ከግንቦት 24, 2013 እስከ ሃምሌ 23, 2013 በጨረፍታ
ዋና ቁጥሮች1አክሌድ እስከ ነሀሴ መጨረሻ ድረስ የተመዘገቡ ኩነቶችን ህትመት ይገታል። ከሐምሌ 24, 2013 እስከ ነሀሴ 28, 2013 ያሉ መረጃዎች የኩነቶች ህትመት ጷጉሜ 1, 2013 ላይ በድጋሚ ሲጀምር የሚለቀቁ ይሆናል። በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን እንዲሁም ኢትዮጵያን የተመለከቱ ሁሉንም የአክሌድ መረጃዎች ማውረድ ይችላሉ።
-
- አክሌድ ከግንቦት 24, 2013 እስከ ሰኔ 23, 2013 ድረስ 60 የተደራጁ የፖለቲካ የግጭት ኩነቶች የመዘገበ ሲሆን 624 የተዘገበ የሟቾች ቁጥር ነበር፤ አክሌድ ከሰኔ 24, 2013 እስከ ሃምሌ 23, 2013 ባለው ወቅት 100 የተደራጁ የፖለቲካ ግጭት ኩነቶች እና 758 የተዘገቡ ሟቾች መዝግቧል።
- ከሰኔ 24, 2013 እስከ ሃምሌ 23, 2013 በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት በተከሰቱ ግጭቶች ከሞቱ ግለሰቦች ውስጥ ትልቁ የሟቾች ቁጥር የሆነው 500 የተመዘገበው በአፋር ክልል ነው። ከግንቦት 24, 2013 እስከ ሰኔ 23, 2013 ባለው ወቅት ከፍተኛ የሞት ቁጥር የሆነው 423 በትግራይ ክልል ተመዝግቧል።
- ከግንቦት 24, 2013 እስከ ሃምሌ 23, 2013 ባለው ጊዜ በተደጋጋሚ የተከሰተው የኩነት አይነት ውጊያ ሲሆን በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ 105 ኩነቶች እና 760 ሟቾች ተመዝግበዋል። በትግራይ ክልል በተደረገ አንድ የአየር ድብደባ ኩነት 64 ሟቾች ተመዝግበዋል።
ዋና ሂደቶች
- ምንም እንኳን አነስተኛ ቢሆኑም በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ከግንቦት 24, 2013 እስከ ሰኔ 23, 2013 ድረስ የተወሰኑ ከምርጫ ጋር የተያያዙ ግጭቶች ተመዝግበዋል።
- በሰኔ ማገባደጃ ላይ የትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር (ትህነግ/ህወሃት) ሃይሎች ከመንግስት ወታደሮች ጋር ተዋግተው አማራ እና አፋር ክልሎች ውስጥ ጨምሮ ሰፊ ግዛቶች ወስደዋል።
- በኦሮሚያ ክልል በኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ወቅት በኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ-ሸኔ) እና የፌደራል እና የክልል የደህንነት ሃይሎች መካከል ውጊያ እንደነበር የተዘገበ ሲሆን ከሰኔ 24, 2013 እስከ ሃምሌ 23, 2013 አነስተኛ ውጊያዎች ተዘግበዋል።
- ከሰኔ 24, 2013 እስከ ሃምሌ 23, 2013 የአፋር የጎሳ ታጣቂዎች እና ከአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር (ኡጉጉማ) ጋር ግንኙነት ያላቸው ታጣቂዎችበአፋር ክልል ጋቢ ዞን 3 ገዳማይቱ ከተማ የሚኖሩ የሶማሌ ነዋሪዎችን ካጠቁ በኋላ በሶማሌ እና አፋር ክልሎች መካከል የነበረው ውጥረት እንደገና አገርሽቷል።
በዚህ ሪፖርት ውስጥ
- ከግንቦት 24, 2013 እስከ ሃምሌ 23, 2013 የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
- የትህነግ እና ኦነግ–ሸኔ አመፆች በኢትዮጵያ ላይ ትንተና
ከግንቦት 24, 2013 እስከ ሃምሌ 23, 2013 የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የኢትዮጵያ ምርጫ በአብዛኞቹ የአገሪቱ ክልሎች ከግንቦት 24, 2013 እስከ ሰኔ 23, 2013 በነበረው ወር ተካሂዷል። ድምጽ አሰጣጡ በሰፊው በሁከት የታጀበ እንደሚሆን ብዙዎች ቢጠብቁም የምርጫው ቀን በከተሞች አካባቢ በሰላም ሲያልፍ በአንዳንድ የገጠር ከተሞች ውስጥ የተበታተነ ሁከት ነበር።
የትህነግ እና ኦነግ-ሸኔ አመፅ ከግንቦት 24, 2013 እስከ ሃምሌ 23, 2013 በነበረው ወቅትም ቀጥሏል። የኦነግ-ሸኔ ኃይሎች ከኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይሎች ጋር በኦሮሚያ ክልል በጉጂ እና ቦረና ዞኖች ተዋግተዋል። በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ እና በምዕራብ ወለጋ ዞኖችም ነበሩ። የትህነግ ታጣቂዎች ከግንቦት 24, 2013 እስከ ሰኔ 23, 2013 በነበረው ጊዜ በመላው ትግራይ ክልል ከኤርትራ እና ኢትዮጵያ ወታደሮች ጋር ውጊያ በማድረግ የትግራይን ዋና ከተማ መቀሌን ጨምሮ ግዛቶችን ተቆጥረዋል። ይህንን ተከትሎ በሰኔ ማገባደጃ የኢትዮጵያ መንግስት ሃይሎች ምስራቃዊ እና ደቡባዊ ትግራይን ለቀው ወጥተዋል።
ከግንቦት 24, 2013 እስከ ሃምሌ 23, 2013 በነበረው ጊዜ በተደጋጋሚ የተከሰተው የፖለቲካ አለመረጋጋት ኩነት አይነት ውጊያ ነበር። ውጊያዎች በትግራይ፣ አማራ፣ እና አፋር ክልሎች ተዘግበዋል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። ከግንቦት 24, 2013 እስከ ሰኔ 23, 2013 በትግራይ ክልል ውስጥ በትህነግ እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መካከል ውጊያ መካሄዱ ተዘግቧል። የፌደራል መንግስት በሰኔ ወር መጨረሻ የአንድ ወገን የተኩስ አቁም ማወጁን አስታውቆ ነበር። ሆኖም ግን ከሰኔ 24, 2013 እስከ ሃምሌ 23, 2013 ባለው ጊዜ ውጊያው ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች ተዛምቷል። የትህነግ ሃይሎች በአማራ እና አፋር ክልል መንግስታት ስር ያሉ ቦታዎችን ለመቆጣጠር ሲሞከሩ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ክልል ልዩ ሃይሎች እና ታጣቂዎች፣ እንዲሁም የአፋር ክልል ልዩ ሃይሎች እና ታጣቂዎች ጋር ተጋጭተዋል። ትህነግ በጎረቤት ክልሎች ላይ ያደረሰውን ጥቃቶች ምክንያታዊ ነው ሲል ያቀረባቸው ሁለት ምክንያቶች የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽነትን ማረጋገጥ እና የፌዴራል መንግሥትን የጋራ የተኩስ አቁም ቅድመ ሁኔታዎችን ዝርዝር እንዲቀበል ማድረግ ናቸው። በሐምሌ ወር ትህነግ ለጋራ የተኩስ አቁም ድርድር የሚሆኑ ቅድመ-ሁኔታዎች ያሉባቸው ሁለት ዝርዝሮች አውጥቷል። የመጨረሻው ዝርዝር የወጣው ሃምሌ 22, 2013 ነበር። የትህነግ ሃላፊዎች ቅድመ-ሁኔታዎቹ ተቀባይነት ካላገኙ ታጣቂዎቻቸው ከፌዴራል ኃይሎች ጋር መዋጋታቸውን እንደሚቀጥሉ አመልክተዋል (ሮይተርስ፣ ነሃሴ 29, 2013፤;ዲደብሊው አማርኛ፣ ነሃሴ 28, 2013)።
በትህነግ እና በፌዴራል መንግስት መካከል እየተካሄደ ባለው ውጊያ በርካታ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች አሁንም ድረስ መጎዳታቸውን ቀጥሏል። ከሰኔ 24, 2013 እስከ ሃምሌ 23, 2013 ባለው ጊዜ 150,000 አማራዎች ከራያ ቆቦ አካባቢ፣ 18,000 ደግሞ ከዋግ ኽምራ ዞን አበርገሌ መፈናቀላቸው ይገመታል። ከአፋር ክልል አባላ፣ ዳሎል፣ ጎልባ፣ እረብቲ፣ መጋሌ፣ እና አፈዴሬ አካባቢዎች ከ70,000 በላይ አፋሮች ተፈናቅለዋል ተብሎ ይታሰባል (ኢሳት፣ ሃምሌ 27, 2013)።
በመላው አገሪቱ ያሉ ሌሎች ግጭቶችም በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ ተጽዕኖ አሳድረዋል። ከሰኔ 24, 2013 እስከ ሃምሌ 23, 2013 ባለው ጊዜ በኢትዮጵያ 25 በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ የተቃጡ ጥቃቶች የተመዘገቡ ሲሆን በአጠቃላይ 420 ሰዎች ሞተዋል። አፋር ክልል በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በደረሰ ጥቃት ከፍተኛው ሞት የተመዘገበበት ክልል ሲሆን ከ420 ሰዎች መካከል 300 የሚሆኑት በክልሉ ጋቢ-ዞን 3 ጋዳማይቱ ከተማ ተመዝግበዋል። ይህ የሞት ቁጠር የተመዘገበው የአፋር ብሔረሰብ ታጣቂዎች እና ከአፋር አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር (ኡጉጉማ) ጋር ግንኙነት ያላቸው የአፋር ብሔረሰብ ታጣቂዎች በጋዳማይቱ ከተማ የሶማሌ ተወላጆች ላይ ጥቃት በሰነዘሩበት ወቅት ነው። በጋዳማይቱ የተፈጸመው ይህ ጥቃት በድሬዳዋ እና ሶማሌ ክልሎች የተቃውሞ ሰልፎችን አስነስቷል።
ከጥቂት ወራት መረጋጋት በኋላ በቤንሻንጉል/ጉሙዝ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ጨምረዋል። ከግንቦት 24, 2013 እስከ ሰኔ 23, 2013 በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተፈጸመ ጥቃት አንድ ሞት ብቻ ተመዝግቦ ነበር። ከሰኔ 24, 2013 እስከ ሃምሌ 23, 2013 32 የሟች ቁጥር ተመዝግቧል። የጉሙዝ ታጣቂ ቡድን አባላት በመተከል ዞን ግልገል በለስ ፓዌ ወረዳ ቢያንስ ሦስት ሰዎች ሲገድሉ በቡለን ወረዳ ማንጊ በር ደግሞ አንድ ሰው በጥይት ገድለዋል። እንዲሁም ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በአንድ ኩነት 15 ሰዎችን ተኩሰው ሲገድሉ በደንቤ ቀበሌ 8 ሰዎችን ገድለዋል። በአሶሳ ዞን ኦዳ ቤልጉዱል ወረዳ ውስጥ 3 ሰዎች ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገድለዋል። በውጊያ ምክንያት የሞቱ ሰዎችም ተመዝግበዋል። ከሰኔ 24, 2013 እስከ ሃምሌ 23, 2013 ባለው ወቅት በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና በጉሙዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ መካከል በተደረገ ውጊያ 100 ሟቾች ተመዝግበዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዘገባዎች አልሻባብ ከሶማሌ ክልል ልዩ ሃይሎች ጋር በሶማሌ ክልል ሸበሌ ዞን ከሰኔ 24, 2013 እስከ ሃምሌ 23, 2013 ባለው ጊዜ መዋጋታቸውን እና ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን ያሳያሉ። በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አልሸባብን የሚያካትቱ ውጊያዎች የተለመዱ አይደሉም።
የትህነግ እና ኦነግ-ሸኔ አመፆች ግምገማ
ሚያዚያ 28, 2013 ላይ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ትህነግ እና ኦነግ ሸኔ የተባሉት ሁለት ታጣቂ ቡድኖች ’አሸባሪ’ ተብለው እንዲሰየሙ ያቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል (የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ሚያዚያ 28, 2013)። ሁለቱም ቡድኖች ከፌደራል መንግስት ጋር እየተዋጉ ሲሆን ባለፉት ወራት እንቅስቃሴዎቻቸው የመጨመር ምልክቶች አሳይተዋል። የብሄር መሰረት ያላቸው እና ለብሄራቸው ሰፊ የፖለቲካ ነፃነት እንታገላለን የሚሉት ትህነግ እና ኦነግ-ሸኔ በሚንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች ጠንካራ ድጋፍ አላቸው። በተመሳሳይ ሁኔታ ሁለቱም ቡድኖች በእነሱ አካባቢዎች ውስጥ ባሉ አናሳ ብሔረሰቦች ላይ ግድያና መፈናቀል በመፈጸም ይከሰሳሉ።
በኢትዮጵያ ውስጥ እንዳሉ ሌሎች ብዙ ግጭቶች ሁሉ ስለትህነግ እና ስለ ኦነግ-ሸኔ ያለው መረጃ የተወሳሰበ እና ለከባድ የዘገባ አድልዎ የተጋለጠ ነው። እያንዳንዱ ተያዘ የሚባል ግዛት ከመንግስት ምንጮች የሚመጣ ተቃራኒ አጽፋዊ ምላሽ ይቀርብበታል። በውጊያ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ግምት ደካማ ነው። ሆኖም የሚታወቁትን፣ የማይታወቁትን እና እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ወደየትኛው አቅጣጫ እንደሚሄድ ለመግለጽ የሚያስችሉ ፍንጮች አሉ።
ስለኦነግ-ሸኔ የሚታወቁ
ኦነግ-ሸኔ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች በሚገኙ በርካታ አዛዧች የሚመራ ነው። በ2010 የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ትጥቅ ለመፍታት ሲወስን አንዳንድ አዛዧች በአዲስ ገቢው የፌዴራል መንግሥት አለመተማመናቸውን በመግለፅ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ባሉ ሩቅ ቦታዎች ውስጥ ተሸሽገው ለመቆየት ወሰኑ (ዘ ኢኮኖሚስት፣ ግንቦት 11, 2013)። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እነዚህ አዛዧች ራሳቸውን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብለው ሰይመዋል። መንግስት ኦነግ-ሸኔ የሚለውን ቃል ይጠቀማል። የኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች በዋናነት በምዕራብ ኦሮሚያ ምስራቅ ወለጋ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች እንዲሁም በደቡብ ኦሮሚያ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች ውስጥ ይንቀሳቀሳሉ።
የኦነግ-ሸኔ የአሁኑ ጥንካሬ በአብዛኛው የሚገናኘው “ቄሮ” በመባል ከሚታወቀው የወጣቶች የተቃውሞ እንቅስቃሴ ከመዳገሙ ጋር ነው። በኦሮሚያ ክልል በመቶዎች የሚቆጠሩ ኦሮሞ ያልሆኑ የአናሳ ብሄር ተወላጆች በአመፁ ተሳታፊዎች የተገደሉባቸውን የ2012 እና 2013 ፀረ-መንግስት አመፅን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት ሃይሎች የቄሮ ወጣቶች ላይ እርምጃ ወስዷል እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ የኦነግ እና ኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) መሪዎች በተያዙበት ወቅት ታስረዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች መንግስትን የፖለቲካ ምህዳሩን በማጥፋት እና ሃይል በመጠቀም በመወንጀል የቄሮን እንቅስቃሴ በመተው ርቀው ወደሚገኙ የኦነግ-ሸኔ መሸሸጊያ ቦታዎች ተሰደዱ (ኢትዮጵያን ኢንሳይት፣ መጋቢት 29, 2013)።
ከነዚህ ጥቃቶች እና እስራቶች ጀምሮ ኦነግ-ሸኔን ያካተቱ የውጊያ ክስተቶች ጨምረዋል (ከዚህ በታች ያለውን ምስል ይመልከቱ)። ኦነግ-ሸኔ ያደረጋቸው አዳዲስ የግዛት መስፋፋቶች ጉጂ፣ ጅማ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ እና ምዕራብ ሸዋን ያካትታሉ። አብዛኛዎቹ ውጊያዎች የሚካሄዱት ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወይም ተልዕኮው እንደ ኦነግ-ሸኔ ያሉ ሀይል የሚጠቀሙ የአመፅ ቡድኖችን መከላከል ከሆነው የኦሮሞ ክልል ልዩ ፖሊስ ጋር ነው። መንግስት ኦነግ-ሸኔን ለመመከት የሚያደርገው ጥረት ቡድኑ በሕጋዊ መንገድ የሽብርተኛ ድርጅት ሆኖ ከተፈረጀ በኋላ የጨመረ ሲሆን 16 ውጊያዎች እና 170 ከውጊያ ጋር በተያያዘ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ተመዝግበዋል።
ታዲያ ኢትዮጵያ በእንደዚህ ዓይነት ሁከት ውስጥ ለምን ብሄራዊ ምርጫ ታደርጋለች? ድምጽ መስጠት በአንፃራዊነት ሰላማዊ በሆኑ የሀገሪቱ ክፍሎች ውስጥ ግጭት እንዲነሳ ያደርጋል? ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት በሀገሪቱ ከፍተኛ መሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ውሳኔዎች የተቀረፀውን አሁን ያለውን ሁኔታ እንመረምራለን ፡፡
አብይ አህመድ ወደ ስልጣን የመጡት በኢትዮጵያ የአመራር ስርአት ውስጥ የህዝበ ወያነ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት)ን ቦታ ለአስርት አመታት የጠበቀው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዲግ) የሀይል ማሽቆልቆል ባጋጠመው ወቅት ነበር። በከፍታቸው ጊዜ የተበላሸ የአስተዳደር ስርዓት እና በጥቂት ልሂቃን የሚደረገውን ማጭበርበር አጋልጠዋል፤ ይህንን ክፍተት ወደስልጣን ሲመጡ ቢወርሱትም። ከዚህ ወዲህ ዙሪያቸው ጠባብ ሆኖ በታማኝነት፣ ልውውጥ ግንኙነቶች፣ እና ችግር ጊዜ ምላሽ አሰጣጥ ላይ የተመሰረተ ነው።
ከትግራይ ክልል ህወሃትን በማፍረስ እና በኦሮሚያ እንደ ጃዋር መሃመድ እና ዳውድ ኢብሳ ያሉ አማራጭ የኦሮሞ ፖለቲከኞችን ወደጎን በማድረግ አብይ ፓርቲያቸው ብልፅግና በመጪው ምርጫ በሰፊ ልዩነት እንደሚያሸንፍ አረጋግጠዋል። ኦሮሚያን እና ትግራይ ለብዙ ወራት በግጭት ሲናወጡ ቢቆይም የምርጫው ውጤት ቀድሞ እንደመታወቁ ምርጫውን ተንተርሶ ሁኔታዎች የመባባስ እድላቸው አነስተኛ ነው። በኦሮሚያ ትልልቅ እና ግጭት የተቀላቀለባቸው ሰልፎችን ያካሄዱ እንደ ቄሮ ያሉ ቡድኖች ከ2010 ወዲህ ወደመንግስት በመግባት እና በተፅእኖ በእጅጉ ተዳክመዋል (ኢትዮጵያን ኢንሳይደር፣ መጋቢት 29, 2013)። የእነዚህ ጥረቶች ውጤታማነት ቀደም ሲል ተረጋግጧል – በጥር 2013 በእስር በሚገኙ የኦሮሞ ፖለቲከኛ የረሃብ አድማ ዘመቻ ሲጀመር ሊደረግ የነበረ የተቃውሞ ሙከራ በጸጥታ ኃይሎች በፍጥነት ተበትኗል፤ በምርጫው ወቅትም ሊደገም የሚችል ነው (ኤፒ፣ የካቲት 29, 2013)።
ለአብይ የበለጠ አሳሳቢ የሚሆነው አማራ ክልል ነው፤ በክልሉ በኦሮሚያ ልዩ ዞን አካባቢ በአጣዬ ከተማ የተከሰቱ ግጭቶች በብዙ መራጮች እንደየመንግስት ብቃት ማነስ እና “የሕግ የበላይነትን ማስከበር ላይ ያለ ድክመት” ተደርገው መታየታቸው አብን ያለው ቦታ እየተጠናከረ እንዲመስል አድርገዋል (ቪኦኤ፣ ግንቦት 26, 2013)። ሚያዚያ አጋማሽ ላይ በባህር ዳር በተካሄደ ሰልፍ ላይ የአብን ደጋፊዎች የብልፅግናን ባነሮችን ሲያቃጥሉ እና ፀረ-ዐቢይ መፈክሮችን ሲያሰሙ ሰልፉ ወደግጭት ተቀይሯል (አዲስ ስታንዳርድ፣ ሚያዚያ 12, 2013)። የፖለቲካ እጣ ፈንታው ቀድሞ ከተወሰነው ከኦሮሚያ ክልል ጋር ሲነፃፀር በብልፅግናን እና አብን መካከል ያለው ውድድር ወደምርጫ መስጫው ክፍሎች የሚወሰድ ነው። አከራካሪ ውጤቶች የምርጫ ቀን ብጥብጥ ሊያስከትሉ ይችላሉ ፡፡
መጪው ምርጫ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን ውጥረቶችን እና የግጭት ደረጃዎችን በእርግጥም ከፍ አድርጎታል። ሆኖም በምርጫው መዳረሻ ያሉ ግጭቶች በአዳዲስ አካባቢዎችም ሆነ በአዲስ መንገድ እየተከሰቱ አይደለም፡፡ ይልቁንም የቆዩ ጉዳዮች የአካባቢ አስተዳዳሪዎች በአዲስ የተደራጀ የፖለቲካ ስርዓት ውስጥ ያልተረጋጋ የፖለቲካ ሁኔታ በሀብታቸው ወይም ድጋፍ መያዛቸው ላይ የሚያመጣውን አደጋ በመረዳታቸው እንደገና እየተነሱ ነው፡፡ በእርግጥም ይህ በመላ ሀገሪቷ በርካታ ቀውሶች ቢኖሩም እንኳን ምርጫው የሚቀጥልበት ምክንያት ነው። ምንም ዓይነት ችግር ቢኖር አብይ ይህንን ምርጫ ታማኞቻቸውን እና በአካባቢ ደረጃ የፓርቲያቸው ተወካዮች ምን ያክል የሀይል ለመገንዘብ ነው፡፡ ከዚህ እውቀት ላይ ተመስርተው የሚያደርጉት ነገር የኢትዮጵያን መፃኢ እድል ለመጪዎቹ ብዙ አመታት ይወስናል። ስለመጪው የኢትዮጵያ ምርጫ የበለጠ ለማግኘት ይህንን የኢፒኦ ልዩ ሪፖርት ይመልከቱ።
የኦነግ-ሸኔ አመፅ ዋና መለያ የውስጣዊ ትስስር አለመኖር እና ቢያንስ በስሩ ያለን አካባቢ በትክክል መቆጣጠር ያለመቻል “ስርአት” ውድቀቶች ናቸው። ይህ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦችን ሞት አስከትሏል። በአንዳንድ የኦሮሚያ ክልል ሥፍራዎች ታጣቂዎቹ “ከሙሉ የአመፅ ቡድን ይልቅ በትንሹ ግንኙነት ያላቸው ታጣቂዎች” ተብለው ይገለጻሉ (ዘ ኢኮኖሚስት፣ መጋቢት 12, 2013)።
የዚህ አለመደራጀቱ ተፈጥሯዊ ውጤት ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚገኙ በኦነግ-ሸኔ የትእዛዝ መዋቅር ስር የማይወድቁ ነገር ኝ ከኦነግ-ሸኔ ጋር የተቆራኙ (በራሳቸው አልያም በመንግስት ስያሜ) በርካታ ታጣቂዎች መኖራቸው ነው።
በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ የሚደርሱት ጥቃቶች እና የማፈናቀል ሙከራዎች በተደጋጋሚ የሚደርሱት በ1970ዎቹ በሺዎች የሚቆጠሩ አማራዎች እና ትግሬዎች በሰፈሩባቸው የምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢዎች ነው። በአናሳ ብሔረሰቦች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች በየሳምንቱ የሚከሰቱ ሲሆን በዚህም ምክንያት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል (ዘላለም ተፈራ፣ ሚያዚያ 2, 2002፤ ቢቢሲ፣ ጥቅምት 24, 2013፤ ሮይተርስ፣ ሚያዚያ 21, 2013፤ አዲስ ስታንዳርድ፣ ሚያዚያ 23, 2013)። መንግስት በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ ለሚደርሱት ጥቃቶች የኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎችን ሲወቅስ የኦነግ-ሸኔ ቃል አቀባይ ክሱን ውድቅ አድርገው እንዲያውም ጥቃቱ ከመንግስት ጋር ግንኙነት ባላቸው ሶስተኛ ወገን እንደሚፈጸም ስሞታ አቅርበዋል (አዲስ ስታንዳርድ፣ ሚያዚያ 23, 2013)። በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ ከሚደርሱ ጥቃቶች ጎን ለጎን የደህንነት ሰራተኞች ከአካባቢው በመቀነሳቸው እና የኦነግ ሸኔ ጥንካሬ ከመጨመሩ ጋር ተያይዞ በኦሮሞዎች እና አብዛኞቹ በ1970ዎቹ ወደአካባቢው በመጡ አማራዎች መካከል የሚፈጠሩ የአካባቢ ግጭቶች ተባብሰዋል።
የተደራሽነት አለመኖት፣ የቀጠለው አለመረጋጋት፣ እና መንግስትም ሆነ ኦነግ-ሸኔ በጋዜጠኞች ላይ የሚያደርጉት ከፍተኛ ጫና በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ላይ ገለልተኛ ምርመራ ለማድረግ እንዳይቻል አድርጓል። ተዓማኒነት ያለው ድርጅት ምርመራ እስኪያደርግ ድረስ አንድን ቡድን የሚደርሱትን ጥቃቶች አድራሽ አድርጎ መፈረጅ በኦሮሚያ ክልል ያለውን ውስብስብ የግጭት ሁኔታ አለመረዳት ይሆናል።።
ስለትህነግ የሚታወቁ
ትህነግ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) አካል ሆኖ ሥልጣን ከያዘበት 1983 ጀምሮ የኢትዮጵያን ፖለቲካ በዋናነት ተቆጣጥሯል። ትህነግ እንደ አማፂ ቡድን ስኬታማ እንዲሆን ያደረገው ቁልፍ ነገር ቡድኑ ላለፉት ሶስት አስርት አመታት በሀገሪቷ ሃብት ላይ የነበረው ታሪካዊ ተጠቃሚነት ነው። ይህም ትህነግ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ የነበረውን ከፍተኛ ስልጣን ያጠቃልላል። ትህነግ የሚቆጣጠረውን ኢሕአዴግ በመቃወም አራት አመት የዘለቀ የተቃውሞ ሰልፎች በኋላ ትህነግ በፌደራል መንግስት ውስጥ ያለውን ስልጣኑን በ2010 አጥቶ ትግራይን ብቻ ወደ ማስተዳደር ወረደ። ይህንን ተከትሎ ትህነግ የትግራይ ክልል ልዩ ሃይሎችን መገንባት ጀመረ። የፌደራል መንግስት ብሄራዊ ምርጫውን በአንድ አመት ለማስተላለፍ ያሳለፈውን ውሳኔ በመተላለፍ ጷጉሜ 2011 ላይ የክልል ምርጫ አካሄደ። ከሁለት ወራት በኋላ ትህነግ በክልሉ የሚገኙ የፌደራል ወታደሮችን አጠቃ (አፍሪካ ኒውስ፣ ህዳር 18, 2013)።
ትህነግ ጥቅምት 25, 2013 ላይ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ በፌደራል መንግስት እና ትህነግ መካከል ግጭት ተቀሰቀሰ (ሮይተርስ፣ ህዳር 28, 2013)። ምንም እንኳን የፌደራል መንግስቱ ትህነግ በውጊያ በአጭር ጊዜ መርታት ቢችልም (በኤርትራ ወታደሮች ተሳትፎ ምክንያት) ሁሊንም ከፍተኛ የፖለቲካ ሃላፊዎች ለመያዝ ያደረገው ጥረት ግን ከትህነግ ሃይሎች ጥቃት ከሩቅ ተራራማ አካባቢዎች ወደሚደረግ የደፈጣ ጥቃት መግባት ጋር ተጨምሮ በፌደራል ወታደሮች ውስጥ ግርግር ፈጥሯል (የኢፒኦን የትግራይ ግጭት ገጽ ይመልከቱ)። ይህ አመፅ ከመጋቢት 2013 ጀምሮ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል (ከዚህ በታች ያለውን ምስል ይመልከቱ)።
መሬት ላይ የፌዴራል ኃይሎች ለመለየት አስቸጋሪ ከሆኑ የትግራይ ክልል ኃይሎች እና የአካባቢ ታጣቂዎች ጋር ገጥመዋል (ኒው ዮርክ ታይምስ፣ ሰኔ 23, 2013)። የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ኃይሎች በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ባልሆኑ ግለሰቦች ላይ የጅምላ ግድያ ፈጽመዋል (የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ሚያዚያ 2013)። ወሲባዊ ጥቃት በጣም ተስፋፍቶ ነበር (ፎሪን ፖሊሲ፣ ሚያዚያ 19, 2013)። የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ሠራዊት ትግራይ ውስጥ የተገኘው ክልሉ ትህነግን በመደገፉ ለመቅጣት ነው የሚለው አመለካከት በቤተሰቦቻቸው ላይ እየደረሰ ባለው ነገር የተማረሩ በርካታ ወጣቶችን በተሳካ ሁኔታ ለመመልመል አስችሏል (ኤፒ፣ ሃምሌ 7, 2013)።
የኤርትራ ወታደሮችን ተሳትፎ እና በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ኢላማ መደረግን ተከትሎ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ማእቀቦችን ጨምሮ በከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጫና በመውደቃቸው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ሸንፈትቶች አስተናገደ (ቢቢሲ፣ ሰኔ 22, 2013፤ ኢቢሲ፣ ሰኔ 26, 2013)። በዚህ ሁኔታ የተበሳጩውና የተጋረጠበት ሰብአዊ እና ወታደራዊ አደጋ ያሳሰበው መንግስት ሰኔ 21, 2013 ላይ ክልሉን ለቆ ለመውጣት ወሰነ (አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ ሰኔ 21, 2013)።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ትህነግ ወደ አፋር እና የሰሜን አማራ ክልሎች መስፋፋቱን የቀጠለ ሲሆን በመላ ኢትዮጵያ አዲስ የስጋት ደረጃን አስነስቷል። በመላው አገሪቱ የሚገኙ የክልል መንግስታት ወጣቶች እንዲደራጁ እና የትህነግን መስፋፋት እንዲታገሉ ጥሪ አቅርበዋል (ቢቢሲ አማርኛ፣ ሃምሌ 19, 2013፤ Bቢቢሲ አማርኛ፣ ሃምሌ 18, 2013፤ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን፣ ሃምሌ 19, 2013)። የትህነግ ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ተዋጊዎች “በደንብ ያልሠለጠኑ የአርሶ አደሮች ታጣቂዎችን” መግጠም ከቀጠሉ ወደ አማራ ክልል ይበልጥ ጠልቀው በመግባት ወደ ጎንደር እና ደብረ ብርሃን ሊሄዱ እንደሚችሉ በጉራ ተናግሯል (ጌታቸው ረዳ፣ ሃምሌ 17, 2013)።
አፋር ውስጥ የተደረጉ ውጊያዎች ትህነግ ግዛቶችን እንዲያገኝ አድርገዋል። የአፋር እና አማራ ክልል ባለሥልጣናት እንዳሉት ከሆነ የትህነግ ኃይሎች በአሁኑ ወቅት በአፋር እና በአማራ ክልሎች ውስጥ ሰፋፊ ቦታዎች ይዘው ይገኛሉ (ሮይተርስ፣ ሃምሌ 15, 2013)። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተፈናቅለዋል (ቪኦኤ፣ ሃምሌ 27, 2013)።
ትህነግ አፋር ክልልን የማጥቃት የመጨረሻ ግቡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በክልሉ ዋና ከተማ ሰመራ መልሶ እንዳይደራጅ እና ቡድኑ የኢትዮጵያ-ጅቡቲ አቅርቦት መስመርን እንዲቆጣጠር ማድረግ ነው። የኢትዮጵያ-ጅቡቲ የትራንስፖርት መተላለፊያ መንገድ የሀገሪቱን ዋና ከተማ ጅቡቲ ከሚገኙ ወደቦች ጋር የሚያገናኝ የድንጋይ ንጣፍ መንገድ ሲሆን ነዳጅ እና ምግብ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት የሚውል ነው። የትህነግ ታጣቂዎች አሁንም ከመንገዱ በመቶዎች ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ቢሆኑም መንገዱ በቅርቡ የአፋር ክልል ልዩ ሃይሎች እና ታጣቂዎች በጋርባ ኢሳ፣ ኡንዱፍቶ፣ እና አይዴቱ ከተሞች ላይ ያደረሱትን ጥቃት በሚቃወሙ ከሱማሌ ክልል በመጡ ሰልፈኞች መንገዱ ለቀናት ተዘግቶ ነበር። (አዲስ ስታንዳርድ፣ ሃምሌ 20, 2013፤ የሶማሌ ክልል ኮሚኒኬሽን፣ ሃምሌ 19, 2013፤ የኢትዮጵያ-ጅቡቲ የአቅርቦት መስመር አካባቢ ያሉ አከራካሪ ድንበሮችን በተመለከተ የኢፒኦን አፋር-ሶማሌ ድንበር ግጭት ገጽን ይመልከቱ)።
ከሰኔ 24, 2013 እስከ ሃምሌ 23, 2013 ባለው ወቅት ትህነግ ያደረገው እንቅስቃሴ ቡድኑ ከአጥቅቶ መሸሽ ወደ የተያዙ ከባድ መሣሪያዎች መጠቀም እና ወደ ዋና መንገዶች ፈጣን አካሄዶችን ማድረግ መሸጋጋሩን አሳይቷል። በየክልላቸው የሚነሱ አመጾችን ለመዋጋት የሰለጠኑት እና የታጠቁት የክልል ልዩ ኃይሎች በአዚህ አይነት ስልት ውጤታማ ካለመሆናቸውም በላይ የመበለጥ እድል አላቸው።
የራሱን የውስጥ መዋቅርም ሆነ ታጣቂዎቹን የማደራጀት እና የማስተዳደር ችሎታው የትህነግ ትልቁ ችሎታ ነው። ወታደራዊ ስኬቱ በድርጅቱ ውስጥ ብዙ ልምድ ያላቸው ግለሰቦች ከመኖራቸው ጋር ሊገናኝ ይችላል (ቢቢሲ፣ ሰኔ 24, 2013)።
ሆኖም ትህነግ ትግራይን ከውጭው ዓለም ጋር የሚያገናኝበትን መንገድ መቆጣጠር እስከሚችል ድረስ አመፁን አሁን ባለው ደረጃ የበለጠ የመቀጠል አቅሙ አጠራጣሪ ነው። በአካባቢያዊ አቀማመጥ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ፣ አፋር፣ እና ሌሎች የክልል እና የኤርትራ ኃይሎች የተከበበ በመሆኑ ነዳጅ ወይም የጦር መሣሪያ ማስገባት አይችልም። በፖለቲካ ሁኔታ ቡድኑ የክልሉን ልሂቃን የያዘ ሲሆን ለዚህም ማሳያ የሚሆነው መንግሥት ክልሉን ተለዋጭ አስተዳደር በማቅረብ በጊዜያዊ ባለሥልጣናት በኩል ሙሉ በሙሉ መተካት አለመቻሉ ነው። ሆኖም ግን የትህነግን መብራት፣ ነዳጅ፣ ምግብ፣ እና ደህንነት የማቅረብ ችሎታ ማቆም ተችሏል። ትህነግ በሰኔ የመጨረሻ ቀናት ከመጣ ወዲህ ትግሬዎች በጨለማ ውስጥ ይገኛሉ። አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ካልተቀየረ ትህነግ ለህዝቡ የማቅረብ አቅም የለውም።
ያልታወቁ
የመረጃ መጥፋት፣ የበይነመረብ መቋረጥ፣ የተከፋፈለ ማህበረሰብ፣ እና ገለልተኛ ጋዜጠኞች ላይ የሚደርስ ማስፈራራት በኢትዮጵያ ውስጥ በጣም አስቸጋሪ የመረጃ ሁኔታ አስከትሏል። በሁለቱ የአመጽ ቡድኖች ዙሪያ ብዙ የማይታወቁ ነገሮች ያሉ ሲሆን አንዳንዶቹ መንግሥት በአገሪቱ ላይ ያለውን የመቆጣጠር ችሎታ ለመገምገም ወሳኝ ናቸው። ያልታወቀው ምን እንደሆነ እና በመተንተን ሙከራዎች ላይ ምን አይነት ተጽእኖ እንዳለው ከዚህ በታች ተብራርቷል።
የትህነግም ሆነ ኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች፣ ጦር መሣሪያዎች፣ እና ገንዘብ ብዛት በትክክል ለመገመት በጣም ከባድ ነው። ለኦነግ-ሸኔ ምን ያህሉ አሁንም እንዳሉ ማወቅ ባይቻልም ብዙ ሺህ ምልምል እና የሰለጠኑ ወጣቶች ሊኖሩት ይችላሉ። የትህነግን ጥንካሬ ለመገምገም ሲሞከር ተመሳሳይ ጉዳዮች አሉ። ቡድኑ በግምት 250,000 በሚሆኑ ተዋጊዎች ቢጀምርም በግጭቱ መጀመሪያ ምን ያክሉ እንዳለቁ እና ምን ያክል ከዚያ ቡሃላ እንደተመለመሉ እና እንደሰለጠኑ ማወቅ አይቻልም (ሮይተርስ፣ ህዳር 4, 2013)።
በኦነግ-ሸኔ ቁጥጥር ስር ያለው የግዛት መጠን እንዲሁ የማይታወቅ ነው፣ በአከባቢው አስተዳደር ውስጥ ለመሳተፍ ምን ያህል ዝግጁ እንደሆኑ ግልፅ አይደለም። ኦነግ-ሸኔ የሚንቀሳቀስበት አከባቢ በአጠቃላይ በርቀት ያለ እንደመሆኑ እንዲሁም የምዕራብ ኦሮሚያን ግጭት በተመለከተ የሚዘግቡ ገለልተኛ የዜና አውታሮች ባለመኖራቸው የትኞቹ ቦታዎች በቡድኑ ቁጥጥር ስር እንደሆኑ ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት በአከባቢ ሃላፊዎች ጥጥብቅ ቁጥጥር ይደረግበታል።
የኦነግ-ሸኔ ኃይሎች በጉጂ ዞን ጉሚ ኤልዳሎ እና ሊበን አውራጃዎችን ጨምሮ በርካታ ቀበሌዎችን ተቆጣጥረናል ብለዋል (የኦሮሞ መግለጫ፣ ነሃሴ 9, 2013)። በዞን ደረጃ ያሉ አስተዳዳሪዎች መፍትሔ የሚያስፈልጋቸው የፀጥታ ችግሮች መኖራቸውን ቢያምኑም የተባለው ግን ውሸት ነው ይላሉ (የጉጂ ዞን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት፣ ነሃሴ 4, 2013)። በእነዚሁ አካባቢዎች ከሚኖሩ ነዋሪዎች እና ሀኪም ቤት ሠራተኞች ጋር የተደረጉ ቃለመጠይቆች ታጣቂዎቹ መሬት መያዛቸውን ያመለክታሉ (ቢቢሲ አማርኛ፣ ሰኔ 11, 2013)።
በተጨማሪም ሁለቱም ድርጅቶች ድጋፍ ለማግኘት ከውጭ ተዋናዮች የመሳተፍ ችሎታቸው ምን ያህል እንደሆነ ግልፅ አይደለም። የኦሮሞ እና የትግራይ ብሄረሰቦች በአውሮፓ እና በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ በኢትዮጵያ ውስጣዊ የፖለቲካ ግጭቶች ታሪክ ውስጥ ትልቅ ሚና የተጫወቱ ብዙ እና ኃይል ያለው የዳያስፖራ ማህበረሰብ አላቸው (ዲደብሊው፣ ሃምሌ 10, 2013)። መንግስትን የሚቃወሙ ዳያስፖራዎች በፌደራል መንግስት የተቋቋሙትን መሰናክሎች በመስበር የአመጽ ቡድኖቹን በገንዘብም ሆነ በሌላ መንገድ ለመደገፍ ምን ያህል ውጤታማ እንደሆኑ አይታወቅም።
በተጨማሪም ሁለቱም ቡድኖች የጦር መሣሪያ እና የገንዘብ ፍሰት ለማግኘት የውጪ አጋር ከሱዳን እና ከግብፅ ለመመስረት ይሞክራሉ። ይህ እንዲፈጠር የሱዳን ፈቃደኝነት ግልፅ አይደለም። ሁለቱም ቡድኖች የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ስራ የሚተው ፖሊሲን አይደግፉም። ግልፅ የሆነው ግን ሁለቱም ቡድኖች ከውጭው ዓለም ጋር ግንኙነቶችን ለመፍጠር የሱዳንን ምስራቃዊ ድንበር ለመጠቀም ይሞክራሉ።
ምንም እንኳን የቅርብ ጊዜ ክስተቶች ሁለቱ ቡድኖች በተወሰነ ደረጃ እየተቀናጁ መሆናቸውን የሚጠቁሙ ቢሆንም በኦነግ-ሸኔ እና በትህነግ መካከል ያሉ ግንኙነቶች ግልፅ አይደሉም (ኤፒ ኒውስ፣ ነሃሴ 5, 2013)። በኦነግ-ሸኔ ተዋጊዎች ውስጥ እድሜያቸውን የትህነግን ሀይሎችን ሲታገሉ ያሳለፉ ትልልቅ ሰዎች እና የትህነግ ታማኝ በሆነው እና ከአገሪቷ ህግ ውጪ ይሰራ በነበረው “አጋዚ” በተባለው አስከፊ የትህነግ ቡድን ልዩ ሃይል እስራት፣ ድብደባ፣ እና ግድያ የደረሰባቸው የኦሮሞ ወጣቶች ይካተታሉ (ግሎባል ሰክዩሪቱ፣ መጋቢት 30, 2008)። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ለማሸነፍ በሚያደርጉት ጥረት በአሁኑ ጊዜ በጋራ ቢሰለፉም እንዲሁም በመንግሥት ሃይሎች በትብብር እንደሚሰሩ በተደጋጋሚ ቢከሰሱም ታሪካዊ ልዩነቶቻቸው ዘላቂ አጋርነትን የማይቻል ያደርጉታል።
የአመጽ ቡድኖቹ ወደየት እየተጓዙ ነው
በቅርብ አመታት ኦነግ-ሽኔ እና ትህነግ ወታደራዊና የአስተዳደር አቅማቸውን አሳድገዋል። ሁለቱም ቡድኖች በየአካባቢዎቻቸው ”የህዝብ ድጋፍ” እንዳላቸው ቢናገሩም የውስጥ ዘገባዎች ድጋፉ ከማስፈራራት እና ለመታዘዝ ከሚደረጉ ጫናዎች ጋር ይያያዛል የሚል ስሞታዎች በማቅረብ ይሸፍኗቸዋል።
ትህነግ በቅርቡ ሽምቅ ውጊያ ስልት ላይ ከተመሠረተ የአመፅ እንቅስቃሴ ወደ ትልልቅ መሣሪያዎችና ታንኮች መደበኛው ጦርነት የሚያካሂድ ቡድን ተቀይሯል። ኦነግ-ሸኔ ትንሽ ግዛትን የሚይዝ የአመፅ እንቅስቃሴ ሆኖ የቀጠለ ሲሆን ይልቁንም በፍጥነት አጥቅቶ ማፈግፈግ ይመርጣል።
ኦነግ-ሸኔ በቅርቡ የህዝብ ግንኙነት አቅሙን ጨምሯል እንዲሁም የአስተዳደር እና የውጭ ግንኙነት ችሎታ ያለው ድርጅት ሆኖ መታየት ይፈልጋል። በቅርቡ በምዕራብ ኦሮሚያ የማዕድን ኩባንያ ሠራተኞች በግዞት የተወሰዱበት ሁኔታ ለዚህ ዋነኛው ምሳሌ ነው (የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ፣ ሰኔ 10, 2013፤ አዲስ ስታንዳርድ፣ ግንቦት 7, 2013)። የማዕድን ቆፋሪዎቹ በዓለም አቀፍ ድርጅት በኩል የተለቀቁ ሲሆን ይህንንም የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመስራት ያገኘውን አዲስ አቅም ለማሳየት በምሳሌነት ተጠቅሟል። የኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ኃይሎች (ታጣቂዎች እና ልዩ ሀይሎች) ጋር የተደረገውን ውጊያ ተከትሎ ምርኮኞችን እየወሰዱ ነው ይህም የመያዝ እና እስረኞችን ለመለዋወጥ ያላቸውን የመደራደር ችሎታን ይጠቁማል። እነዚህ ችሎታዎች አዲስ እና እየጨመሩ ያሉ ይመስላሉ።
ፌደራል ኃይሎች ላይ ከተነሳው አመፅ ጎን ለጎን የኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች በምዕራብ ኦሮሚያ አናሳ ብሄሮች ላይ አሰቃቂ ጥቃቶችን በመፈጸም እንዲሁም አጣዬ ከተማ ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች ከአማራ ክልል ልዩ ፖሊስ ጋር በተደረገው ግጭት ውስጥ በመሳተፍ ይከሰሳሉ (የኢፒኦን የከሚሴ ግጭት ገጽ)። የኦነግ-ሸኔ ቃል አቀባዮች ሁለቱንም ክሶች ውድቅ አድርገው ይልቁንም ከመንግስት ጋር ግንኙነት ያላቸው ታጣቂዎች ላይ ጣታቸውን ይጠቁማሉ። ተጠያቂው ማንም ይሁን ማን ኦነግ-ሸኔ በሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች መንግስት በደህንነት ላይ ያለውን ሃይል እያጣ ሲሄድ አካባቢዎቹ ወደአለመረጋጋት እየገቡ ነው፤ ኦነግ-ሸኔ ለጥቃት የተጋለጡ የማህበረሰብ ክፍሎች ወይ ከላከል አይችልም አልያም አይፈልግም።
የመንግሥት ኃይሎች የፀጥታ ኃይላቸውን ሲያጡ እና ኦነግ-ሻኔ በአደጋ ተጋላጭ በሆኑ ሕዝቦች ላይ ጥቃቶችን ለመከላከል አይተካውም ፣ ወይም አይችልም ፣ ምክንያቱም ኦነግ-ሻኔ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑባቸው አካባቢዎች ወደ ሁከት ውስጥ የሚገቡ ይመስላል።
ኦነግ-ሸኔ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ቦታ እያገኘ ቢመስልም በምርጫ ወቅት የኦሮሞ ክልል ኃይሎች ያሳዩት ሁከትን የመከላከል አቅም አስደናቂ ከመሆኑም በላይ ታጣቂዎችን ለመዋጋት የሚያስችል ጠንካራ አቋም ላይ እንዳሉ ያመለክታል (ከምርጫ ጋር ላይ የተያያዙ ተጨማሪ ትንተና ኢፒኦ ሳምንታዊ :- ከሰኔ 12, 2013 እስከ ሰኔ 18, 2013፤ ኢፒኦ ልዩ ዘገባ:- የኢትዮጵያ ምርጫ እና የአብይ የፖለቲካ እጣፈንታዎች፣ ሰኔ 3, 2013 ላይ ያግኙ)።
ትህነግም ሆነ ኦነግ-ሸኔ ተመሳሳይ አሰራር እየተከተሉ ሲሆን ይህም በፌደራል ቁጥጥር ሥር መተዳደር እንዳይቻል ማድረግ ነው። ይህ ለፌዴራል መንግሥት በጣም ውድ የሆነ አካሄድ ለሌሎች የአገሪቱ ዜጎች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ማግኘት የማይችሉ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ ግለሰቦች ላይ ስቃይ ያስከትላል (አዲስ ስታንዳርድ፣ መጋቢት 18, 2012፤ ዋሺንግተን ፖስት፣ ሰኔ 25, 2013)። አሰራሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ አካባቢያዊ ድጋፍን ለማግኘት ቢያስችልም በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ታጣቂ ቡድኖች ሊሰጡ የማይችሏቸውን ሸቀጦች እና አገልግሎቶች መጠየቅ ሲጀምሩ ይህ የአከባቢ ድጋፍ በፍጥነት ያበላሻል። የትኛውም ቡድን እውነተኛ የአስተዳደር አቅም እስኪያገኝ ድረስ – ማለትም መብራት ማብራት እና የነዳጅ ማደያዎችን መሙላት – በእነሱ ተጽዕኖ ሥር ያሉ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎች ይሰቃያሉ።