የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
በአማራ ክልል በፋኖ ታጣቂዎች እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል የሚደረገው ውጊያ ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል የፋኖ ታጣቂዎች በሰሜን ሸዋ ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት አድርሰዋል። በሌላ የክልሉ ስፍራ በምዕራብ ጉጂ ዞን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) — በመንግሥት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ተብሎ የሚጠራው — ከመንግስት ኃይሎች ጋር ዳግም ያገረሸውን ውጊያ ተከትሎ የተለያዩ ቦታዎችን ተቶጣጥሯል።
በአማራ ክልል ውጊያዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል
በአማራ ክልል በፋኖ ታጣቂዎች እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል ውጊያዎች በምስራቅ ጎጃም፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች መደረጋቸው ተዘግቧል። ልክ እንደበፊቱ ሳምንት የባለፈው ሳምንትም አብዛኛዎቹ ውጊያዎች የተደረጉት በምዕራብ ጎጃም ዞን ነበር። በሰሜን ሸዋ ዞን በሸዋ ሮቢት ከተማ እየተካሄደ ያለውን ውጊያ ተከትሎ በፖሊስ ጣቢያ ላይ በደረሰ የሞርታር ጥቃት አራት ፖሊሶች ሲሞቱ ሌሎች አራት ቆስለዋል። በምስራቅ ጎጃም ዞን ሰኞ ገበያ እና ደብረ ወርቅ ከተሞች በፋኖ ታጣቂዎች ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ባተደረገው ዘመቻ በአጠቃላይ 41 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል። በምዕራብ ጎጃም ዞን ፈረስ ቤት ከተማ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች የካቲት 24 ጀምሮ ለአራት ቀናት በተደረገ ውጊያ ቁጥራቸው ለጊዜው በውል ያልተገለጸ የሰው ህይወት ጠፍቷል። የመንግስት ኃይሎች ከታጣቂዎች ጋር ውጊያ አድርገው ከተማዋን የካቲት 17 ቀን ከተቆጣጠሩ በኋላ በከተማዋ የሚደረግው ውጊያ ተባብሷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የካቲት 26 ቀን የፋኖ ታጣቂዎች ከባህር ዳር፣ ደብረታቦር፣ ንፋስ መውጫ፣ ጋሸ እስከ አላማጣ ከተሞች ድረስ ያለውን የከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ጉዳት በማድረሳቸው በክልሉ ሰፊ የመብራት መቆራረጥ አስከትሏል።1የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ‘በህዝቡ ስቃይ የሚሰራ የትኛውም ፖለቲካ ውጤቱ ምንም መሆኑን መረዳት ይገባል፣’ የካቲት 26, 2016 የካቲት 28 ቀን የአማራ ክልል መንግስት ባለፉት ጥቂት ወራት በክልሉ በተከሰተው ውጊያ ወደ 15 ቢሊዮን ብር የሚገመት ንብረት — ወደ 264 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር — የሚጠጋ ንብረት መውደሙን አመልክቷል።2አዲስ ስታንዳርድ፣ ‘ዜና፡- በቅርቡ በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ወታደራዊ ግጭት ከ15 ቢሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሷል፣’ የካቲት 29, 2016 በተመሳሳይ ቀን የአለም የገንዘብ ድርጅት የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ግጭት መስፋፋቱን አስመልክተው ስጋታቸውን ገልፀው ግጭቶቹን “አስጨናቂ እና አሳሳቢ” ሲሉ ገልጥፀዋል።3አሸናፊ እንዳለ፣ ‘“አስጨናቂ እና አሳሳቢ”፡ አይ ኤም ኤፍ በአማራ፣ ኦሮሚያ በተከሰቱ ግጭቶች ላይ፣’ የኢትዮጵያ ሪፖርተር፣ የካቲት 30, 2016 የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ማብቃቱን ተከትሎ እየተሻሻለ የመጣው የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ግንኙነት ላይ እየሰፋ ያለው ግጭት አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።
የኦነሠ/ኦነግ-ሸኔ በኦሮሚያ ምዕራብ ጉጂ ዞን ውስጥ የተቆጣጠረው ግዛት
ባለፈው ሳምንት በኦነሠ/ኦነግ-ሸኔ እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል ውጊያዎች በአርሲ፣ በምዕራብ ጉጂ፣ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና በምዕራብ ወለጋ ዞኖች መደረጋቸው ተዘግቧል። በምዕራብ ጉጂ ዞን የካቲት 25 ቀን ኦነሠ/ኦነግ-ሸኔ ኃይሎች በገላና ወረዳ በኮምቦልቻ፣ ኤጀርሳ፣ መታር እና ጀሪም ቀበሌዎችን ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጋር ከተዋጉ በኃላ ተቆጣጥረዋል። በመሆኑም በመቶዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ሠራተኞች እና የቀበሌ ታጣቂዎች በኦነሠ/ኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች ሊደርስባቸው የሚችለውን ጥቃት በመፍራት ከእነዚህ አካባቢዎች ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ተሰደዋል።4ሸዋንግዛው ወጋየሁ እና እሸቴ በቀለ፣ ‘በመቶዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞች ከምዕራብ ጉጂ ወደ ኮሬ ዞን መሸሻቸውን የዐይን እማኞች ተናገሩ፣’ ዲደብሊው አማርኛ፣ የካቲት 30, 2016
የካቲት 28 ቀን በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ የፋኖ ታጣቂዎች ዘጠኝ ሰላማዊ ሰዎችን ተኩሰው ገድለዋል። በኦሮሚያ ክልል በሚተዳደረው ነገር ግን በሁለቱም አማራ እና ኦሮሞ ብሔረሰቦች የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳበት በዚህ ወረዳ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት፣ ውጊያ እና ንብረት መውደም ምክንያት የሆኑ ድንበር ተሻጋሪ ክስተቶች በወረዳው ተደጋግመው ይከሰታሉ።5አዳነ ካሴ፣ ታምራት ቸሩ፣ ተገኝ ሲሻው እና ዋጋው ቦጋለ፣ ‘እ.ኤ.አ. ከ1991 ጀምሮ በኢትዮጵያ ከአስተዳደራዊ ወሰን ጋር የተያያዙ ግጭቶችን እና ተግዳሮቶቻቸውን መረዳት፣’ ኮጀንት ሶሻል ሳይንስ፣ ነሐሴ 17, 2015
ኢትዮጵያ በጨረፍታ
ከየካቲት 23–29, 2016
ይህ መረጃ/ዳታ ከየካቲት 23–29, 2016 ያለውን ጊዜ ይሸፍናል። አክሌድ መረጃን እንዴት እንደሚሰበስብ እና ኩነቶችን እንዴት እንደሚመድብ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የአክሌድን የኮድ መጽሐፍን ይመልከቱ። በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንዳንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በሚቀጥሉት ሳምንታት ዳታ ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
የኩነት አይነቶች
ውጊያዎች: 35 ኩነቶች
ፍንዳታዎች/ የርቀት ግጭት: 1 ኩነት
ሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሱ ጥቃቶች: 7 ኩነቶች
የአመፅ ግጭት: 1 ኩነት
ሰልፎች: 1 ኩነት
ግጭት ያለበት የተቃውሞ ሰልፍ: 1 ኩነት