚህ በተጨማሪም ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የነበረው አለም ባንክ አካባቢ በማርያም ሰፈር የሸገር ከተማ የፀጥታ ኃይሎች 50 ቆርቆሮ መዝረፋቸውም ተነግሯል።
በቡራዩ ከተማ በቅርቡ የተቋቋመው ‘የኦሮሚያ እና ብሔር ብሔረሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስ’ የምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች ተዋካዮች የሆኑ ሁለት አባላት መታሰራቸው ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች በምስራቅ ወለጋ ዞን በነቀምቴ ከተማ መጋቢት 28 ቀን ተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። ሰልፈኞቹ ከኃይማኖታቸው ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ መንግስት ጣልቃ ይገባል ሲሉ ከሰዋል። የታሰሩት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን (ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ) ጋር እስካሁን ካልታረቁ አምስት ጳጳሳት መካከል ሳይሆኑ አይቀሩም። በሊቀ ጳጳስ አቡነ ሳዊሮስ እና ሁለት ሊቃነ ጳጳሳት ከተሾሙ 26 ጳጳሳት እና የኦሮሚያ እና ብሔሮች ብሔረሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስ ካቋቋሙት መካከል 21 ጳጳሳት እና ሦስት ሊቀነ ጳጳሳት በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ወደ ቀድሞ ሹመታቸው ተመልሰዋል።21የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት፣ ‘ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፣’ መጋቢት 21, 2015 ይህ የሆነው በየካቲት ወር የተከሰተውን አለመረጋጋት እና ግጭት ተከትሎ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ እና የኦሮሚያ እና ብሔር ብሔረሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስ መካከል የተደረሰውን ስምምነት መቀበላቸውን የሚገልፅ ድብዳቤ ካስገቡ በኃላ ነው (ለበለጠ መረጃ ኢፒኦ ከጥር 24 እስከ የካቲት 21, 2015 ወርሃዊ፡ የኃይማኖት አለመግባባቶች እና የመንግስት ጣልቃ ገብነት በኢትዮጵያ ይመልከቱ)።
በመጨረሻም መጋቢት 28 ቀን በሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን አፍዴም ወረዳ ዳባማራ በተባለ ቦታ የአፋር ብሔር ታጣቂዎች ከሶማሌ ብሔር ታጣቂዎች ጋር የተዋጉ ሲሆን በዚህም ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ሰዋች መሞታቸው ተዘግቧል።