በዚህ ዘገባ ውስጥ የተካተቱ
- ከሚያዚያ 23 እስከ ግንቦት 23 በጨረፍታ
- አበይት ክንውኖች
- ከሚያዚያ 23 እስከ ግንቦት 23 ድረስ የተከሰቱ ቁልፍ ኩነቶች
- ወርሀዊ ትኩረት፡ የሰላም ንግግር ቢሞከርም በኦሮሚያ ዳግም ግጭት ተቀስቅሷል
ከሚያዚያ 23 እስከ ግንቦት 23 በጨረፍታ
አበይት ክንውኖች
- ከሚያዚያ 23 እስከ ግንቦት 23 ድረስ አክሌድ 88 የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች እና 273 ሪፖርት የተደረጉ ሟቾች መዝግቧል።በሀገሪቱ ከተመዘገቡት የፖለቲካ ግጭት ክስተቶች ወደ ግማሽ ያህሉ ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ ያደረጉ ኩነቶች ናቸው።
- ባለፈው ወር በኦሮሚያ ክልል በፖለቲካ ግጭት ምክንያት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኩነቶች እና ሪፖርት የተደረጉ ሟቾች ቁጥር ሲመዘገቡ፣ 58 ኩነቶች እና 203 ሪፖርት የተደረጉ ሟቾች ተመዝግበዋል። በኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ እና በመንግስት መካከል እየተደረገ የነበረው የሰላም ንግግር ያለስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ በክልሉ የሚስተዋሉ የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ቁጥር እየጨመሩ መተዋል።
- ከሚያዚያ 23 እስከ ግንቦት 23 ድረስ 25 የሰልፎ ኩነቶች የተመዘገቡ ሲሆን ግማሽ ያህሉ በአማራ ክልል የተከሰቱ ናቸው። አብዛኛው በአማራ ክልል የተደረጉ ሰልፎች መንግስት እያደረገ ባለው ‘ፅንፈኞች’ ላይ ያነጣጠር እርምጃ/ኦፕሬሽን ጋር የተያያዘ ነው።
ከሚያዚያ 23 እስከ ግንቦት 23 ድረስ የተከሰቱ ቁልፍ ኩነቶች
ወርሀዊ ትኩረት፡ የሰላም ንግግር ቢሞከርም በኦሮሚያ ዳግም ግጭት ተቀስቅሷል
ከታህሳስ እስከ ሚያዚያ 2015 ባለው ጊዜ ውስጥ ኩነቶች በአንጻራዊ ሁኔታ ከቀነሱ በኋላ ከኦነግ-ሸኔ – እንዲሁም የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦኤልኤ) በመባል የሚታወቁት – ጋር የተያያዙ ኩነቶች ከሚያዚያ 23 እስከ ግንቦት 23 ድረስ ባለው ወር በከፍተኛ ሁኔታ የጨመሩ ሲሆን ይህም እ.ኤ.አ. በ2022 ከነበሩት ኩነቶች ጋር ሲነጻጸር የግጭት ደረጃው ተመሳሳይ በሆነ መልኩ ዳግም ተመልሷል (ከዚህ በታች ያለውን ግራፍ ይመልከቱ)። ሁለቱም የመንግስት እና የኦነግ-ሸኔ ተወካዮች ወደፊት ለሰላም ንግግር ለመገናኘት ፈቃደኛ መሆናቸውን ቢገልጹም ከሚያዚያ 23 እስከ ግንቦት 23 ድረስ ባለው ወር በሁለቱ ወገኖች መካከል ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣው ጦርነቶች ምክንያት ጊዜያዊ መረጋጋቱ በማቋረጡ የተኩስ አቁም ስምምነት በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሊደረስ ይችላል የሚለው አስተሳስብ ላይ ጥርጣሬ ፈጥሯል።
ከኦነግ-ሸኔ ጋር ተያይዞ ለሁለተኛ ጊዜ እየጨመረ ለመጣው ግጭት በርካታ ምክንያቶች አስተዋፅዖ አድርገው ሊሆን ይችላል። የድርድር አካሄዶች አድካሚ ሲሆኑ1ሰማ ሃንዴ ኦጎቹ-ፉ፣ ‘ከጦር ሜዳ ውጭ፡ የእርስ በእርስ ግጭቶች ድርድሮች እና አፈታት ውስጥ ያሉ የቡድን የፖለቲካ ተለዋዋጭነት ፣’ ፖለቲካ ሪሰርች ኳርተርሊ፣ እ.ኤ።አ. ጁላይ 11, 2016 ሁለቱም መንግሥት እና ኦነግ-ሸኔ በአንድ የጋራ ስምምነት ውሳኔ ላይ ለመድረስ የውስጥ ችግር ሊኖርባቸው ይችላል። ምንም እንኳ ሁለቱም ወገኖች ጫና እና ድካም እየተጋፈጡ ቢሆንም ጠንካራ የድርድር ነጥብ ለማግኘት የሌላውን ድክመቶች ለመፈለግ ጠንካራ ምክንያት አሏቸው።
ግጭቶች የምረጡኝ ዘመቻዎችን አደናቅፈዋል። በርካታ እጩዎችን ኢላማ ያደረጉ ግድያዎች ተዘግበዋል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) እጩዎች በቢሾፍቱ ከተማ (ኦሮሚያ) እና አጣዬ (አማራ) የተገደሉ ሲሆን የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) እጩዎች ደግሞ በመተማ (አማራ) እና መተከል (ቤኒሻንጉል/ጉሙዝ) በጥይት ተገድለዋል።
የኦነግ–ሸኔ እንቅስቃሴ መቀጠል እና ወደ ምስራቅ አቅጣጫ መሻገር
ከሚያዚያ 23 እስከ ግንቦት 23 ድረስ ባለው ወር አክሌድ የኦነግ-ሸኔ የተሳተፈበት 42 የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች የመዘገበ ሲሆን ከእነዚህም 29ኙ ከመንግስት ኃይሎች ጋር የተደረጉ ውጊያዎች ነበሩ። ኦነግ-ሸኔ ከወር በፊት በአንድ የጦርነት ኩነት ላይ ብቻ የተሳተፈ በመሆኑ ይህ ከፍተኛ ጭማሪ እንዳለ ያሳያል። አስገራሚው ነገር ቡድኑ ቀደም ሲል የኦነግ-ሸኔ እንቅስቃሴ ከተመዘገበባቸው አካባቢዎች ውጪ በርካታ ጦርነቶችን ያደረገ በመሆኑ የጂኦግራፊካል ለውጥ እንዳለ አሳይቷል። ቀደም ሲል የኦነግ-ሸኔ እንቅስቃሴ በምዕራብ እና በደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል ላይ ያተኮረ ነበር። ከዚህ በፊት በምስራቅ ሸዋ ዞን አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ውጊያዎች ብቻ የነበሩ ሲሆን ከሚያዚያ 23 እስከ ግንቦት 23 ድረስ ባለው ወር ግን ብዙ ቁጥር ያላቸው ጥቃቶች እና ጦርነቶች በዞኑ ተከስተዋል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። ከእነዚህ ውጊያዎች መካከል የተወሰኑት ከኦነግ-ሸኔ ጋር በተገናኘ ታስረው የነበሩ እስረኞች ቢሾፍቱ፣ ወለንጪቲ እና በቆጂ ከተሞችን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች እንዲፈቱ ምክንያት ሆኗል።
ጦርነቱ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በኦነግ-ሸኔ እንቅስቃሴ በተለያዩ አካባቢዎች የተጀመረው የሁለቱም ልዑካን ቡድን በሚያዚያ 25 ከታንዛኒያ የሰላም ድርድር ከተመለሱ በኋላ ነበር።2ጁሊያ ፓራቪሲኒ፣ “በኢትዮጵያ እና በኦሮሞ አማፂያን መካከል የተደረገ የመጀመሪያው ዙር የሰላም ድርድር ያለስምምነት አበቃ”፣ ሚያዚያ 25, 2015 ከጥቂት ቀናት በኋላ በሚያዚያ 29 ቀን የኦነግ-ሸኔ ኅይሎች በምስራቅ ሸዋ ዞን ወለንጪቲ ከተማ በአፋር ክልል የወረዳ የብልፅግና ፓርቲ ሀላፊ የሆኑት አቶ ኦመር ለማን ጨምሮ ሰባት ሰዎችን ጥቃት በመፈፀም ገድለዋል። በነጋታው የኦነግ-ሼኔ ኃይሎች ከፌዴራል ሠራዊት ወታደሮች ጋር በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳሚ ቱሉ ተዋግተዋል። በግንቦት 7 ቀን የኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት ሰንዝረው ቢያንስ አራት ፖሊሶችን ገድለው እስረኞችን አስፈትተዋል። በመጨረሻም ግንቦት 12 ቀን በአርሲ ዞን በበቆጂ ከተማ የቀበሌ ታጣቂዎች ላይ የኦነግ-ሸኔ ጥቃት በማድረሱ ውጊያ የተቀሰቀስ ሲሆን አራት ሰዎች መሞታቸው ታውቋል።
የኦነግ-ሸኔ ተወካዮች መንግስት – በምስራቅ ሸዋ ዞን የሚገኙ አካባቢዎችን ጨምሮ – በይዞታዎቹ ላይ ጥቃት መሰንዘሩ በታንዛኒያ ውጊያ ለማስቆም የተደረሰውን “መግባባት” ጥሷል ሲሉ ከሰዋል።3ኦኤልኤፍ-ኦኤልኤ፣ ‘የሰላም ንግግሮችን እና የገዢውን የቅርብ ጊዜ ጥቃቶች በተመለከተ (ኦኤልኤፍ-ኦኤልኤ ጋዜጣዊ መግለጫ)፣ ግንቦት 6, 2015 በመንግስት በኩል የኦሮሚያ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ በኦሮሚያ ክልል የተፈጠረውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት መንግስት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸው “በሰሜን የተፈጠረውን ጦርነት መንግስት እንደፈታ ሁሉ አሁንም መንግስት በክልሉ የተፈጠረውን የሰላም እጦት ለመፍታት እየሞከረ ነው” ብለዋል።4ዶይቸ ቬለ አማርኛ፣ ‘በኦሮሚያ ክልል ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት ድጋፍ ተጠየቀ፣’ ሚያዚያ 30, 2015 የሰላም ንግግሩ በ”ቁልፍ ጉዳዮች” ላይ መግባባት ሳይደረስ መጠናቀቁን ከሚያመላክት ሁለቱ ወገኖች ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ5አዲስ ማለዳ፣ ‘የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት” ቁልፍ በሆኑ የፖለቲከ ጉዳዮች ላይ መግባባት አልታቻለም አለ፣’ ሚያዚያ 25, 2015፤ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት፣ ‘የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ፣’ ሚያዚያ 25, 2015 ውጪ በታንዛኒያ ሰለነበረው ውይይት ምንም ተጨማሪ መረጃ አልወጣም። የተረጋገጠ ቢሆንም አንዳንድ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ኦነግ-ሸኔ ሌሎች የፖለቲካ ተዋናዮችን ያሳተፈ የሽግግር መንግስት ለመመስረት ያቀረበውን ጥያቄ መንግስት አልተቀበለውም።6ቢቢሲ አማርኛ፣ ‘መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን ያላስማማው የሽግግር መንግሥት ምሥረታ ጉዳይ መሆኑ ተነገረ፣’ ሚያዚያ 25, 2015፤ ሪፖርተር፣ ‘ኢትዮጵያ- ድርድሩ የከሸፈበት ምክንያት ታወቀ፣’ ሚያዚያ 28, 2015
በኦሮምያ ውስጥ ግጭት እንደገና እየጨመረ በሄደ ቁጥር በሰላማዊ ህዝብ ላይ የሚደርሰው ጫናም ይጨምራል። ባለፉት ሁለት ዓመታት በተፈጠረ ግጭት የገበያ መስተጓጎል እንዲሁም በተፋላሚ ወገኖች መካከል በሚገኙ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት አስከትሏል።7አዲስ ስታንዳርድ፣ ‘ዜና፡ በኦሮሚያ ክልል በጉጂ ዞኖች በተነሳ ግጭት ሰላማዊ ዜጎች “በዝምታ” እየተሰቃዩ ነው-ዘገባ፣’ ግንቦት 8, 2015 አክሌድ እ.ኤ.አ. በ2023 አመት (ከታህሳስ 2015 ጀምሮ) በኦሮሚያ ክልል በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠሩ ከ100 በላይ የጥቃት ክስተቶችን የመዘገበ ሲሆን ከሚያዚያ 23 እስከ ግንቦት 23 ድረስ ባለው ወር 30 የጥቃት ክስተቶችን መዝግቧል። በክልሉ ባለው አጠቃላይ የፀጥታ ችግር የታጠቁ ቡድኖች – አንዳንዶቹ ከኦነግ-ሸኔ ጋር ግንኙነት ያላቸው ወይም አጋር ነን የሚሉ – እየተበራከቱ መጥተዋል።8ካትሪን ሁሬልድ፣ ‘አመጺ ወይስ ሽፍታ? ህይወቱ የኢትዮጵያን ድብቅ አማጺያንን ያንጸባርቃል፣’ ዋሽንግተን ፖስት፣ ግንቦት 13, 2015 እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ድረስ በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙ የግጭት ዞኖች እስከ 800,000 የሚደርሱ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።9የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ፣ ‘ኢትዮጵያ – ሁኔታ ሪፖርት፣ ግንቦት 29 ቀን 2023፣’ ግንቦት 21, 2015 እነዚህ አሳሳቢ ጉዳዮች ቢኖሩም የሰላማዊ ሰዎች ሁኔታ በግጭቱ አቅጣጫ ላይ ብዙም ተጽእኖ ወይም ምንም ተጽእኖ የላመጡም።
የሰላም ሂደቱ አቅጣጫ
ሁለተኛው ዙር የሰላም ንግግር፣ የሚደረግ ከሆነ፣ በኢትዮጵያ አስቸጋሪ የፖለቲካ ምኅዳር ውስጥ ሊካሄድ ይችላል። የአገሪቱ ሕገ-መንግሥት፣ የብሔር ሚና እና የብሔር ፌዴራሊዝም የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች በኦነግ-ሸኔ እና በፌዴራል መንግሥት መካከል የሚነሱ የክርክር ነጥቦች ሲሆኑ የፌዴራል መንግሥት ከብሔር ፌደራሊዝም ጋር ያለውን ግንኙነት ለማስተካከል እየታገለ የሚገኝ ነው። በታህሳስ ወር ኦነግ-ሸኔ ያወጣው የፖለቲካ ማኒፌስቶ ቡድኑ ለኦሮሞ ህዝብ “ራስን በራስ የማስተዳደር”፣ የኦሮሚያን “ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት” እና ለኦሮሞ ህዝብ “ማህበራዊ-ባህላዊ መብቶች” ቁርጠኛ መሆኑን አብራርቷል።10ኦነግ-ኦኤልኤ፣ ‘አጭር የፖለቲካ ማኒፌስቶ፡ ከትጥቅ ትግል ወደ ሰላም ተስፋ፣’ ጥር 15, 2015 አሁን ካለው መንግስት ጋር ሙሉ ለሙሉ የማይጣጣም ባይሆንም የብሔር ፌዴራሊዝም ሚናን የሚቀንስ ወይም የሚያጠፋ የሀገሪቱ ሕገ-መንግስት ለውጥ የተፋላሚ ወገኖችን የፖለቲካ አጀንዳ የበለጠ የተራራቀ እንዲሆን ያደርገዋል
ከሁሉም በላይ የሚያሳስበው በታሪክ ከዚህ በፊት ትጥቅ የማስፈታት ሂደቶች በአግባቡ ባለመፈጸማቸው እና በአጠቃላይ አንዱ ሌላውን በተስማሙት ውሳኔዎች መሠረት እንደሚሠራ እምነት ማጣት የትኛውም ወገን ሌላውን እንደ ታማኝ የድርድር አጋር አድርጎ አይመለከተውም።11ዲን ጂ. ፕሩት፣ ‘የብስለት ንድፈ ሃሳብ የት ነው?’ ኢንስቲትዩት ፎር ኮንፍሊት አናሊሥ ኤንድ ሪዞሊሽን፣ ጆርጅ ሜሰን ዩኒቨርሲቲ በኦነግ መሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው እንግልት እና ህገ-ወጥ እስር ብዙ የኦነግ-ሸኔ (ኦኤልኤ) አባላት ትጥቅ የማስፈታት ስምምነት ላይ ቢደረሰ መንግስት የተስማማበትን ግዴታ አይፈፅምም ብለው እንዲጠራጠሩ አድርጓቸዋል።12አዲስ ስታንዳርድ፣ ‘ዜና፡- ኦነግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ከፖሊስ ቁጥጥር ውጪ ከጠፉ በኋላ የአለም አቀፍ ስምምነቶችን መተላለፍ አስጠንቅቋል፣’ ግንቦት 3, 2015 በሌላ በኩል ቡድኑን የሚወክለው የፖለቲካ ወይም የወታደራዊ እዝ መዋቅር ባለመኖሩ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ከኦነግ-ሸኔ ጋር ለመደራደር ማመንታታቸውን ገልፀው ነበር።13የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ‘የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽንን ምን ተግዳሮት ገጠመው? ኢቲቪ | ሲትዮጵያ | ዜና፣’ ህዳር 20, 2015 ከክልሉ መንግስት የተወሰነ ፈቃደኛ ቢሆንም ለባህላዊ የሰላም አማራጮች ወይም በባህላዊ ድርድር ለመፍታት ያሉ ሁኔታዎች ባለፈው አመት ትንሽ ለውጥ አሳይተውል (ለበለጠ መረጃ ኢፒኦ ወርሃዊ ከሕዳር 22 እስከ ታህሳስ 22, 2015ን ይመልከቱ)።
የውጭ አጋሮች በታንዛኒያ ከሚገኙ ተወካዮች እና ከአካባቢው ቡድኖች ጋር በከፍተኛ ደረጃ በመስራት በሰላም ሂደቱ ውስጥ ተሳትፈዋል። በዩናይትድ ስቴትስ አለም አቀፍ ልማት ኢነርጂ ደህንነት ፕሮጀክት የተደገፈ እና በግንቦት 4 እና 5 በአምቦ ከተማ የተካሄደው የሁለት ቀናት ኮንፈረንስ በኦሮሚያ በሚገኙ ሲቪል ማህበረሰብ አባላት መካከል የሰላም ውይይት ለማዳበር በማሰብ ባህላዊ መሪዎችን እና የዩንቨርስቲ መምህራንን እንዲሁም በመካከለኛ ደረጃ የሚገኙ የመንግስት ባለስልጣናትን አስባስቦ ነበር።14አዲስ ስታንዳርድ፣ ‘ዜና፡- በኦሮሚያ የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም በመንግስትና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል ያለው ትብብር እንዲቀጥል ማህበረሰቡ አሳሰበ፣’ ግንቦት 5, 2015 ይህ አዎንታዊ እርምጃ ቢሆንም የኦነግ-ሸኔ ተወካዮች ተሳታፊ ያልነበሩ ሲሆን የኮንፍረንሱ ግብአት ከጉባኤው የውይይት ዓላማዎች አልፈው አልሄዱም።
በኦነግ-ሸኔ እና በመንግስት ኃይሎች ላይ በቅርብ ጊዜ የተደረጉ ለውጦች ሁለቱም ወገኖች ጠንካራ የድርድር አቅም ለማግኘት የሌላውን ድክመት መፈተሽ እንዲቀጥሉ እንደ ማበረታቻ ሆኗቸዋል። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እንደሌሎች የኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስታት ባለፈው ወር ልዩ ኃይሉን እንደገና በማዋቀር ላይ ይገኛል (ለበለጠ መረጃ ኢፒኦ ከመጋቢት 23 እስከ ሚያዚያ 22, 2015 ወርሀዊን ይመልከቱ)። ባለፉት ሁለት አመታት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ኃይሎች እንዲሁም የሪፐብሊካኑ ጋርድ በኦነግ-ሸኔ ላይ በተደረጉት ዘመቻ ሲሳተፉ የቆዩ ቢሆንም ሽምቅ ተዋጊዎችን በዋነኝነት ሲዋጋ የነበረው የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል ነበር። ሆኖም ከሚያዚያ ወር ጀምሮ ይህ ኃይል የለም። በንድፈ ሀሳብ ደረጃ ይህ ኃይል ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር – የክልል ፖሊስ፣ የፌዴራል ፖሊስ ወይም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጋር – ተዋህዷል። የልዩ ኃይሉ እንደገና መዋቀር በመንግስት አቅም ላይ አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ተጽእኖ ሊያመጣ የሚችል ቢሆንም ይህ በትክክል እንዴት ሊገለጽ እንደሚችል በአሁኑ ጊዜ ግልፅ አይደለም። በግንቦት ወር የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ባከናወናቸው አንዳንድ ኦፕሬሽኖች በአማጺያን እንቅስቃሴ ለሦስት ዓመታት ያህል ተዘግቶ የነበረው የደምቢ ዶሎ-ጋምቤላ መንገድ እንዲከፈት ተድርጓል።15ዲስ ስታንዳርድ፣ ‘በምዕራብ ኢትዮጵያ የጋምቤላ- ደምቢዶሎ መንገድ ከሶስት ዓመታት በኋላ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፣ ሰራዊቱ ሰላምን አረጋግጣለሁ አለ’ ግንቦት 28, 2015 ሆኖም ባለፈው ወር በመንግስት የተወሰዱ ተጨማሪ እርምጃዎች በመሬት ያዞታ ላይ ብዙም ለውጥ ያላስገኙ ሲሆን የኦነግ-ሸኔ ኅይሎች ሰፊውን የኦሮሚያን ገጠራማ አካባቢዎች እንደተቆጣጠሩ ናቸው። የኦነግ-ሸኔ አጋር የነበሩት ሁለት የተባበሩት የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት እና ኮንፌደራሊስት ኃይሎች አባላት – ህወሓት/ትህነግ እና የጋምቤላ ህዝቦች ነፃነት ሠራዊት16ዲደብሊው አማርኛ፣ ‘የጋምቤላ ነጻነት ግንባር ሙሉ በሙሉ ከትጥቅ ትግል መውጣቱን ዐስታወቀ፣’ ሚያዚያ 18, 2015 –ትጥቅ መፍታታቸው ቡድኑ ከአሁን በኋላ ወደ ሱዳን ድንበር በመሻገር ወሳኝ ግንኙነት እንዳይኖረው ሊያድርግ ይችላል ማለት ነው።.
ባለፈው ወር ግጭት ቢጨምርም መንግስትም ሆነ የኦነግ-ሸኔ ተወካዮች ሁለተኛ ዙር የሰላም ድርድር ሊኖር እንደማይችል አልገለፁም። ሁለቱም ወገኖች ‘ሰላማዊ’ መፍትሄ ለመፈለግ በቃል ቁርጠኞች ቢሆኑም እርስ በእርስ መጠቃቃታቸውን ቀጥለዋል። ዋናው ነገር ሁለቱም ወገኖች በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ያለውን የፀጥታ ሁኔታ ለመቆጣጠር የቻሉ አይመስልም በዚህም ሰላማዊ ሰዎችን ለጥቅም ተኮር ወንጀል እና ኢኮኖሚያዊ ችግር በማጋለጥ ግጭቱ ዋጋ እያስከፈለ ይገኛል። ኦነግ-ሸኔ በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳዲስ አካባቢዎች እየወሰደ ያለው እርምጃ ቡድኑ በኦሮሚያ ክልል የበለጠ እየተስፋፋ መሆኑን ወይም ደግሞ መንግስትን ተጨማሪ የሰላም ንግግር እንዲያደርግ ግፊት ለማሳደር የሚደረግ ሙከራ ሊሆን ይችላል።