ኢትዮጵያ በቁጥር (ከመጋቢት 24, 2010 እስከ ሐምሌ 16, 2013)1እነዚህ ቁጥሮች የሚያመለክቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደስልጣን ከመጡበት መጋቢት 24, 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገሪቱ የተከሰቱ የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶችን፣ በዚህ ምክንያት የደረሱ የሞት ጉዳቶች፣ እንዲሁም በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ የተቃጡ ጥቃቶችን ነው።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 1,704
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 8,735
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 4,640
ኢትዮጵያ በቁጥር (ከሐምሌ 10, 2013 እስከ ሐምሌ 16, 2013)2በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተካተቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ቁጥሮች ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ። በተለይም በወቅታዊ የትግራይ ሁኔታ ላይ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ጥቃት በተመለከተ ዘገባዎች ቀስ ብለው በሚቀጥሉት ሳምንታት ሊወጡ ይችላሉ።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 39
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 223
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 61
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን እዚህ፣ ሁሉንም የአክሌድ ስራዎች ደግሞ እዚህ ጋር በመጫን ያገኛሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ የትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሃት) ታጣቂዎች ወደ አፋር ክልል ገብተዋል፡፡ ከኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይልና ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጋር ጥምረት ከፈጠረው የአፋር ክልል ልዩ ኃይል ጋር ከፍተኛ ውጊያ ካደረጉ በኋላ በፋንቲ ራሱ-ዞን 4 ያሉ ሦስት ወረዳዎች ተቆጥረዋል፡፡ ትህነግ በደቡባዊ አቅጣጫ ወደ አማራ ክልል በማምራት ባለፈው ሳምንት በቆቦ ከተማ አካባቢ ውጊያዎች አካሂዷል፡፡ በተጨማሪም በትግራይ ያለው ግጭት ጥቅምት 2013 ላይ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በአማራ ክልል መንግስት በሚተዳደረው ምዕራብ ትግራይ ዞን በሚገኘው የማይ–ጋባ አካባቢ በትህነግ ታጣቂዎች እና የአማራ ክልል ኃይሎች መካከል ውጊያዎች ነበሩ፡፡ ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል አመራር ጥያቄ በሺዎች የሚቆጠሩ የቀበሌ ታጣቂዎች፣ የፋኖ ወጣቶች፣ እና ከተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች የተወጣጡ የክልል ልዩ ሀይሎች ወደፊት ከትህነግ ጋር ለሚደረጉ ውጊያዎች በሰሜን አማራ አካባቢዎች ተሰብስበዋል፡፡
በትህነግ ታጣቂዎች እና በአፋር ክልል ኃይሎች መካከል የተካሄደው ውጊያ ከፍተኛ በመሆኑ ሰብዓዊ ዕርዳታን በአፋር ክልል በኩል ወደ ትግራይ ማዘዋወር የማይቻል ሆኗል፡፡ ሐምሌ 11, 2013 ላይ ማንነቱ ካልታወቀ ቡድን የሆኑ ታጣቂዎች በአፋር ክልል ከሰመራ ከተማ በ115 ኪ.ሜ. (70 ማይል) በአውሲ-ዞን 1 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለም ምግብ ፕሮግራም የጭነት ተሽከርካሪዎች ሲያልፉ ጥቃት በመሰንዘር የ የምግብ እርዳታ ወደ ትግራይ አንዳይገባ አድርገዋል (ቢቢሲ፣ ሐምሌ 16, 2013)፡፡ ሆኖም ግን የዓለም ምግብ ፕሮግራም የሰብዓዊ ዕርዳታ ከአዲስ አበባ ወደ ትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀሌ በአውሮፕላን ማድረጉን ቀጥሏል (ቪኦኤ አማርኛ፣ ሐምሌ 12, 2013)፡፡
ሰሞኑን በተቀሰቀሰው ሁከት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ተገድለዋል፡፡ አንዳንድ ግምቶች ከሐምሌ 10-12, 2013 በአፋር ክልል በፋንቲ ራሱ-ዞን 4 በያሎ ወረዳ የትህነግ ታጣቂዎች በትንሹ 20 በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ሰዎች መግደላቸውን ያመለክታሉ (ኢሳት፣ ሐምሌ 12,2013፤ቢቢሲ፣ ሐምሌ 16, 2013)፡፡ የአፋር ክልል መንግስት ትህነግ የፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ ከፋንቲ ራሱ-ዞን 4 ውባ፣ ጠሩ፣ ጉዲና፣ ያሎ፣ እና አውራ ወረዳዎች ወደ 70,000 ያህል ሰዎች መፈናቀላቸውን ገልጿል (ቪኦኤ አማርኛ፣ ሐምሌ 15, 2013)፡፡ የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ባለፈው ሳምንት በአፋር እና አማራ ክልሎች በተካሄደው ውጊያ ተሳትፈዋል ያሏቸውን ህፃናት በርካታ ታሪኮች አቅርበዋል በርካታ ዘገባዎችን አቅርበዋል (የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት፣ ሐምሌ 16, 2013)፡፡ በተመሳሳይ ጊዜ ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የሆኑ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች የኦሮምያ ክልላዊ መንግስት በአፋር የሚካሄደውን የመንግስት ጥረት ለመደገፍ እድሜያቸው ያልደረሱ ሰዎችን በግዳጅ ወንጅለዋል (አዲስ ስታንዳርድ፣ ሐምሌ 19, 2013)።
አሁን ባለው የትግራይ ግጭት ምክንያት በተለያዩ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች የሰፈሩ ኤርትራዊያን ስደተኞች (የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት፣ ሐምሌ 16, 2013)። ሐምሌ 14, 2013 አካባቢ የትህነግ ታጣቂዎች በትግራይ ክልል ሰሜን-ምዕራብ ትግራይ ዞን ውስጥ ወደሚገኘው የአዲ ሃሩሽ የኤርትራ የስደተኞች ካምፕ ገብተዋል፡፡ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውለው ሞባይል ስልኮቻቸውን ነጥቀዋል (ኤፒ፣ ሐምሌ 16, 2013)። ሐምሌ 15, 2013 በስደተኞች ካምፕ ውስጥ በትህነግ ታጣቂዎች እና በአማራ ክልል ልዩ ኃይሎች መካከል ከባድ ውጊያ ተቀስቅሷል። በተኩስ ልውውጡ ወቅት ስድስት ስደተኞች መገደላቸው ተዘግቧል (ሮይተርስ፣ ሐምሌ 15, 2013)።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በመላ አገሪቱ በትህነግ በኩል የሚካሄደውን ቀጣይ ወታደራዊ እርምጃ የሚያወግዙ እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን እንዲሁም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ (ሁለተኛ ዙር) ውሃ መሙላትን ደግሞ የሚደግፉ ሰልፎች ተካሂደዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ግድቡን በበርካታ ዙሮች ለመሙላት ያቀደ ሲሆን የመጀመሪያውን ዙር የውሃ ሙሌት ባለፈው አመት አካሂዷል፡፡ ሰልፎቹ በፌዴራል ወይም በክልል መንግስታት የተዘጋጁ ይመስላል፡፡ የመጀመሪያው ሰላማዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሐምሌ 11, 2013 በአፋር ክልል ዞን 1 ሎጊያ ከተማ በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች የተካሄደ ሲሆን ሰልፈኞቹ የትህነግ ታጣቂዎች ወደ አፋር ክልል መግባታቸውን በማውገዝ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡ የተቃውሞ ሰልፉ የተካሄደው ትህነግ በአፋር ክልል ፋንቲ ራሱ-ዞን 4 ውስጥ በያሎ ወረዳ አርብቶ አደሮችን ካጠቃ አንድ ቀን በኋላ ነው (የአፋር ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት፣ ሐምሌ 10, 2013)፡፡ ሐምሌ 14, 2013 ላይ በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ ትህነግን የሚቃወሙ እና ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ የሚሰጡ ሰልፎች ተካሂደዋል፡፡ በማግስቱ በሀገሪቷ ዋና ከተማ አዲስ አበባ እና በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ጂንካ እና ሀዲያ ከተሞች ተመሳሳይ ሰልፎች ተካሂደዋል፡፡ በሳምንቱ ውስጥ ተጨማሪ ሰልፎች በሻሸመኔ (ኦሮሚያ) እና በከንባታ (ደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል) ከተሞች ነበሩ፡፡
ሐምሌ 16, 2013 ላይ ልጆቻቸው በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች ወላጆች በአዲስ አበባ በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሰልፍ አካሂደዋል፡፡ ወላጆቹ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአንድ ወገን የተኩስ አቁም ውሳኔውን ተከትሎ የፌዴራል ኃይሎች ከለቀቁ በኋላ በክልሉ የቀሩ ልጆቻቸውን እንዲመለሱ እንዲያመቻች ጠይቀዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግጭት በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቀጥሏል፡፡ መተከል ዞን በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ሁከት ካለባቸው አካባቢዎች አንዱ በመሆኑ ከጥር 2013 ጀምሮ በፌዴራል ትዕዛዝ ስር ነው (ስለግጭቱ የበለጠ ለመረዳት የኢፒኦ የመተከል ግጭት ገጽን ይመልከቱ)፡፡ ባለፈው ሳምንት ከጉሙዝ ታጣቂ ቡድን ጋር ግንኙነት እንዳለው የተዘገበ ማንነቱ ያልታወቀ ታጣቂ ቡድን በአሶሳ ዞን ኦዳ ቤልጉል ወረዳ የቀድሞው የቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል ልዩ ሃይሎች ሃላፊ የነበሩ ግለሰብን ጨምሮ ሶስት ግለሰቦችን ገድሏል (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር፣ ሐምሌ 15, 2013፤ ኢሳት፣ ሐምሌ 16, 2013)፡፡ በተመሳሳይ የባሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲን ወክሎ በማንዱራ ወረዳ ለቤንሻጉል/ጉሙዝ ክልል ም/ቤት የሚወዳደር አጩ በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ግልገል በለስ ከተማ ውስጥ “የጉሙዝ ታጣቂ ቡድን” ተብሎ በተዘገበ ቡድን ተገድሏል (ኢሳት፣ ሐምሌ 16, 2013)፡፡ ሐምሌ 15, 2013 ላይ የጉሙዝ ብሄር ታጣቂ ቡድን ታጣቂዎች በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ ማንጊ በር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አንድ የሺናሻ ብሄር ወጣት ገድለዋል፡፡ በወጣቱ ቀብር ወቅት በአካባቢው ከሚገኘው ከመከላከያ ሰራዊት ኮማንድ ፖስት የሆኑ ወታደሮች ለቀስተኞች ላይ ተኩሰው አራት ሰዎችን አቁስለዋል (ቢቢሲ አማርኛ፣ ሐምሌ 17, 2013፤ ኢሳት፣ ሐምሌ 16, 2013)፡፡ በዞኑ ያለው የኮማንድ ፖስት ኃላፊ በእሳቸው ትዕዛዝ ስር ያሉ ወታደሮች በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ እንዳልተኮሱ ተናግረዋል (ቢቢሲ አማርኛ፣ ሐምሌ 17, 2013)፡፡
ሳምንታዊ ትኩረት: በአማራ፣ ትግራይ፣ እና በአፋር ክልሎች ያለውን ግጭት መረዳት
ትህነግ ሰሞኑን ወደ አፋር እና ሰሜናዊ አማራ ክልል መስፋፋቱ በመላው ኢትዮጵያ አዲስ ስጋት ፈጥሯል፡፡ በርካታ የኢትዮጵያ ክልል መንግስታት የክልል ጦርን ወደ ግንባር በመላክ ምላሽ ሰጥተዋል (ሮይተርስ፣ ሐምሌ 9, 2013)፡፡ የአፋር እና አማራ ክልል መንግስታት ወጣቶች ወሰናቸውን ለመከላከል እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ አስተላልፈዋል (ቢቢሲ አማርኛ፣ ሐምሌ 19, 2013፤ ቢቢሲ አማርኛ፣ ሐምሌ 18, 2013)፡፡ በተመሳሳይ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አዳነች አበቤ የከተማው ወጣቶች ውትድርና እንዲቀላቀሉ አሳስበዋል (ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ሐምሌ 19, 2013)፡፡ ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የተመለመሉ ወጣት ወንዶችና ሴቶች ለስልጠና ተልከዋል (ኢቢሲ፣ ሐምሌ 19, 2013)፡፡
ውጊያው ከትግራይ/አማራ ክልል ድንበር በስተደቡብ ያሉ አካባቢዎች ደርሷል፤ በአሁኑ ወቅት ያሉ ዘገባዎች የትህነግ ታጣቂዎች ከአዲ አርቃይ ከተማ (ሰሜን ጎንደር ዞን) በኩል አልፈው ከአማራ ኃይሎች ጋር ዛሪማ ውስጥ እየተዋጉ እንደሆነ ያመለክታሉ፡፡ የአዲ አርቃይ ከተማ ነዋሪዎች ትህነግን የንግድ ድርጅቶችን በመዝረፍ ከሰዋል (ኢሳት፣ ሐምሌ 19, 2013)፡፡ ደባርቅ ያሉ ምንጮች ከአዲ አርቃይ፣ ማይ ፀብሪ፣ ዛሪማ፣ እና ፀለምት ከተሞች በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች የትህነግን መቅረብ በመሸሽ ወደ ከተማው እየጎረፉ ነው (ሮይተርስ፣ ሐምሌ 19, 2013)፡፡ የትህነግ ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ታጣቂዎች “ካልሰለጠኑ የገበሬ ታጣቂዎች” ጋር መገናኘት ከቀጠሉ ወደ አማራ ክልል ዘልቀው በመግባት እስከ ጎንደር እና ደብረብርሃን ድረስ እንደሚደርሱ ተናግረዋል (ጌታቸው ረዳ፣ሐምሌ 17, 2013)፡፡
በአፋር የተነሱ ውጊያዎች ለትህነግ ተጨማሪ ግዛቶች አስገኝተዋል። ባለፈው ሳምንት በአፋር ክልል በአባላ፣ ያሎ፣ አውራ፣ ኢዋ፣ እና ጉሊና ወረዳዎች በአፋር ክልል ሃይሎች እና ትህነግ መካከል ውጊያዎች ተመዝግበው ነበር (ከታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። እንደ አንድ የአፋር ክልል ቃል አቀባይ ገለፃ የትህነግ ታጣቂዎች በአፋር/ትግራይ ክልሎች ድንበር ዙሪያ በአፋር ክልል ዞን 4 ውስጥ አውራ፣ ኢውዋ፣ እና ጉሊና ወረዳዎችን ተቆጣጥረዋል (ሮይተርስ፣ ሐምሌ 15, 2013)፡፡ እንደተጠቀሰው ትህነግ በአንድ ክስተት ቢያንስ 20 በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን የገደሉ ሲሆን እየተካሄደ ባለው ውጊያ 70,000 ሰዎች ተፈናቅለዋል፤ እንዲሁም ከአፋር ክልል ልዩ ፖሊስ መኮንኖች ቁጥራቸው ያልታወቁ የሞት ቁጥሮች ተመዝግበዋል (ኤኤፍፒ፣ ሐምሌ 15, 2013፤ ኢሳት፣ ሐምሌ 12, 2013)፡፡
የትህነግ አፋር ክልልን የማጥቃት የመጨረሻ ግብ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በክልሉ ዋና ከተማ ሰመራ እንዳይሰባሰብ እና የኢትዮጵያ/ጅቡቲ አቅርቦት መስመርን መቆጣጠር ነው፡፡ የኢትዮጵያ/ጅቡቲ የትራንስፖርት መተላለፊያ መንገድ ነዳጅ እና ምግብ ለማስገባት የአገሪቱን ዋና ከተማ በጅቡቲ ከሚገኙ ወደቦች ጋር የሚያገናኝ የተጠረገ መንገድ ነው፡፡ ምንም እንኳን የትህነግ ታጣቂዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች ርቀው ቢገኙም በአሁኑ ወቅት መንገዱ ከዚህ ጋር ባልተያያዘ ከአፋር ክልል የመጡ ታጣቂዎች እና ልዩ ኃይሎች ጋርባ ኢሳ፣ ኡንዱሁፍቶ፣ እና አይደቱ ከተሞች ላይ ያደረሱትን ጥቃት በሚቃወሙ ከሶማሌ ክልል በመጡ ሰልፈኞች ተዘግቷል፡፡
ባለፈው ሚያዝያ በአፋር/ሶማሌ ድንበር አካባቢ የተከሰተው ሁከት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአከራካሪዎቹ አካባቢዎች ውስጥ በሚገኙ በርካታ ከተሞች የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎችን ከሰረዘ በኋላ የተፈጠረ ነው (አዲስ ስታንዳርድ፣ ሐምሌ 20, 2013፤ የሶማሌ ክልል ኮሚኒኬሽን)፡፡ (በኢትዮጵያ/ጅቡቲ መንገድ ያሉ አካባቢዎች ላይ ያሉ ታሪካዊ አለመግባባቶች ላይ የበለጠ መረጃ ለማግኘት የኢፒኦን የአፋር-ሶማሌ ድንበር ግጭት ገጽን ይመልከቱ፡፡)
ትህነግ ባለፈው ሳምንት ያደረገው መስፋፋት የትግራይ ታጣቂዎች ከደፈጣ ወደ መደበኛ የጥቃት ስልት በመሸጋገር የተያዙ ከባድ መሣሪያዎችን የሚጠቀሙበትና ወደዋና መንገዶች በፍጥነት የሚያቀኑበት አዲስ የጦርነት ምዕራፍ አሳይቷል፡፡ በተወለዱበት ክልል አመፅን ለመዋጋት የሰለጠኑ እና የታጠቁ የክልል ልዩ ኃይሎች እንደዚህ ዓይነት ስልቶች ላይ ውጤታማ ሊሆኑ የማይችሉ እና ብልጫ የሚወሰድባቸው ናቸው፡፡ ህዳር 2013 ላይ ትህነግን አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከሁሉም ዋና ዋና እና ትንንሽ ከተሞች ማስወጣት የቻለው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ ትህነግ ምን ያክል ጉዳት አንዳደረሰ ግልፅ አይደለም፡፡ ሰኔ መጨረሻ ገደማ ከትግራይ ክልል ከለቀቁ በኋላ የፌደራል ኃይሎች በትህነግ ታጣቂዎች ላይ እስካሁን ከፍተኛ ዘመቻ አላካሄዱም፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ትህነግ እንደሚለው ተሸንፎም ሆነ የፌዴራል መንግሥት እንደዳለው ሰብአዊ እርዳታ እንዲደርስ ግልጽ አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ኃላፊ የአንድ ወገን የተኩስ አቁም ውሳኔ በተመለከተ የፌዴራል ኃይሎች ከፌዴራል መንግሥት ትዕዛዞችን እየጠበቁ መሆናቸውን አስታውቀዋል (የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ሐምሌ 13, 2013)፡፡ በተጨማሪም ባለፈው ወር መጨረሻ ላይ ከትግራይ ክልል የወጡት የኤርትራ ኃይሎች ሁኔታ ግልጽ አይደለም፡፡
አሜሪካ በፌዴራል መንግሥት፣ በአማራ ክልል ባለሥልጣናት፣ እና በትህነግ መሪዎች ላይ የጣለችው ማዕቀብ ተፋላሚ ወገኖችን ወደ ሰላም ስምምነት እንዲገቡ ለማድረግ ብዙም ወይም ምንም ውጤት የሌለው ይመስላል (አልጀዚራ፣ ግንቦት 16, 2013)። መንግስት ያወጀውን የተኩስ አቁም “የታመመ ቀልድ” ብሎ የጠራው ትህነግ የትግራይን ደህንነት አማራን እና የኤርትራን ኃይሎች በማሸነፍ እስኪያረጋግጥ ድረስ ትግሉን እንደሚቀጥል ቃል ገብቷል (ኤፒ፣ ሰኔ 22, 2013)። በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥትም የሰላም ውይይቶች ዕድልን የሚቀንስ ጠንካራ አቋም ወስዷል። መንግስት ትህነግን አሸባሪ ድርጅት ብሎ ከመሰየም እና የትህነግ ሃላፊዎችን ላይ ክስ ከመመስረት ባለፈ ‘‘የሽብር ቡድኑን `የመከላከያ ሰራዊት` ብሎ መጥራትን’’ የመሳሰሉ “የሽብር ቡድኑን ፍላጎት የሚያራምዱ” ቃላትን ከተጠቀሙ የሚዲያ ድርጅቶችን የመዘገብ መብቶችን እንደሚሽር አስፈራርቷል (ኦል አፍሪካ፣ ሐምሌ 16, 2013፤ ቪኦኤ፣ ሐምሌ 16, 2013)።
ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ትህነግ በቅርብ ጊዜ ከትግራይ ክልል ውጭ ስለሚያደርገው መስፋፋት ብዙም አላለም። የቀጠለው ጦርነት የሰብአዊ አቅርቦቶችን ከመጏጏዝ ያገደ ሲሆን ከሚያስፈልገው ምግብ ወደ ትግራይ ክልል የደረሰው 1% ብቻ ነው (ቢቢሲ፣ ሐምሌ 17, 2013)።
ከምርጫ ጋር የተያያዙ ክርክሮች ወቅታዊ ሁኔታ
ሐምሌ 14, 2013 የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ ከምርጫ ጋር የተያያዘ የክርክር ጥያቄ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቧል (ኢዜማ፣ ሐምሌ 15, 2013)። ኢዜማ በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል በሚገኙ 28 የምርጫ ክልሎች ምርጫዎች እንደገና እንዲካሄዱ ጠይቋል። ኢዜማ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 68 የምርጫ ክልሎችን የሚመለከት ክርክር ቢያቀርብም ምርጫ ቦርድ የምርጫውን ውጤት ከማስተላለፉ በፊት የምርጫ ጥያቄዎችን ለማጣራት ባለመቻሉ ፓርቲው ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ለማቅረብ ወስኗል። ምርጫ ቦርድ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው 68 የምርጫ ክልሎች በአንዱ ብቻ ምርጫ በድጋሚ እንደሚካሄድ አስታውቋል (ኢዜማ፣ ሐምሌ 15, 2013)። የፓርቲው ጥያቄዎች ማስፈራራት፣ ከምርጫ ጋር የተያያዘ ሁከት፣ የተመዘገቡ እጩዎች በድምጽ መስጫ ወረቀቶች ላይ አለመካተት፣ እና የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካዮች ሳይገኙ የድምፅ ቆጠራን መካሄድን ያካትታሉ።
እስካሁን ኢዜማ የምርጫውን ውጤት አስመልክቶ ለፍርድ ቤት አቤቱታ ያቀረበ ብቸኛ ፓርቲ ነው። ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫው መጀመሪያ ወደ ጎን በመደረጋቸው፣ ሙሉ በሙሉ ለመውጣት በመምረጣቸው፣ ወይም እነአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ለምሳሌ በሰሜናዊ ግንባር ውጊያ የተጠመዱ በመሆናቸው ክርክር አላቀረቡም። በምርጫ ደንቡ መሠረት ከምርጫ ቆጠራ እና ውጤት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ቅሬታዎች የምርጫ ቦርድ በቀረቡ አቤቱታዎች ላይ ውሳኔ በሰጠ በ10 ቀናት ውስጥ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማቅረብ አለባቸው (የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር አዋጅ፣ አዋጅ ቁጥር 1162/2011፣ አንቀፅ 155)። ጠቅላይ ፍርድ ቤት በምርጫ ደንቡ መሠረት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።