በቁጥር: ኢትዮጵያ, ከግንቦት 12, 2014-ግንቦት 18, 2015
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 1,104
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 5,809
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 2,581
በቁጥር: ኢትዮጵያ, ከግንቦት 12-18, 20151በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ በመረጃ ቋታችን ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 19
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 44
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 38
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን ከኢፒኦ የመረጃ መዝገብ እንዲሁም በዋናው የአክሌድ ኤክስፖርት መሳሪያ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
በኦሮሚያ፣ በጋምቤላ እና በአማራ ክልሎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች እና ውጊያዎች ቀጥለዋል። በአዲስ አበባ የፀጥታ ኃይሎች ሙስሊም ተቃዋሚዎችን በኃይል አፈነዋል። ባለፈው ሳምንት አክሌድ በኦሮሚያ ውስጥ አምስት የውጊያ እና ስምንት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠሩ የጥቃት ኩነቶችን መዝግቧል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። ሁሉም የተመዘገቡት ውጊያዎች በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል የተደረጉ ሲሆን እነዚህ ውጊያዎች የተከሰቱት በጉጂ፣ ምዕራብ ጉጂ እና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች ነው። በተለይም ከዚህ ቀደም ምንም አይነት የኦነግ-ሸኔ እንቅስቃሴ ባልተመዘገበባቸው ከተሞች ኦነግ-ሸኔ አዲስ እንቅስቃሴ ማድረጉን ቀጥሏል። አብዛኛዎቹ እነዚህ ጥቃቶች ከቡድኑ ጋር ግንኙነት ያላቸውን እስረኞችን የመፍታት አላማ ያላቸው ይመስላል። ለምሳሌ በግንቦት 12 ቀን ኦነግ-ሸኔ እንደሆኑ የተገመቱ የታጠቂ ቡድን አባላት በአርሲ ዞን በበቆጂ ከተማ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት የሰነዘሩ ሲሆን የአካባቢው ታጣቂዎች አሰልጣኝን ጨምሮ አራት ሰላማዊ ሰዎችን ገድለዋል። ቡድኑ በከተማው ከሚገኝ አንድ እስር ቤት እስረኞችንም ማስፍታት ችሎ ነበር።
አሁንም ውጥረቱ ከፍተኛ ቢሆንም የአማራ ክልል ባለፈው ሳምንት በአንጻራዊ ሁኔታ የተረጋጋ ነበር። ግንቦት 17 ቀን በምዕራብ ጎጃም ዞን ባህር ዳር ከተማ ሙሉ አለም አዳራሽ አካባቢ የከነማ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ክለባቸውን ለመደገፍ ወደ ሀዋሳ ለመጓዝ በአውቶብስ እየተሳፈሩ በነበሩበት ወቅት ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች ሁለት የእጅ ቦንቦችን ወርውረዋል። በዚህ ጥቃት 23 ሰዎች ቆስለዋል።2 አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ‘በንጹሀን የባሕር ዳር ከነማ ደጋፊዎች ላይ የደረሠው ጥቃት መወገዝ የሚገባው የፀረ ሰላም እንቅስቃሴ መኾኑን ድረስ ሳኅሉ (ዶ.ር) ገለጹ፣’ ግንቦት 17, 2015 በማግስቱ በኦሮሚያ ልዩ ዞን ደዋ ሀሬዋ ወረዳ መልካ ዲዱ ቀበሌ የመንግስት ኃይሎች – የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የአማራ ክልል ፖሊስ ኃይሎች – ከኦነግ-ሸኔ ጋር ተዋግተዋል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አንድ የኦነግ-ሸኔ አባል መግደሉን ሌላ አንድ የቡድኑን አባል ማቁሰሉን እና ሁለት የኦነግ-ሸኔ አዛዦችን መያዙን ገልጿል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በጋምቤላ ክልል ድንበር ዘለል እና በጎሳ ግጭት ተከስቶ ነበር። ግንቦት 12 ቀን ከደቡብ ሱዳን የመጡ የሙርሌ ብሔረሰብ ታጣቂዎች ወደ ኢትዮጵያ ተሻግረው በኑዌር ዞን በማኩኤ ወረዳ ቢልኪቾ ቀበሌ እና ዋንታዎ ወረዳ መታር ከተማ በፕሮቴስታንት መካነ እየሱስ ቤተክርስትያን ላይ ህጻናትን ለማፈን በሰላማዊ ሰዎች ላይ ተኩስ የከፈቱ ሲሆን በዚህም ጥቃት 12 ሰዎች መቁሰላቸው እና 10 ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል።3የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስትያን፣ ‘በጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማታራ ቀበሌ በምዕመናን ላይ የደረሰውን ጥቃት አስመልክቶ ከኢት/ወ/ቤ/ክ መካነ ኢየሱስ የቀረበ የድጋፍና የፀሎት ጥሪ፣’ ግንቦት 21, 2015 በማግስቱ በኢታንግ ልዩ ወረዳ በፒግኑዋ እና ሌር ቀበሌዎች እንዲሁም በጋምቤላ ከተማ በኑዌር እና በአኙዋክ ብሔረሰብ ታጣቂዎች መካከል የእርስ በእርስ ግጭት ተቀስቅሷል።4የጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት፣ ‘በጋምቤላ ክልል በኢታንግ ልዩ ወረዳና በጋምቤላ ከተማ ሰሞኑን ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር በቁጥጥር ስር መዋሉን የክልሉ መንግስት አስታወቀ፣’ ግንቦት 17, 2015 ግጭቱ የጀመረው ከአንዱ ብሔር የተውጣጡ ታጣቂዎች በጀልባ ሲቀዝፍ የነበረውን የሌላኛውን ብሔር ታጣቂ በጥይት ተኩሰው ከገደሉ በኃላ ነው። በኢታንግ ልዩ ወረዳ እና በጋምቤላ ከተማ በተቀሰቀሰው ግጭት በትንሹ አምስት ሰዎች መሞታቸውና ሰባት ሰዎች መቁሰላቸው ተነግሯል። የሁለቱም ወገኖች ሰላማዊ ሰዎች ቤታቸውን ለቀው እንዲሰደዱ የተገደዱ ሲሆን በርካታ ቤቶችም ተቃጥለዋል።
በአዲስ አበባ ግንቦት 18 ቀን ከጁምዓ ሰላት በኋላ በመርካቶ በሚገኘው ታላቁ አንዋር መስጊድ በተካሄደው ሰልፍ ላይ የፀጥታ ኃይሎች ጥይት በመተኮሳቸው የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን እና ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ ተቃዋሚዎች መቁሰላቸው ተነግሯል። ህዝበ ሙስሊሙ በመርካቶ በሚገኘው ታላቁ አንዋር መስጂድ እና ፒያሳ በሚገኘው አል ኑር መስጊድ በመሰባሰብ በኦሮሚያ ክልል አዲስ በተቋቋመው ሸገር ከተማ ውስጥ በመንግስት እየደረሰ ያለውን መስጊድ ማፍረስን በማውገዝ ሰልፍ ወጥተዋል።5 ዶይቸ ቬለ አማርኛ፣ ‘በአንዋር እና በኒ መስጊዶች ሙስሊሞች ዛሬ ተቃውሞ አሰሙ፣’ ግንቦት 18፣ 2015 በአል ኑር መስጊድ የተደረገው ተቃውሞ በሰላም የተጠናቀቀ ሲሆን በታላቁ አንዋር መስጂድ የፀጥታ ኃይሎች – የፌዴራል ፖሊስ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ እና የሪፐብሊካን የጥበቃ ኃይሎች – ወደ ታላቁ አንዋር መስጂድ ቅጥር ግቢ በመግባት ህዝቡ ላይ አስለቃሽ ጭስ እና ጥይት በመተኮሳቸው ተቃውሞው ወደ ብጥብጥ ተቀይሯል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በኋላ እንደገለጸው አራት ሰላማዊ ሰዎች፣ እንዲሁም 37 የፖሊስ አባላት እና 15 “የፖሊስ አጋዥ ኃይሎች” ጉዳት ደርሶባቸዋል። እንደ ኮሚሽኑ ገለጻ ሰልፉን በማደራጀትና በመምራት የተከሰሱ 114 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።6አዲስ አበባ ፖሊስ፣ ‘የአርብ (የጁምዓ) ሶላት ከተጠናቀቀ በኋላ በመርካቶ አካባቢ በተፈጠረ ረብሻና ግርግር የሰው ሕይወት ሲያልፍ ህግ በማስከበር ስራ ላይ በተሰማሩ የፖሊስ አባላት ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፣’ ግንቦት 18, 2015 በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ አዲስ በተቋቋመው ሸገር ከተማ እየተካሄደ ባለው የቤቶች እና መስጊዶች ፈረሳ ምክንያት ያለው ቁጣ እየጨመረ መጥቷል። እንደ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከሆነ በሸገር ከተማ ከ19 ያላነሱ መስጊዶች ፈርሰዋል።7ሪፖርተር፣ ‘በመስጊድ በመፍረሳቸው ምክንያት ከፍተኛ ተቃውሞ ተቀስቅሷል፣’ ግንቦት 19, 2015 ምክር ቤቱ የጋራ ምክክር እስኪደረግ ድረስ ማፍረስ እንዲቆም ለኦሮሚያ ክልል መንግስት እና ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ደብዳቤ ጽፎ ነበር።8 የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ ‘የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት “በሸገር ሲቲ” እየፈረሱ ላሉት መሰጂዶች በአሰቸኳይ እንዲቆም ለኦሮምያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ደብዳቤ ፃፈ፣’ ሚያዘያ 28, 2025፤ የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ ‘የጠቅላይ ምክር ቤቱን የመስጂዶች ፈረሳን ጥያቄን ምላሽ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ባለመስጠቱ ለአፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ምክር ቤቱ ደብዳቤ ጻፈ፣’ ግንቦት 10, 2015 ምክር ቤቱ ለጥያቄያቸው ምላሽ ባለማግኘቱ በሀገሪቱ የሚገኙ ሙስሊሞች የማፍረስ ሂደቱን እንዲቃወሙ ጠይቋል።9የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ ‘በፕሬዝዳንቱ የተመራዉ ልዑክ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አደረገ,’ ግንቦት 18, 2015 ከዚያን ጊዜ በኃላ ከፖሊስ ኃላፊዎች ጋር ለመወያየት ተወካዮችን የላከ ሲሆን ግጭቱን ተከትሎ ለቀናት ተዘግቶ የነበረውን የአል ኑር መስጊድ በድጋሚ ተከፍቷል። በኢትዮጵያ ከኃይማኖት ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ ውጥረተች እየጨመሩ መጥተዋል (ለበለጠ ዝርዝር የኢፒኦ ከጥር 24 እስከ የካቲት 21, 2015 ወርሃዊ፡ የኃይማኖት አለመግባባቶች እና የመንግስት ጣልቃ ገብነት በኢትዮጵያ ይመልከቱ)። በትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር ተያይዞ ያለው ውጥረትም ከፍተኛ ሲሆን ባለፈው ሳምንት 10 ሊቃነ ጳጳሳትን በትግራይ ውስጥ እና በውጭ ሀገር የሚገኙ ሀገረ ስብከት ለመሾም ማቀዳቸውን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ራሳቸውን ለማግለል የወሰኑትን ውሳኔ ማጠናከራቸውን ያመላክታል።10አዲስ ስታንዳርድ፣ ‘ዜና፡ የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች 10 ኤጲስ ቆጶሳትን ሊሾሙ ማቀዳቸውን አስታወቁ፣’ ግንቦት 15, 2015 ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር ግንኙነት ያለው የማኅበረ ቅዱሳን ቲቪ የኃይማኖት ግጭትን የሚቀሰቅሱ ይዘቶች ያላቸውን ዘገባዎች ሰርቷል ከሳምንት በፊት ታግዶ የነበረው የመገናኛ ብዙኃን እገዳው ተነስቶለታል።11 ቮይስ ኦፍ አሜሪካ አማርኛ፣ ‘ባለሥልጣኑ በማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ያሳለፈውን ጊዜያዊ እግድ ማንሣቱን አስታወቀ፣’ ግንቦት 18, 2015
በተጨማሪም በሰሜናዊው ግጭት የተፈናቀሉ በሺዎች የሚቆጠሩ የሃገር ውስጥ ተፈናቃዮች የፌዴራል መንግስት ወደ መኖሪያ ስፍራቸው እንዲመልስላቸው እና በሰላም ስምምነቱ መሠረት ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ውጪ ያሉ ኃይሎች እንዲወጡ የሚጠይቅ ሰልፍ በትግራይ ክልል አድርገዋል። ሰልፈኞቹ በግንቦት 15 ቀን ቢያንስ በሰባት ቦታዎች ማለትም በመቀሌ፣ በአድዋ፣ በአክሱም፣ በአዲግራት፣ በሽሬ፣ በአቢ አዲ እና በሁመራ የተቃውሞ ስልፍ አድርገው ነበር። ከሁለት ቀናት በኋላ የኤርትራ መከላከያ ሠራዊት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተልዕኮ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት፣ የመንግስታቱ ድርጅት የደህንነት ዲፓርትመንት፣ የአለም ጤና ድርጅት እና ሌሎች አለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ ልዑካንን ጨምሮ ሌሎች ኤጀንሲዎች መልእክተኞቻቸው ገምሃሎ መንደር ከመግባት ክልክሏቸዋል። የኤርትራ መከላከያ ሠራዊት መንገድ ዘግቶ መልክተኞቹን ያስቆመው በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ዞን ታህታይ አዲያቦ ወረዳ ወላ ንህቢ ላይ ነው። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ መንግስትም የአፍሪካ ህብረት የሰላም ስምምነት ክትትልና ማረጋገጫ ቡድን ተግባራቱን እንዳይፈጽም የኤርትራ መከላከያ ሠራዊት ከልክሏል ሲል ከሷል።12ጂያንሉካ ሜዞፊዮሬ፣ ቤተልሄም ፈለቀ እና ሄዋን ብሬናን፣ ‘የእርዳታ ሰራተኞች ለሲኤንኤን እንደተናገሩት ከሆነ የኤርትራ ኃይሎች የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ተልዕኮ በኢትዮጵያ ትግራይ እንዳስቆሙ፣’ ሲኤንኤን፣ ግንቦት 18, 2015 የአፍሪካ ህብረት የሰላም ስምምነት ክትትልና ማረጋገጫ ቡድን ለዘለቄታው የጦርነት ማቆም ስምምነት የጋራ ኮሚቴ አባላት ባወጡት መግለጫ፣ “በአገር ውስጥ ተፈናቃዮችና ስደተኞች ወደ ቀድሞ ቦታቸው እንዲመለሱ በማመቻቸት ጉዳት የደረሰባቸው አካባቢዎች የዜጎችን ደህንነትና ጥበቃ ማሳደግ እንደሚገባ አሳስበዋል።”13አዲስ ስታንዳርድ, ‘ዜና፡ የአፍሪካ ህብረት ክትትል ቡድን ዲዲአር ማፋጠን፣ በትግራይ የሚገኙ ተፈናቃዮችን መመለስ እንዳለባቸው ትኩረት ሰጥቷል፣ ከኢትዮጵያ መከላከያ የውጭ የሆኑ ኃይሎች ለቀው መውጣት ላይ ዝም ብሏል፣’ ግንቦት 18, 2015
በመጨረሻም ግንቦት 18 ቀን የትህነግ/ህወሓት ኃይሎች በክልሉ ርዕሰ መዲና መቀሌ አቅራቢያ በምትገኘው ላጪ በተባለ ቦታ የተለያዩ ፀረ ታንክ እና ሞርታርን የመሰሉ የቡድን መሳሪያዎችን በፕሪቶሪያ የተፈረመው የሰላም ስምምነት መሠረት በአፍሪካ ህብረት የሚመራው የሰላም ስምምነት ክትትል እና ማረጋገጫ ቡድን በተገኘበት የጦር መሳሪያዎቹን ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አስረክበዋል። ትህነግ/ህወሓትም ተዋጊዎቹን ትጥቅ በማስፈታት ወደ 11 የመልሶ ማቋቋሚያ ካምፖች ማስገባት በይፋ ጀምሯል።