በቁጥር (ከመጋቢት 24, 2010 እስከ ሚያዚያ 1, 2013)1 እነዚህ ቁጥሮች የሚያመለክቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደስልጣን ከመጡበት መጋቢት 24, 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገሪቱ የተከሰቱ የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶችን፣ በዚህ ምክንያት የደረሱ የሞት ጉዳቶች፣ እንዲሁም በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ የተቃጡ ጥቃቶችን ነው።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 1,439
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 6,505
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 3,746
ሁሉንም የአክሌድ ስራዎች እዚህ ጋር በመጫን ያገኛሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
በሱማሌ እና አፋር ክልሎች መካከል የባለቤትነት ጥያቄ በተነሳባቸው ቦታዎች ላይ የተነሳ ግጭት ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ተፋፍሞ የቀጠለ ሲሆን በግምት የ100 ግለሰቦች ህይወት አልፏል። በግጭቱ ላይ በዋናነት ከተሳተፉት የአካባቢ ሚሊሻዎች በተጨማሪ የሱማሌ እና አፋር ክልሎች ልዩ ሀይሎች ተሳትፈዋል። እንዲሁም በምዕራባዊ ኦሮሚያ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች በኦሮሞ ነፃነት ግንባር-ሸኔ ተዋጊዎች እና የፌደራል መንግስቱ ሀይሎች መካከል የሚካሄደው ውጊያ ጨምሯል። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር-ሸኔ ተዋጊዎች በአካባቢው በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ባልሆኑ ግለሰቦች ላይ ያደረሱትን ጥቃት እና በነዋሪዎች መካከል የተነሱ ከፍተኛ ግጭቶችን ተከትሎ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ አማራዎች ከዞኑ እና በዙሪያው ከሚገኙ ሌሎች የምዕራብ ኦሮሚያ ዞኖች ተፈናቅለዋል። በተጨማሪ በደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ውስጥ ራስን በራስ ከማስተዳደር ጋር የተያያዙ ግጭቶች የክልሉን ሰላም አና ደህንነት እየተፈታተኑ ይገኛሉ።
የግጭት አካሄዶች በትግራይ ያሉ ግጭቶች ከየካቲት መጨረሻ ወዲህ እየቀነሱ መምጣታቸውን ያሳያሉ። የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር (ት.ህ.ነ.ግ.) ሀይሎች ከዋና ከተሞች እና መንገዶች ወጣ ብለው የሚገኙ ገጠራማ አካባቢዎችን ለመያዝ የሚያደርጉትን ጥረት በመተው ወደ ጥፋት አድርሶ የመሸሽ እንቅስቃሴ ቀይረዋል።
በተጨማሪም 6ኛው ጠቅላላ ምርጫ እየደረሰ እንደመሆኑ ከምርጫ ጋር የተያያዙ ግጭቶች እየተደጋገሙ መጥተዋል። በዚህ ሳምንት የምርጫ ጣቢያዎችን አሰጣጥ ተከትሎ በሱማሌ እና አፋር ክልሎች መካከል ከተነሳው ግጭት በተጨማሪ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን)ን ወክሎ በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ተመራጭ የነበረ ግለሰብ መገደሉን አክሌድ መዝግቧል።
ወቅታዊ የትግራይ ግጭት ሁኔታ
በትግራይ ከየካቲት መጨረሻ ወዲህ ግጭቶች እየቀነሱ መጥተዋል። ይህም የሆነው የት.ህ.ነ.ግ. ሀይሎች ከዋና ከተሞች እና መንገዶች ወጣ ብለው የሚገኙ ገጠራማ አካባቢዎችን ከመያዝ ይልቅ ጥፋት አድርሶ የመሸሽ እንቅስቃሴ መከተል በመጀመራቸው ነው። ምንም እንኳን በትግራይ ማእከላዊ እና ምስራቃዊ ዞኖች ውስጥ ያሉ ግጭቶች እየቀነሱ ቢሆንም አሁንም ቢሆን አልፎ አልፎ በግጭት ውስጥ የማይሳተፉ ግለሰቦች የጥቃት ኢላማ እየሆኑ ነው። በመጋቢት 20, 2013 ከት.ህ.ነ.ግ. ጋር ግንኙነት ያላቸው ሀይሎች ከአድዋ ወደ ተምቤን (መአከላዊ ዞን) የሚጓዝ መኪና በማጥቃት ያልታወቀ ቁጥር ያላቸው በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ገድለዋል (ኢቢሲ, መጋቢት 30, 2013)። ዘገባዎች በሰለቅለቃ ከተማ ሰሜን ትግራይ ውስጥ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደሮች ቢያንስ 33 በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን መግላቸውን እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ታግተው መለቀቃቸውን ያሳያሉ።
የኤርትራ ሀይሎች ከኢትዮጵያ እየለቀቁ መሆናቸውን ዘገባዎች ቢያመላክቱም አሁንም ግን በትግራይ መአከላዊ ክፍል በብዛት አሉ። በአሁኑ ወቅት ከት.ህ.ነ.ግ. ጋር ግንኙነት ባላቸው ሀይሎች እና የፌደራል መንግስት ሀይሎች መካከል ግጭት ያለው በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች ውስጥ ነው።
ክልላዊ ምልከታ:- የአፋር እና ሱማሌ ክልሎች ግጭት
በዚህ ሳምንት በሱማሌ እና አፋር ክልሎች መካከል የባለቤትነት ጥያቄ በተነሳባቸው ቦታዎች ላይ በተነሳ ግጭት 100 የሚገመቱ ግለሰቦች ህይወት አልፏል (ቢቢሲ, መጋቢት 28, 2013; አል ጀዚራ, መጋቢት 29, 2013)። በአንድ በኩል ግጭቱ ሲባባስ በሌላ በኩል ደግሞ እርስ በእርስ በሚካሰሱት ሁለቱ ወገኖች መካከል ንግግሮች ተካሂደዋል (ቪኦኤ, መጋቢት 28 2013; የሱማሌ ክልል ግንኙነት ቢሮ, መጋቢት 28, 2013; DW አማርኛ, መጋቢት 29, 2013)። የአፋር ክልል የግንኙነት ቢሮ በመጋቢት 24 እና 28, 2013 የሱማሌ ክልል ልዩ ሀይሎች ሀንሩክ፣ ገላኖ፣ እና ገዋኔ ወረዳዎች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ገልጷል። በሌላ በኩል የሱማሌ ክልል ግንኙነት ቢሮ በመጋቢት 24 እና 28, 2013 የአፋር ክልል ልዩ ሀይል ኡጉጉማ ከሚባሉ ሚሊሻዎች ጋር በመሆን በዳውዲ፣ ከረፋ፣ ደአውዲድ፣ ገውሪአን፣ ከላሌ እና ደንሌሄ ቀበሌዎች በግጭቱ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ማጥቃታቸውን ገልጷል።
ባለፈው ሳምንት የምርጫ ቦርድ 30 የምርጫ ጣቢያዎችን በሱማሌ ክልል ስር ማካተቱን ተከትሎ በሁለቱ ክልሎች መካከል ውጥረት ተከስቷል። የአፋር ክልል ውሳኔውን መቃወሙን ተከትሎ (የኢትዮጵያ ሪፖርተር, መጋቢት 12, 2013) የምርጫ ቦርድ 30ዎቹን ጣቢያዎች ሰርዞ የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች በአጎራባች ቀበሌዎች ተመዝግበው እንዲመርጡ መክሯል (የምርጫ ቦርድ, መጋቢት 15, 2013)። የሱማሌ ክልል መንግስት የምርጫ ቦርድን ውሳኔ በመቃወም የምርጫ ጣቢያዎቹ የማይከፈቱ ከሆነ ´´በምርጫው ለመወዳደር እንደሚቸገር´´ አስታውቋል (የሱማሌ ክልል ግንኙነት ቢሮ, መጋቢት 16, 2013)።
የሰላም ሚኒስቴር ግጭቱን ለመፍታት ሁለቱን ወገኖች እና ሌሎች ስለሀገሪቷ ሰላም እና ደህንነት ጉዳይ የሚመለከታቸውን መጋቢት 30, 2013 ለውይይት ጠርቷል፤ በውይይቱ የሁለቱ ክልሎች መሪዎች ተሳትፈዋል። በውይይቱ ማጠቃለያ ሁለቱም ቡድኖች ግጭቱን ለማቆም የተስማሙ ሲሆን ልዩ ሀይሎቻቸውን ወደወሰኖቻቸው ለመመለስ እና ከዚህ በፊት የተደረሱ ስምምነቶችን ለማክበርና ለማስፈፀም ተስማምተዋል። በተጨማሪም የፌደራል መንግስት በቅርቡ የተከሰተውን ግጭት እንዲያጣራ ተስማምተዋል (የሰላም ሚኒስቴር, መጋቢት 30, 2013)።
አካባቢው በሱማሌ እና አፋር ክልሎች መካከል ተደጋጋሚ ግጭቶች የሚስተዋልበት ነው። ከጥር መጨረሻ እስከ የካቲት መጨረሻ 2013 አክሌድ በሱማሌ እና አፋር ሚሊሻዎች መካከል በአፋር ክልል በሚሌ፣ አዳር እና አሚቤራ ወረዳዎች ውስጥ የተካሄዱ 3 ክስተቶችን መዝግቧል። በ2011/2012 በተከሰቱ ግጭቶች ከ30 በላይ ግለሰቦች በእነዚሁ አካባቢዎች መሞታቸው ይታወሳል።
ከምርጫ ጋር የተያያዙ ክርክሮች እና ግጭቶች
ከምርጫ አስቀድሞ ባለው ጊዜ በርካታ ከምርጫ ጋር በተያያዘ ያሉ ክርክሮች ግጭቶችን ያስከተሉ ሲሆን አዳዲስ ግጭቶችም እየተከሰቱ ነው። ባለፈው ሳምንት የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን)ን ወክሎ ቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ለክልሉ ምክር ቤት ተወዳዳሪ የነበረ ግለሰብ መተከል ዞን ውስጥ በካርባር አካባቢ ተገድሏል (የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ, ሚያዚያ 1, 2013)። አብን የአማራ ብሄርተኝነት ፓርቲ ሲሆን በአማራ ክልል እና ከክልሉ ውጪ ያሉ አማራዎችን ፍላጎቶች ለማስከበር የቆመ ፓርቲ ነው። መተከል ዞን ባለፈው አመት ከፍተኛው ግጭት ከተመዘገበባቸው የሀገሪቷ አካባቢዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን አብዛኛዎቹ ግድያዎች ባልታወቁ የብሄር ሚሊሻዎች ግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ አማራዎች ላይ የሚፈፀሙ ናቸው (ለበለጠ መራጃ ኢፒኦ መተከልን በተመለከተ የሰራውን ትንተና ይመልከቱ)። አብን ለአማራዎች ፍላጎት የሚሟገት እንደመሆኑ በመተከል የተፈፀመው ግድያ ፓርቲው በመጪው ምርጫ በክልሉ ውስጥ የሚያደርገውን ተሳትፎ ለመግታት ሊሆን ይችላል።
በተጨማሪም የሐረሪ ህዝብ ክልል መንግስት በክልሉ ውስጥ የማይኖሩ የሀረሪ ተወላጆች ለክልሉ ምክር ቤት በሚደረገው ምርጫ እንዲሳተፉ ያቀረበው ጥያቄ በምርጫ ቦርድ ውድቅ ተደርጏል። ምንም እንኳን ክልሉ ባለፉት 5 ምርጫዎች የነበሩ አሰራሮችን እንደማመሳከሪያ ቢያቀርብም ምርጫ ቦርድ አሰራሩ የህገ-መንግስቱ እና ሌሎች የምርጫ ህጎች ድጋፍ እንደሌለው በመግለፅ ጥያቄውን ሳይቀበል ቀርቷል (ምርጫ ቦርድ, ሚያዚያ 1, 2013)።
ሌሎች ክልሎች
የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል
ራስን በራስ ከማስተዳደር ጥያቄዎች ጋር የተያያዙ ግጭቶች የክልሉን ሰላም አና ደህንነት እየተፈታተኑ ይገኛሉ። በዚህ ሳምንት መጋቢት 29, 2013 አካባቢ ከጉማዴ ህዝቦች ልዩ ወረዳ አስመላሽ ኮሚቴ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሚሊሻዎች በሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን አማሮ ወረዳ በቡኒት፣ አልፋጮ፣ እና አቡሎ ቀበሌዎች ውስጥ 12 በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ሲገድሉ 8 ደግሞ አቁስለዋል። ይህንኑ ጥቃት ተከትሎ ከ11,000 በላይ የቆሬ ተወላጆች ተፈናቅለዋል (አዲስ ስታንዳርድ, መጋቢት 30, 2013)።
ኦሮሚያ ክልል
የኦነግ-ሸኔ ተዋጊዎች እና ፌደራል ሀይሎች በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ኩዩ እና ዳግም ወረዳዎች እና በሆሮ ጉዱሮ አቤ ዶንጎሮ እና ኮምቦልቻ ወረዳዎች ውጊያ አካሂደዋል። የመንግስት ምንጮች 14 የኦነግ-ሸኔ ተዋጊዎች መገደላቸውን እና 143 ደግሞ ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ በኩዩ እና ዳግም ወረዳዎች ውስጥ መታሰራቸውን ጠቁመዋል (ኢቢሲ, ሚያዚያ 2, 2013; DW አማርኛ, ሚያዚያ 4, 2013)።
የመጋቢት 29, 2013 (ሳምንት ውስጥ) በኦነግ-ሸኔ ተዋጊዎች እና ፌደራል ሀይሎች መካከል በአቤ ዶንጎሮ (ሆሮ ጉዱሮ፣ ኦሮሚያ) አካባቢ በተደረገ ውጊያ 39 የኦነግ-ሸኔ ተዋጊዎች እንዲሁም ኮምቦልቻ ዙሪያ በሚገኙ ገጠራማ አካባቢዎች (ሆሮ ጉዱሮ፣ ኦሮሚያ) ያልታወቀ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች ተገድለዋል። በግጭቱ ምክንያት በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች ወደኮምቦልቻ ከተማ ተፈናቅለዋል።
በተጨማሪም ባሳለፍነው ሳምንት ኦነግ-ሸኔ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ አብዛኞቹ አማራ የሆኑ ከ20 በላይ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ገድሏል። መጋቢት 27, 2013 ላይ የኦነግ-ሸኔ ተዋጊዎች በቢላ እና ጊዶሮ ወረዳዎች አማራ የሆኑ ነዋሪዎችን አጥቅተው 12 በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ገድለዋል። መጋቢት 28, 2013 ላይ የኦነግ-ሸኔ ተዋጊዎች የመንደር ወረዳ አቤ ዶንጎሮ (ሆሮ ጉዱሮ፣ ኦሮሚያ) ነዋሪዎች ላይ ጥቃት ፈፅመው 3 የማህበረሰብ ሚሊሻ አባላትን እና 3 በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ገድለዋል። በምላሹ የአካባቢ ሚሊሻዎች 2 የኦነግ-ሸኔ ተዋጊዎችን መግደላቸውን ምንጮች ገልፀዋል (ቪኦኤ, መጋቢት 29, 2013 )። በዚሁ እለት የኦነግ-ሸኔ ተዋጊዎች በምስራቅ ወለጋ 6 በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ገድለዋል። በተጨማሪ በመጋቢት 6 (ወር ውስጥ) በአንፊሎ (ምዕራብ ወለጋ፣ ኦሮሚያ) የኤሌክትሪክ መስመሮች ለመቀጠል የተጏዘ ቡድንን በመጥለፍ ግለሰቦቹን ደብድበው ከሶስት ቀናት ቡሀላ ለቀዋል፤ መኪናዎችን በእሳት አያይዘዋል።
በመጋቢት 24 እና 26, 2013 መካከል 10 የጅማ ዩንቨርስቲ ሰራተኞች መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ በመሞከር እና የኦሮሞ ነፃነት ጦርን በመደገፍ በሚል ታስረዋል (አዲስ ስታንዳርድ, መጋቢት 30 2013)።
ቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል
በቅርቡ በማንዴራ መተከል ዞን ቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል እና በጃዊ አዊ ዞን አማራ ክልል ውስጥ ባልታጠቁ ግለሰቦች ላይ በደረሰው ጥቃት የተሳተፉ 15 ያልታወቁ ታጣቂዎች መጋቢት 28 2013 ላይ ቤንሻንጉል/ጉሙዝ መተከል ዞን ውስጥ በሰፈሩ የፌደራል ሀይሎች ተገድለዋል (DW አማርኛ, መጋቢት 28, 2013)።
አማራ ክልል
ያለፈው ሳምንት የኢፒኦ ሳምንታዊ ትንተና በአማራ ክልል በኦሮሞ ዞን እና በዙሪያው በሚገኙ ከተሞች በኦሮሞ እና አማራ ማህበረሰብ መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት በማጀቴ፣ አጣዬ እና ዱሙጋ ከተሞች ተኩሶች እንደነበሩ አካቶ ነበር። በአጣዬ በነበረ ግጭት የቆሰሉ 12 የኦሮሞ ሚሊሻዎች መጋቢት 26, 2013 በሸዋ ሮቢት ከተማ (ሰሜን ወሎ፣ አማራ) አመፅ ተግባር ላይ በነበሩ ግለሰቦች ከነበሩበት አምቡላንስ ተጎትተው ተገድለዋል።