በቁጥር: ኢትዮጵያ, 19-25 መስከረም 20161በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ በመረጃ ቋታችን ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 21
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 63
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 30
በቁጥር: ኢትዮጵያ, መስከረም 20, 2015- መስከረም 25, 2016
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት: 1,170
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 3,744
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር: 1,626
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን ከኢፒኦ የመረጃ መዝገብ እንዲሁም በዋናው የአክሌድ ኤክስፖርት መሳሪያ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
አማራ ክልል በአንፃራዊነት የተረጋጋ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል የግጭት ኩነቶች ቁጥር በመጠኑ ጨምሯል። ባለፈው ሳምንት በእነዚህ ሁለት ክልሎች የተከሰቱ አብዛኛው የፖለቲካ ግጭቶች የፋኖ ታጣቂዎችን እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔን የተሳተፉ ነበር።
ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል ሦስት ውጊያዎች እና አንድ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ተዘግበዋል። የፋኖ ታጣቂዎች እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በሰሜን ወሎ ዞን በላሊበላ ከተማ አቅራቢያ እና አርቢት ጋሸና ተዋግተው ነበር። ሁለቱ ወገኖች በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ፣ መተማ እና ደልጊ አካባቢዎችም ተዋግተው ነበር። በሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከባድ መሳሪያ መተኮሱ ተነግሯል። በተጨማሪም በኦሮሚያ ልዩ ዞን በአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ጃራ ቀበሌ የፋኖ ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው የአንድ አርሶ አደር ህይወት አልፏል። ከሐምሌ ወር መጨረሻ ጀምሮ በፋኖ ታጣቂዎች እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል ተከታታይ እና ጠንካራ ውጊያዎች በመከሰታቸው በሐምሌ 28 ቀን የፌዴራል መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲያውጅ አድርጓታል። ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ በክልሉ ውስጥ ባሉ በርካታ ከተሞች እና አካባቢዎች የከባድ መሳሪያ ድብደባ፣ የአየር ድብደባ እና ውጊያዎች ተከስተዋል (ለተጨማሪ መረጃ የኢፒኦ ሳምንታዊ: ሐምሌ 22-28, 2015ን እና የኢፒኦ ወርሃዊ፡ ከሐምሌ 25 እስከ ነሐሴ 25, 2015ን ይመልከቱ)።
በኦሮሚያ ክልል ባለፈው ሳምንት አስር የጦርነት ኩነቶች እና አራት በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተሰነዘሩ ጥቃቶች መከሰታቸው ተዘግቧል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። አብዛኛው ውጊያዎች – ከአስሩ አራቱ – በሰሜን ሸዋ ዞን በፋኖ ታጣቂዎች እና በኦነግ-ሸኔ መካከል የተደረጉ ናቸው። በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ ላይ በሚገኘው በዚህ ዞን ሁለቱም ታጣቂዎች ከመንግስት ኃይሎች ጋርም ተዋግተዋል። መስከረም 21 ቀን የኢትዮጵያ አየር ሃይል በሰሜን ሸዋ ደራ ወረዳ ጅሩ ዳዳ ቀበሌ ውስጥ በኦነግ-ሸኔ ላይ ሁለት ዙር የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ፈፅሟል። ከዚህ ቀደም በዚህ ዞን በጣም የተለመዱት ኩነቶች በኦነግ-ሸኔ እና በመንግስት ኃይሎች መካከል የሚደረጉ ውጊያዎች እና በኦነግ-ሸኔ በሰላማዊ ሰዎች (በተለይም የአማራ ተወላጆች) ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ነበሩ። ሆኖም በፋኖ ታጣቂዎች እና በኦነግ-ሸኔ መካከል በዚህ አካባቢ የሚደረጉ ውጊያዎች ከሐምሌ 2015 መጨረሻ ጀምሮ ሪፖርት መደረግ የጀመሩ ሲሆን ይህም በአማራ ክልል በፋኖ ታጣቂዎች እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል ከሚደረገው ጠንካራ ውጊያ ጋር በተመሳሳይ ጊዜ የተደረገ ነው።
በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በፋኖ ታጣቂዎች እና በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች – በኦሮሚያ ክልል ፖሊስ እና በቀበሌ ሚሊሻዎች – መካከል አራት ውጊያዎች መደረጋቸው ተመዝግቧል። እነዚህ ሁለት ወገኖች ከመስከረም 21 እስከ 23 በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በአቤ ዶንጎሮ ወረዳ በቱሉ ገና ቀበሌ ተዋግተዋል። መስከረም 23 ቀን የፋኖ ታጣቂዎች በአቤ ዶንጎሮ ከተማ ተኩስ ከፍተው ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ ሰላማዊ ሰዎችን ከገደሉ እና ካቆሰሉ በኃላ ከኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ጋር በከተማዋ ተዋግተዋል። በዚህ ዞን ከነሔሴ 24 2015 ጀምሮ የፋኖ ታጣቂዎች ከመንግስት ኃይሎች ጋር ውጊያ በማድረግ ተሳትፈዋል።
በኦሮሚያ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት በተለያዩ ታጣቂዎች እና የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ነው። መስከረም 20 ቀን ኦነግ-ሸኔ በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ እና በምስራቅ ሸዋ ዞን በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት ያደረሰ ሲሆን በደራ ወረዳ በትንሹ 17 ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል። ከሁለት ቀናት በኋላ ቡድኑ በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ወረዳ ጋራ ጉሬዛ አርሴማ ፀበል ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ አንድ ቄስን ጨምሮ ሁለት የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችን በመግደል ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ ሰዎችን አፍኖ ወስዷል። መስከረም 20 ቀን በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ በኮኮፌ ቀበሌ የመንግስት ኃይሎች ሁለት የባጃጅ ሹፌሮችን ተኩሰው የገደሉ ሲሆን ሌሎች ሁለት ሰዎችን አቁስለዋል። ከዚህ ጥቃት በስተጀርባ ያለው ምክንያት አልታወቅም።
አዲስ በተመሰረተው የመካከለኛው ኢትዮጵያ ክልል በመስከረም 14 ቀን ማንነቱ ያልታወቀ ታጠቂ ቡድን (የመስቃን ብሔር ታጣቂ እንደሆነ የተገመተ) ከገበያ በመመለስ ላይ በነበሩ በሰባት የማረቆ ተወላጅ በሆኑ ሰላማዊ ሰዎች ላይ በዲዳ ቀበሌ ጥቃት ካደረሰ በኃላ በመስቃን እና በማረቆ ወረዳዎች ውጥረት ነግሷል። በዚህ ጥቃት ሶስት ሰዎች ሲሞቱ አራቱ ቆስለዋል። በመስቃን ወረዳ የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው ቀበሌዎች በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት እና ከመስከረም 20 እስከ 22 ጥቃቱ የቀጠለ ሲሆን ከ2000 በላይ ሰዎች መኖሪያቸውን ለቀው ተሰደዋል። በዚህ ጥቃት ከ80 በላይ ቤቶች ተቃጥለዋል።
የመስቃን ወረዳ ነዋሪዎች በበኩላቸው የማረቆ ብሔር አባላት ጥቃት አድርሰዋል ሲሉ ከሰዋል።2ቪኦኤ አማርኛ፣ ‘በመስቃንና በማረቆ ወረዳዎች የቀበሌዎች ይገባኛል ግጭት ሰዎች እንደተገደሉ ነዋሪዎች ገለፁ፣’ 20 መስከረም 2016 ባለፉት ሁለት አስርተ አመታት በመስቃን ወረዳ በሚገኙ ዘጠኝ ቀበሌዎች ላይ በሚነሳ የይገባኛል ጥያቄ ምክንያት በሁለቱ ብሔረሰቦች መካከል አለመግባባት አለ። በእነዚህ ቀበሌዎች በሰኔ መጨረሻ ላይ ግጭት ተቀስቅሶ ነበር (በዚህ ግጭት ላይ ለበለጠ መረጃ ለማግኘት የኢፒኦ ሳምንታዊ: ከሰኔ 24-30, 2015ን፤ የኢፒኦ ሳምንታዊ: ሐምሌ 8-14, 2015ን እና የኢፒኦ ሳምንታዊ: ሐምሌ 15-21, 2015ን ይመልከቱ)። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ነሐሴ 13 ቀን 2015 ዓ.ም. ሲመሰረት የማረቆ ወረዳ ልዩ ወረዳ እንዲሆን የወሰነ ሲሆን የመስቃን ወረዳ ድግሞ ከቡታጅራ ከተማ ጋር በመሆን የምስራቅ ጉራጌ ዞን እንዲሆን ተወስኗል።