በዚህ ከሚያዚያ 18 – ግንቦት 1, 2017 ያለውን ሁኔታ በሚሸፍን ዘገባ

በጤና ባለሙያዎች የተሻለ ክፍያን በመጠየቅ በመላው ኢትዮጵያ የተቃውሞ ሰልፎችን አካሄዱ
ባለፈው ሳምንት አክሌድ ዋና ከተማዋን አዲስ አበባን ጨምሮ በመላ ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በጤና ባለሙያዎች የተካሄዱ ቢያንስ 25 የተቃውሞ ሰልፎችን መዝግቧል። የጤና ባለሙያዎች በተለያዩ ጤና ጣቢያዎች እና ሆስፒታሎች የደመወዝ ጭማሪ እና ለሐኪሞች ነፃ የጤና መድህንን ጨምሮ ሌሎች ጥቅማጥቅሞችን ጠይቀዋል። የተቃውሞ ሰልፎቹ በሳምንቱ መጨረሻ እና ግንቦት 4 ቀን ቀጥለዋል። ከደመወዝ ጭማሪ በተጨማሪ በትግራይ ክልል የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉ የጤና ባለሙያዎች ከጥቅምት 2013 እስከ ጥቅምት 2015 ድረስ በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት ወቅት ላከናወኗቸው ሥራዎች ለ17 ወራት ያልተከፈላቸው ክፍያ እንዲከፈላቸውም ጠይቀዋል። የጤና ባለሙያዎች በተለይም የህክምና ዶክተሮች ለዓመታት የደመወዝ ጭማሪ እንዲደረግላቸው ሲጠይቁ ቆይተዋል። ለምሳሌ የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኅበር የደመወዝ ጭማሪና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች እንዲደረግለት የሚጠይቅ ደብዳቤ በየካቲት 30 ቀን 2023 ዓ.ም. ለመንግስት አስገብቶ ነበር።1ቴለግራም @ቲክቫህ-ኢትዮጵያ፣ ሚያዚያ 26, 2017 ነገር ግን በመላ ሀገሪቱ እየናረ የመጣው የኑሮ ውድነት በተለይም የመኖሪያ ቤት፣ የምግብ እና የትራንስፖርት አገልግሎት በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የሚነሳውን የደመወዝ ጭማሪ ጥሪ እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል።
በዚህም መሠረት በመጋቢት 30 ቀን አካባቢ የጤና ባለሙታዎቹ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ዘመቻ ጀምረዋል። በሚያዚያ 3 ቀን ለመንግስት 12 ጥያቄዎችን የያዘ ደብዳቤ ያስገቡ ሲሆን መንግስት ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ እንዲሰጥ 30 ቀናት ሰጥተዋል።2 አዲስ ስታንዳርድ፣ “ዜና፡ የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ለፍትሃዊ ክፍያ፣ የመድን ሽፋን ዘመቻ የጀመሩ ሲሆን ጥያቄዎቻቸው ካልተመለሱ የስራ ማቆም አድማ እንደሚያደሩ አስጠነቀቁ” መጋቢት 30, 2025፤ ቴለግራም @ቲክቫህ-ኢትዮጵያ፣ ሚያዚያ 26, 2017 12ቱ ጥያቄዎች የደመወዝ ጭማሪ፣ የትርፍ ሰዓት ክፍያ፣ ነፃ የጤና መድህን፣ ቤት ወይም የቤት መስሪያ መሬት እና የነጻ መጓጓዣን ያካተቱ ናቸው። መንግስት ለጥያቄያቸው እስከ ግንቦት 12 ድረስ ምላሽ ካልሰጠ ቀጣዩ እርምጃቸው የስራ ማቆም አድማ እንደሚሆን አስጠንቅቀው ነበር። ባለፈው ሳምንት የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ መንግስት ጥያቄዎቻቸውን በጊዜው እንዲመልስ የተደረጉ የማስጠንቀቂያ ሰልፍ ነበሩ።
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በቅርቡ የፀደቀው አዋጅ 1362/2017 የጤና ባለሙያዎችን የረጅም ጊዜ ችግሮች የሚፈታ መሆኑን ያምናል።3ፌስቡክ @ኢትዮጵያኤፋኤምኦኤች, ሚያዚያ 2, 2017፤ ፌስቡክ @ኢትዮጵያኤፋኤምኦኤች, ሚያዚያ 1, 2017፤ ዩቲዩብ @ኤፋኤምኦሄልዝኢትዮጵያ፣ ሚያዚያ 7, 2017 ይህ አቋም ግንቦት 4 ቀን በጤና ጥበቃ ሚኒስትር በድጋሚ የተገለፀ ሲሆን መንግስት በሰኔ ወር በሚጀመረው የበጀት ዓመት የጤና በጀቱን ለማሳደግ መዘጋጀቱን እና በአዲሱ አዋጅ ላይ የተመስርቱ ቀጣይ ማሻሻያዎች እንደሚደረጉ ገልፀዋል።4ዩቲዩብ @ኢቢሲዎርልድ, ግንቦት 4, 2017 የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የህዝብ ግንኙነትና ጤና ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ የጤና ባለሙያዎች ያነሱት ጥያቄ ተገቢ መሆኑን አምነው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሚቀበላቸው መሆኑን ገልፅው በአጭር ጊዜ፣ በመካከለኛ እና በረጅም ጊዜ እቅድ ለመፍታት ማቀዱን ተናግረዋል። ኃላፊው መንግስት በቅርብ ጊዜ ለጤና ባለሙያዎች ደሞዝ ጭማሪ ማድረጉን ጠቁመው ከተለያዩ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ጋር በመቀናጀት ለሠራተኛው የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ለማሰጠት እየተነጋገረ መሆኑንም ጠቁመዋል።5ኃይማኖት ደስታ፣ “የጤና ባለሙያዎች ላቀረቧው ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጣቸው ማህበራት ጥሪ አቀረቡ፣” ሪፖርተር፣ ሚያዚያ 26, 2017
ብዙ የጤና ባለሙያዎች በቅርቡ የተደረገው የደመወዝ ጭማሪ በቂ እንዳልሆነ ያምናሉ። ሠራተኞቹ እንደሚሉት መንግሥት ጥያቄያቸውን አንድ በአንድ ባለመመለሱ ምክንያት በግንቦት 5 ቀን የአንድ ሳምንት ከፊል የሥራ ማቆም አድማ መጀመራቸውን ያሳወቁ ሲሆን በዚህ የከፊል የሥራ ማቆም አድማ ወቅት አገልግሎት የሚሰጡት ለአደጋ ጊዜና ለከፍተኛ ሕክምና እንዲሁም ለእናቶችና ሕፃናት ብቻ ነው።6ቢቢሲ አማርኛ “የጤና ባለሙያዎች የጠሩት ከፊል የሥራ ማቆም አድማ መጀመሩን ተናገሩ፣” ግንቦት 5, 2017 የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ለእያንዳንዳቸው 12 ጥያቄዎች በሳምንቱ መጨረሻ ግልፅ ምላሽ ካልሰጠ ሙሉ የሥራ ማቆም አድማ ለማድረግ ዝተዋል።7ቴሌግራም @ቲክቫህ-ኢትዮጵያ፣ ግንቦት 5, 2017
እንደ ጃዋር መሀመድ እና ታዬ ደንደአ ያሉ የተለያዩ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች የጤና ባለሙያዎችን ጥያቄ አስተጋብተዋል። ይሁን እንጂ የጤና ባለሙያዎች እና ማህበሮቻቸው ፖለቲከኞች እንቅስቃሴያቸውን ከመቀላቀል እና ጥያቄዎቻቸውን ወደ ፖለቲካ ዘመቻ ከመቀየር እንዲቆጠቡ ጠይቀዋል።8ቴሌግራም @ቲክቫህ-ኢትዮጵያ፣ ግንቦት 1, 2017፤ ቴሌግራም @ቲክቫህ-ኢትዮጵያ፣ ሚያዚያ 29, 2017
ከዚህ በፊት መንግስት ለእንደዚህ አይነት የተቀናጁ እንቅስቃሴዎች ቦታ ያልሰጠ ሲሆን እንደ ማስፈራራት እና እስራት ባሉ ዘዴዎች በመጠቀም ተመሳሳይ እንቅስሴዎችን ለማፈን ሲሞክር ቆይቷል። ከሚያዚያ 29 ቀን ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ እና በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ከዚህ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ መንግስት ቢያንስ 10 ዶክተሮችን በቁጥጥር ስር አውሏል። በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል ግንቦት 3 ቀን በአማራ ክልል ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው የታስሩት የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ይገኙበታል።9ቢቢሲ አማርኛ፣ “የጤና ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት እና ሦስት ዶክተሮች ታሰሩ፣” ግንቦት 4, 2017 አብዛኛዎቹ እነዚህ ዶክተሮች እስከ ግንቦት 5 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ ከእስር ተፈተዋል።10ቢቢሲ አማርኛ፣ “የጤና ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት እና ሦስት ዶክተሮች ታሰሩ፣” ግንቦት 4, 2017፤ ቴሌግራም @ቲክቫህ-ኢትዮጵያ፣ ግንቦት 4, 2017
የሱዳን ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ – ተቃዋሚ ቡድን በጋምቤላ አንዲት ትንሽ ቀበሌ ተቆጣጠረ
ሚያዝያ 22 ቀን የሱዳን ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ – ተቃዋሚ ቡድን ታጣቂዎች በደቡብ ሱዳን የፀጥታ ኃይሎች ከደረሰባቸው ጥቃት በማፈግፈግ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ከድንበር እስከ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት በመጓዝ በጋምቤላ ክልል በላሬ ወረዳ በፓጋክ ቀበሌ የሚገኘውን የቢልኩን መንደር ተቆጣጥረዋል። ታጣቂዎቹ ተኩስ በመክፈት በርካታ ቤቶችን ሲያቃጥሉ በርካታ ነዋሪዎችን ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል። የኢትዮጵያን ባንዲራንም አውርደው የደቡብ ሱዳንን ባንዲራ በቀበሌው እንዲውለበለው አድርገዋል። በማግስቱ ሚያዝያ 23 ቀን የሱዳን ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ – ተቃዋሚ ቡድን ታጣቂዎች በላሬ ወረዳ ባልታወቀ ቦታ ከክልሉ ፖሊሶች ጋር ተዋግተዋል። በዚህም በደርዘን የሚቆጠሩ ፖሊሶች እና የላሬ ወረዳ አስተዳዳሪ ቆስለዋል። አስተዳዳሪው ወደ አካባቢው የተጓዙት የተፈናቀሉትን ነዋሪዎች ለመጠየቅ እና የድንበሩን ሁኔታ ለመገምገም ነበር። የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ ከታጣቂዎቹ ጋር ከመዋጋት እንደተቆጠቡ አንድ ዘገባ ገልጿል።11ቢቢሲ አማርኛ፣ “የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል አንድ አካባቢን “መቆጣጠራቸው” እና የወረዳ አስተዳዳሪን ማቁሰላቸው ተገለጸ፣” ሚያዚያ 24, 2017
በደቡብ ሱዳን እና በጋምቤላ የሚኖሩት ብሔረሰቦች አብዛኞቹ ተመሳሳይ በመሆናቸው በእነዚህ አካባቢዎች ያለው የፖለቲካ ውጥረት ድንበር አቋርጦ የመሄድ አዝማሚያ አለው። መንስኤውም በተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር የሚመራው የሱዳን ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ – ተቃዋሚ ቡድን በየካቲት ወር መጀመሪያ ላይ የፀጥታ ኃይሎች ከተቃዋሚው ቡድን ጋር ግንኙነት ያላቸውን የፖለቲካ እና ወታደራዊ ግለሰቦች ላይ ያነጣጠረ እስር እየፈፀመ ነው በማለት ከከሰሰ በኃላ ጀምሮ በደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር እና ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር መካከል ያለው ውጥረት ከየካቲት ወር መጨረሻ ጀምሮ ተባብሷል። ይህ የፖለቲካ አለመረጋጋት ከመጋቢት 23 እስከ ሚያዚያ 22 የተደረጉ ጦርነቶች ካለፈው ወር ጋር ሲነጻጸር የ32% ጭማሪ እንዲኖረው ያደረገ ሲሆን አክሌድ በደቡብ ሱዳን ከ82 በላይ እንደዚህ ያሉ የጦርነት ኩነቶችን መዝግቧል። ከመጋቢት 23 እስከ ሚያዚያ 22 ባለው ጊዜ ውስጥ በኪር ቁጥጥር ስር ያለ መከላከያ ኃይል የኑዌር ብሔረሰቦችን በበዛት ካቀፈው የሱዳን ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ – ተቃዋሚ ቡድን ታጣቂዎች እና ነጭ አርሚ ከሚባለው ቡድን ጋር በብዛት የተዋጉ ሲሆን ውጊያዎቹ በአብዛኛው የተከሰቱት በጆንግሌይ እና በላይኛው ናይል ግዛቶች ሲሆን ሁለቱም ግዛቶች የኢትዮጵያ ጋምቤላ ክልል አዋሳኝ ናቸው።
በአማራ እና ኦሮሚያ እየተካሄደ ከለው ጦርነት ጎን ለጎን እየተካሄደ ያለው አፈና
ከሚያዚያ 10 እስከ ግንባት 1 ቀን ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ አክሌድ አራት አፈናዎችን የመዘገበ ሲሆን ሶስቱ በኦሮሚያ ክልል እና አንዱ በአማራ ክልል የተፈፀሙ ናቸው። በሚያዚያ 24 ቀን የቅማንት ብሔረሰብ ታጣቂዎች በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ኩመር አካባቢ 15 ሰላማዊ ሰዎችን አፍነው መውሰዳቸው ተነግሯል። የተወሰኑት መምህራን የሆኑት ታጋቾቹ ከአይከል ወደ ነጋዴ ባህር በህዝብ አውቶቡስ እየተጓዙ ነበር። የቅማንት ብሔረሰብ ንቅናቄ ቡድኖች በአማራ ክልል ለሚኖረው ቅማንት ማህበረሰብ የበለጠ የራስ ገዝ አስተዳደር እንዲኖር የሚንቀሳቀሱ ናቸው። ብሔር ብሔረሰቦች በኢትዮጵያ የብሔር ፌደራሊዝም ሥርዓት መሠረት የክልል አስተዳደር እና የፖለቲካ አደረጃጀት መሠረት በመሆኑ እነዚህ የፖለቲካ ንቅናቄዎች የቅማንት ብሔረሰብ የሚኖርባቸው አካባቢዎች በአማራ ክልል ውስጥ የልዩ ዞን ማዕረግ ሊኖራቸው ይገባል ብለው ይከራከራሉ (ስለዚህ ግጭት የበለጠ መረጃ ለማግኘት የኢፒኦን የቅማንት ግጭት ገፅ ይመልከቱ)። በአማራ ክልል በፋኖ ታጣቂዎች እና በመንግስት መካከል የተፈጠረው ግጭት በሚያዝያ ወር 2015 ከተጀመረ በኃላ በአማራ ክልል የሚደረግ አፈና መጨመር የጀመረ ሲሆን ከሚያዝያ 2015 ዓ.ም ጀምሮ 47 አፈናዎች የተመዘገቡ ሲሆን ግማሾቹ በፋኖ ታጣቂዎች የተፈፀሙ ናቸው። አክሌድ በቅማንት ታጣቂዎች የተፈፀሙ ስድስት አፈናዎችን ብቻ ነው የመዘገበው። እነዚህ አፈናዎች እየተካሄዱ ያሉት ግጭት እየተደረገ ባለበት ጎን ለጎን ሲሆን የሚደረጉትም ለኢኮኖሚ ጥቅም ወይም የታጠቁ ቡድኖች ከመንግስት ጋር ከሚያደርጉት ትግል ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል ምክንያቱም አንዳንድ ጊዜ እነዚህ አፈናዎች የአካባቢ ባለስልጣናት ላይ ያነጣጠሩ በመሆነቸው ነው። የፋኖ ታጣቂዎች እና የፀጥታ ኃይሎች በክልሉ የሚያደርጉት ውጊያ የቀጠለ ሲሆን አብዛኞቹ ጦርነቶች የተመዘገቡት በምዕራብ ጎጃም ዞን ነው።
በኦሮሚያ ክልል የፋኖ ታጣቂዎች፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) — በመንግስት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ እየተባለ የሚጠራው — እና ማንነቱ ያልታወቀ የታጠቀ ቡድን አፈናዎችን እንደፈጸሙ ተነግሯል። ሚያዚያ 19 ቀን ማንነታቸው ያልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች ከአቦምሳ ወደ አዳማ ይጓዝ የነበረን የህዝብ ማመላለሻ መኪና በአርሲ ዞን በአቦምሳ ከተማ አቅራቢያ በምትገኘው ክሬሸር በሚባል መንደር በማስቆም ቁጥራቸው በውል ያልተገለጸ መንገደኞችን አፍነው ወስደዋል። ከሳምንት በኋላ ሚያዚያ 26 ቀን በምስራቅ ወለጋ ዞን በጊዳ አያና ወረዳ ዲቾ ቀበሌ ዘመናዊ መሳሪያ የታጠቁ የፋኖ ታጣቂዎች እንደሆኑ የተጠረጠሩ ታጣቂዎች ከጊዳ አያና ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ መኪና በማስቆም 10 ሰዎችን አግተዋል። ታጣቂዎቹ ሹፌሩን በማስፈራራት ተሽከርካሪውን እንዲያቆም ካደረጉት በኋላ ተሳፋሪዎችን በፆታ ከለዩ በኃላ ሁለት የሐገር ሽማግሌዎችን ጨምሮ ሀብታም ናቸው በለው ያስቧቸውን 10 ሰዎች ወደ ጫካ መውሰዳቸውን የዓይን እማኞች ገልፀዋል። በማግስቱ ታፍነው ከተወሰዱት የሐገር ሽማግሌዎች መካከል ሁለቱ የተፈቱ ሲሆን የተቀሩት ሰላማዊ ሰዎች ግን የት እንዳሉ የተገለፀ ነገር የለም። የኦነሠ/ኦነግ–ሸኔ ታጣቂዎችም በምስራቅ ቦረና ዞን ጉሚ ኢዳሎ ወረዳ ከነገሌ ቦረና ከተማ ወደ ጉሚ ይጓዝ የነበረውን ተሽከርካሪ በማስቆም 13 የአካባቢው የመንግስት ሠራተኞችን ጨምሮ 18 ግለሰቦችን አፍነው መስዳቸው ተነግሯል።
አፈናዎች በሀገሪቱ በተለይም በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ላይ ተፅእኖ እያሳደሩ ይገኛሉ። እስከ አሁን እ.ኤ.አ. 2025 አክሌድ 25 አፈናዎችን የመዘገበ ሲሆን 10ሩ በአማራ እና 11ዱ በኦሮሚያ ተመዝግበዋል። አፈናዎችን በመፍራት ብዙ ሰዎች በተቻለ መጠን ላለመጓዝ ይመርጣሉ; መጓዝ ካለባቸው ብዙውን ጊዜ የአየር በረራዎችን የሚመርጡ ሲሆን ይህም ከተለመደው የህዝብ መጓጓዣ የበለጠ ውድ ነው።