በቁጥር (ከመጋቢት 24, 2010 እስከ መስከረም 7, 2014)1እነዚህ ቁጥሮች የሚያመለክቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደስልጣን ከመጡበት መጋቢት 24, 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገሪቱ መከሰታቸው የተዘገበ የግጭት ኩነቶችን ነው።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 2,007
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 11,886
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 5,501
በቁጥር (ከመስከረም 1, 2014 እስከ መስከረም 7, 2014)2በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተካተቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ቁጥሮች ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 14
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 87
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 60
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን እዚህ፣ ሁሉንም የአክሌድ ስራዎች ደግሞ እዚህ ጋር በመጫን ያገኛሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
በኢትዮጵያ አዲስ ዓመት የመጀመሪያ ሳምንት ውስጥ ውጊያዎች እና በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች በሀገሪቱ ውስጥ ቀጥለዋል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። ሆኖም የተመዘገቡት ግጭቶች ቁጥር የቀደሙትን ሳምንታት ያክል አልነበረም። ባለፈው ሳምንት የመንግስት ሃይሎች በአማራ ክልል መቄት፣ ሃሮ፣ እና ዛሪማ ከተሞችን እንደገና ተቆጣጥረዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን በልጉዲ አካባቢ ከትግራይ ህዝብ ነጻነት ግንባር (ትህነግ/ህወሃት) ታጣቂዎች ጋር መዋጋቱን ቀጥሏል። እንደዚሁም መስከረም 4, 2014 ላይ ከትህነግ ጋር ግንኙነት ያላው የሳምሪ ቡድን እና ለቅማንት ብሔረሰብ የበለጠ የራስ ገዝ አስተዳደር እንዲኖር የሚታገሉት የቅማንት ኮሚቴ ታጣቂዎች ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ክልል ልዩ ሃይሎች፣ እና የአማራ ታጣቂዎች ጋር በምዕራብ ጎንደር ዞን ሌንጫ ተዋግተዋል። እንደ መንግስት ገለፃ ፀረ-መንግስት የሆኑት እና ከትህነግ እና የቅማንት ብሄረሰብ ታጣቂዎች ጋር ግንኙነት ያላቸው ሃይሎች ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ከሱዳን ነው።
ወደ ትግራይ ክልል ያለው የሰብዓዊ ተደራሽነት እየተሻሻለ ቢሆንም የክልሉ ሁኔታ መባባሱን ቀጥሏል (የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት፣ መስከረም 6, 2014)። በመንግስት የሚደረጉ ገደቦችን እና የመላኪያ የጭነት መኪኖች እጥረትን ጨምሮ አንዳንድ ጉዳዮች የሚፈለገውን የሰብዓዊ ዕርዳታ ወደ ትግራይ ክልል እንዳይደርስ እንቅፋት መሆን ቀጥለዋል። እንደ መንግሥት እና የተባበሩት መንግሥታት ኢትዮጵያ መሠረት ለትግራይ ክልል ዕርዳታ ካደረሱ 466 የጭነት መኪናዎች ውስጥ የተመለሱት 38 ብቻ ናቸው (የተባበሩት መንግሥታት ኢትዮጵያ፣ መስከረም 6, 2014፤ የሰላም ሚኒስቴር፣ መስከረም 7, 2014)። ይህም በአፋር ክልል በኩል ከጅቡቲ ወደብ ወደ ትግራይ ምግብ ሊያመላልሱ የሚችሉ የጭነት መኪናዎች እጥረት ፈጥሯል። የጭነት መኪኖቹ ያልተመለሱበት እርግጠኛ ምክንያት እስካሁን አልታወቀም። በተጨማሪም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት መንግስት ያስቀመጣቸውን አስር ኬላዎች የጭነት መኪና እንቅስቃሴን እያጓተቱ መሆኑን ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግሥት እነዚህን የፍተሻ ኬላዎች ወደ ሁለት ዝቅ ማድረጉን አሳውቋል (የተባበሩት መንግሥታት ኢትዮጵያ፣ መስከረም 6, 2014፤ የሰላም ሚኒስቴር፣ መስከረም 7, 2014)።
ባለፈው ሳምንት በአማራ እና በአፋር ክልሎችም የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደረግ ጥሪ ቀርቧል። እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በአፋር እና በአማራ ክልሎች 1.7 ሚሊዮን ሰዎች “በግጭቱ ምክንያት የምግብ ዋስትና አጥተዋል ተብሎ ተዘግቧል” ብሏል (የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት፣ መስከረም 6, 2014)። በሰሜናዊው ክፍል ስላለው የሰብአዊ ቀውስ የበለጠ ለማወቅ ኢፒኦ ሳምንታዊ :- ከነሃሴ 29, 2013 እስከ ጳጉሜ 5, 2013ን ይመልከቱ።
በአማራ እና አፋር ክልሎች በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች የግጭት ሰለባ መሆናቸው ቀጥሏል። ባለፈው ሳምንት የግጭቱን መዘዝ የሚያሳዩ የተለያዩ ዘገባዎች ወጥተዋል። አንድ ዘገባ የትህነግ ሃይሎች በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ወረባቡ ወረዳ በ018፣ 020፣ እና 09 ቀበሌዎች 24 በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎችን መግደላቸውን አሳይቷል (አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ መስከረም 6, 2014)። ከዚህም በላይ መስከረም 5, 2014 ላይ በወረባቡ በትህነግ የተተወ የእጅ ቦንብ ፈንድቶ ሦስት ልጃገረዶች ሲሞቱ ሌላ አንድ ደግሞ ቆስላለች። በዘገባው መሰረት ልጆቹ የእጅ ቦምቡን ምን እንደሆነ ሳያውቁ ነክተውታል (አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ መስከረም 5, 2014)።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በኦሮሚያ ክልል የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ ጥቃት ማድረሱን ቀጥሏል። መስከረም 6, 2014 ላይ በምስራቅ ወለጋ ዞን ቂረሙ ወረዳ ውስጥ ኦነግ-ሸኔ 17 ሰዎችን ገድሏል፤ ስድስት ሰዎች እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም (ዲደብሊው አማርኛ፣ መስከረም 8, 2014)።
ባለፈው ሳምንት የአማራ፣ ሲዳማ፣ ጋምቤላ፣ እና የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ልዩ ኃይሎች በክልሉ መንግሥት ግብዣ ቤንሻንጉል/ጉሙዝ ክልል ደርሰዋል (ቢቢሲ አማርኛ፣ መስከረም 4, 2014)። እነዚህ የክልል ልዩ ኃይሎች በመተከል ኮማንድ ፖስት ሥር ሆነው ክልሉን ለማረጋጋት ይረዳሉ። በክልሉ ውስጥ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች እና ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂ ቡድኖች መካከል እንዲሁም በጉሙዝ ታጣቂ ቡድን እና በመንግሥት ኃይሎች መካከል የሚደረጉ ውጊያዎች በተደጋጋሚ ይመዘገባሉ። በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሚመራ ኮማንድ ፖስት ጥር 15, 2014 ላይ ክልሉ ዘላቂ ሰላም ለመፍጠር ቢቋቋምም ብዙም አልተሳካም። መስከረም 3, 2014 ላይ በደባቴ (አማራ ክልል) እና ግልገል በለስ መካከል ባለ አካባቢ የጉሙዝ ታጠቂ ቡድን ከፌዴራል ፖሊስ እና የአካባቢው የቤንሻንጉል/ጉሙዝ ታጣቂዎች ጋር ተዋግቷል። በዕለቱም የካማሺ ዞን ነዋሪዎች ታጣቂ ቡድኖች ካማሺ ከተማ ላይ ያደረሱትን ጥቃት ተቃውመው ሰልፍ አድርገዋል። መንግስት በታጣቂ ቡድኖች ላይ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀው የጉሙዝ ታጣቂ ቡድኑ የጉሙዝን ህዝብ እንደማይወክል ገልፀዋል። በቤንሻንጉል/ጉሙዝ ውስጥ ስላለው ግጭት የበለጠ ለማወቅ ኢፒኦ ወርሀዊ፡- ከሃምሌ 25, 2013 እስከ ነሃሴ 25, 2013 እና የኢፒኦን የመተከል ግጭት ገጽን ይመልከቱ።
ሳምንታዊ ትኩረት: የአሜሪካ ማዕቀብ በኢትዮጵያ ላይ3ቲዚያና ኮርዳ በሚላን ዩኒቨርሲቲ በኤንኤኤስፒ (ኔትዎርክ ፎር ዘ አድቫንስመንት ኦፍ ሶሻል አንድ ፖለቲካል ስተዲስ) እጩ የፒኤችዲ ተመራቂ ተመራማሪ ናት። ምርምሮቿ በአለም አቀፍ ግንኙነት፣ በውጭ ፖሊሲ ትንተና፣ ማዕቀቦች፣ እና የፖለቲካ ግጭት ላይ ያተኩራሉ።
ባለፉት ጥቂት ሳምንታት የመንግስት አጋር በሆኑት የአማራ ክልል ልዩ ሃይሎች፣ የአማራ ክልል ታጣቂዎች፣ እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደሮች በትህነግ ሃይሎች ላይ የሚያደርጉት ጥቃት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። በክረምቱ ወቅት የትህነግ ወታደሮች ወደቡብ አቅጣጫ ባደረጉት እንቅስቃሴ የታየው የግዛት ቁጥጥር ተገትቷል እና ሁለቱም ወገኖች መሄጃ የሌለበት ጥግ ላይ የቆሙ ይመስላል።
በከባድ መሳሪያ የመደብደብ እና በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰዎችን የጥቃት ኢላማ የማድረግ ክሶች በሁለቱም ወገኖች ላይ እየቀረቡ ሲሆን በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ሞት ጨምሯል። መድኃኒቶች እያለቁ ሲሆን የሃኪም ቤት ሰራተኞች ከሰኔ ጀምሮ አልተከፈላቸውም (ኤፒ ኒውስ፣ መስከረም 10, 2014)። እየከፋ እየሄደ ባለ ሁኔታ ውስጥ የዩናይትድ ስቴትስ (አሜሪካ) ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን “እሜሪካ በሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ግጭት በሚያራዝሙ ድርጊቶች ወይም ፖሊሲዎች ላይ የሚሳተፍ፣ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን የሚፈጽም ፣ ወይም የሰብአዊ ተደራሽነትን እና የተኩስ አቁም ሥራን የሚያደናቅፍ ማንኛውንም ቡድን ኢላማ ማድረግ እንድትችል የሚያደርግ አዲስ ማእቀብ መጣል የሚያስችል ፍቃድ የሚሰጥ’’ የህግ አስፈፃሚ ትእዛዝ ፈርመዋል” (ዩኤስኤድ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ መስከረም 7, 2014)።
ይህ የህግ አስፈፃሚ ትእዛዝ በኢትዮጵያ ግጭት ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ለመረዳት በርካታ ከግምት ውስጥ መግባት ያለባቸው ነገሮች አሉ። ይህ በኢትዮጵያም ሆነ በትህነግ ሃላፊዎች ላይ ማዕቀብ ለመጣል የመጀመሪያው እርምጃ ቢሆንም ይህ ትዕዛዝ ማዕቀብ መጣል ሳይሆን ማዕቀብ የመጣል ማስፈራሪያ ነው። ትዕዛዙ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እና ግምጃ ቤት በሁሉም ቡድኖች በኩል ያሉ እና በኢትዮጵያ የሰላም ድርድር እንዳይደረግ እንቅፋት የሚፈጥሩ ላይ ወደፊት ማዕቀብ መጣል እንዲችሉ ስልጣን የሚሰጥ ነው። አሜሪካ ግጭቱን የሚያቃልሉ እርምጃዎች እንዲወሰዱ የምትጠብቅበት የጊዜ ገደብ አልተሰጠም (አልጀዚራ፣ መስከረም 8, 2014)።
በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ ለመጣል የወጣው የህግ አስፈፃሚ ትዕዛዝ መለቀቅ ጉልህ ሲሆን ምክንያቱም እነዚህ ማዕቀቦች ቀደም ሲል ከተቀመጡት ሌሎች የማዕቀብ ፍቃዶች ተጨማሪ በመሆናቸው ነው። አንዳንድ ድርጊቶች ላይ ሰፊ ማዕቀቦችን ለመጣል መጀመሪያ የማዕቀብ ፕሮግራም መፈጠር አለበት። አበለዚያ በአንድ ግለሰብ ላይ ማዕቀብ ለመጣል የሚፈልጉ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነት ያለው እና ለየትኛውም ሀገር ወይም ግጭት ብቻ ያልሆነውን ዓለም አቀፍ ‘የማግኒትስኪ’ ሕግ (ጂኤሎኦኤምኤጂ)ን መጠቀም ይኖርባቸዋል (ሂዩማን ራይጽ ፈርስት፣ ሚያዚያ, 2011)። ይህ አማራጭ በትግራይ ክልል የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ላይ ላላቸው ሚና በኤርትራ መከላከያ ሰራዊት አዛዥ ጄነራል ፊሊጶስ ወልደዮሃንስ ላይ ማዕቀብ ለመጣል ጥቅም ላይ ውሏል (የአሜሪካ የግምጃ ቤት መምሪያ፣ ነሃሴ 17, 2013)።
አሜሪካ አዲሱን የማዕቀብ አገዛዝ ስታስተዋውቅ የማዕቀቡን የሕግ ማዕቀፍ “የአባሪ ዝርዝር” ከአስፈፃሚው ትእዛዝ ጋር በማያያዝ በማዕቀቡ ሊጠቃለሉ የታለሙ ግለሰቦችን ዝርዝር በመለየት ያሳውቃ። ዓርብ የታተመው የህግ አስፈፃሚ ትእዛዝ ኢላማ ውስጥ ያሉ አካላት እና ግለሰቦችን ዝርዝር ስላላካተተ ይህ ዝርዝር እስኪታተም ድረስ እንደ “ባዶ” ይቆጠራል። 2006 ላይ የአሜሪካ ባለሥልጣናት በደቡብ ሱዳን ላይ ማዕቀብ ሲጥሉ መጀመሪያ ያደረጉት ማዕቀቡ የተጣለባቸውን ግለሰቦች ሳያሳውቁ ነበር (የአሜሪካ የግምጃ ቤት መምሪያ፣ መጋቢት 25, 2006)። የኢትዮጵያ ጉዳይ ከደቡብ ሱዳን ጋር ተመሳሳይ ከሆነ ማዕቀብ የተጣለባቸው ግለሰቦች ዝርዝር በሚቀጥለው ወር ውስጥ ይፋ ይሆናል። ማዕቀቡም የተወሰኑ አካላት እርስ በርሳቸው እንዳይተባበሩ ይከለክላል፤ ለምሳሌ:- የአሜሪካ መሳሪያ አምራቾች ለኤርትራም ሆነ ለኢትዮጵያ የጦር መሣሪያ እንዳይሸጡ ሊከለከሉ ይችላሉ (አዲስ ስታንዳርድ፣ መስከረም 11, 2014)።
በግልጽ እንደሚታየው አሜሪካ እስካሁን ያልተደረገው በሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች በሰላማዊ ውይይት ለመሳተፍ ፈቃደኝነታቸውን እንዲያሳዩ ትፈልጋለች። የሰሞኑ የአሜሪካ መግለጫዎች እንደሚያመለክቱት የፌደራል መንግስቱ በትግራይ ላይ ”የጣለው ገደብ” ሊቆም ያስፈልጋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ አስከፊነት ባለፉት ሳምንታት ተባብሷል። ት የትግራይ አስከፊ ሁኔታ መባባሱን አመልክቷል (የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት፣ መስከረም 6, 2014)። የፌደራል መንግስት እገዳው በከፍተኛ ሁኔታ መቅለሉን ሆኖም ኝ በአማራ እና አፋር ከትግራት ሃይሎች ጋር ባለው ውጊያ ምክንያት ከፍተኛ የእርዳታ ፍላጎት እንዳለ አመልክቷል። መንግሥት ለትግራይ የታሰበው እርዳታ ከህዝቡ ይልቅ ለትህነግ ኃይሎችን እየተላለፈ እንደሆነ ይጠረጥራል። እርዳታን በትግራይ ለሚገኙ ዜጎች አድርሶ ለትህነግ ታጣቂዎች እንዳይደርስ የማድረግ ጉዳይ ለድርድር በር ለመክፈት ዋና ነገር ነው።
በተጨማሪም አሜሪካ የትኞቹን ሂደቶች (ለምሳሌ:- በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ የሚመራው የአፍሪካ ህብረትን እንቅስቃሴ ወይም የቱርክን ሽምግልና) እንደምትቀበል አላሳወቀችም። ምንም እንኳ ኢላማ ያላቸው ማዕቀቦች ግለሰቦች የሰላም ሂደቶችን እንዲቀላቀሉ ቢያነሳሱም አንዳንድ አደጋዎች አሏቸው። ማዕቀቦች በተለይም የንብረት አለመንቀሳቀስ ከአሜሪካ ጋር ጠንካራ ትስስር (እና ንብረት) ያላቸውን ግለሰቦች ይጎዳል። በአገር አቀፍ ደረጃ ብዙ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት እንዲህ ዓይነት ትስስር ቢኖራቸውም የአማራ ክልል አመራሮች እና የታጣቂዎች አዛዦች በዚህ የመጎዳት እድል የላቸውም። በመሆኑም የተጠቀሰው ማዕቀብ ውጤት በኢትዮጵያ ውስጥ የታጠቁ ቡድኖችን የበለጠ አክራሪነት ሊሆን ይችላል፤ በማዕቀብ ዝርዝር ውስጥ መካተት የበለጠ ‹መጥፎ ጠባይ› ሊያስከትል ይችላል።
ይህ አሜሪካ በኢትዮጵያ እና ትህነግ ባለስልጣናት ላይ ምን ያህል አቅም አላት? እና ማዕቀቡ ጦርነቱ ከተጀመረ ከወራት በኋላ መጽደዉ ምን ውጤት ይኖረዋል? የሚሉ ጥያቄዎችንም ይጭራል። አሜሪካ የኢትዮጵያ የረዥም ጊዜ የንግድ አጋር እና ከፍተኛውን የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅራቢ እንደመሆኗ መጠን በእርግጥ በአዲስ አበባ ውስጥ ትልቅ ተጽዕኖ አላት። በተመሳሳይ ትህነግ የቀድሞ የማዕከላዊ ስልጣን ኃይል እንደመሆኑ ከአሜሪካ ጋር ረጅም ታሪክ እና ግንኙነት አለው፤ እንዲሁም ጠንካራ የኢትዮጵያ (ብዙ ሊባል የሚችሉ ትግሬዎችን ጨምሮ) ዲያስፖራ አለ። ሆኖም በአዲስ አበባ እና በአሜሪካ መካከል ያለው ግንኙነት እጅግ የተበላሸ እንደመሆኑ አሜሪካ በሁለቱም ላይ ያለው ሃይል አጠያያቂ ነው። በተጨማሪም አሜሪካ በትህነግ ፖለቲካ እና ሃይሎች ላይ ያላት ሃይል ትንሽ ይመስላል።
በታተመ ደብዳቤ የተነገረውን ማዕቀብ አቢይ “ተመሳሳይ ነገሮችን በተለያየ መልኩ የሚያይ አግባብ ያልሆነ ግፊት” ሲሉ ተቃውመዋል (አብይ አህመድ፣ መስከረም 7, 2014)። በተጨማሪም የትህነግ ታሪካዊ እና የአሁን ሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በመጠቆም ፓርቲያቸውን ብልጽግና ሃገሪቱን ወደተሻለ ፍትሃዊ ልማት ለመምራት ምርጫውን ‘‘በከፍተኛ ልዩነት’’ ማሸነፉን ገልጸዋል (አብይ አህመድ፣ መስከረም 7, 2014)። ሆኖም በትግራይ ክልል ያሉ መራጮች ባለው አለመረጋጋት ምክንያት በአጠቃላይ ምርጫው አልተሳተፉም።
ማዕቀቡ ከተዋወቀበት ጊዜ ጋር የተያያዘው ጉዳይም አለ። ትህነግ እያጠቃ ከነበረባቸው የሃምሌ እና ነሃሴ ወራት ይልቅ የትህነግ ፈጣን እርምጃ እየተገታ ባለበት ወቅት የተጣለው ማእቀብ አሜሪካ የጦርነቱ ውጤትም ሆነ የሰላም ውይይቱን በተመለከተ ገለልተኛ እንዳልሆነች ጥርጣሬ እንዲነሳ አድርጓል (ኤኤ፣ ሰኔ 24, 2013)። በተጨማሪም አጠቃላይ ምርጫውን ተከትሎ መስከረም 24, 2014 ላይ አብይ ከብልጽግና አባላት ጋር ቃለ መሐላ ይፈፀማሉ። አዲሱን የስልጣን ዘመናቸውን ትህነግን በማሸነፍ ለመጀመር ይጓጓሉ። በከፍተኛ ቀውስ ውስጥ እያሉ እና በአሜሪካ ውስጥ ያሉ ንብረቶች በተያዙበት ሁኔታ አዲስ የሥልጣን ዘመን መጀመር ለአብይ አገዛዝ ትልቅ ጉዳት ይሆናል።
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ በከፍተኛ ሁኔታ የተከፋፈለ ነው እና ለማዕቀቡ ያለው ድጋፍም ሆነ ተቃውሞ በነባር የፖለቲካ መስመሮች ላይ ይወድቃል። የትህነግ ደጋፊዎች እና ሌሎች የመንግሥት ተቺዎች በአንድ ብሔር ሕዝብ ላይ ጦርነት በመክፈት፣ ምርጫ ማጭበርበር፣ እና በመላ አገሪቱ ጋዜጠኞች እና የማህበረሰብ አንቂዎች ላይ እርምጃ በመውሰድ የሚከሷቸው የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ የሚጣለውን ማዕቀብ ይደግፋሉ። የመንግሥት ደጋፊዎች ደግሞ ኢ-ፍትሐዊ እና ወገንተኛ ሲሉ ይኮንኗቸዋል፤ እንዲሁም ከ1983 እስከ 2010 በነበረው የትህነግ አገዛዝ ወቅት ከነበረው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አንጻር ይመለከቷቸዋል። በተለይም በአሜሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሲሆን በትውልድ አገራቸው ካሉ የንግድ አጋሮች ጋር ከፍተኛ ግንኙነት አላቸው። ምንም እንኳን ማን እንደሚጣል እና ለማንሳት ምን አይነት ቅድመ-ሁኔታዎች እንደሚኖሩ ገና መገለጽ ቢኖርበትም ማዕቀቡ ይጎዳል።
ከምርጫ ጋር የተያያዙ ክርክሮች ወቅታዊ ሁኔታ
ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ (ከሰኔ ጀምሮ በአንዳንድ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ዘግይቷል) መስከረም 20, 2014 ላይ በሐረሪ፣ ሶማሌ፣ እና ደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ይካሄዳል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በመራጮች ምዝገባ ላይ የቀረቡለትን የቅድመ-ምርጫ አለመግባባቶች አልፈታም በሚል የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ባለፈው ሳምንት ራሱን ከምርጫው አግልሏል (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር፣ መስከረም 7, 2014)። በሶማሌ ክልል ኦብነግ ጠንካራ ተቃዋሚ ፓርቲ ሲሆን የአብይን ብልጽግና ፓርቲን ይገዳደራል። ኦብነግ አብይ የተለያዩ ታጣቂ የተቃዋሚ ቡድኖች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ከጋበዙ በኋላ ህዳር 2010 ላይ ከ24 ዓመታት የትጥቅ ትግል በኋላ ወደ ክልሉ ተመልሶ ተዋጊዎቹን በትኗል።
እንደ ምርጫ ቦርድ ከሆነ በአጠቃላይ ከአምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ ሦስቱ – ኦብነግ፣ ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ፣ እና የኢትዮጵያን ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ፓርቲ- መጪው ምርጫ ላይ አይሳተፉም (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር፣ መስከረም 10, 2014)። በመሆኑም በሶማሌ ክልል በመጪው ምርጫ የሚሳተፉት ብልጽግና ፓርቲ እና የምዕራብ ሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ብቻ ናቸው። በሶማሌ ክልል ተቃዋሚ ፓርቲዎች የመራጮች ምዝገባ ላይ ያሉ ጥሰቶችን በተመለከተ አቤቱታቸውን አቅርበዋል። በእነዚህ ጥያቄዎች መሠረት ምርጫ ቦርድ በ11 የምርጫ ክልሎች የምርጫ ምዝገባን አስቁሟል፤ ይህም ለምርጫው መዘግየት አስተዋፅኦ አድርጓል። ነሃሴ 2013 ላይ ምርጫ ቦርድ በጅጅጋ 1 እና 2 የምርጫ ክልሎች እና ቀብሪደሃር ከተማ እና ወረዳ የመራጮች ምዝገባን ሙሉ በሙሉ ሰርዟል። ለቀሩት የምርጫ ክልሎች የምርጫ ቦርድ የምርጫ ምዝገባን በከፊል ለመሰረዝ ወስኗል።