ኢትዮጵያ በቁጥር (ከመጋቢት 24, 2010 እስከ ህዳር 24, 2014) 1 እነዚህ ቁጥሮች የሚያመለክቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደስልጣን ከመጡበት መጋቢት 24, 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገሪቱ መከሰታቸው የተዘገበ የግጭት ኩነቶችን ነው።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 2,303
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 13,268
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 5,922
ኢትዮጵያ በቁጥር (ከህዳር 18, 2014 እስከ ህዳር 24, 2014) 2በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተካተቱ አንድ አንድ ኩነቶች በዘገባ መዘግየት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት ቁጥሮች ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።
- የተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች – 21
- በተደራጁ የፖለቲካ ግጭቶች ህይወታቸው እንዳለፈ የተዘገቡ ሰዎች – 255
- በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ በተቃጡ ጥቃቶች ህይወታቸው ያለፈ – 76
ኢትዮጵያን በተመለከተ በቁጥር የተደገፉ መረጃዎችን እዚህ፣ ሁሉንም የአክሌድ ስራዎች ደግሞ እዚህ ጋር በመጫን ያገኛሉ።
የሁኔታዎች አጭር መግለጫ
ባለፈው ሳምንት የመንግስት ሃይሎች በአማራ ክልል ጋሸና፣ ላሊበላ፣ እና ሸዋ ሮቢት ከተሞችን ጨምሮ 16 አካባቢዎችን መልሰው ተቆጣጥረዋል (የኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት፣ ህዳር 22, 2014፤ የኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት፣ ህዳር 22, 2014፤ የኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት፣ ህዳር 24, 2014)። በትግራይ ህዝብ ነጻነት ግንባር (ትህነግ/ህወሓት) ስለተፈጸሙ ግድያዎች፣ መድፈሮች፣ እና የንብረት ውድመቶች ዘገባዎች ወጥተዋል። በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሟቾች እና የተደፈሩ ሰዎች ቁጥር አልታወቀም። ይህ በእንዲህ እንዳለ የትህነግ ባለስልጣናት ወደ ትግራይ ክልል ለማፈግፈግ የወሰኑት “አሁን ያለው ሁኔታ ከተገመገመ በኋላ ነው” ብለዋል (ደብረፂዮን ገብረሚካኤል፣ ህዳር 26, 2014)።
በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ቦታዎች ትህነግ እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)-ሸኔ ሃይሎችን እንዲሁም የውጭ ጣልቃ ገብነትን በመቃወም ሰልፎች ተካሂደዋል (ከዚህ በታች ያለውን ካርታ ይመልከቱ)። በኢትዮጵያ የሚደረገውን የውጭ ጣልቃ ገብነት በመቃወም ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፎች በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት እና በአማራ ክልል ርዕሰ መዲና ባህርዳር ከተማ ተካሂደዋል።
የሱዳን መንግስት እንደገለጸው ህዳር 18 ላይ የሱዳን ጦር ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የኢትዮጵያ ታጣቂዎች ጋር በሁለቱ ሀገራት ድንበር ላይ እንደተዋጋ ገልጿል (ቪኦኤ፣ ህዳር 18, 2014)። ቢያንስ 20 የሱዳን ወታደሮች ተገድለዋል (ብሉምበርግ፣ ህዳር 18, 2014)። የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን ውንጀላ ውድቅ አድርጎ የሱዳን መንግስት ኢትዮጵያን ለማጥቃት ታጣቂዎችን በመርዳት ላይ ነው ሲል ወቅሷል (ኢሳት፣ ህዳር 18, 2014)። ሌላ ዘገባ ህዳር 17 እና 18 ላይ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ደለሎ ቁጥር 6 እና ጥሀ አከባቢዎች ከትህነግ ጋር ግንኙነት ያለው የሳምሪ ቡድን ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ ከአማራ ክልል ልዩ ሃይሎች፣ እና ከአማራ ታጣቂዎች ጋር ተዋግቷል (ኢሳት፣ ህዳር 18, 2014)። የሱዳን ወታደሮች ከሳምሪ ቡድን ጋር በመሆን የኢትዮጵያ ወታደሮችን ሲዋጉ እንደነበር ተዘግቧል (ኢሳት፣ ህዳር 18, 2014)።
በኦሮሚያ ክልል የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይሎች እና ኦነግ-ሸኔ በምስራቅ ሸዋ ምስራቅ ወለጋ እና ጉጂ ዞኖች መዋጋት ቀጥለዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በምስራቅ ወለጋ ዞን ኢባንቱ የአየር ድብደባ ማካሄዱ ተዘግቧል (ኦዳ ታርቢ፣ ህዳር 21, 2014)። በተጨማሪም በክልሉ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ባልሆኑ ሰዎች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች ቀጥለዋል። ባለፈው ሳምንት በምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ አቅራቢያ ባለ ቦታ አንድ የኦሮሞ ባህላዊ መሪ (አባ ገዳ)ን ጨምሮ ቢያንስ 14 ሰዎች ተገድለዋል። ቢቢሲ አማርኛ እና አዲስ ስታንዳርድ ለጥቃቱ ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ታማኝ የሆኑ ኃይሎችን ተጠያቂ ያደረጉ የተጎጂዎችን ቤተሰቦች አነጋግረዋል። የክልሉ መንግስት ለግድያው ተጠያቂው ኦነግ-ሸኔ ነው ሲል ከሷል። መንግስት ይህን ጥቃት ተከትሎ በምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ አቅራቢያ በሚገኝ አካባቢ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይሎች ከኦነግ-ሸኔ አባላት ጋር ተዋግተው 16 ሰዎች ሞተዋል ሲል ገልጿል (አዲስ ስታንዳርድ፣ ህዳር 24, 2014)። የኦሮሚያ መንግስትም ከጥቅምት 22 እስከ ህዳር 21 በነበረው ወቅት የኦነግ-ሸኔ አባላት በጉጂ እና በባሌ ሁለት ሌሎች የአባ ገዳ ሽማግሌዎችን መግደላቸውን ገልጿል (ኢሳት፣ ህዳር 24, 2014)።
ሳምንታዊ ትኩረት: በግዛት ቁጥጥር ላይ ያሉ ለውጦች
በጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የሚመራው የፌደራል መንግስት ታማኝ ሃይሎች ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብዙ ቦታዎችን ከትህነግ ማስመለስ ችለዋል። ይህ ዘገባ በተጠናቀረበት ወቅት የፌደራል መንግስቱ ጥቅምት መጨረሻ ላይ በህወሃት የተቀማቸውን የደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች (ደቡብ ወሎ፣ አማራ ክልል) መቆጣጠሩን ተናግሯል (ሮይተርስ፣ ህዳር 27, 2014)።
ወታደራዊ ድሎቹ ለፌደራል መንግስቱ ብዙ ነገሮችን ያመለክታሉ። ከሁሉም በፊት ትህነግ ዋና ከተማዋን አዲስ አበባን የማስፈራራት አቅም የለውም። የደሴ እና ኮምቦልቻ ጥቅምት ላይ መያዝ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ አድርጎ ነበር (ኢፒኦ ሳምንታዊ: ከጥቅምት 20, 2014 እስከ ጥቅምት 26, 2014)። የፌደራል መንግስቱ የተቀናጀው ድል እንደ የሰዓት እላፊ ገደቦች ያሉ የአደጋ ጊዜ እርምጃዎችን ሊያቀል ይችላል።
ይሁን እንጂ ይህ ሽንፈት የግጭቱን ማብቃት የማሳየት እድሉ አናሳ ነው። የትህነግ ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ትህነግ ከኮምቦልቻ እና ደሴ ያፈገፈገው በእቅድ መሰረት ነው ሲል የገለፀው ይህ መግለጫ ከመውጣቱ ከቀናት በፊት በሺዎች የሚቆጠሩ የትህነግ ታጣቂዎች ወደ ሰሜን መሄዳቸውን በሚያሳይ በአልጀዚራ አረብኛ የታተመ ምስል ጋር ይስማማል (አልጀዚራ፣ ህዳር 24, 2014)። ከስልክ አውታር ጋር የተያያዙ ጉዳዮች እና በአካባቢው የነጻ ጋዜጠኞች እጥረት ተጨማሪ ዘገባዎችን ለመስራት አስቸጋሪ ያደርገዋል።
የትህነግ መሪዎች ምንም ያቅዱ ትህነግ ወደ ደቡብ መግፋቱን የመቀጠል አቅሙ ውጤታማ በሆነ መንገድ የተዳከመ እና የትህነግ ታጣቂዎች ከትግራይ ክልል ውጭ የሚደረጉ ውጊያዎች የመቀጠል ችሎታ የመኖሩ እድል የጠበበ ነው። የፌደራል መንግስቱ “እጅግ በጣም ብዙ” የትህነግ ተዋጊዎችን መያዙን ተናግሯል እንዲሁም ተጨማሪ ተዋጊዎች አቢይ እጅ እንዲሰጡ ላቀረበላቸው አጠቃላይ ጥሪ ምላሽ መስጠታቸው አሳውቋል (የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣ ህዳር 28, 2014)። ሌላ በመንግስት የወጣ ዘገባ እነዚህ ቁጥሮች በሺዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ያመላክታል (ፋና፣ ህዳር 25, 2014)። በተጨማሪም በካሳ ጊታ፣ ጭፍራ፣ ጋሸና፣ እና ባቲ ላይ በመንግስት ሃይሎች እና በትህነግ ታጣቂዎች መካከል ለተከታታይ ሳምንታት የተካሄደው ጦርነት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሰው ህይወት አጥፍቷል።
መንግስት በአፋርም ሆነ በአማራ ክልል እንዲሁም በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ታጣቂዎችን ማሰባሰብ ለአሁኑ ስኬቱ አስተዋፅዖ የነበረው ይመስላል። በተጨማሪም ትህነግ ታጣቂዎቹ በሁለቱ ክልሎች በፈጸሟቸው ወንጀሎች ምክንያት ከሀገር ውስጥ እና ከአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ከፍተኛ ጫና እየገጠመው ነው (አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ጥቅምት 30, 2014)። ባሳለፍነው ሳምንት ትህነግ ከወጣ በኋላ በመንግስት የተላለፈው የቪዲዮ ምስል የተዘረፉ ባንኮች እና ጉዳት የደረሰባቸው የህዝብ ህንፃዎችን እንዲሁም የትህነግ ታጣቂዎች ለቀው ሲወጡ በግጭት ውስጥ ተሳታፊ ያልነበሩ ሰዎችን ተኩሰው መግደላቸውን የሚናገሩ ሃዘን ላይ ያሉ ቤተሰቦችን አሳይቷል (ኢቢሲ፣ ህዳር 25, 2014)።
ከቻይና፣ ቱርክ፣ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የተውጣጡ ሰው አልባ አውሮፕላኖችም መንግስት በተጎናጸፋቸው አዳዲስ ስኬቶች ውስጥ ሚና ተጫውተዋል እየተባለም ሲሆን እነዚህ ሀገራት መንግስትን ወደ ትግራይ ላለው ተደራሽነት በእንቅፋትነት የሚከሱትን አሜሪካን እና አጋሮቿን በማስቆጣት የፖለቲካ ዋጋ ከፍለውም ቢሆን “አሁን ያለውን መንግስት ህልውና በማረጋገጥ” መስዋእትነት ለመክፈል ፍቃደኛ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይጠቁማል (ኦሪክስ፣ ህዳር 22, 2014፤ ቢቢሲ፣ ነሃሴ 14, 2013)። የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በጦርነቱ ላይ ለውጥ መምጣት ከጀመረ ከጥቂት ጊዜ በኋላ በአዲስ አበባ ጉብኝት ሲያደርጉ (ብሉምበርግ፣ ህዳር 22, 2014) የአሜሪካ ባለስልጣናት ግን “አለም አቀፍ እውቅና ባለው የሰው ልጅ ላይ ከፍተኛ ጥሰት መብቶች” በሚል ኢትዮጵያ ከቀረጥ-ነጻ ወደ አሜሪካ ገበያ ያላትን እርል ባለፈው ወር አግዶ ነበር (ቪኦኤ፣ ጥቅምት 23, 2014)።
የኢትዮጵያ ሰራዊቶች ተጨማሪ ከተሞችን መልሶ ለመያዝ ወደ ሰሜን መገስገስ በቀጠለበት ወቅት የግጭቱ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ግልጽ አይደለም። የመንግስት በሺህ የሚቆጠሩ ተዋጊዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉ እና ከፍተኛ አመራሮችን የመግደሉ ዘገባ እውነትነት ላይ የተመሰረተው የትህነግ የተዋጊ ሃይል ስፋት መቀነስ ለማወቅ አስቸጋሪ ነው። በተመሳሳይ የኢትዮጵያ መንግስት ባለፈው አመት ያካሄደው ቁጥጥር ውድነት አንጻር ጦርነቱን ወደ ትግራይ ክልል መግፋት ይቻል ወይም ይፈልግ አይታወቅም። ግልፅ የሆነው ግን የኢትዮጵያ መንግስት በሃገር ውስጥ በአማራ እና አፋር ክልል ታጣቂዎች ላይ በመመስረት በአለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ከአሜሪካ እና አውሮፓ በመሸሽ ወደ ኢሚሬትስ ፣ቻይና፣ እና ቱርክ በመጠጋት በድጋሚ ለመሰባሰብ መቻሉ ነው።