በቁጥር፡ ኢትዮጵያ, ጥቅምት 10-16, 20161በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ በመረጃ ቋታችን ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት፡ 21
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር፡ 50
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር፡ 8
በቁጥር፡ ኢትዮጵያ, ጥቅምት 11, 2015–ጥቅምት 16, 2016
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት፡ 1,178
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር፡ 3,784
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር፡ 1,477
ኢትዮጵያን የሚመለከቱ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን ከኢፒኦ የመረጃ መዝገብ እንዲሁም በዋናው የአክሌድ ኤክስፖርት መሳሪያ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ባለፈው ሳምንት በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ውጊያዎች መመዝገባቸው የቀጠለ ሲሆን በትግራይ ክልል ወሳኝ የፖለቲካ ክስተቶች ተዘግበዋል።
የፋኖ ታጣቂዎች ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጋር በአማራ ክልል በምዕራብ ጎጃም ዞን በቡሬ፣ በምስራቅ ጎጃም ዞን በእናርጅ እናውጋ ወረዳ፣ በሰሜን ሸዋ ዞን በደብረ ብርሃን እና መሃል ሜዳ ከተሞች፣ በሰሜን ወሎ ዞን በሐብሩ፣ መርሳ፣ ጉባ ላፍቶ፣ ወልዲያ እና ራያ ቆቦ ወረዳዎች ተዋግተዋል። እንዲሁም ሁለቱ ቡድኖች በደቡብ ወሎ ዞን በወይግድ ወረዳ እና ባህርዳር ከተማ አቅራቢያ በመሸንቲ አካባቢ ተዋግተዋል።2ቪኦኤ አማርኛ፣ ‘በአማራ ክልል በቀጠለው ግጭት በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ እንደኾነ ተገለጸ፣’ ጥቅምት 16, 2016 ጥቅምት 12 ቀን በቡሬ ወረዳ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር ከተዋጋ በኃላ የቁጭ ከተማን መልሶ ተቆጣጥሯል። በአማራ ክልል ምንም እንኳን ውጊያዎች የቀጠሉ ቢሆንም የፀጥታ ሁኔታው በተወሰነ ደረጃ መሻሻል መጀመሩን ምልክቶች እየታዩ ሲሆን የባሕርዳር፣ ጎንደር እና ደብረ ብርሃን ከተሞች አስተዳዳሪዎች ሐምሌ 28 ቀን የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ በከተሞቹ የተጣለውን የሰዓት እላፊ በከፊል አሻሽለዋል።3የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ‘የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ግምገማ፣’ ጥቅምት 11, 2016; የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዥን(ኢሳት)፣ ‘ኢትዮጵያ-ኢሳት የአማርኛ ዜና ጥቅምት 11, 2016፣’ ጥቅምት 11, 2016
በኦሮሚያ ክልልም በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና በኦሮሞ ነፃነት ግንባር(ኦነግ)-ሸኔ መካከል የሚደረገው ውጊያ ቀጥሏል። ከነዚህ ውጊያዎች አብዛኛዎቹ – ከዘጠኙ ስምንቱ – በሰሜን ሸዋ ዞን መመዝገባቸውን ቀጥለዋል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ በዚህ ዞን ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፖለቲካ ግጭት ተመዝግቧል። በሴንተር ፎር ዴቭሎፕመንት ኤንደ ካፓሲቲ ቢዩልድንግ የተሰራ ጥናት በከልሉ በግጭት ምክንያት 1.3 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች መፈናቀላቸውን እና በመቶዎች የሚቆጠሩ የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ጉዳት እንደደረሰባቸው ወይም እንደወደሙ አመላክቷል።4ሴንተር ፎር ዴቭሎፕመንት ኤንደ ካፓሲቲ ቢዩልድንግ (ሲዲሲቢ)፣ ‘በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ያለውን ግጭት ማስቆም አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን ለማስገንዘብ የተዘጋጀ የፖሊሲ ማብራርያ፣’ ጥቅምት 6, 2016 ከዚህ በተጨማሪ በክልሉ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች ቀጥለዋል። ባለፈው ሳምንት ኦነግ-ሸኔ በሰሜን ሸዋ ዞን ወረ ጃርሶ ወረዳ ውስጥ በውል ባልታወቀ ቦታ ከገበያ ሲመለሱ የነበሩ 21 ሰዎችን ማገቱ ተነግሯል። በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ሁለት ወራት የውጪ ዜጎችን ጨምሮ ሰላማዊ ሰዎችን በማገት ገንዘብ የማስከፈል ድርጊት እየጨመረ መምጣቱ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል።
በትግራይ ክልል የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የምስራቅ፣ የደቡብ፣ የማዕከላዊ፣ የደቡብ ምስራቅ፣ የሰሜን ምዕራብ እና የምዕራብ ዞኖች የህዝብ ግንኙነት ጽህፈት ቤቶች ኃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩ ስድስት ሰዎችን ከስልጣን አንስቷል። ኃላፊዎቹ በክልሉ ገዢ ፓርቲ በሆነው የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር (ትሕነግ/ህወሓት) በተጠራ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ መቀሌ ከተማ ከገቡ በኃላ “የስነ ስርዓት ጥሰት” ፈጽመዋል በሚል ምክንያት ከስልጣናቸው ተነስተዋል።5አዲስ ማለዳ፣ ‘መንግስት የማያውቀው ስብሰባ በመቀሌ ከተማ መጠራቱን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አስታወቀ፣’ ጥቅምት 17, 2016 የክልሉ የጊዜያዊ አስተዳደር ኃላፊ አቶ ጌታቸው ረዳ ጳጉሜ 2015 ውስጥ በሶስት የተቃዋሚ ፓርቲዎች የተመራ ተቃውሞን በማስመልከት በሰጡት ምላሽ የጊዜያዊ አስተዳደሩ በክልሉ ገጠራማ አካባቢ ድጋፍ እንዳያገኝ ለማድረግ እየሰራ ያለ “ያልታወቀ ቡድን” መኖሩን ጠቅሰው ነበር።6የትግራይ ቲቪ፣ ‘የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕረዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሰጡት መግለጫ፣’ ጳጉሜ 1, 2015 የትሕነግ/ህወሓት ፓርቲ ጥቅምት 17 እና 18 የካድሬ ስብሰባ ለማድረግ እቅዶ የነበረ ቢሆንም የጊዜያዊ አስተዳደሩ እንደዚህ አይነት ስብሰባ እንደሌለ አስተባብሏል። ስብሰባው አቶ ጌታቸው ረዳን እና ጊዜያዊ አስተዳደሩን ለመገምገም ያለመ መሆኑ ተነግሯል።7ቢቢሲ አማርኛ፣ ‘ህገወጥ የተባለው የህወሓት ካድሬዎች ስብሰባ ዋንኛ አጀንዳው ምን ነበር?፣’ ጥቅምት 19, 2016 ይሁንና ስብሰባው ይህንን አላማ ሳያሳካ የተጠናቀቀ ሲሆን በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ሌላ ዙር ስብሰባ ለማዘጋጀት ታቅዷል። በትግራይ ክልል የአስተዳደር መዋቅሮች ውስጥ በተለይም በትሕነግ/ህወሓት እና በጊዜያዊ አስተዳደሩ መካከል የተፈጠረው ውጥረት ሊቀጥል የሚችል ሲሆን በክልሉ እንደገና አንዳንድ ግጭቶች እንዲከሰቱ ሊያደርግ ይችላል።
በመጨረሻም በቅርቡ ከደቡብ ሱዳን የተፈናቀሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች በጋምቤላ ክልል አኙዋክ ዞን ጎግ ወረዳ ውስጥ በሚገኘው የፑኝዶ የስደተኞች ካምፕ መድረሳቸው ተነግሯል።8የጋምቤላ ክልል መንግስት የፕሬስ ሴክሬተሪያት ጽህፈት ቤት፣ ‘በደቡብ ሱዳን ፑቻላ አካባቢ በተከሰተ ግጭት ከ8,500 በላይ ጥገኝነት ጠያቂዎች ጋምቤላ ክልል መግባታቸውን በስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎት የጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፣’ ጥቅምት 8, 2016 ምንም እንኳን አዲስ ከመጡ ስደተኞች ጋር በተያያዘ የተዘገበ ግጭት ባይኖርም አካባቢው ሩቅ በመሆኑ ከዚህ በፊት ድንበር አካባቢ በሚገኙ የስደተኞች ካምፖች ውስጥ ከደቡብ ሱዳን የሆኑ አካላት የተሳተፉበት የተወሰኑ አለመረጋጋቶች መከሰታቸው ተዘግበው ነበር።