የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
በትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሓት) ከፍተኛ አመራሮች መካከል የተፈጠረው ልዩነት ባለፈው ሳምንት የበለጠ የሰፋ ሲሆን ይኽውም በትግራይ ክልል ተጨማሪ አለመረጋጋት እንዳይፈጥር ስጋት ደቅኗል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በአማራ ክልል ውጊያዎች እና ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶች መከሰታቸው ተዘግቧል።
ትህነግ/ህወሓት ወደ ቀድሞ ፓርቲነት እንደገና ለመመለስ ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ ተደረገ
ነሐሴ 3 ቀን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ትህነግ/ህወሓት ወደ ቀድሞ ፓርቲነቱ ለመመለስ ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ያደረገ ሲሆን በምትኩ ፓርቲውን ‘በልዩ ሁኔታ’ ስር መዝግቦታል።1ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ‘የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት) የሕግ ሰውነት ጉዳይን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ፣’ ነሐሴ 3, 2016 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መሠረት ፓርቲው በግጭት ውስጥ በመሳተፋቸው ምክንያት የተሰረዙ ፓርቲዎችን ወደ ቀድሞ ፓርቲናታቸው ለመመለስ የህግ ገደብ በመኖሩ ወደ ነበሩበት መመለስ አይቻልም።2ሲሳይ ሳህሉ፣ ‘ሕወሓት ወደነበረበት ሕጋዊ ሰውነት ለመመለስ ያቀረበው ጥያቄ ቀርቶ በልዩ ሁኔታ ተመዘገበ፣’ ሪፖርተር፣ ነሐሴ 5, 2016 ፓርቲው ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በፊት ወደ ነበረበት ደረጃ ለመመለስ ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ በመደረጉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ትህነግ/ህወሓት የምዝገባ ሂደቱን ለማጠናቀቅ በቀጣይ ስድስት ወራት ውስጥ የጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርግ፣ አዲስ አመራሮች እንዲመርጥ እና የፓርቲውን የመመሥረቻ ህግ እንዲያፀድቅ ጠይቆታል።3የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ‘የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት) የሕግ ሰውነት ጉዳይን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ፣’ ነሐሴ 3, 2016 በተጨማሪም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርዱ አባላት ተሳትፎን እና ጉባኤው ድንጋጌዎችን ጠብቆ መካሄዱን ለማረጋገጥ ፓርቲው ከጠቅላላ ጉባኤው 21 ቀናትን አስቀድሞ ሊያሳውቀው እንደሚገባ አሳስቧል።
የዚህ ወደ ቀድሞ ፓርቲነቱ ለመመለስ ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ መደረግ ከዚህ ቀደም በጥቅምት 2016 በተደረገው የትህነግ/ህወሓት የፓርቲ ኮንፈረንስ ወቅት ልዩነቶች ስለመኖሩ የታየበትን እየሰፋ የመጣውን ልዩነት ይበልጥ አሳይቷል። በትግራይ በቀድሞ ትህነግ/ህወሓት ውስጥ የተፈጠሩ አንጃዎች/ቡድኖች በአንድ በኩል የምርጫ ቦርድን ውሳኔ ውድቅ በማድረግ የትህነግ/ህወሓት የህግ ሰብዕና እንደገና መመለስ አለበት በማለት የሚከራከረው በትህነግ/ህወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው ቡድን ይገኝበታል። ደብረጽዮን የፌዴራሉ መንግሥት በፕሪቶሪያ ስምምነት መሠረት በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገባ ጠይቋል።4ቢቢሲ አማርኛ፣ ‘ህወሓት በምርጫ ቦርድ ‘በልዩ ሁኔታ’ መመዝገቡን እንደማይቀበለው አስታወቀ”፣’ ነሐሴ 5, 2016፤ ወልደሥላሴ ኃይላይ አበራ፣ ‘ኦፕ-ኤድ: የመቀሌ ጩሀት: የህወሓት አንጃ እና ከትግራይ ጦርነት በኋላ ያለው የህዝባዊ ቅቡልነት ጥያቄ፣’ አዲስ ስታንዳርድ፣ ነሐሴ 6, 2016 የፌዴራል መንግሥት በበኩሉ የትህነግ/ህወሓትን የሸብርተኛ ድርጅትነት ፍረጃን በማንሳት ኃላፊነቱን መወጣቱን በማመላከት ምላሽ የሰጠ ሲሆን ትህነግ/ህወሓት በስምምነቱ መሠረት የሀገሪቷን የህግ የበላይነት እንዲያከብር አጽንኦት ሰጥቷል።5በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት፣ ‘የፕሪቶሪያ ስምምነት መነሻና መድረሻው ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ተቋማትን ማክበር ነው!፣’ ነሐሴ 6, 2016 ይሁንና በደብረጽዮን የሚመራው የትህነግ/ህወሓት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን እና የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ትህነግ/ህወሓት ‘በልዩ ሁኔታ’ እንዲመዘገብ የተቀመጡ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን ሳይከተል ጉባኤ እንዳያደርግ የሰጡትን ማስጠንቀቅያ ችላ በማለት ነሐሴ 7 ቀን የፓርቲውን 14ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ማካሄድ ጀምሯል።6ፌስቡክ @ዲደብሊውአማርኛ፣ ነሐሴ 7, 2016፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ‘የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓት) ጠቅላላ ጉባዔውን ሊያደርግ መሆኑን በመገናኛ ብዙኃን መነገሩን ተከትሎ ቦርዱ ለፓርቲው የጻፈው ደብዳቤ ከታች ተያይዟል፣’ ሐምሌ 25, 2016፤ ቢቢሲ አማርኛ፣ ‘ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ህወሓት ሕጋዊ ሰውነቱን መልሶ ሳያገኝ ጉባኤ እንዳያካሂድ አስጠነቀቁ፣’ ሐምሌ 17, 2016
ሌላኛው የትህነግ/ህወሓት ቡድን ደግሞ ፓርቲውን ሪፎርም በማድረግ ከፌዴራል መንግሥት ጋር በቅርበት ለመሥራት ፍላጎት ያለው በጌታቸው ረዳ — የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ኃላፊ—የሚመራው ቡድን ነው።7ወልደሥላሴ ኃይላይ አበራ፣ ‘ፕ-ኤድ:: የመቀሌ ጩሀት: የህወሓት አንጃ እና ከትግራይ ጦርነት በኋላ ያለው የህዝባዊ ቅቡልነት ጥያቄ፣’ አዲስ ስታንዳርድ፣ ነሐሴ 6, 2016 በተፈጠረው ክፍፍል ምክንያት ጌታቸው እና ሌሎች ተጨማሪ 14 የፓርቲው የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የ14ኛውን ጠቅላላ ጉባኤ ‘በችኮላ’ የተጠራ እና የተወሰኑ የፓርቲውን አባላት ከአባልነት ለመሰረዝ ያለመ መሆኑን በመግለጽ በስብሰባው ሳይሳተፉ ቀርተዋል።8ኤክስ@ረዳ_ጌታቸው, ነሐሴ 7, 2016 ይህ የውስጥ ውዝግብ በትግራይ ሌላ ዙር አለመረጋጋት ሊፈጥር ይችላል። የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕረዝዳንት ጀነራል ታደሰ ወረደ ከሁለቱ አንጃዎች አንዳቸውን በመደገፍ ወይም በመቃወም ምንም አይነት ሰልፍ እንዳይደረግ ከልክለዋል።9ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር እና ልደት አበበ፣ ‘ሐምሌ 5, 2016 የአለም ዜና፣’ ዲደብሊው አማርኛ፣ ሐምሌ 5, 2016
ውጊያዎች እና ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶች በአማራ ክልል
በአማራ ክልል በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የሚደረጉ ውጊያዎች የቀጠሉ ሲሆን በአዊ፣ በምስራቅ ጎጃም፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜን ወሎ እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች ውስጥ ውጊያዎች መደረጋቸው ተዘግቧል። በደቡብ ጎንደር ዞን ውስጥ ትልቅ ከተማ በሆነቸው እና በቢ22 አውራጎዳና ላይ በሚትገኘው በደብረ ታቦር ከተማ ከሐምሌ 27 እስከ 30 ድረስ የዘለቀ የሶስት ቀናት ውጊያ ተደርጓል።
አክሌድ ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶችንም መዝግቧል። ባለፈው ሳምንት ለገንዘብ ሲባል የታገተ የሰብዓዊ ድጋፍ ሠራተኛ ቆየት ብሎ ማንነታቸው ባልተገለፀ ታጠቂ ቡድን በሰሜን ወሎ ዞን ዳውንት ወረዳ ውስጥ ተገድሏል።10ሪሊፍ ዌብ፣ ‘በአማራ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ ሠራተኛ ግድያን በማስመልከት የተሰጠ መግለጫ፣’ ነሐሴ 8, 2016 ሐምሌ 27 ቀን የታጠቁ ሰዎች በምዕራብ ጎንደር ዞን አውላላ አኩሻራ ካምፕ አቅራቢያ ተኩስ በመክፈት የሱዳን ስደተኞችን አቁስለዋል። በክልሉ ማንነታቸው ያልተገለፀ ታጣቂዎች ስደተኞችን ኢላማ ማድረጋቸው እየጨመረ የመጣ ችግር ሆኗል። የፀጥታ ችግሩን በመቃወም በግንቦት ወር ውስጥ በሺህዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ካምፑን ለቀው ወጥተዋል።
ኢትዮጵያ በጨረፍታ
ሐምሌ 27-ነሐሴ 3, 2016
ይህ መረጃ/ዳታ ሐምሌ 27 እስከ ነሐሴ 3, 2016 ያለውን ጊዜ ይሸፍናል። አክሌድ መረጃን እንዴት እንደሚሰበስብ እና ኩነቶችን እንዴት እንደሚመድብ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የአክሌድን የኮድ መጽሐፍን ይመልከቱ። በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተከሰቱ አንዳንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በሚቀጥሉት ሳምንታት ዳታ ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
የኩነት አይነቶች
ውጊያዎች: 60 ኩነቶች
ፍንዳታዎች/ የርቀት ግጭት: 0 ኩነት
ሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሱ ጥቃቶች: 9 ኩነቶች
የአመፅ ግጭት: 0 ኩነት
ሰልፎች: 0 ኩነት
ግጭት ያለበት የተቃውሞ ሰልፍ: 0 ኩነት