በቁጥር: ኢትዮጵያ, ከመጋቢት 30, 2014-ሚያዚያ 6, 2015
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 1,143
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 6,116
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 2,600
በቁጥር: ኢትዮጵያ, ከመጋቢት 30-ሚያዚያ 6, 20151በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ በመረጃ ቋታችን ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 19
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 32
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 16
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን ከኢፒኦ የመረጃ መዝገብ እንዲሁም በዋናው የአክሌድ ኤክስፖርት መሳሪያ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ በአማራ ክልል የክልሉ ልዩ ኃይልን ወደ ሌሎች የፀጥታ መዋቅር ለመቀላቀል የታቀደውን ዕቅድ የሚቃወሙ ስልፎች የቀጠሉ ሲሆን የፀጥታ ኃይሎች እነዚህን ስልፎች በኃይል መበተናቸው እና የሞት አደጋ መድረሱም ሪፖርት ተደርጓል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በክልሉ ፀጥታ ለማስከበር በተንቀሳቀሰበት ወቅትም የውጊያ ኩነቶች ተመዝግበዋል። የተቀረው የአገሪቱ ክፍል በአንጻራዊ ሁኔታ ሰላማዊ ነበር።
በአማራ ክልል የክልል ልዩ ኃይልን ወደ ሌሎች የፀጥታ መዋቅር ለመቀላቀል የታቀደውን ዕቅድ በተመለከተ የሚደረገው ተቃውሞ የቀጠለ ሲሆን ባለፈው ሳምንት በክልሉ ቢያንስ በ18 ቦታዎች የተካሄዱ ሰልፎች ተመዝግበዋል (ስለ ተነሳው ግርግር ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ኢፒኦ ሳምንታዊ: መጋቢት 23-29, 2015 ይመልከቱ)። በአማራ ክልል በፀጥታ ኃይሎች ቢያንስ በአምስት ቦታዎች በተወሰደው እርምጃ ቢያንስ 15 ሰዎች መሞታቸውን አክሌድ ዘግቧል። በፌዴራል መንግስት ውሳኔ ላይ የተቀሰቀስው ቁጣ የክልሉን ልዩ ኃይል ከሌሎች የፀጥታ መዋቅር ጋር መቀላቀል የአማራ ክልል ወደፊት በትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር ሊደርስበት የሚችለውን ጥቃት መከላከል እንዳይችል ያደርገዋል በሚል ፍራቻ ላይ የተመሰረተ ነው። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አምስት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የገዥው ብልፅግና ፓርቲ ውሳኔ “ህገ-ወጥ ነው” ሲሉ አውግዘዋል።2ዶይቸ ቬለ አማርኛ፣ ‘የልዩ ኃይሎች አደረጃጃት የቀሰቀሰዉ ዉዝግብ፣’ ሚያዚያ 3, 2015
ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል ውጊያዎችም ተመዝግበዋል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። ሚያዚያ 1 ቀን በቆቦ ከተማ የመከላከያ ሠራዊት ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር የተዋጋ ሲሆን የሶስት ታጣቂዎች ህይወት መጥፋቱ ተዘግቧል። በመኪና ወደ አዲስ አበባ ይጓዙ የነበሩ ሁለት የሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞችም በተኩሱ መሃል ተገድለዋል።3ካቶሊክ ሪሊፍ ስርቪስ፣ ‘ካቶሊክ ሪሊፍ ስርቪስ በኢትዮጵያ ሁለት ሰራተኞችን በማጣታቸው ሀዘኑን ገለጸ፣’ ሚያዝያ 2, 2015 በተጨማሪም ሚያዝያ 2 እና 3 ቀን በደብረ ብርሃን የአማራ ክልል ልዩ ኃይል እና አጋር የፋኖ ታጣቂዎች ከመከላከያ ሠራዊት ጋር የተዋጉ ሲሆን በከተማው አቅራቢያ በሚገኝ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ በትንሹ ሁለት ሰዎች በተባራሪ ጥይት ተመተው ህይወታቸው አልፏል።4የኢትዮጵያ ሚዲያ ስርቪስ፣ ‘ኢኤምኤስ መረጃ እሮብ ሚያዚያ 4, 2015፣’ ሚያዚያ 4, 2015 በሰሜን ሸዋ ዞን መዘዞ ከተማ በፋኖ ታጣቂዎች እና በአማራ ክልል ፖሊስ መካከል ውጊያ የተደረገ ሲሆን ታጣቂዎቹ በከተማው የሚገኘውን ፖሊስ ጣቢያ መቆጣጠራቸውን ታውቋል።
በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት መሠረት የክልል መንግሥታት “የክልሉን የፖሊስ ኃይል ያደራጃል፤ ይመራል፤ የክልሉን ሰላምና ጸጥታ ያስጠብቃል።”5ኮንስቲትውት ፕሮጅክት፣ ‘የ1987 የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣’ ሚያዝያ 19, 2014 ሁሉም ክልሎች የፖሊስ ኃይሎች ሲኖሯቸው ልዩ ኃይል ለመጀመሪያ ጊዜ እ.ኤ.አ. በ2008 የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባርን ለመመከት በሶማሌ ክልል ተቋቋመ።6አዲስ ስታንደርድ፣ ‘ኒውስ አለርት፡ የሶማሌ ክልል ካቢኔ የመንግስትን የክልል ልዩ ኃይል የመበተን የመቀላቀል እቅድን በሙሉ ድምፅ አፀደቀ፣’ ሚያዚያ 2, 2015፤ ሂዩማን ራይትስ ዎች፣ ‘ኢትዮጵያ፡ ‘ልዩ ፖሊስ’ 10 ገደለ፣’ እ.ኤ.አ ሜይ 28, 2012 በሚያዚያ 2013 በሶማሌ እና በአፋር ክልል ድንበሮች በተከሰቱት ውጊያዎች ጨምሮ እ.ኤ.አ. ከ2008 ጀምሮ የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተፈፀሙ ግድያዎች ላይ እጁ እንዳለበት ተመላክቷል (በሶማሌ/አፋር ክልሎች የድንበር ግጭት ላይ የበለጠ መረጃ ለማግኘት የኢፒኦ አፋር–ሶማሌ የድንበር ግጭት ገጽን ይመልከቱ)። በሚያዚያ 2 ቀን የሶማሌ ክልል ካቢኔ የክልሉ ልዩ ኃይሎችን “እንደ ምርጫቸው በመከላከያ፣ በፌዴራል ፖሊስ ወይም በክልል ፖሊስ ውስጥ ወደ ተለያዩ የፀጥታ መዋቅሮች” በማዋሃድ የፌዴራል መንግስትን መመሪያ ለመከተል በሙሉ ድምጽ ወስኗል።7አዲስ ስታንደርድ፣ ‘ኒውስ አለርት፡ የሶማሌ ክልል ካቢኔ የመንግስትን የክልል ልዩ ኃይል የመበተን የመቀላቀል እቅድን በሙሉ ድምፅ አፀደቀ፣’ ሚያዚያ 2, 2015
ከ2010 ጀምሮ በኢትዮጵያ በተከሰቱ ግጭቶች ውስጥ የክልል ልዩ ኃይሎች የበለጠ ተሳትፎ አድርገዋል። አክሌድ ቢያንስ 270 በልዩ ኃይሎች የተፈፀሙ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃቶችን የመዘገበ ሲሆን ይህም ከ2010 ጀምሮ የተፈጸሙ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠሩ የጥቃት ኩነቶች 16 በመቶውን ይይዛል። ልዩ ኃይሎችን ለመበተን የተደረሰው ውሳኔ በመንግስት የሚደገፉ ግጭቶች በአጠቃላይ እንዲቀንስ ሊያደርግ ይችላል ወይም በቀላሉ ግጭቶች ወደ ሌላ የመንግስት አካል ሊዛወር ይችላል። የኦሮሚያ ክልል እና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ባለስልጣናት የፌዴራል መንግስትን ውሳኔ በማክበር የልዩ ኃይላቸውን በታቀደው መሠረት ወደ ሌላ የፀጥታ መዋቅር ለመቀላቀል መወሰናቸውን አስታውቀዋል።8ቮይስ ኦፍ አሜሪካ አማርኛ፣ ‘የኦሮሚያ ክልል የልዩ ኃይል አደረጃጀትን ሥምሪት ማቆሙን አስታወቀ፣’ ሚያዚያ 5, 2015 ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ዋና ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ የክልል ልዩ ኃይሎች በሀገሪቱ የፀጥታ መዋቅር ዝርዝር ውስጥ ከዚህ በኃላ እንደ ሌሉ ገልፀዋል።9የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መከላከያ ሰራዊት፣ ‘ከዛሬ ጀምሮ የክልል ልዩ ኃይል የሚባል አደረጃጀት የለም – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣’ ሚያዚያ 7, 2015
በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ጉብኝት ስፖንሰር አላደረጉም በሚል ሱቆች እና ሆቴሎች መዘጋታቸውን በመቃወም የቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ ተደርጓል።10የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን፣ ‘ኢሳት አማርኛ ዜና ሚያዚያ 2, 2015፣’ ሚያዚያ 2, 2015 መጋቢት 16 ቀን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የጉራጌ ዞን እንደ ክልል እንዲቋቋም ባቀረቡት ጥያቄ ላይ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ለመምከር የጉራጌ ዞን አስተዳደር ማዕከል ወደ ሆነችው ወልቂጤ ከተማ ተጉዘው ነበር። ነገር ግን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ወቅት የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ለመመካከር የተመረጡት ሰዎች “ስለ ዞኑና ስለ ከተማው በቂ እውቀት የላቸውም” በማለት ከቤት ባለመውጣት ተቃውሞ አሰምተው ነበር (ለበለጠ መረጃ ኢፒኦ ሳምንታዊ: መጋቢት 16-22, 2015 ይመልከቱ)።11ዮናታን ዘብዴዎስ፣ ‘ወልቂጤ ውስጥ ከቤት ያለመውጣት አድማ መደረጉን ነዋሪዎች ተናገሩ።’ ቮይስ ኦፍ አሜሪካ አማርኛ፣ መጋቢት 16, 2015፤ ማኅሌት ፋሲል፣ ዩሃንስ ገብረ እግዚያብሔር፣ ‘የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ጉብኝት በወልቂጤ፣’ ዶቼ ቬለ አማርኛ፣ መጋቢት 16, 2015