በቁጥር: ኢትዮጵያ, ከሰኔ 17, 2014-ሰኔ 23, 2015
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 1,088
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 4,936
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 2,126
በቁጥር: ኢትዮጵያ, ከሰኔ 17-23, 20151 በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ በመረጃ ቋታችን ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 8
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 19
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 6
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን ከኢፒኦ የመረጃ መዝገብ እንዲሁም በዋናው የአክሌድ ኤክስፖርት መሳሪያ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
የኦሮሚያ ክልል በኢትዮጵያ የፖለቲካ ግጭት ማዕከል ሆኖ ቀጥሏል። ባለፈው ሳምንት በሆሮ ጉዱሩ ዞን በኮምቦሻ እና በጮመን ጉዱሩ ወረዳዎች በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ መካከል “ጠንካራ” ውጊያዎች መደረጉ ተዘግቧል።2አዲስ ማለዳ፣ ‘በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በመንግሥት የጸጥታ አካላትና በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መካከል ጠንካራ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ፣’ ሰኔ 25, 2015 ውጊያው የተጀመረው ሰኔ 17 ሲሆን ሳምንቱን ሙሉ መቀጠሉ ተነግሯል። በውጊያው ቢያንስ 10 ሰላማዊ ሰዎች እና ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የኦነግ-ሸኔ አባላት መሞታቸው ተነግሯል። ብዙ ሰላማዊ ሰዎችም ቤታቸውን ጥለው ለመሰደድ ተገደዋል። መንግስትን እና ኦነግ-ሸኔ የሚወክሉ ልዑካን በሚያዚያ 25 ቀን ከታንዛኒያ የሰላም ንግግር ከተመለሱ በኋላ በግንቦት ወር በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለው ጦርነት እንደገና ተባብሷል (ለበለጠ መረጃ ኢፒኦ ከሚያዚያ 23 እስከ ግንቦት 23, 2015 ወርሀዊን ይመልከቱ)።
በክልሉ በሰላማዊ ሰዎች ላይም የሚደርሰው ጥቃት ቀጥሏል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። ባለፈው ሳምንት በምስራቅ ሸዋ ዞን ቦሰት ወረዳ በኑራ ሄራ ቀበሌ እና በቦሌ ከተማ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች – የኦነግ-ሸኔ አባላት ናቸው ተብለው የተገመቱ ታጣቂዎች – ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ ሰላማዊ ሰዎችን ገድሏል። ታጣቂዎቹ አርሶ አደሮች የእርሻ መሬታቸውን ለቀው እንዲወጡ ያስገደዱ ሲሆን ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎችንም አፍነው ወስደዋል። ኦነግ-ሸኔ ከዚህ ታጣቂ ቡድን ጋር አለው የተባለውን ግንኙነት ውድቅ በማድረግ ታጣቂው ቡድኑ የኦነግ-ሸኔን ስም በማጥፋቱ ኦነግ-ሸኔ ከቡድኑ ጋር መዋጋቱን ተናግሯል።3ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ፣ ‘በምስራቅ ሸዋ ዞን ኦነግ ሸኔ/ኦኤልኤ ነኝ እያለ የሚጠራ የታጠቀ ቡድን በሰላማዊ ሰዎች ላይ አሰቃቂ ወንጀል እና ንብረት ዘረፋ እየሰራ መሆኑን ነዋሪዎች ገለፁ” ሰኔ 21, 2015
በአማራ ክልል በርካታ የፖለቲካ ግጭቶችም ተመዝግበዋል። ሰኔ 18 ቀን የመንግስት ኃይሎች – የአማራ ክልል ፖሊስ እና የቀበሌ ታጣቂዎች ናቸው ተብሎ የሚገመት – በሰሜን ወሎ ዞን ጊዳን ወረዳ ሙጃ ከተማ የፋኖ ታጣቂዎችን ትጥቅ ለማስፈታት ሲሞክሩ ከቡድኑ ጋር ተዋግተዋል። በውጊያው አንድ ፖሊስ እና ሁለት የቀበሌ ታጣቂዎችን ጨምሮ ሦስት የመንግስት ኃይሎች መገደላቸው እና አራት ሰዎች መቁሰላቸው ታውቋል። በተመሳሳይ ቀን በጊዳን ወረዳ ዋልካ መንደር የቆቦ ከተማ አስተዳደር አባላትን ሲያጓጉዝ የነበረ መኪና ላይ አንድ ማንነቱ ያልታወቀ ታጣቂ ቡድን ተኩስ ከፍቷል። በተሽከርካሪው ላይ ጉዳት የደረሰበት ቢሆንም በሰው ላይ የደረሰ ምንም ጉዳት የለም።