በቁጥር፡ ኢትዮጵያ, ኅዳር 15-21, 20161 በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ በመረጃ ቋታችን ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት፡ 31
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር፡ 137
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር፡ 59
በቁጥር፡ ኢትዮጵያ, ኅዳር 16, 2015 -ኅዳር 21, 2016
- የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች ብዛት፡ 1,256
- በፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር፡ 3,859
- በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት ሪፖርት የተደረጉ የሟቾች ቁጥር፡ 1,357
ኢትዮጵያን የሚመለከቱ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን ከኢፒኦ የመረጃ መዝገብ እንዲሁም በዋናው የአክሌድ ኤክስፖርት መሳሪያ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች የፖለቲካ ግጭቶች የቀጠሉ ሲሆን የብዙ ሰዎችን ህይወት የቀጠፉ ክስተቶች ተዘግበዋል። በአንጻሩ ሌሎች የሀገሪቷ አካባቢዎች ሰላማዊ ሆነው ቆይተዋል።
በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (በመንግሥት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ተብሎ በሚጠራው) መካከል በታንዛንያ የተደረገው የሰላም ንግግር ኅዳር 11 ቀን ያለስኬት ከመጠናቀቁ በፊት እና በኋላ ባሉት ቀናት በኦሮሚያ ክልል የሚከሰቱ ግጭቶች ከፍተኛ ጭማሪ አሳይተዋል። ኅዳር 22 ቀን የኦሮሚያ ክልል መንግሥት በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት/ኦነግ-ሸኔን “የመዋጋት ጥረቱን ማጠናከሩን” ገልጿል።2አዲስ ስታንዳርድ፣ ‘የኦሮሚያ ክልል መንግስት በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ገለፀ፣’ ኅዳር 22, 2016 ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና ኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት/ኦነግ-ሸኔ መካከል በምስራቅ ወለጋ ዞን ኢበንቱ ወረዳ በተደረጉ ውጊያዎች በግምት 11 የሚሆኑ የሟቾች ቁጥር ተዘግበዋል።
በኅዳር 14 እና 17 መካከል ባለው ጊዜ ውስጥ ማንነታቸው በውል ያልተለዩ ታጣቂዎች በአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ለሙ እና ሶሌ ዲገሉ ቀበሌዎች ቢያንስ 36 ሰላማዊ ሰዎችን ገድለዋል።3ሮይተርስ፣ ‘የኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል የኦነሠ አማፂዎችን “ብዙ” ሰዎችን ገድሏል በማለት ከሰሰ፣’ ኅዳር 22 ,2016 የጥቃቱ ሰለባ በዋነኝነት ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ሲሆኑ በብሔር አማራ ናቸው። የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ለጥቃቱ ኦነሠ/ኦነግ-ሸኔን የከሰሰ ሲሆን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት/ኦነግ-ሸኔ ቃል አቀባይ በበኩሉ ውንጀላውን አስተባብሎታል።4አዲስ ስታንዳርድ፣ ‘ዜና: በኦሮሚያ ክልል በአርሲ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች በተፈፀሙ ሁለት የተለያዩ ጥቃቶች 45 አማኞች ተገደሉ፣’ ኅዳር 21, 2016 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ባወጣችው መግለጫ ግድያውን አውግዛ ጥቃቱን በማስመልከት “የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዝምታ” ላይ ቅሬታ አሰምታለች።”5ዲደብሊው አማርኛ፣ ‘የማክሰኞ ኅዳር 25, 2016 የአለም ዜና፣’ ኅዳር 25, 2016 ጉባኤው ለሁሉም የኃይማኖት ተቋማት ድምጽ ለመሆን እና የሚደርስባቸውን ጥቃት ለመከላከል የተቋቋመ ነው። በተመሳሳይ በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ ዘጠኝ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ-ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ አባላት ባልታወቁ ታጣቂዎች ታፍነው መወሰዳቸው ከተዘገበ ከሦስት ቀን በኋላ አስክሬናቸው ተገኝቷል። አንዳንድ ምንጮች ለጊዳሚ ወረዳ ግድያ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን ተጠያቂ አድርገው ዘግበዋል።6አዲስ ስታንዳርድ፣ ‘ዜና: በኦሮሚያ ክልል በአርሲ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች በተፈፀሙ ሁለት የተለያዩ ጥቃቶች 45 አማኞች ተገደሉ፣’ ኅዳር 21, 2016 ይህ በእንዲህ እንዳለ የወንጌላዊያን ቤተ-ክርስቲያን ለግድያው ማንነቱ ያልተገለፀ ቡድንን ተጠያቂ በማድረው መንግሥት የድርጊቱን ፈፃሚዎች ለፍትህ እንዲያቀርብ ጠይቃለች7የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ፣ ‘በቄሌም ወለጋ ዞን፤ በጊዳሚ ወረዳ በአባላቶቿ ላይ የደረሰውን ግድያ አስመልከቶ ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የተሰጠ መግለጫ፣’ ኅዳር 25, 2016 (በኢትዮጵያ ኃይማኖትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን በሚመለከት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የኢፒኦ ወርሃዊ፡ ከመጋቢት 23 እስከ ግንቦት 23, 2014ን ይመልከቱ)።
በአማራ ክልል በፋኖ ታጣቂዎች እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል የሚደረጉ ውጊያዎች እንደቀጠሉ ሲሆን በሰሜን ሸዋ፣ በሰሜን ወሎ እና በምዕራብ ጎጃም ዞኖች ጦርነቶች መደረጋቸው ተዘግቧል (ከታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። የተቆጣጠሩት ቦታ መኖሩ ባይዘገብም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የፋኖ ታጣቂዎች በምዕራብ ጎጃም ዞን በጢስ አባይ እና በባሕር ዳር ከተሞች መካከል ባለው ዋና መንገድ ላይ በሚገኘው የነገደ ማርያም አካባቢ ተዋግተዋል። ይህ ጦርነት የመከላከያ ሠራዊት በፋኖ ታጣቂዎች ስር የምትገኝ መሆኑ የሚነገረው የጢስ አባይ ከተማን ለመቆጣጠር ከመሞከሩ ጋር በተያያዘ ነው።8የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ፣ ‘በቄሌም ወለጋ ዞን፤ በጊዳሚ ወረዳ በአባላቶቿ ላይ የደረሰውን ግድያ አስመልከቶ ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የተሰጠ መግለጫ፣’ ኅዳር 25, 2016
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በአማራ ክልል ሚያዝያ 2015 በፋኖ ታጣቂዎች ላይ ዘመቻ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ከርቀት የሚፈፀሙ ጥቃቶች ከፍተኛ ድርሻ ነበራቸው። ባለፈው ሳምንት ብዙ የሰው አልባ አውሮፕላን እና የከባድ መሳሪያ ጥቃቶች መፈፀማቸው የተዘገበ ሲሆን እነዚህ ጥቃቶች በአማራ ክልል ከተዘገቡ ግድያዎች 72% ይሸፍናሉ። ኅዳር 17 ቀን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በፋኖ ታጣቂዎች ይዞታዎች ላይ በፈፀመው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት በምስራቅ ጎጃም ቡቢኝ ወረዳ ዋበር የሚገኝ ምግብ ቤትን የመታ ሲሆን ቢያንስ 20 ሰዎች ተገድለዋል። ከሁለት ቀን በኋላ ኅዳር 19 ቀን በሰሜን ወሎ ዞን ቡጊና ወረዳ በሲኖ ትራክ መኪና በመጓዝ ላይ የነበሩ የፋኖ ኃይሎች ላይ በማነጣጠር በተፈፀመ ሌላ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት በአንዳንድ ምንጮች ግምት መሠረት ብዛታቸው እስከ 50 የሚሆኑ ሰዎች ተገድለዋል።9የኢትዮጵያ የሚዲያ አግልግሎት፣ ‘ኢኤምኤስ ዜና ሐሙስ ኅዳር 20, 2016፣’ ኅዳር 20, 2016 ነግር ግን የተጠቀሰውን የሟቾች ቁጥር ማረጋገጥ አልተቻለም። ኅዳር 20 ቀን በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ኃይሎች የተተኮሰ ከባድ መሳሪያ በደቡብ ወሎ ዞን ወገል ጤና ከተማ ከደላንታ አንደኛ ደረጃ ሆስፒታል ውጪ ላይ የሆስፒታሉን አምቡላንስ የመታ ሲሆን ቢያንስ አምስት ሰዎች ተገድለዋል። በመጨረሻም ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል ዋና ከተማ ባሕርዳር ሁለት የእጅ ቦምብ ጥቃቶች መፈፀማቸው የተመዘገበ ሲሆን በእነዚህ ጥቃቶች ምክንያት ግን የደረሰ ምንም ጉዳት የለም።
ከኦሮሚያ እና አማራ ክልል ውጪ በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ግጭቶች እየቀነሱ ሲሆን ይህ ደግሞ የፖለቲካ ግጭቶች በተመሳሳይ ወቅት በብዙ የሀገሪቱ አካባቢዎች ይከሰቱ ከነበረበት ከባለፉት ዓመታት ጋር እጅግ የሚቃረን ነው። ጉልህ የግጭት መቀነስ ከሚታይባቸው አካባቢዎች መካከል በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን፣ የጋምቤላ ክልል እና በቀድሞ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል አካባቢዎች የወላይታ ዞን እና የአሌ ልዩ ወረዳን ጨምሮ ያሉ አካባቢዎች ይገኙበታል።